Showing posts with label Amharic. Show all posts
Showing posts with label Amharic. Show all posts

Thursday, December 14, 2017

በሊቢያ ኢትዮጵያዊ "እንደ ውሻ እንጂ እንደ ሰው አይቆጠርም"

በሊቢያ ኢትዮጵያዊ "እንደ ውሻ እንጂ እንደ ሰው አይቆጠርም"

ድሕነትን ሸሽተው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ መንገድ የገቡት ኢትዮጵያውያን በሊቢያ የቀውስ ወጥመድ ውስጥ ወድቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ እንደሚሉት በሊቢያ በሰደፍ ጭምር ይደበደባሉ፣ ገንዘባቸውን ይዘረፋሉ ለእስርም ይዳረጋሉ።
የ21 አመቷ ራሕማ አሕመድ ከአስራ አምስት ቀናት በፊት በሊቢያ እስር ቤት ነበረች። ወጣቷ በእስር ቤት ድብደባ ገጥሟታል። እግሮቿም  መራመድ ቸግሯቸዋል። "እቃ ገዝተን ልንበላ ከታክሲ ስንወርድ የሆነ ሰው እየፈለግን ነበር ብለው ወስደው እስር ቤት አስገቡን ብር አምጥታችሁ ነው የምትወጡት ተብሎ 3,000 ዶላር ተጠየቅን። እግሬ አሁን ተመቶ ነው ያለው። ሳንቲም አስልኪ ብለው ነው የመቱኝ። እኔ ደግሞ ገንዘብ የሚልክልኝ ሰው የለኝም። እህት የለኝም። ወንድም የለኝም። ከየት ነው የማስልክላቸው?"
"እግሯ ተመቶ አሁን ከእሷ ጋር እየተሰቃየሁ ነው።"  የምትለው የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ዘይነብም ከራሕማ ጋር ታስራ ነበር። "3,000 ዶላር ተጠይቀን  የቤተሰቦቻችሁ ቁጥር ንገሩን ብለው ሲደበድቡን ወንዶቹ ከጣራ ላይ አስወጥተውን ከጣራ ላይ ወድቃ እግሯን የተሰበረችው። አሁን 15 ቀን አልሞላንም። እሷ እግሯ ተሰብሮ ተኝታለች ።አሁን አንድ ቤት ውስጥ ቁጭ ብለናል ።"
ራሕማ እና ዘይነብ ጓደኛሞች ናቸው። እንጀራ ፍለጋ ከትውልድ ቀያቸው ወደ ሱዳን ከዚያም ወደ ሊቢያ ያመሩትም አብረው ነበር። ሁለቱም በርስ በርስ ጦርነት በታመሰችው ሊቢያ ላለፉት አራት አመታት ኖረዋል። የሜድራኒያን ባሕርን ተሻግረው የተሻለ ነገር ይገኝበታል ሲባል ከሰሙት አውሮጳ ለመድረስ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ገንዘብ ከፍለው ያደረጉት ሙከራ አልሰመረላቸውም።
"እኔ የደሐ ልጅ ነኝ" የምትለው ራሕማ ከቤተሰቦቿ ጋር ግንኙነት የላትም። የእጅ ስልኳ ተወስዶባታል። "መጥፎ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት" ትላለች ያለችበትን ሁኔታ ስታብራራ። ራሕማ ከቤተሰቦቿ ገንዘብ አስልካ ሁሉ ታውቃለች። እርሷ እንደምትለው ግን ይኸ የእሷ እጣ ፈንታ ብቻ አይደለም።"ብዙ ልጆች እስር ቤት የሚወልዱ አሉ። ብዙ ደላላ ቤት የሚጎዱ አሉ። ብዙ ብር ከኢትዮጵያ ቤት አሽጠው የተላከላቸው ሰዎች አሉ። እንደዚህ አይነት ብዙ ሰዎች አሉ።"
Libyen Europa Migration Zustände in Flüchtlingslagern (picture-alliance/AP Photo/M. Brabo)
በሊቢያውያን ታግተው ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ከተላከላቸው መካከል "ስቃይ ውስጥ ነው ያለሁት" የሚለው ሰይፈል ሁሴን ይገኝበታል። የሰሐራ በርሐን አቋርጦ ሊቢያ የደረሰው ሰይፈል ከአንዴም ሁለት ጊዜ ታግቶ ታስሮ ያውቃል። "ከእስር ቤት ለመውጣት ወደ 8,000 ዶላር {ከኢትዮጵያአስልኪያለሁ። ድብደባ ሲበዛ ቤተሰብ ጋ ደወልኩ። በክላሽ በሰደፍ እየመቱ ነው ገንዘብ እንዲላክ የሚያስገድዱት። ቤተሰቦቼ ሳለቅስ ያላቸውን የሌላቸውን ተበዳድረው ላኩልኝ። ከወጣሁ በኋላ ትሪፖሊ ልላካችሁ አለን። ትሪፖሊ ነው የምልካችሁ ብሎ ከዛ መንገድ ላይ ተያዝን አሁንም። ከዛ በሊዎሊድ ገባን። በሊዎሊድ ገብተንም ለአንድ ሰው 5,500 ዶላር አምጡ አለን። ከዛም በኋላ አመት ሙሉ ስንቀጠቀጥ ስንቀጠቀጥ ቤተሰብ ስደውል ስደውል መጨረሻ ላይ ቤት ሸጠው ላኩልኝ።"
