Sunday, May 20, 2018

ጤፍንና ገበሬውን ከኢትዮጵያ የማጥፋት ዘመቻ

ጤፍንና ገበሬውን ከኢትዮጵያ የማጥፋት ዘመቻ?!
ውድ ኢትዮጵያውያን ይህንን ጽሁፍ በትእግስት እንድታነቡትና ሁኔታውን በውል እንድትመረመሩት አሳስባለሁ::
ኢትዮጵያ በግብርና ምርት ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ብትደርስ የሚጠላ ዜጋ የለም።ሆኖም አግባብ ባለውና የተፈጥሮ ሚዛንን በጠበቀ መንገድ እንጂ፤ እንዲሁ በምእራባውያን ፍላጎትና ግፊት ምንነቱ ባልታወቀ የኬሚካል ውህድ በመጣ ዘር መሆን የለበትም።በተመረዘ ምርት ከመጥገብ በጤና መራብ ይሻላልና።
ሰሞኑን በሳይንስና በቴክኖለጂ ሚንስቴር በኩል አንድ የምስራች የመሰለ አስደንጋጭ ዜና ይፋ ሆኖዋል።
ከዜናው እንጀምር።
"የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር አንድ ጊዜ ተዘርተው ለ10 እና ለ 20 አመታት በውሀ ብቻ ምርት መስጠት የሚችሉ የጤፍ እና የማሽላ ዝርያዎች በምርምር መገኘታቸውን አስታወቀ።
የተገኘው የጤፍ ዝርያ አንድ ጊዜ ከተዘራ በኋላ ለ10 አመት የማይሞት እና በየሶስት ወሩ ውሀ ብቻ ካገኘ ምርት መስጠት የሚችል ነው ተብሏል።
አዲሱ የጤፍና የማሽላ ዝርያ አንድ ጊዜ ተዘርቶ ለ20 አመት ድጋሚ መዝራት ሳያስፈልግ በየሶስት ወሩ ምርት መስጠት ይችላል ነው የተባለው።
አሁን ላይም ዝርያዎቹን ለሃገሪቱ ገበሬዎች ለማከፋፈል የዘር ብዜት ስራ እየተሰራ ሲሆን፥ ዝርያዎቹ በ2011 ዓ.ም የምርት ዘመን ለገበሬው የሚከፋፈሉ ይሆናል።
በኢትዮጵያዊ ተመራማሪ የተገኙት እነዚህ ዝርያዎች የኢትዮጵያን የሰብል ልማት ታሪክ መቀየር እንደሚችሉ ታምኖባቸዋል።"ይላል ዜናው።
ልብ በሉ!ይህ ግኝት በኢትዮጵያዊ ተመራማሪ አማካኝነት ተገኘ ተባለ እንጅ የግኝቱ ባለቤት የትኛው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ በግልጽ አይታወቅም።"በኢትዮጵያውያን አማካኝነት"የሚለውም የተለመደው የምእራባውያን ማምታቻ መሆኑን ከልምድ እናውቃለን::
በኢትዮጵያውያን አማካኝነት ወይም በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል በተካሄደ ምርምር የተገኘ ቢሆን ኖሮ፤ ይህ አይነቱ ዘር ለኢትዮጵያውያን ገበሬዎች እንደማይሆንና እንደማይጠቅምም በግልጽ ይታወቅ ነበርና ቀድሞ ቅድመ ዝግጅት ይደረግበት ነበር::ምክንያቱም የኢትዮጵያ ገበሬ ለምሳሌ ጤፍ ሲዘራ ቅድመ ዝግጅቱን በሰኔ ወር አጠናቅቆ ሃምሌ ላይ ዘርቶ ወቅቱን ጠብቆ አርሞና ጎልጉሎ ታህሳስ አካባቢ አጭዶና ከምሮ ከውቂያ በሁዋላ ምርቱን ይሰበስባል። ምርቱን ከሰበሰበ በሁዋላ ቃርሚያውን ለከብቱ ያበላል፤ጭዱንም እንደዚያው።
