Sunday, August 12, 2018
በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል
Friday, August 3, 2018
ተስፋ ሰጭው የሳይንስ ትግበራ -የሮኬት ሙከራ
‹‹የተማሪዎችን ፈጠራ በእውቀት እና በገንዘብ የምንደግፍበት ወቅት ነው›› የባሕርዳር ሳይንስ ማበልፀግያ ማዕከል፡፡
ሳይንስ ለችግሮች መፍትሄ ለማምጣት የምንጥርበት የእውቀት እና ክህሎት መድረሻ ነው። የሁሉም ስኬታማ ሳይንስ መነሻው ችግር ፣ ትንንሽ ሙከራዎች እና የሚያድጉ ፍላጎቶች ናቸው።
የተማሪዎቹ ግኝት ከሶስት ዓመታት በላይ የወሰደ ሳይንሳዊ ግኝት ነው የሚሉት የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋየ ሽፈራው ሳይንስን መተግበር እንደተጀመረ ማሳያ ነው ይላሉ።
Sunday, July 29, 2018
የአቶ ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ
የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አቶ ዘይኑ ጀማል ስለ አሟሟታቸው "አመላካች መረጃዎች እና ማስረጃዎች" መገኘታቸውን የተናገሩ ሲሆን "በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዴት እንደሞተ፣ ለምን እንደሞተ የሚገልጹ መረጃዎችን ለኅብረተሰቡ" እናሳውቃለን ብለዋል።
Monday, May 21, 2018
በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶምን ለማስፋፋት ፕሮቴስታንት አዋጇን በይፋ ጀምራለች
በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶምን ለማስፋፋት ፕሮቴስታንት አዋጇን በይፋ ጀምራለች
"ሰው መንፈስ ነው" የሚለው የፕሮቴስታንቱ ትምህርት የሰዶማውያን አስተምህሮ ነው። በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሥር እየሰደደ የመጣውና ብዙ ክርስቲያኖችን እያወዛገበ ያለው የእምነት ቃል እንቅስቃሴ/ Word faith movement / አስተምህሮ በአሁን ሰዓት በፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቶት ታላላቅ በሚባሉ ፓስተሮች ሳይቀር ይህ እንግዳ የሆነ አጋንንታዊ ትምህርት በየመድረኮቻቸው በስፋት እየተሰበከ ነው።የእምነት ቃል እንቅስቃሴ በርካታ ክህደትና ኑፋቄ ያለው አስተምህሮ ሲሆን በዋነኛነት "ሰው መንፈስ ነው ነፍስ አለው በሥጋ ውስጥ ያድራል"የሚለው ትምህርት ግን ግብረ ሰዶማውያን የፈጠሩትና ሰዶማዊነትን በሃይማኖት ሽፋን ለማስፋፋት ሆን ተብሎ የታቀደ አጋንንታዊ አስተምህሮ ነው። ሰው መንፈስ ነው በሥጋ ውስጥ ያድራል የሚሉት የፕሮቴስታንት ሰባኪዎች በሥጋችን የምንሰራው ማናቸውም ዓይነት ኃጢአት እና ነውር ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ኅብረት አያቋርጠውም፤ እኛም የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችን ላይ የሚያመጣብን አንዳችም ዓይነት ተጽኅኖ የለውም የሚልና ትውልዱን መረን የለሽ የሚያደርግ በድፍረት ኃጢአት ክርስቲያኖች እንዲመላለሱ የሚያበረታታ በማር የተለወሰ መርዝ ነው። ሰው መንፈስ ነው በሥጋ ውስጥ ያድራል ማለት ልክ እንደ ዳዊትና ማኅደር ወይም እንደ መጽሐፍና ቦርሳ ማለት ነው መጽሐፍ ቦርሳ ውስጥ ይቀመጣል ቦርሳው ቢቆሽሽና ቢጨቀይም መጽሐፋ ላይ የሚያመጣው ተጽኅኖ የለም የሚለው የፕሮቴስታንቱ ፍልስፍና በሥጋችን ምንም ነገር ብንፈጽም ሰው የሚባለው ዋነኛው መንፈሳችንን አያረክሰውም አያቆሽሸውም ባዮች ናቸው። ወገኖቼ መጽሐፍ ቅዱስ "ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች ፍጻሜዋ ግን ሞት ነው" ብሎ እንደ ሚነግረን ይህ ትክክለኛ የሚመስለውና የሰዎችን ልቡና በቀላሉ ለማሳመን በሰይጣናዊ ጥበብ የተወጠነው ትምህርት ክርስቲያኖችን ሙሉ ለሙሉ ከእግዚአብሔር የሚለይና ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያራቁት የድፍረት ኃጢአትን የሚያለማምድ ክህደት ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን ሥጋችንም መንፈሳችንም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ እንዲሆን ነው እንጂ በመንፈስ ስለ መቀደስ ብቻ አያስተምረንም ። " እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:1)::
መግለጫ
ሰዶማውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸው ዕቅድ ምንድን ነው ?