የቀድሞው አምባገነን ሞአመር ጋዳፊ በምዕራባውያኑ ጣልቃ ገብነት እና ሕዝባዊ ተቃውሞ ከሥልጣን ከወረዱ ጀምሮ መንግሥታዊ ሥርዓቷ በፈራረሰው ሊቢያ አፈና የተለመደ ግን ደግሞ አሰቃቂ ተግባር ሆኗል። አፈናው ሊቢያን እንደ መሸጋገሪያ የሚጠቀሙ አፍሪቃውያን በታጣቂዎች እጅ  እንደ ባሪያ እንዲሸጡ አድርጓቸዋል። ድርጊቱ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ እና ውግዘት ቢገጥመውም ዘላቂ መፍትሔ የማግኘቱ ነገር አጠያያቂ ይመስላል። ሰይፈል በሊቢያ ካፈኑት ቡድኖች መካከል አንዱ በኤርትራዊ ይመራ እንደነበር ተናግሯል።
"እኛን ይዞን የነበረው ኤርትራዊው ወሊድ የሚባለው ወኪል የትም አገር አለው። ከሱማሌም አለው። በዱባይም ያስመጣል። ይኸን ስራ እስካሁን ድረስ ይሰራል። {የሚላከውን ገንዘብየሚቀበሉ ሰዎች አሉ። ሲታወቅበት ሌላ ሰው ይቀይራል።" ይላል።
በሊቢያ የሚገኙት ስደተኞች እንደሚሉት ግፍ እና መከራው በወንዶች ላይ ይበረታል። ሴቶቹ ከሰው ቤት ተቀጥረው በመሥራት የዕለት ጉርሳቸውን ማግኘት ይችላሉ። ይሁን እና ወርሐዊ ደሞዛቸው በአግባቡ አይከፈላቸውም። ቢከፈላቸው እንኳ ፖሊስን ጨምሮ በሊቢያውያኑ ተመልሶ ይዘረፋሉ። "አባታቸው ሞቶባቸው ልጆቼን አሳድጋለሁ ብዬ ነው ከአገሬ የወጣሁት። ልጆቼንም መርዳት አልቻልኩም።" የምትለው ዘይነብ ይኸው ገጥሟታል። "እዚህ በጣም ተሰቃይቼ ነው ያለሁት። በሰሐራ ስመጣ ስንት ጓደኞቼ ከአጠገቤ ሞተው እዚህ ደረስኩ። እዚህ ደርሼ አንድ አመት እንኳ ልጆቼን መርዳት አልቻልኩም። የምሰራው ይጠፋብኛል። አጠራቅሜ እልካለሁ ስል የሚላክበት መንገድ የለም። ባለፈው ደግሞ ፖሊስ ገብቶ ብዙ የሰራሁትን ብዙ ብር ወሰደብኝ። ሥራ ቦታ ደግሞ ብሬን አልከፈሉኝም።"
ራሕማ ባዶ እጇን መሆኗ አብዝቶ ቢያሳስባትም ወደ አገሯ መመለስ ትሻለች። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ሳምንት በሊቢያ የሚገኙ ዜጎቹን ለመመለስ ማቀዱን ገልጦ ነበር። ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሊቢያ የሚገኙ እና ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ለሚፈልጉ ዜጎች የተዘጋጁ ሶስት የስልክ ቁጥሮች አሰራጭቷል። ኢትዮጵያውያኑን የመመለሱ ተግባር ስለ መጀመሩ ለማረጋገጥ በተደጋጋሚ ያደረግንው ሙከራ ግን አልሰመረም።
ዘይነብ እንደምትለው ወደ ስልክ አድራሻዎቹ ላይ በተደጋጋሚ ቢደውሉም ምላሽ አላገኙም።  "የሚደርስብን መከራ ከፍቷል" የምትለው ዘይነብ እንደ ሰው አይቆጥሩንም ስትል ትናገራለች።
"ኢብን ወሊድ የሚባል ቦታ ላይ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተሽጠው ፤ ሁለቴ ተሽጠው ብር ተጠይቀው እየተገረፉ ያሉ ልጆች አሉ። እዚህ ኢትዮጵያ ዜጋ እና ሌላ ዜጋ እንደ ውሻ ነው እንጂ እንደ ሰው አይቆጠርም። መንገድ ላይ ታርዶ ነው እንደ ውሻ የሚጣለው። እንደ ሰው አይቆጥሩንም።Read more here
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ

