የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጂግጅጋ ከተማ በተፈጸመው ድርጊት የሰው ህይዎት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጂግጂጋ ከተማ በተፈጸመው ድርጊት የሰው ህይዎት በመጥፋቱ ማዘናቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈም በድሬዳዋ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ ህይዎታቸውን ባጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሃዘን መግለጻቸውን፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ከተሞች የተፈጸመውን ድርጊትም በጽኑ አውግዘዋል።
መሰል ብጥብጥና ግጭቶችም መደገም እንደሌለባቸው ጠቅሰው፥ ድርጊቱ በአስቸኳይ እንዲቆምም አሳስበዋል።
ከሰሞኑ በጂግጂጋ ከተማ በተፈጸመ ድርጊት የሰው ህይዎት የጠፋ ሲሆን፥ ቤተ ክርስቲያንም ተቃጥሏል።
ከዚህ ባለፈም በርካታ ሰዎች ለጉዳት ተዳርገዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ተፈናቅለዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረ ግጭትም ለሰው ህይዎት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።
በዛሬው እለትም የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ በጂግጂጋ ከተማ በመግባት ሰላም እንዲያስከብሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።
Monday, August 6, 2018
ዶክተር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጂግጅጋ ከተማ በተፈጸመው ድርጊት የሰው ህይዎት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Recent Articles
Recent Video Uploads
Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube
Ethiopia Today
- Active a minute ago with many
- videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies, Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time
No comments:
Post a Comment