Tuesday, June 18, 2024

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

 ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ያቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ። ዛሬ እና ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ፣ ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።
ሶስቱ ጋዜጠኞች የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” ማድረጉን በመጥቀስ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት ነበር። ከአቤቱታ አቅራቢዎች አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ በላይ ከእስር የተፈታው፤ ዛሬ ሰኞ ሰኔ 10፤ 2016 ከሰዓት መሆኑን ባለቤቱ በላይነሽ ንጋቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግራለች።
“ኢትዮ ኒውስ” የተሰኘው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ በላይ፤ በህዳር 2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለው በኋላ ለሰባት ወራት በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በእስር ላይ ቆይቷል። ጋዜጠኛው ባለፈው ግንቦት ወር አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መዘዋወሩ ይታወሳል።
አስር ወራትን በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በእስር ያሳለፈው ሌላኛው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ፤ ባለፈው አርብ ሰኔ 7፤ 2016 ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ከተደረገ በኋላ በማግስቱ ከእስር መለቀቁን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል። “ምኒልክ” እና “ዓባይ”በተሰኙ የበይነ መረብ እና የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናሎች ላይ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ፕሮግራም ያዘጋጅ የነበረው ቴዎድሮስ፤ በፖሊስ ቁጥር ስር የዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፓርላማ ከጸደቀ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነበር።
 ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ


No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time