Monday, October 16, 2017

አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

አቶ በረከት ስምኦን
በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል።
አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ተነግሯል።
አቶ በረከት ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስገባታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ በቢሮአቸው ተገኝተው የነበሩት ሀሙስ ዕለት ነበር።
አቶ በረከት በተመሳሳይ ጊዜ ከሁለት የሃላፊነት ቦታቸው የተነሱ ሲሆን ለሥራ መልቀቃቸው ግልፅ ያለ ምክንያት አልቀረበም።
ነገር ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ብዙም ደስታኛ እንዳልነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።
በተለይ ማዕከሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚያቀርባቸው ሃገር አቀፍ የፖሊሲና የአስተዳደር ጥናቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩና በመንግሥት ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ብዙም ተቀባይነት አግኝተው ተግባራዊ አለመደረጋቸው ለቅሬታቸው ምክንያት እንደሆነ ይነገራል።
ቢሆንም ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ያላቸውን ሃላፊነት ለመልቀቅ ሌላ ተጨማሪ ምክንያት እንዳላቸው ማረጋገጥ አልተቻለም።
የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል በአቶ አባይ ፀሐዬ ዋና ዳይሬክተርነት የሚመራ ተቋም ነው።
አቶ በረከት ስምኦን ከቀደምት የኢህአዴግ አመራሮች መካከል የሚመደቡ ሲሆን የገዢው ፓርቲ አንድ አካል የሆነው የብአዴን አመራር አባል ናቸው።
አቶ በረከት ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነቶች ላይ የቆዩ ሲሆን፤ የማስታወቂያ ሚኒስትርና የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። Read more here

ኢትዮ-ቴሌኮምና በኢንተርኔት ዋጋ እና ፍጥነት የተማረሩ ደንበኞቹ

kids playing with a phone
በስራ ጉዳይ ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚጓጓዘው ወንድሜነህ እንግዳ በርካታ የአፍሪካ ሃገራትን የመጎብኘት አጋጣሚ አግኝቷል። በቅርቡም ወደ ኬንያ ለሳምንት ያህል አምርቶ ነበር። በእነዚህ አጋጣሚዎችም ሃገሩ ኢትዮጵያ አልፎም መኖሪያው አዲስ አበባ ከመሰል ከተሞች ጋር ያላትን ልዩነትና ምስስል መታዘብ ችሏል።
"ከሁሉም ከሁሉም በበርካታ ሃገራት የማስተውለው የኢንተርኔት ፍጥነት እና አቅርቦት ጉዳይ ያስደንቀኛል" ይላል ወንድሜነህ። "የእነዚህ ሃገራት መንግስታት ኢንተርኔት ለአንድ ሃገር ዕድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የተረዱት ይመስላል" ሲል ትዝብቱን ያስቀምጣል። "አንድ ቀን ኢትዮጵያም እንደጎረቤት ሃገራት ፈጣንና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ኢንተርኔት ታቀርብ ይሆናል። ማንያውቃል. . . " ይላል ወንድሜነህ።
የቴሌኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ዕድገት አብይ ማሳያ የሆነው የኢንተርኔት አገልግሎት አሁን አሁን አስፈላጊነቱ ከምንም ጊዜ በላይ እየጨመረ እንደመጣ አያጠራጥርም። ዓለማችን በሉላዊነት አንድ እንድትሆን ትልቅ ሚና ከተጫወቱ ቴክኖሎጂዎች መካከልም ቁንጮ ሆኖ ይቀመጣል።
የዓለም አቀፉ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ማሕበር በአውሮፓውያኑ 2016 ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በቴሌኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ከዓለም 169ኛ ደረጃ ከአፍሪካ ደግሞ 33ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ሞሪሺየስ የምትመራው የአህጉራችን የቴሌ ዘርፍ ጎረቤት ሃገር ኬንያን 9ኛ ላይ ሲያስቀምጥ፤ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ በተከታታይ 20ኛ 22ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ታላቅ ቅናሽ