የዴንማርክ የዕምነት እና የግብረ ሰዶማዊነት ፕሮፋይል
ዴንማርክ እና ግብረሶዳማውያን
ዴንማርክ በኢትዮጵያ
Tuesday, May 15, 2018
ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አቅርበው ስልጣን ላይ ያሉ ሹመኞች ጉዳይ እየተጣራ ነው
ዋዜማ ራዲዮ -በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችንና ሌሎች የክልልና የፌደራል መንግስት ሰራተኞችን የትምህርት ማስረጃዎች የማጣራት ስራ ተጀመረ።
ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ከትምህርት ሚንስቴር ጋር እያደረገ ባለው ምርመራ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ተለይተዋል።
Tilaye Gete (PhD) – Photo: MoE
ከቅርብ ወራት ወዲህ በኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በተጭበረበረና በሐሰት የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞችና አመራሮች ላይ የተጀመረው የማጽዳት ዘመቻ ወደ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከፍ ብሎ መታየቱ አንዳንድ ባለስልጣናትን እያሰቆጣ መሆኑን ዋዜማ ከምንጮች ለማወቅ ችላለች፡፡
ዘመቻው በርካታ ስመ-ጥር ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረጉ ስለማይቀር ምርመራው እንዲቆም ወይም እስካሁን በተደረገው ማጣራት ላይም ከህግ ይልቅ በፖለቲካዊ ውሳኔዎች ታይቶ እንዲታለፍ አንዳንድ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጫና እያሳደሩም ይገኛሉ፡፡
በፌደራል መንግስት ስር ያሉ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛና በመካከለኛ የአመራር ደረጃዎች ያሉ ኃላፊዎች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተሹመው በመገልገል ላይ ካሉት የበርካታ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ለኢህአዴግ ጽ/ቤትና ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ተልኳል ተብሏል፡፡
በዚሁ የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ባለቤት ናቸው ተብለው የተለዩት ለዓመታት ከመምሪያ ኃላፊነት እስከ ሚኒስትር ዲኤታነት እስከ ሚኒስትርነት ባሉ ማዕረጎች በኃላፊነት ተሹመው በማገለገል ላይ ያሉ መሆናቸውም ታውቋል፡፡
ከዚሁ አነጋጋሪው የሰነድ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ የትምህርት ሚኒስቴር ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመለየት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ከመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌጤ ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ጥላዬ በፓርላማ ቀርበው ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተጠቅመው ወደ መንግስት ቢሮ የገቡ የስራ ሀላፊዎችንና ሰራተኞችን ለመቆጣጠርና ማስረጃዎቹንም ለመለየት የተጀረመው ስራ አልቆ በዚህ አመት ስራ ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ ስራው ከጠናቀቀ በኋላ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው በስራ ላይ የተገኙትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ እንደሚጀመርም ተነግሯል፡፡
በኦሮምያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ በሁለት ዙር ሲያጣራ ቆይቷል፡፡ በተደረገው የማጣራት ስራም በክልሉ ከ6,400 በላይ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው የተቀጠሩ ሰራተኞች ራሳቸውን አጋልጠው ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡
ሌሎች 8,300 የመንግስት ሰራተኞች ደግሞ የትምህርት ማስረጃቸው ሀሰተኛ እንደሆነ ተጠቁሞባቸው እየተጣራ መሆኑም ተሰምቷል።
በጋምቤላ ክልልም ባለፈው አመት በተደረገ ማጣራት የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሀላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናትና ሰራተኞች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተሹመውና ተቀጥረው እንደሚሰሩ ተደርሶባቸዋል፡፡
አሁን የትምህርት ሚኒስትር ከመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር ጀመርኩት ያለው የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመቆጣጠር የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ሲጠናቀቅ በሁሉም የትምህርት ማሰልጠኛ ተቋማት ስራ ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ዛሬ ለመንግስት ባለስልጣናት ማሳሰቢና ገለጻ ሰጡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ረፋዱን(ግንቦት 7) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለተሰበሰቡ የተለያዩ
የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በስራዎቻቸውና አሰራር ዙሪያ ገለጻና ማሳሰቢያ ሰጡ ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ መድረክ ላይ የራሳቸውን ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ በዚሁ ጽሁፋቸውም የአመራር ጥበብን በተመለከተ ገለጻ አድረገዋል። የህዝበ አገልጋይ ምን አይነት ሰብዕና ሊላበስ እንደሚገባና ምነ አይነት አገልግሎት በምን አይነት ጊዜና ቦታ መስጠት እንዳለበትም በተለያዩ አብነቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ገለጻቸው ወቅት እንዳሉትም፤ ሳምንታዊው የካቢኔ ስብሰባ ከአርብ ወደ ቅዳሜ መለወጡንና ሚኒስትሮች አርብ በስብሰባ ስም ጊዜ ማባካን እንደሌለባቸውና መደበኛ ስራቸውን እንዲሰሩ አሳስበዋል። አገሪቷ እያደገች መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ አድጋለች ከማለት ባሻገር በተጨባጭ ህዝቡ ምን ያህል ተጠቅሟል የሚለውን መፈተሽና ማረጋገጥ አለብን ሲሉም አስታውቀዋል። እያንዳንዱ የመንግስት አመራርም አሰራሩን ግልጽና ለህዝብ የማይደበቅ ማድረግ እንደሚገባውም ዶክተር አብይ አሳስበዋል። እያንዳንዱ ሚኒስትር ከዚህ በኋላ ለስብሰባ ሲመጣ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ሚኒስትር ሃሳብ አመንጪ እንጂ አቃቂር አውጭ አይደለም” ሲሉም ነው አጽንኦት የሰጡት። ከባለስልጣናት ጉዞ ጋር በተያያዘም ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተለይም በውጭ አገራት ባንኮች አካውንት ያላቸው ባለስልጣናት በአካውንቶቻቸው ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና ለዚህም አገራት ትብብር እያደረጉ መሆናቸውን
