Wednesday, March 26, 2025

በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተመረተ ነው!

 በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተመረተ ነው!

ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት የሚገኝበት አቅም መፈጠሩን በግብርና ሚኒስቴር ዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ሃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ገለጹ።
ኢትዮጵያ እምቅ የዓሣ ሀብት ቢኖራትም በተለያዩ ተግዳሮቶች ምክንያት በዘርፉ ተጠቃሚ ሳትሆን መቆየቷን በግብርና ሚኒስቴር ዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ሃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ተናግረዋል።
በሀገር ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ የዓሣ ልማት ዘርፍ ማነቆ የሆኑ ተግዳሮቶችን በመፍታት ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።
በዚህም በዓሣ ምርታማነት ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አንስተው፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውስጥ የዓሣ ሀብት ልማት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን በአብነት ጠቅሰዋል።
በግድቡ በስፋት ተፈላጊ የሆኑ የዓሣ ዝርያዎች እየተመረቱ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህም በቀን ከ14ሺህ 500 ቶን በላይ የዓሣ ምርት የሚገኝበት አቅም መፈጠሩን አብራርተዋል።
በሕዳሴ ግድብ ውስጥ የተለያዩ የዓሣ ዝርያዎች መኖራቸውን የገለጹት ዶክተር ፋሲል የሚመረተው ዓሣ ተፈላጊነት ከፍተኛ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።
ዘርፉ ካላው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባለፈ ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ በቀጣይ የዓሣ ምርትን የበለጠ ለማሳደግ የዓሣ ጫጩቶችን ማሠራጨት እና ዓሣ በሌለባቸው የውሀ አካላት ላይ ዓሣ የሚመረትባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ የዓሳ ሀብት ባለሙያ አቶ ቡሸን ፉፋ በበኩላቸው፥ የሕዳሴ ግድቡ በክልሉ የዓሣ ምርት መመረቱ የክልሉን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንስተዋል።
በዘርፉ 64 ማኅበራት መደራጀታቸውንና ከእነዚህ ውስጥ 23 ማኅበራቶች የሥራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
በቀጣይም ወደ ሥራ ያልገቡ ማኅበራትን ወደ ሥራ ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
All reactions:
1.8K

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time