60 ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉት የሚናገረው ኢትዮ ቴሌኮም ከእነዚህ ውስጥ 17 ሚሊዮን ያክሉ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርኔት አግልግሎት ተጠቃሚ ናቸው። የኢትዮ ቴሌኮም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ እንደሚናገሩት የ3ጂ ኢንተርኔት በአሁኑ ሰዓት በመላ ሃገሪቱ የተስፋፋ ሲሆን ተጠቃሚዎችም አገልግሎቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ ይገኛሉ።
ኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔት በተለይም ደግሞ በተንቀሳቃሽ ስልክ የሚቀርበውን አገልግሎት በዝቅተኛ ታሪፍ ለደንበኞቹ ያቀርባል ሲሉ ይናገራሉ አቶ አብዱራሂም።
"አይሲቲ አፍሪካ የተባለ ድርጅት በሚያወጣው ደረጃ መሠረት ኢትዮጵያ በተንቀሳቃሽ ስልክ ኢንተርኔት ዋጋ በዝቅተኛው ደረጃ ላይ ትገኛለች። ይህም ማለት 0.03 ዶላር በአንድ ደቂቃ ዋጋ ላይ ትገኛለች። በተነፃፃሪ ደግሞ ኬንያ በ0.07 ዶላር የአንድ ደቂቃ ኢንተርኔት ትሸጣለች" በማለት አቶ አብዱራሂም ያስቀምጡታል።
ወንድሜነህ ግን በዚህ ሃሳብ የሚስማማ አይመስልም። "እኔ በሄድኩባቸው እንደ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ የመሳሰሉ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የተንቀሳቃሽ ስልክ ኢንተርኔት አግልግሎት በተነፃፃሪ እጅጉን ርካሽ እና ፈጣን ሆኖ ነው ያገኘሁት" ሲል ያስረግጣል።
የቴሌኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆነው ተክሊት ሃይሌም ሃሳቡ ተመሳሳይ ነው። "በቅርቡ ግብፅ ሄጄ የኢንተርኔት አግልግሎቱን በርካሽ ዋጋ መጠቀም ችያለሁ። ያውም እጅግ ፈጣን የሆነ አገልግሎት" ሲል ይናገራል።
ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የሚያቀርበውን የኢንተርኔት አግልግሎት ዋጋ ከኬንያው ሳፋሪኮም ጋር ለማነፃፀር እንደሞከርነው የኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔት አቅርቦት መጠን ባደገ ቁጥር ዋጋው እጅግ ከፍ እያለ ይመጣል።
ሳፋሪኮም ዝቅተኛውን የ5 ሜጋ ባይት ኢንተርኔት በ5 ሽልንግ ወይም አሁን ባለው የምንዛሪ ዋጋ 1ብር ከ30 ሳንቲም አካባቢ ያቀርባል። ኢትዮ ቴሌኮም ደግሞ የ25 ሜጋ ባይት ኢንተርኔት በ5 ብር ያቀርባል። በዚህ ረገድ ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ሲሆን የኢንተርኔት መጠኑ ከፍ ሲል ግን ሳፋሪኮም እጅግ በተሻለ ዋጋ ኢንተርኔትን ለደንበኞቹ ያቀርባል። ለምሳሌ ኢትዮ ቴሌኮም 1ጂቢ በ165 ብር ሲሸጥ በተነፃፃሪ ሳፋሪኮም 1ጂቢ በ500 ሽልንግ ወይም አሁን ባለው የምንዛሪ ዋጋ በ130 ብር አካባቢ ይሸጣል።
መረጃዎቹን ከኢትዮ ቴሌኮም ከሳፋሪኮም ድረ-ገፆች የተገኙ ናቸው
አጭር የምስል መግለጫመረጃዎቹ ከኢትዮ ቴሌኮምና ሳፋሪኮም ድረ-ገፆች የተገኙ ናቸው