አስታውቀዋል። ከዚህ በኋላም የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ልዩ ልዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ከሚከታተሏቸው ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ጋር የስራ
ስምምነት መፈጸም እንደሚገባቸውና ስራቸውን በዚህ አግባብ እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከስብሰባው በሁዋላ ባለስልጣናቱን ከአዳራሽ ይዘው በመውጣት በአጼ ሚኒሊክ፣ በአጼ ኃይለሥላሴ እና
በደርግ ዘመን የተለያዩ ታሪካዊ ድርጊቶች የተፈጸሙባቸው በቤተመንግስት የሚገኙና እስካሁን ድረስ ዝግ የነበሩ የተለያዩ
ክፍሎችን አስከፍተው እንዲጎበኟቸው አድርገዋል።
በዚህም ባለስልጣናቱ የነገስታቱን የግብር ቤቶች፣ አጼ ሀይለስላሴ የተገደሉበትን፣ የደርግ ጄኔራሎች የተረሸኑባቸውን
ክፍሎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት ጎብኝተዋል።
ምንጭ ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Monday, May 14, 2018
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር ለመፍታት ተወስነ
በእስርና እንግልት ላይ የነበረውን የአርበኞች ግንቦት ስባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ከእስር ለመፍታት ተወስኖ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የተመራ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመለከቱ።
መረጃውን ለዋዜማ ያደረሱና ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደነገሩን አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈታ ውሳኔ ከተላለፈ በርካታ ቀናት ተቆጥረዋል። በቅርቡ ከእስር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።
አንድ የፍትሕ ሚንስቴር ባልደረባ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ጉዳዩ በመስሪያ ቤታቸው አካባቢ መነጋገሪያ እንደነበርና ጉዳዩ በከፍተኛ ባለሥልጣናት በኩል በምስጢር ተይዞ ቆይቷል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ሲፈታ በቀጣይ በሚኖራቸው የፖለቲካ ሚና ላይ ንግግር መደረግ አለበት ብለው የሚያምኑ ወገኖች እንዳሉ የነገሩን እኚሁ ግለሰብ በማረሚያ ቤቶች፣ በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ፣ ግንባሩ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ብድኖች እና በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽሕፈት ቤት መካከል መግባባት ለመፍጠር እየተሞከረ መሆኑን መስማታቸውን ነግረውናል። በአንዳርጋቸው ጉዳይ በአራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች መካከል ስለነበረ ውይይት ብዙ የተሰማ ነገር የለም። ይሁንና ብአዴን የሚደርስበትን የሕዝብ ጫና ለማስታገስ የአንዳርጋቸውን መለቀቅ ሳይገፋፋ እንዳልቀረ ይገመታል።
ስለጉዳዩ ከአንዳርጋቸው ቤተሰቦችም ሆነ ከአርበኞች ግንቦት 7 እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ወሬው ባለፉት 3 ቀናት በስፋት መሰማት የጀመረው ውሳኔውን በተለያየ ደረጃ ያሉ ሰዎች እንዲያውቁት በመደረጉ ሊሆን እንደሚችል የዋዜማ ምንጮች ተናግረዋል። የአቶ አንዳርጋቸው መፈታት በድርጅታቸው፣ አልፎም በአገሪቱ ፖለቲካ አቅጣጫ ላይ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ ብዙዎች በቅርበት የሚከታተሉት ጉዳይ ይሆናል።
አቶ አንዳርጋቸው ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ከሰንአ አውሮፕላን ጣቢያ በየመን እና በኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ሰራተኞች ታፍኖ መወሰዱ ይታወሳል። በእስር ላይም የተለያዩ ግፍና ማሰቃየት እንደተፈጸመበት ቤተሰቦቹ እና የትግል ጓዶቹ ይናገራሉ። በተቃራኒው፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ ቀርበው አንዳርጋቸው በጥሩ ሁኔታ መያዙን እንዲያውም “ከተማ ይጎበኛል፣ ላብቶፕ ተሰጥቶች መጽሐፍ እየጻፈ ነው” ብለው መናገራቸው ይታወሳል። ተመድ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የእንግሊዝ መንግሥት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አንዳርጋቸው እንዲፈታ ሲጎተጉቱ መቆየታቸው ይታወቃል።
ዋዜማ ራዲዎ
Sunday, May 13, 2018
የሺህ ማይል መንገድ በአንድ ይጀመራል
የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት ጥያቄ ወደ ህልውና ጉዳይ ተለውጦ፥ የነጻነት፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ትግል በርትቶ፥ በኦሮሞ ፕሮቴስት የጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ፥ ጎንደር ላይ በፈነዳው ህዝባዊ አመጽ ወደ አማራ ተጋድሎ ከፍ በማለቱ፥ በወያኔ ኢሕአዴግ ስርዓትና በገዥዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጠረ፥
ይህ አስደንጋጭ ክስተት መረን የለቀቀውን የሕወሃት/ኢሕአዴግ ፋሺስታዊ መንግስት የግዛት መሰረቱን ያናጋ፣ የገዥዎችን ህልውና አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፥ የስርአቱ ቁንጮዎች ሳይወዱ በግድ ፈጣን የማደናገሪያ ምላሽ ለመስጠት ተገደዱ፥ በተሃድሶ ስም የተነሳባቸውን የለውጥ ትኩሳት ለማስታገስ ብዙ ድንጋይ ፈነቀሉ።
ይህ ነበር እንግዲህ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የለውጥ ንፋስ ያመጣው፥