ከዚያ በሁዋላ ያ መሬት እንደገና ለአቅመ ጤፍ መዝሪያ ለመድረስ የራሱ የጊዜና የአየር ንብረት ሁኔታ ይፈልጋል።ይህ አይነቱ የጊዜና የአየር ንብረት ሁኔታ ደግሞ ከአዲሱ ግኝት ጋር ይጋጫል።በአዲሱ የዘር ግኝት መሰረት ዘሩ አንዴ ተዘርቶ ውሃ በማጠጣት ብቻ በየሶስት ወሩ ምርት ይሰጣል ከተባለ፤ የአረምና የጉልጉሎ ጉዳይ በየትኛው የጊዜ ልኬት ይከናወናል?አዱሱ ዘር ከተዘራ አረምም ጉልጉሎም የለም ከተባለ እንዲህ አይነት ምርት የጤፍ አለመሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል::ጤፍ በሃምሌ ይዘራል ሲባልኮ ሃምሌ ክረምት ስለሆነና ጤፍም ውሃ ስለሚፈልግ በዚያ ወቅት በመዘራቱ ምክንያት ውሃ እንደልብ ስለሚያገኝ ይስማማዋል ማለት አይደለም::ውሃ ብቻ ሳይሆን ከጸሃይ ብርሃንና ከደመና ጋር የተያያዘ የራሱ ፍላጎትና ጸባይ አለው::ከመሬት ጋርም እንዲሁ::ባጭሩ ጤፍ ውሃ ብቻ ስላገኘ ምርት የሚሰጥ ሰብል አይደለም።እንደዚያ ቢሆን ኖሮ በየትኛውም አካባቢና አገር ወይም በማንኛውም አይነት ውሃ ጠገብ የመሬት አይነት መብቀልና ምርት መስጠት ይችል ነበር::
ይህ ብቻ አይደለም አንድ የኢትዮጵያ ገበሬ ውሃ እንደ ልቡ አገኘ ብለን እናስብና በአዱሱ ግኝት አማካኝነት በየሶስት ወሩ ምርት ማግኘት ቻለ ብንል እንኩዋ፤ምርቱ ታጭዶ ከተከመረ በሁዋላ ራሱን በቻለ የጊዜ ልኬት መሰረት በጸሃይ ብርሃን መድረቅ አለበት::ለውቂያ ለመድረስ የግድ የታህሳስ አካባቢን የጸሃይ ብርሃን ይፈልጋል።ጤፍን ካጨዱ በሁዋላ ከጊዜው ቀደም ብሎ ወይም አሳልፎ መውቃት አይቻልም።በህዳር የታጨደን ጤፍ በጣም ቢዚ ነኝና ወደ መጋቢት ወይም ወደ ግንቦት አካባቢ እወቃዋለሁ የሚባልበት አካሄድ የለም::ወይም ጤፍን በመስኖ አማካኝነት ባሻን ጊዜ ዘርተን ባሻን ጊዜ ወቅተን የምናመርተው ምርት አይደለም።
የኢትዮጵያ ገበሬ የተፈጥሮን ሚዛን ጠብቆ ለብዙ ሺ ዓመታት ሲያመርተውና ሲመገበው ብሎም ሌላውን ሲመግብበት የኖረው የኢትዮጵያ ጤፍ በአይነቱም በአፈጣጠሩም በጸባዩም በይዘቱም በአየርና በመሬት ምርጫውም ሆነ በአመራረት ሂደቱ ከሌሎች ሰብሎች ፍጹም የተለየ ሰብል ነው::ጤፍ እንኩዋን በየሶስት ወሩ በአመት ሁለት ጊዜ ሊያመርቱት የማይችሉት ለየት ያለ ሰብል ነው።ሆኖም ዘመኑ የቴክሌጂ ነውና ተቻለ!ሊሉን ይችላሉ።ይህ ከተቻለ፤የተቻለበት ምክንያት የውስጥ ይዘቱ ወይም የጤፉ ፍሬ /ኢንግሪዲየንት/ የጤፍ ሳይሆን መልኩና ዘሩ ጤፍ መስሎ፤ነገር ግን ሌላ መርዛማ ኬሚካል ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው።ወይም ከጤፍ የሚገኘውን ነገር ያላካተተ ሌላ ባእድ ነገር!