ወጥ-አልባነት

ወንድሜነህም ሆነ ተክሊት በአንድ ተጨማሪ ነገር ይስማማሉ። በኢትዮ-ቴሌኮም የኢንተርኔት አቅርቦት ወጥ-አልባነት። "የዋጋው ነገር እንዳለ ሆኖ" ይላል ወንድሜነህ "አንዳንድ ወቅት ዘለግ ላለ ጊዜ የምትጠቀምበት ኢንተርኔት በሌላ ወቅት በደቂቃዎች ውስጥ ያልቅብሃል። በምን ዓይነት መስፈርት እንደሚሰራ ግልጽ አይደለም" ይላል።
በመንግስት ሥራ የምትዳደረው መክሊት የ2ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ነች። "2ጂም ሆነ 3ጂ ልዩነቱ አይታየኝም። እንደውም አንዳንዴ 3ጂ ከሚጠቀሙ ጓደኞቼ የኔ ኢንተርኔት ፈጥኖ ይገኛል" ትላለች። "አንዳንድ ጊዜ በ5 ብር የገዛሁትን ጥቅል አገልግሎት ረዘም ላለ ጊዜ እጠቀማለሁ ሌላ ጊዜ ወዲያው ያልቅብኛል" ስትል ትናገራለች።

ሞኖፖሊ

የኢትዮጵያን ቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ በበላይነት የሚቆጣጠረው ኢትዮ ቴሌኮም ሌላ ምርጫ የሌላቸውን ደንበኞቹን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ እያሳደገ ቢመጣም የኢንተርኔት ነገር ለብዙዎች አሁንም አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
ተክሊት ለዚህ ችግር መፍትሄው አማራጭን ማስፋት ነው ይላል። "እኔ ቴሌኮም ለውጭ ድርጅት ይሸጥ ወይም አክሲዮን ይሰጥ የሚል እምነት የለኝም። ነገር ግን ለሃገር ውስጥ ድርጅቶች ዘርፉን ክፍት ማድረግ ቢቻል በሚቀጥሉት ዓመታት ቴሌኮም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሁሉም ማቅረብ እንደሚቻል አምናለሁ" ሲል ይናገራል።
"ኬንያ የሄድኩ ጊዜ ሳፋሪኮም፣ ኤይርቴል እና ቴልኮም የተባሉ አበይት አማራጮች ስላሉ ሰው እንደፍላጎቱ አማርጦ ሲጠቀም ተመልክቻለሁ። እኛ ሃገር ስትመጣ ግን ያለህ አማራጭ አንድ እና አንድ ነው። እሱም አሰራሩ ወጥ ነው ብዬ አላምንም" ሲል ወንድሜነህ በሌሎች ሃገራት የታዘበውንና የሃገሩን ሁኔታ ይተርካል።
ጨምሮም "እንደኬንያ በመሳሰሉ ሃገራት ረከስ ባለ ዋጋ ተገዝቶ ከግለሰቦች ቤት አልፎ በሕዝብ ማመላለሻ ባሶች ውስጥ ሳይቀር የሚገጠመው 'ዋይፋይ' ኢትዮጵያ ውስጥ ከብቸኛው አቅራቢ ኢትዮ-ቴሌኮም በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የማይታሰብ ነው" ይላል።
ethio-telecom
ኢትዮ-ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎትን ከማስፋት ባለፈ ጥራት እና ፍጥነት ላይ እየሰራ እንደሆነ አቶ አብዱራሂም ይናገራሉ። "ታሪፍን በተመለከተ በተከታታይ እያየን ማሻሻያ የምናደርግበት ጉዳይ ነው። የሚቆም ጉዳይ" አይደለም ይላሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም ከኬንያው ሳፋሪኮም ጋር በትብብር ሊሠራ ነው ተብሎ በተለያዩ ዜና ምንጮች የተነገረው መሠረተ ቢስ መሆኑን አቶ አብዱራሂም ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ሆኖም መክሊት እና ወንድሜነህን የመሳሰሉ ደንበኞች አሁንም ጥያቄ ያነሳሉ። "መች ይሆን ኢንተርኔት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሁም በአስተማማኝ ፍጥነት የምናገኘው?" በማለት. . . Read more here

Saturday, October 14, 2017

ካርታው ከወር በፊት ታይቶ ይቅርታ ሲጠየቅበት ስህተት ቢሆን ኑሮ አሁን ባልተደገመ ነበር!