አንድ አጋጣሚ በመጠበቅ አንገቱን አቀርቅሮ ያደፈጠው የኦሮሞ ወጣት ቄሮ ጣና ኬኛ ኦሮሞ የኛ በሚል የአንድነት ማዕበል እየቀዘፈ ከመሃል ሸዋ እስከ ወለጋ ተጠራርቶ ጣናን ዘይሮ በውቧ ባህርዳር የአማራ ዋና ከተማ ተዝናንቶ ቁሰለኛውን ጎንደር በፍቅር እስትንፋስ ጠግኖ፥ ወጣትነት መልካም ነው ያለምንም አደራዳሪ ከአንተ በፊት እኔን ያርገኝ በሚል ቃል ዲዳን ታሪካቸውን አድሰው ተመለሱ።
የጣንን ጉብኝት ተከትሎ፥ ወጣቱ የኦሮሞ ፖለቲከኛ፥ ክልሉን ቄሮ በሚል ምትሃታዊ ስም አደራጅቶ፥ ቲም ለማን አስመርቶ፥ አብይን በቀኝ አዲሱን በእግራ አሰልፎ አቶ ለማ መገርሳ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው በሚል አማላይ ቃል ታጅቦ እንደ ሀምሌ ዝናብ ሳያጉረመርም በገዱ ግዛት በአማራ አደባባዮች ላይ ድንገት ተከሰተ። ወያኔዎች ሱሪያቸው መላላት ጀመረ፥ የአማራ እና የኦሮሞ ትብብር ሽብር ለቀቀባቸው።
በቲም ለማ መገርሳ Team Lema Megersa እና በገዱ አንዳርጋቸው ቡድን መደጋገፍ የወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ቁንጮዎች ዓይናቸው ደም ለበሰ፥ ህዝብ አምርሯልና የፈየደው ነገር የለም እንጂ በሚስጥርም ሆነ በይፋም ሹም ሽር ለማድረግ ሞከሩ።
ከዚህ በፊት ሲጠሩት የያዘውን ሁሉ ይጥል የነበረው ገዱ አንዳርጋቸው Gedu Andargachew ያልተገመተ ጽናት አሳየ፥ በእስራት ማስፈራሪያም ሆነ በስራ ቅያሬ ከቦታው ንቅንቅ የማይል ጀግና ወጣው፥ የሰጡትን የአምባሳደርነት ሹመት ስራየን አልጨረስኩም አልቀበልም አላቸው።
ብዙም ሳይቆይ ለግዛቷ የመበታተን፣ ለህዝቧ የመጠፋፋት አደጋ ለገጠማት አገራችን ኢትዮጵያ ይታደጋል ያሉትን የፖለቲካ ሃኪም ዶክተር አብይ አህመድን ከኋላ ሸሽገው፥ አንደበተ ርቱዕ ጀግና የሆነውን የኦሮምያ ክልል አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ለማ መገርሳን አስመርቶ፥ የአማራው ክልል አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው Gedu Andargachew ለውጡን በፊታውራሪነት እየመራው መሆኑ ግልጽ ሆነ።
የሃይል ሚዛኑን ላለማስነጠቅ ወያኔ ተፍጨረጨረች ግን አልሆነም፥ ቄሮ መሃል አዲስ አበባ መግባቱን አራት ኪሎ ቤተመንግስት ወረድ ብሎ በመሌኒየም አዳራሽ በወጣቱ የኦሮሞ አቀንቃኝ ዜማ አይናቸው እስኪፈጥ ድረስ ትለቃለህ ትሰዳለህ በሚል ፉከራ ለወያኔ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፥
ቲም ለማ እና ቲም ገዱ አዲስ አበባ ተጠርተው በኢቲቪ ማብራሪያ እንዲሰጡ፥ ጥርስ የሌለው ውሻ ሆኖ ቀረ እንጂ ለማስፈራራት ተሞከረ፥ አቶ አዲሱ Addisu Arega Kitessa የኦሮምያ ሙሁራን ይዞ፥ አቶ ንጉሱ ጥላሁን Nigussu tilahun የአማራ ሙሁራን ጋር ተደጋግፈው የወያኔውን አፈቀላጤ አፉን አስያዙትና በሚዲያ ዙሪያ ድል ተመዘገበ፥ Nigussu Tilahun አቶ ንጉሱ ጥላሁን በጭንቅላቱ ላብ እያጠመቀው መንዜነቱን በእልህ አስመሰከረ፥ እሰይ መክት አማራ ተባለ።
ሳይታሰብ ሊውጧቸው ነው ሲባል ለማና አብይ ከቲም ገዱ ጋር ተመሳጥረው ወያኔን ሸበለሉት፥ ዶክተር አብይ ሹመት ነው፤ ወይስ ምርጫ በሚባል የሚያሻማ ቃል Prime Minister Dr. Abiy Ahmed ጠቅላይ ሚኒስቲር ሆኖ ቁጭ አለና ነገራት ሁሉ በወያኔ ላይ ድንገት ተገለባበጡ።
የወያኔ ጉጅሊዎች አቦይ ስብሃትና አባይ ዲቃሎቻቸውን ይዘው ከፖለቲካው ጨዋታ ውጭ ሊሆኑ ስንዝር ቀርቷቸዋል፥ በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ ባህርዳር ላይ አይተውት የማያውቁት ውርደት ገጥሟቸው ለጌታቸው አሰፋ ስሞታ ሊናገሩ ወደ አዲስ አበባ መሄዳቸው ተሰምቷል።
ከዚያ በኋላ እየተከሰተ ያለው ነገር ቅጽበታዊ ነው፥ ትግሉ በይፋ ተጀመረ፥ የጥሎ ማለፍ ጨዋታው አገር ውስጥ ገባ፥ ታዋቂ ነን የሚሉ ድርጅቶች የጫጉላ ጊዜያቸው አለፈ፥በተለይ በውጭ የሚገኙት በሆነ ባልሆነው ሰበር ዜና ማስወራት ቀረና የሚያራግበው ሰው ቀነሰ፥ እውነቱ ግን ተቃዋሚው የሚያደርገውን ትግል አቁሞ ሳይሆን አገር ውስጥ በሚደረገው ግብግብ ቀልቡ ስለ ተያዘና ስራውን ወደዛ ስላደረገ ብቻ ነው።
ታዲያ እሄን ከውስጥ የተጀመረ የለውጥ ሂደት ተከትሎ ትግል ቀዘቀዘ፥ ለውጡ ተፋዘዘ፥ የሚሉ አንዳንድ ወገኖች በምናይበት ጊዜ፥ እነዚህ ሰዎች አንድም እኛ ያላማሰልነው ወጥ አይወጥወጥ በሚል የእኔነት አባዜ ተለክፈዋል፥ ወይም የፖለቲካን ሀ. ሁ.... አልተገነዘቡም በሚል እሄን ለማለት ተገደድን።
ፖለቲካ ተለዋዋጭ ነው፥ ፖለቲካ ሰጥቶ የመቀበል ተክህኖ የሚጠይቅ ጨዋታ ነው፥ የፖለቲካ ጉዞ እንደ ሁኔታው የትግል ስትራቴጅ እያወጣህ የምታስኬደው ፈጣን ነገር እንጂ እንደ ኃይማኖት አንድ ቦታ ግትር ብለህ ቆመህ የምትጠብቅበት የቁልቁለት መንገድ አይደለም ይላሉ ሙያውን ያጠኑ ሰዎች።
ነገር ሳላበዛ በምሳሌ ላስረዳና ላብቃ፥
አንዳንድ ጊዜ ዲል ያለ ሰርግ ተደግሶላቸው ያገቡ ሴቶች፥ በተለያየ ምክንያት መውለድ ላይ ይዘገያሉ፥ ታዲያ በትዳር ህይወታቸው የሚናገሩት አዲስ ነገር ገና ስላላፈሩ፥ ሰዎች በተዳሩ ቁጥር ስለራሳቸው ሰርግና ምላሽ እያሰቡ፥ ሌላውም ስለ እነርሱ ሙሽርነት ብቻ እንዲያወራ ይፈልጋሉ፥ እንዲያውም የእነርሱ ስም ካልተጠራማ ሰርግ በእኛ ጊዜ ቀረ አይነት ወሬ ይዘው የአዲሶቹን ሰርገኞች ፌስታና ድግስ በማናናቅና፥ ሙሽሮችን በማሸማቀቅ ተጽዕኖ ለመፍጠር ይሞክራሉ።
ሰሞኑን በተቃዋሚው ጎራ እየተሰማ ያለው ትግሉ ቀዘቀዘ የለውጥ ሂደቱ ተፋዘዘ ማለት ከዚህ የተለየ አይደለም። በተለይም ድምጻቸው ጎልቶ ይሰማላቸው በነበሩ የውጭ ሚዲያዎችና ዳያስፖራ ተቃዋሚዎች ተዘውትሮ ይነሳል።
ሲጀመር ትግል ይቁም ያለ ማንም ሰው የለም፥ በዚህም ሆነ በዚያ ያሉ ሰዎች ይቁም ቢሉም የህዝብ ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ፥ የትግል ስልቱ ይቀያየራል እንጂ ጨርሶ ሊቆም አይችልም።
አሁንም ትግሉ ከዳር አገር ወደ መሃል አገር ገባ እንጂ አልቆመም፥ የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቼውም በላይ እየታገለ ነው።
ታላቋ ሮም በአንድ ቀን አልተገነባችም፥ የሺህ ማይል መንገድ በአንድ ይጀመራል እንደምሉት
እንዲያ በዳዴ የጀመሩት ትግል ዛሬ ላይ ደርሷል፥ የዶክተር አብይ መንግስት ፈተናውን በአሸናፊነት ይወጣል ወይስ ይወድቃል በሂደት የሚታይ ነገር ነው።
እኛ ግን ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት እየተመኘን የአማራን ህዝብ እናደራጃለን፥ ትግላችን እንቀጥላለን።
ቲም ገዱ አንዳርጋቸው የቲም ለማን ድል በወያኔ ኢሕአዴግ ላይ እንዲደግም በማንኛውም መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የለውጥ ጉዞ እያበረታታን ለስር ነቀል ለውጥ እንታገል። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል፥
አማራ ሆይ መክት!