ይህ በትክክል የምእራባውያን ሴራ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃ መደርደር ይቻላል::ባጭሩ ግን ጤፍ በባህሪው በየሶስት ወሩ ሊደርስ የሚችል ሰብል ካለመሆኑም በላይ ውሃ ስላገኘ ብቻ የሚመረት ሰብልም አይደለም!በዚህ መሰረት ይህን አዲሱን የጤፍ ግኝት በመዝራት የሚቆጠበው ምንድነው?ስንል ምላሹ ለዘር የሚሆነውን ሰብል ብቻ የሚል ይሆናል!ይህ ደግሞ ትርፍ አይባልም።ምክንያቱም በአንድ ሄክታር ላይ/አንድ ስቴዲየም በሚያክል መሬት ላይ/ ጤፍ ለማምረት የሚዘራው ዘር 20 ወይም 30 ኪሎ ግራም ጤፍ ብቻ በቂ ነውና።
ይህን ለመቆጠብና ገበሬውን ለማገዝ ከተባለ ደግሞ አስቂኝ እገዛ ይባላል!ገበሬውን ለማገዝ ከተፈለገ ከፍተኛውን የማዳበሪያ እዳ መቀነስ ወይም በነጻ መስጠት ያልቻለ ሴክተር ይህን ለገበሬው ጥቅም ስል ያደረኩት ነው ሊል አይችልም!ይህ ብቻ አይደለም።ገበሬው ይህን ዘር ዘርቶ ለ 10 እና ለ 20 ዓመታት ሳይዘራ ቁጭ አለ ማለት፤ ብዙ ነገር ማለት መሆኑ እንዳለ ሆኖ፤ያ መሬት ለሌላ ግልጋሎት እንኩዋ መዋል አይችልም ማለት ነው።የጤፍ መሬት ደግሞ ዘንድሮ ጤፍ ቀጥሎ ሌላ እየተዘራበት የሚብላላ የመሬት አይነት ነው።ጤፉ ታጭዶ ቃርሚያውን ከብቶች ሲመገቡት እንኩዋ ከምግብነት ባለፈ መሬቱ በከብቶች እንዲረገጥና መሬቱም እንዲናፈስ እንዲፍታታ የሚያደርጉበት ዘዴ ነው።የጤፍ መዝሪያ ወቅት ከመድረሱ በፊት ማሽላም ምንም እየተዘራበት የሚቆይ መሬት ነው።ገበሬው በእያንዳንዱዋ እለት የሚፈጽማት ተግባር ከተፈጥሮ ሚዛንና ከአየር ጸባይ ብሎም ከሌሎች ከወቅት ጋር ከተቆራኙ፤ ያለ ፊዚክስ ቀመር ፍሰታቸውን ጠብቀው ከሚተካኩ ከወቅት ክፍልፋዮች ጋር ራሱን አስማምቶና አዋህዶ የሚኖር ሊቅ ነው።ገና ለገና ምንም ምርጫ የሌለውና በማዳበሪያ እዳ እስረኛ የሆነ ማሃይም ነው ተብሎ የባእዳን ፍላጎት በግፍ ሊጫንበት አይገባም።ስለዚህ እንዲህ ያለውን ነገር የአገር በቀል ተመራማሪ ሊቀምረውና በኢትዮጵያ መሬት ላይ በኢትዮጵያዊ ገበሬዎች አማካኝነት ተግባራዊ ሊያደርገው አይደፍርም አይሞክርም ነበር።ነገር ግን ፍላጎቱና ግፊቱ ከምእራባውያን ሆነና ያለምንም የግንዛቤ ማስባጫ ትምህርትና ያለአንዳች ማብራሪያ በቀጣዩ ዓመት ለገበሬዎች ይከፋፈላል ተባለ።ይህንን አካሃድ አንድ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያዊ ነገሩ እስኪገባው ድረስ ሊቃወም፣ አስረዱን ሊልና፤ ሊጠይቅ ይገባል።ለገበሬውና ለሴክተር መስሪያ ቤቱ ብቻ የሚተው ጉዳይም አይደለም!
ለመሆኑ የትና እንዴት፤መቸና በምን መልኩ፤ በየትኛው ቤተ ሙከራና በየትኛው ክልል በሚገኝ መሬት ላይ ተሞከረ?ተሞክሮ ውጤታማ የሆነበት የምርምር ጣቢያ የት የሚገኝ ነው?ስለዚህ ጉዳይስ ሴክተር መስሪያ ቤቱ ለህዝቡ ጅምሩንና ሂደቱን የገለጸው መቸ ነው?ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።ሚንስቴር መ/ቤቱ በዚህ ጉዳይ ላይ እየተመራመረ እንደሆነ/እንደነበረ/
በምንም አይነት መንገድና ሁኔታ ፍንጭ የሰጠበት ጊዜ የለም።ለዚህ ነው የኢትዮጵያውያን ግኝት ሊሆን አይችልም!ብሎ በድፍረት እውነታውን ለመናገር የተደፈረው።ይህ በቀጥታ የምእራባውያን ሴራ ነው!
ይህ ነገር ተግባራዊ ሆነ ማለት ብዙ ጉዳቶች እንደሚኖሩት ለማንም ባይሰወርም፤ተግባራዊ ሆኖ ምርት ይስጥም አይስጥም ፣የኢትዮጵያ ጤፍ አብቃይ መሬቶች በሙሉ ከ 10 ዓመት በሁዋላ ሙሉ በሙሉ ይመክናሉ!ጤፍም ብቻ ሳይሆን፤ማንኛውንም አይነት ዘር ሊቀበሉ የማይችሉ በድን መሬቶች እንደሚሆኑ ከወዲሁ ግልጽ መሆን አለበት!ከ 10 ዓመት በሁዋላ የኢትዮጵያ ገበሬዎች ሴክተር መ/ቤቱን ማለትም ምእራባውያኑን፤"10 ዓመት ሞልቶናልና ዘሩን ድጋሚ ስጡን"ሲሉ የሚያገኙት ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችልም ለአስተዋይ ኢትዮጵያውያን አይሰወርም።ስለዚህ ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል እላለሁ!
Daniel Tomas 

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time