Friday, August 3, 2018

ተስፋ ሰጭው የሳይንስ ትግበራ -የሮኬት ሙከራ

ተስፋ ሰጭው የሳይንስ ትግበራ፡፡

‹‹የማዕከሉ ሙከራዎች ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ለመድረስ ላሰበችው እቅድ አቅም ይሆናል።››
‹‹የተማሪዎችን ፈጠራ በእውቀት እና በገንዘብ የምንደግፍበት ወቅት ነው›› የባሕርዳር ሳይንስ ማበልፀግያ ማዕከል፡፡

ሳይንስ ለችግሮች መፍትሄ ለማምጣት የምንጥርበት የእውቀት እና ክህሎት መድረሻ ነው። የሁሉም ስኬታማ ሳይንስ መነሻው ችግር ፣ ትንንሽ ሙከራዎች እና የሚያድጉ ፍላጎቶች ናቸው።
በባሕርዳር ሳይንስ ማበልፀግያ ማዕከል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ሮኪቶችን ማምጠቅ የሚቻልበትን ሳይንሳዊ ትግበራ እየሰሩ ነው።
የ11ኛ ክፍል ተማሪዎቹ ናሆም ፈረጃ እና ኑር አህመድ አባይ በውሃ ሃይል እምቅታ እና በኬሜካል የሚመጥቁ ሮኪቶችን ሰርተዋል።
የተማሪዎቹ ግኝት ከሶስት ዓመታት በላይ የወሰደ ሳይንሳዊ ግኝት ነው የሚሉት የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋየ ሽፈራው ሳይንስን መተግበር እንደተጀመረ ማሳያ ነው ይላሉ።
ዶክተር ተስፋየ እውነታው ግን ተማሪዎቹ በውሃ እምቅታና በኬሜካል ሊያመጥቁ የሚችሉ ትግበራዎችን በግሃድ ማሳየት የሚችሉበት አቅም ፈጥረዋል።
የሚሰሩት ቁሳቁስ በአከባቢው ከሚገኙት በመሆኑ የሚወነጨፈው ሮኪት ለሃገራዊ ጥቅም የሚውል አይደለም። እንደነዚህ አይነት ሙከራዎችን ግን ከትንሽ እስከ ትልቅ ችግር ለመፍታት እንዲያስችል ወደ ምርት ለማስገባት እገዛዎች ያስፈልጉናል ብለዋል።
የተማሪዎችን ፈጠራ ጥቅም ላይ ለማዋል ተጨማሪ እውቀት ማበልፀግ እና በገንዘብ የምንደግፍበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ለመድረስ ላሰበችው እቅድም አቅም የሚያጎለብቱ በመሆኑ ተማሪዎቹ የተሻለ ስልጠና እንዲያገኙ በገንዘብ እንዲደገፉ መስራት እንደሚያስፈልግ ዶክተር ተስፋየ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ






No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time