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር። Tiruneh Yirga
የአማራ ብሔርተኝነት ወግ በቤተ መንግሥት
በጣት ከሚቆጠሩ ደቂቃዎች በኋላ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ዶ/ር አቢይ አህመድ)፣ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ (አቶ ደመቀ መኮንን)፣የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ( አቶ ብናልፍ አንዷለም)፣የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ወደ መድረኩ መጡ፡፡
በመቀጠል አቶ ንግሡ ስለፕሮግራሙ በማስተዋወቅ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ የምግቢያ ንግግር እንዲያደርጉ ጋበዟቸው፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የመግቢያ ንግግር በአጭሩ፤
እንደ እሳቸው ገለጻ ወደ 23, 000 የሚደርስ ቁጥር ከቀይ ሽብር እና ደርግ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያን ጥሎ የተሰደደ ወይም በውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያ አለ፡፡ ይቅር ተባብለን አገራቸው ገብተው በሰላም መኖር አለባቸው አሉ፡፡ የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያምንም ይቀርታ አድርገንላቸው አገራቸው መጥተው መኖር አለባቸው አሉ፡፡
ስለ ሲኖዶሱ ሲናገሩም ፓትርያኩን አቡነ ማትያስን እንዳገኟቸውና ውጭ ስላለው ሲደኖዶስ እንዳወያይዋቸው፤ ሰላም ወርዶ አንድ ሆነው ጠንካራ ቤተ ክርስቲያን እንድትኖር ምኞታቸው እንደሆነ እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡
በመቀጠል በተለይ የብሔርተኝነትን ነገር ሲያነሱ ባልተቤታቸውን (ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽን) ምሳሌ በማድረግ ጉዳዩን ማብራራት ቀጠሉ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በዚህ የእራት ግብዣ ላይ ቀዳማዊት እመቤቷ ታድመዋል፡፡ ሌሎች ግብዣዎች ላይ እንዳልተገኙ ገልጸው የዕለቱ ግብዣ ግን የአማራዎች እንደሆነ ሲነገራቸው እንደመጡ ተናገሩ፡፡ ይህንን ሲናገሩ እኛ አጨበጨብን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የሚያስጨበጭብ አይደለም አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለፍቅር፣ስለአንድነት፣ስለይቅርባይነት በርካታ ቁምነገሮችን አካፈሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረው እንደጨረሱ አቶ ንጉሡ መድሩኩን እንዲመሩ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ጋበዙ፡፡ ዳንኤልም መጠነኛ ንግግር አድረጎ ውይይቱን በመምራት ለተለያዩ ሰዎች ዕድል ሠጡ፡፡
የእለቱ ሁለት ዓይነት ታዳሚዎች፤
=============
ታዳሚ አንድ-ኢትዮጵያዊያኖቹ ብቻ
---------------
ያው እንደተለመደው በርካታ አባቶቻቸችን እና እናቶቻችን አማራ የሚታወቅበትን የኢትዮጵያዊነት ባህርይ አስተጋብተዋል፡፡ አንዳንድ ወጣቶችም በተመሳሳይ በዚሁ መንገድ ተጉዘዋል፡፡ ስለ ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች አንስተዋል፡፡
ታዳሚ ሁለት-አማራየሆኑ ኢትዮጵያዊያኖቹ፤
---------------------------
በዚህ ምድብ ሥር የሚካተቱት ስለአማራ ብሔርተኝነት መንስኤውም ግቡም ከኢትዮጵያዊነት ጋር ስላለው ግንኙነትም አብራርተዋል፡፡ አስረድተዋል፡፡ የአማራ ብሔርተኝነት የተወለደው በበደል፣በመከፋት፣በመገፋት ነው፡፡ እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለመላው ጥቁር ሕዝብ መኩሪያ በሆነው ታሪኩ እንዲያፍርበት ተሠራ፡፡ እምዬ ምኒልክን ያህል መሪ ስም መጥራት እንኳን እንዲያሸማቅቅ ተደረገ፡፡ አማራ አገር ቢያቀና ነፍጠኛ ተባለ፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲል ማን ኢትዮጵያዊ ያልሆነ አለ ተብሎ ትምክህተኛ ተባለ፡፡ በተለይ በሁለተኛው ሚኒሊየም (ከ1000-2000 ) በተካነወኑ የአማራ ታሪኮች አማራ እንዲያፍር ሌት ተቀን ተሠራ፡፡ ቀና እንዳይል በሚያሸቅቅ ሁኔታ ደባ እና በደል እተሠራበት፡፡ በመሆኑም ከታሪኩም ከባህሉም እንዲነጠል በተደራጀ መንገድ ተዘመተበት፡፡
ከኢኮኖሚውም እንዴት እንደተነጠ እና እንደተበደለ በርካታ ማነጻጸሪዎች እየቀረቡ አስተያየት ተሠጠ፡፡ ለአብነትም በኢትዮጵያ ካሉ ደረጃ አንድ ኮንትራክተሮች ውስጥ እንደው ስም ያለው አንድ ኮንትራክተር አለን? የሚል ጥያቄያዊ ትችት ቀረበ፡፡ ከኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን ከፖለቲካውም የደረሰበበትን መገለል ተነግሯል፡፡ በመሆኑም የአማራ ብሔርተኝነትን የፈጠረው ከ1983 ዓ.ም. በኋላ የደረሰበት በደል እንደሆነ በበርካታ ወንድምና እህቶች ተብራርቷል፡፡ (የአንዳንዶቹን ስም ያልገለጽኩት ያው በሚታወቅ ምክንያት ነው፡፡ )
የአማራ ብሔርተኝነት ለማንም ስጋት እንደማይሆን በተለይ ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴ አብራርተዋል፡፡ ሕወሃት ስትመሠረት ጠላት አብጅታ ነው፡፡ አማራን ጠላት አድረጋ፡፡ የአማራ ብሔርተኝነት ግን ማንንም በጠላትነት አልሳለም፡፡ ራሱን ለመከላከል እንጂ፡፡ (ነገሩ ያው የመክት ጉዳይ ነው!) አማራ መቼም ቢሆን መቼም በኢትዮጵያዊነት አይደራደርም፡፡ ነገር ግን አማራ ደግሞ ላይመለስ አማራ ሆኗል፤ አማራ ነው፡፡ በመሆኑም የአማራ ብሔርተኝነት ለማንም ስጋት እንዳልሆነ ተብራርቷል፡፡
አብሮ በመድረኩ የተነሳው አማራ ክልልም ሆነ ብአዴን፣ ጸረ አማራ ወይም አማራ ጠል ከሆኑ አማራሮች እንዲላቀቅ ነው፡፡ እነዚህ አማራን የሚጠሉ ጸረ አማራ አመራሮች አማራን በመምራትም ሆነ እንደ ጆፌ አሞራ ሌሎችን በመዞርና አማራን በማጥቃት መቀጠል እንደሌለባቸውም ተወስቷል፡፡
በተለይ ከየክልሉ የሚፈናቀሉ አማራዎች ጉዳይ በዚህ ምሽትም ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡ ብጹእ አባታችን አቡነ አብርሃም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
የወሎ ቴሪሸሪኬር ሆስፒታልም ብዙ ሰው ከተናገረበት ጉዳይ አንዱ ነበር፡፡ ከከሚሴና አካባቢዋ የታደሙት አባቶች በአሸባሪነት ተከሰው ስለደረሰባቸው ግፍ ( ሽንት ሁሉ ይሸናባቸው እንደነበር) ሁሉንም ሰው ወደ ሐዘን ድባብ በከተተ ሁኔታ ተናግረዋል፡፡ ከሰሜን ወሎ የመጡ አንድ ጎልማሳም ስለወልዲያ፣ቆቦና መርሳ ሁኔታ ተናግረዋል፡፡ ሼክ አሊ አላሙዲንንም ለማስፈታት እንዲሞክሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዝጊያ ንግግራቸው፤
===============
በታወቀው ንግግር አዋቂነታቸው እና በበርካታ ምሳሌዎች አሁንም ስለመተባበር፣ስለ አንድነት፣ ስለ ይቅር ባይነት በተለይም እምዬ ምኒልክን በምሳሌነት በማንሳት አስረድተዋል፡፡ የንጉሥ ተክለሃይማኖትና የእምዬን ታሪክ አውስተዋል፡፡ ማርከው የሚያክሙ እንዲሁም የሚሾሙ መሆናቸውን እና ይቅር ባይነታቸውን በአርያነት አንስተው አስረድተዋል፡፡
በመጋረጃ የተሸፋፈነውን የጃንሆይን ዙፋን አስከፍተው መኩሪያችን እንደሆነ፣ከመስከረም ጀምሮ ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ሁሉ ተናገሩ፡፡ ላይኛው ቤተ መንግሥትንም (የምኒሊክ ቤተ መንግሥትንም)አስደናቂነት እና ሁላችንም የየድርሻችንን መወጣት እንዳለብን ተናግረዋል፡፡
የወሎ ቴሪሸሪ ኬር ሆስፒታልንም ከአቶ ደመቀ ጋር እንደተነጋገሩ እና ትኩረት እንደሚሰጡበት ተናግረዋል፡፡
የሼክ አሊ አላሙዲን ጉዳይንና ሌሎች በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ እሰረኞችን በሚመለከት ለመወያየት የፊተችን ሐሙስ ወደ ሳዑዲ እንደሚሔዱ ነግረውናል፡፡
ሦስት የመውጪያ ወጎች፤
========
አንድ
-----
አንዳንድ ሰዎች፣በዚሁ መድረክም ጭምር፣ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ቦታዎች መዟዟር እና መንቀሳቀስ ስላበዙ ጊዜ እንስጣቸው፤አሁን በየቦታው ቢዞሩም ቢሮ ሆነው ሥራ ባይሰሩም የሚል አንድምታ ያለው ንግግር ስለበዛ ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መደበኛ ሥራቸውን እና ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮችን እንደውም ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ሁለት፤
------
ጠቅላዩ በዚሁ ግብር ላይም ጭምር እንደታየው ስለደረሰ በደል ስለተወራ እሳቸውም ብዙዎቻችን ተበድለናል አሉ፡፡ ለዚህም ደግሞ ፊታቸው ላይ የወጣውን ማድያት አሳዩን፡፡ ስለማዲያቱ ሁኔታ ይምታውቀው ባልተቤታቸው እንደሆነችም ተናገሩ፡፡
( ይቺን ነገር ለታዳሚው ከመናገራቸው በፊት በእራት ሰዓት እኔና ጓደኞቼ (ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣አንዷለም አባተ/የአጸዴ ልጅ፣ምንዳራለው ዘውዴ፣ዶ/ር ሰጥአርጋቸው) ወደተቀመጥንበት መጥው ስለነበር የእኔን እጅ ይዝው ፊታቸውን አሳዩኝ፡፡) ፊቴን ማድያት በማዲያት እንዲሆን ያደረጉትን ልበቀል ብል ስንት ሰው ማሰር አለብኝ? አሉ፡፡ በመበቃቀል ፍቅር አይገነባም አሉ፡፡
ሦስት፤
------
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስም በብዙ ሰዎች በበጎ ተነስቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንዲህ አሉ፡፡ ሰዎች ብዙ ጊዜ በአድናቆት የሚናገሩት ስለ አቶ ገዱና አቶ ለማ መገርሳ እንዲሁም አልፎ አልፎ ስለ እኔ ነው አሉ፡፡ ነገር ግን መርሳት የሌለባችሁ ከእኛ ጀርባ አንድ ሰው ያሉ መሆናቸውን ነው አሉ፡፡ እሳቸውም አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው አሉ፡፡
በሉ ደህና እደሩ፡፡ ከምሽቱ 4፡30 አካባቢ ውይይቱ ተጠናቀቀ፡፡ እኔም ሌሊት ጻፍኩት፡፡ ለቴሌቪዥንም ይሁን ለሬዲዮ ቀረጻ አልተደረገም፡፡ ሞባይልም ካሜራም የለም፡፡"
(ውብሸት ሙላት)
Tuesday, February 6, 2018
“በአባቶቻችን ተጋድሎ የተገነባችውን ኢትዮጵያ እኛም አስውበንና አንድነቷን አስጠብቀን ለቀጣይ ትዉልድ የማሻገር ታርካዊ ኃላፍነት አለብን”
[OBN 29 05 2010]
የፌዴራል ስርዓቱን አደጋ ውስጥ ሊጥሉ የሚችሉ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለይቶ አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ የሕዝቡን መሻት ማሳካት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን በዝርዝርተመልክቷል፡፡ ፍትሃዊ የኃብት ክፍፍል፣ አሳታፊ የፖለቲካ ስርዓት፣ ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን በጥብቅ ዲስፒሊን በመስራት የሕዝብ እርካታን ማረጋገጥ ጊዜ የማይሰጠው መሰረታዊ አጀንዳ ስለመሆኑ መክሯል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በመተባበር የሀገራችንን ቀጣይ ጉዞ የማቅናት ሚናውን ዛሬም እንደትላንቱ መጫወት እንደሚገባውም ተወያይቷል፡፡
የፌዴራላዊ ስርዓታችንን አደጋ ላይ የጣሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን፣ ሕዝቡ በመሪ ድርጅቱ ላይ እንዲያምጽ ያስቻሉ የመልካም አስተዳደር እጦቶችን፤ስልጣን ህዝብን ማገልገያ መሳሪያ መሆኑንበመዘንጋትበርስትነት ይዞ ለግል ምቾትና ጥቅም ቅድሚያ መስጠትን፣ በነጻነት ተዘዋውሮ የመስራት መብትንነፍጎ በመቶ ሺህዎችየሚቆጠሩ ሕዝቦችንእስከማፈናቀል የደረሰ ድርጊትን፤ በኢንቨስትመንት ስም የመንግስትና የህዝብ መሬት መመዝበሩን፤እንዲሁም የሕዝቦች ሰላምና ጸጥታ መደፍረሱን እና የመሳሰሉትንእየተፈጸሙ ያሉ አደገኛ ድርጊቶችን ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ አምርሮ በመታገል የሀገራችንን ሕልውና መታደግ ልዩ ትኩረት የሚሹ አበይት ጉዳዮች መሆናቸውን በዝርዝር ተመክሮባቸዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተከሰቱ ግጭቶች የበርካታ ዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል፤የሕዝቦች በሰላም ዉሎ ማዳር፣ ወጥቶ መግባት ከፍተኛ ስጋት ላይ ወድቃል፡፡ለእነዚህ ችግሮች መከሰት ኃላፊነቱን ወስዶእርማት ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ አጽንኦት ሰጥቶ በመምከር አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ቀንደኛ የሕልውናችን ጠላት ድህነት መሆኑ ቢታወቅም ይህንን ጠላት ለመዋጋት በመንግስት፣ ድርጅትና ሕዝብ ትስስር ሊሰራ እንደሚገባውና አዳዲስ ሃሳቦችን አያፈለቀ አመራር የመስጠት ጉዳይ ከድርጅታችን እንደሚጠበቅ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው ድርቅ፣ ግጭት፣ስደት፣ የሕዝብ መብዛትያልተደራጀ ኢኮኖሚና ያልደበረ የዲሞከራሲ ባህል ባለበት ሀገርነገሮች እንዲባባሱ ከማድረግ አልፎ የሀገር ህልውናን አደጋ ውስጥ እስከመጣል እንደሚደርስ ታውቆየተሻለች ሀገር የመፍጠሩና ብዙ ተረካቢ የማፍራቱ ተግባር በጥንቃቄና በኃላፊነት ስሜት እንዲከወን በዝርዝር ተመክሯል፡፡
ይህንንም ከማሳካት አኳያ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ተግባራት መካከል ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ከጊዜያዊ መጠለያ ወደ ቋሚ ቦታ ማስፈር፤የወጣቶችን የስራ አጥነትን በመቀነስ የኑሮ ሁኔታቸውን ማሻሻል፤ የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራሮችን ማስተካከል፤የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ማዘመን፤ፍርድ ቤት፣አቃቤህግ፣ፖሊስ፣ የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮችን መልሶ ማደረጀት፤ሰላምና ፀጥታ በማስከበር የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ይገኙበታል፡፡
በመላ የሀገራችን ህዝቦች ይሁንታ አፋን ኦሮሞ የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆንድርጅታችን ይሰራል፡፡ በተጨማሪም በሂደት ላይ ያሉና ያልተጠናቀቁ መሰረታዊ የህዝብ ጥያቂዎች በጥብቅ ዲስፕልን እዲፈጸሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በድርጅቱተጠያቅነትን ለማረጋገጥ፤መድረኩ የሚጠይቀውን የትግል ልክ በብቃት ለመፈፀም፣ በቀጣይም ጥንካሬውን አጎልብቶ መጓዝ ይችል ዘንድ 14የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት እንዲተኩ እና4 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም እሰከሚቀጥለው ጉባኤ እንዲታገዱና አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በማስጠንቂያ እንድታለፍ የወሰነ ሲሆን የዉስጠ ድርጅት ዲሞክራሲ የማስፋትና የአመራሩን የሃሳብና የተግባረ አንድነት ይበልጥ ማጠናከር በቀጠይነት እዲሰራበት ተመክሮዋል፡፡
================================
ለዘመናት ትከሻህ ላይ ተጭኖ የነበረውን የጭቆና ቀንበር ለመስበር ሁልጊዜም ታሪክ እየዘከረው የሚኖር አኩሪመስዋዕትነት ከፍለሃል፡፡ በከፈልከው መስዋዕትነት ከሌሎች ወንድሞችህ ጋር በመሆን አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመፍጠር፤ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲና ሁሉን አቀፍ መብቶች የተረጋገጡባትን የበለፀገች ሀገር ለመገንባት መሰረት ጥለሃል፡፡ በተጀመረው የግንባታ ሂደት ውስጥ የመጡ ተስፋ ሰጪ ድሎች እንዳሉ ሁሉ የጭቆና መሰረት የሆኑ አስተሳሰቦችና አሰራሮችን የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችም ይታያሉ፡፡ በነዚህ አዝማሚያዎች ላይም የጀመርከውን ትግል አጠናክረህ መቀጠል ያንተም ሆነ የወንድም ሕዝቦች የሕልውና ጉዳይ ነው፡፡
የመደብ ጭቆና ምን ያህል አስከፊ እንደሆና አዎንታዊ ለውጥን እንደሚገታ ባለፈው ታሪክህ ካንተ በላይ የሚገነዘብ የለም፡፡ በአሁኑም ሰዓት ተመሳሳይ መደባዊ ጭቆና ዳግም በሀገራችን እንዳያቆጠቁጥ ትግልህን አጠንክረህ መቀጠል ይገባሃል፡፡
================================
በሁሉም የታሪክ ምዕራፍ ላይ የኦሮሞ ሕዝብ ባለፈበትየትግል ሂደት ውስጥ እናንተም መስዋዕትነት ከፍላችኋል፡፡ አሁንም በደረስንብት የትግል ምዕራፍ ውስጥ ከሕዝባችሁና ከመሪው ድርጅታችሁ ኦህዴድ ጋር በመሰለፍ ዋንኛው ሥራ የሆነውን ሃሳብን የማፍለቅና የትግሉን አቅጣጫ በጥናትና በምርምር የማሳየት የማይተካ ሚናችሁን እንደሁል ጊዜው መወጣት ይኖርባችኋል፡፡ ድርጅታችን ኦህዴድ፣ ምሁራንን ባላቸው አደረጃጀትም ሆነ በግል ክህሎታቸው፣እውቀትና የአመራር ብቃትም ጭምር አብሮ ለመስራት የጀመረውን ሥራ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ ለመቀጠል ወስኗል፡፡ በዚሁ መሰረት የተከበራችሁ የኦሮሞ ምሁራን የጀመራችሁትን ጠንካራና ተኪ የሌለው ሚናችሁን በመወጣት አጠናክራችሁ ትግሉን እንድትቀጥሉ፣ ለስኬትም እንድትረባረቡ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
================================
የኦሮሞ ሕዝብ ባደረገው ትግል የራሱን ክልል መስርቶ ያሉበትን ችግሮች ለመፍታትና ራዕዮቹን ለማሳካት ትልቅ የመንግስት መዋቅር ዘርግቷል፡፡ በዚህ መዋቅርውስጥ የሕዝባችንን ችግር መፍታት የሚቻለው ከእውቀትና ክህሎት በተጨማሪጠንካራ ዲሲፒሊን ባለው የመንግስት ሰራተኛ ነው፡፡ በመሆኑም፣በመንግስት መዋቅር ውስጥ እየፈጠረበት ያለውንየመብት ጥሰት፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ እየተስፋፋ ያለው ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ኢ-ፍትሃዊነትና የዴሞክራሲ እጦት ችግሮችን ለመፍታትየክልላችን መንግስት ሰራተኞች ቁልፍ ሚና አላችሁ፡፡ሕዝባችንን አንገት ያስደፋውን ዋነኛ ችግሩንበመቅረፍ ብልጽግናን ለማስፈን፣ የማስፈፀም አቅምን ለማጎልበት፣ቀን ከሌሊት ተግታችሁ የመስራት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
================================
በክልላችን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ከሕዝባችን ጋር በተለይም ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት የሕዝባችንን ጥቅምና ሀብት ሲዘርፉ የነበሩ ኮንትሮባንዲስቶች ላይ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም በክልላችን የተጀመረውን ሪፎረም ለማደናቀፍ ዝርፊያ ድርጊታቸውን ማስቀጠል የሚፈልጉ የተደራጁ ኪራይ ሰብሳቢዎች የከፈቱትን ጥቃት ለመመከት በግንባር ቀደምነት ተሰልፋችሁ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍላችኋል፡፡ በዚሁም የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ሕልውና እንዲቀጥል ድርሻችሁን በመወጣት ከአደጋ እየታደጋችሁ ትገኛላችሁ፡፡
================================
ተንሰራፍቶ የቆየውን ጭቆና ለማስወገድ ሕዝባችን ሲያካሄድ በነበረውን መራራ ትግል ውስጥ የመርነት ሚናንተቀብለህ መስዋዕትነት በመክፈል የዛሬው ምዕራፍ ላይ እንዲደርስ የበኩልህን አስተዋፅኦ አበርክተሃል፡፡ ጠንካራ ድርጅት ያላ ጠንካራ አባል ሊታሰብ አይችልም፡፡ ኦህዴድ ያለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት እንዲወጣ አሁን በደረሰበት የትግል መድረክ የሚመጥን ቁመና እንዲኖረው ለማስቻልና ለማስቀጠል የድርጅታችን አባላት የድርጅታችሁን አላማ በጥብቅ ዲስፒሊን ለማሳካት ቀን ከሌሊት መታገል ይገባችኋል፡፡ ሕዝባችን በተለያየ ደረጃ እያደረገ ባለው ትግል ውስጥ አባሎቻችን በግንባር ቀደምነት በመሳተፍና በመምራት ችግሮችን በኃላፊነትመፍታት ይገባቸዋል፡፡ አሁን የደረስንበት የትግል ምዕራፍ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት በቅድሚያ በመክፈል ለሌሎች ምሳሌ በመሆን የድርጅታችሁን ተልዕኮ በተሰማራችሁበት መስክ ሁሉ በማሳካት የሕዝባችንን ጥያቄ በአፋጣኝ እየመለሰ፣ ትግሉን በግንባር ቀደምነት በመምራት አዲሲቷን ኢትዮጵያ እውን የማድረግ ኃላፊነቱን የሚወጣ፣ ጠንካራና ከለውጥ ጋር ራሱን የሚያሳድግ ድርጅት እውን እያደረጉ መጓዝትኩረት የሚሻ በመሆኑ ይህንንም በብቃት መወጣት ይገባችኋል፡፡
================================
በኦሮሞ ሕዝብ የለውጥ ጉዞ ውስጥ ባላችሁ እውቀትና ኃብት በተደራጀም ሆነ ባልተደራጀ መልኩ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ለመወጣት ስታደርጉ የነበረውን ርብርብ የሚፈታተኑ ሁኔታዎች እንደነበሩ እና መድረኮችም አስቸጋሪ እንደነበሩ ኦህዴድ ይገነዘባል፡፡ በሕዝባችን አንድነትናሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ፣ባላችሁ ተሞክሮዎና ትስስር፣ በኃብትና በመሳሰሉት ሁሉ እንድትሳተፉና የሕዝባችንን ችግር በጋራ እንድንፈታ፤ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችም እንዲመቻቹ ኦህዴድ ጠንክሮ እንደሚሰራ ሊያረጋግጥ ይወዳል፡፡ በዚሁ መሰረት በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች በሕዝባችን ጥቅም ላይ ያለምንም ድንበርና ልዩነት በጋራ እንድንሰራ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
================================
ድርጅታችን ኢህአዴግ፣በሀገራችን ሕዝቦች ላይ የተጫነውን ጸረ-ዴሞክራሲ፣ ድህነት፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና ኋላቀርነትን ለመፍታት ባደረገው እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ ድሎችን ማስመዘገብ የጀመረው በውስጡ ያለውን ችግር በተከታታይ በመፈተሽና በመፍታት ላይ ነው፡፡ በቅርቡ በኢህአዴግ ደረጃ በተደረገ ግምገማ በእህት ድርጅቶቹ መካከል የተፈጠረው ያልተገባ ግንኙነትበሂደትም ወደ ጥቅም ቡድተኝነት እያደገ በመምጠቱ የነበረው ግንኙነት እያሻከረ እንዲሄድ አድረገዋል፡፡ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴም ጉዳዩን በጥልቀት በመገምገም ማንኛውም ግንኙነቶች መርህና መርህ ላይ ብቻ እንዲመሰረቱና ዴሞክራሲያዊ ትግልን ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ ለማስቻል ትኩረት ሰጥቶ ተወያይቶበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ በዚሁ መሰረት የእህት ድርጅቶች አሁን በደረስንበት የትግል ምዕራፍ በግንባራችን ኢህአዴግ ተገምግመው አቅጣጫ የተቀመጠባቸውን ጉዳዮች ያለምንም መሸራረፍ እንዲፈፀሙና የሕዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት ርብርብ እንድናደርግ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
================================
በብዝሃነት ለተገነባች ሀገራችን ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የህልዉና ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እንደ ነብር ዥንጉርጉር የሆነው የእርስ በእርስ ግንኙነታችን የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ የሚያስችል አሰራርና ባህል ማዳበር ያስፈልገዋል፡፡ከሃይል የፀዳ፣ በዉይይትና በምክክር የሚያምን፣ ይበልጥ ለሀገር የሚበጅ ሃሳብ የሚፈልቅበት የውይይት ባህል እንዲዳብር የፖለቲካ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡በዚህ ወሳኝ ወቅት የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተዋይነትና አርቆ አሳብነት የሚፈተንበት ጊዜ መሆኑ ግለፅ ነው፡፡ በመቀራርብና በመነጋገር የፖለቲካ ባህላችንን እንድናሻሽል ብሎም የሀገራችንን መፃኢ ዕድል በጋራ ማበጀት እንችል ዘንድ ተቀራርበን እንድንሰራ ድርጅታችን ይፈልጋል፡፡
================================
የኢትዮጵያ ብሔር፤ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በችግርም ሆነ በመልካም ጊዜ በጋራ ተፈትነው ትላንትን መሻገር ችለዋል፡፡ ለገጠማቸው ፈተናዎችምእኩል የታገሉና መሰዋትነት የከፈሉ ህዝቦች ናቸው፡፡ ሀገራችን ህልዉ ሆና እድትቀጥል ከማስቻላቸዉ ባሻገር በዓለም ታሪክ ውስጥ ጉልህ ቀለም እንዲኖራት አድርገውለዛሬ ትውልድ አሰረክበዋል፡፡በአባቶቻችን ተጋድሎ የተገነባችውን ኢትዮጵያ እኛም አስውበንና አንድነቷን አስጠብቀን ለቀጣይ ትዉልድ የማሻገር ታርካዊ ኃላፍነት አለብን፡፡በአንድ እጅ ማጨብጨብ አይቻልምና ይህን ሀላፍነታችን በብቃት እንድንወጣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትንበማጠናከር፣ የጋራ እሴቶቻችንን በማጎልበት፣ የተጀመረው መልካም ጅማሮ ዳር እንዲደርስ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለስኬቱ በጋራ እንድንረባረብ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ጥር 29/05/2010 ዓ.ም
Thursday, December 28, 2017
በጦርነት እየታመሰች ባለችው የመን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የሚደርስልን አጣን እያሉ ነው።
Tuesday, December 26, 2017
መረጋጋት ያልቻሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
Recent Articles
Recent Video Uploads
Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube
Ethiopia Today
- Active a minute ago with many
- videos