የፍሽስት ወያኔ ሚዲይ ትልቁ የፖለቲካ መሳሪያ እና የአማራ ክልል አዋሳኝ ድምበር ድጋሚ ሴራ--ሰሎሞን ይመኑ
No automatic alt text available.
የተከዜ ማዶ አምባገነን ፍሽስት ፈላጭ ቆራጩ ዘረኛው የማፊያ ጎረምሳ ቡድን በማን አለብኝነት እና የህዝብን ጥያቄ እና ድምጽ በመናቅ በትቢት ልቡ ያበጠው የዘገምተኞች ስብስብ ዛሬም ጥቅምት 2/2010 በቁጥጥሩ ስር ባለው የግሉ ሚዲያ ኢቢሲ ላይ ስለ ሰንደቅ አላማ በሰራው ዶክመንተሪ ከወር በፊት አሳይቶት የነበረው አይነት ተመሳሳይ ካርታ አያይዞ ያቀረበ ሲሆን በካርታው ላይም የአማራ ክልልን ከኤርትራና ሱዳን አዋሳኝ ውጭ በማድረግ የትግራይ ክልልን እንዴት ቤንሻጉል ጉምዝ ድረስ እንደሚወስደው ያሳያል፡፡ የቀረበው ዶክመንታሪ በአሁኑ ሰአት ከኢቢሲ ድህረ ገጽ የጠፍ ሲሆን በወቅቱ ግን ካርታውን ያስቀረሁት በመሆኑ ከስር ማየት ይቻላል፡፡ የፌስቡክ ሊንኩም የጠፍ ሲሆን የጠፍው ሊንክም ይሄ ነው(http://www.ebc.et/-/-ebc-02-2010-)
ዲሞክራሲያዊ በሆኑ ሃገራትና መንግስታት ሚዲያው ለህዝቦቹ ወይም ለአድማጭ እና ተመልቾቹ የሃሰት ዘገባ ካቀረበ፣ታሪክና እውነታን አዛብቶ ካቀረበ፣ዘገባን ሚዛናዊ ባልሆነ መንገድ አጋኖ ካቀረበ፣ትክክለኛ መረጃ ካላቀረበ፣እንዲሁም የገዥውን መንግስት የፖለቲካ ስራ ህጋዊ ሽፍን ሰጥቶ ከሰራ ይህን ባደረገ የመንግስትም ይሁን የግል ሚዲያ ህጋዊ ተጠያቂ የሚያደርግ የዳበረ ህግ እና ህጉንም የሚያስፈጽም ገለልተኛ ተቋም አላቸው፡፡
በተቃራኒው እንደ ወያኔ ባሉ አምባገነን እና ፍሽስት ዘረኛ መንግስት ግን ሚዲያውን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ በመጠቀም ኋላቀር የሆነውን ሳንሱር መጠቀም እና ስልታዊ የሆነ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ይታወቃሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ለነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ በር በመዝጋት፣ የኢንተርኔት ፖሊሲ በማውጣትና በመገደብ እንዲሁም በመቆጣጠር፣የሀሰት ፀሃፊያን የገንዘብ ድጋፍ በመስጠትና የሚፈልጉትን እንዲጽፉ በማድረግና በአጠቃላይ የሚፈልገውን የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ለማስፈጸም በመንግስት ቁጥጥር ስር የሆነ ሚዲያ ላይ መመስረት እና ለመንግስት ቅርበት ያላቸውን ሚዲያዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ዋነኛ የወያኔ አይነት ፍሽስት አምባገነን መንግስታት መገለጫ ነው፡፡
እንደ ወያኔ አይነት ዘረኛ ፍሽስት authoritarian(ፈላጭ ቆራጭ)መንግስት ሚዲያውን በባለቤትነት መያዙ የፖለቲካ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠርና የፈለገውን ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት ዋነኛ መሳሪያው ስለሆነ ነው፡፡ አምባገነኖቹ የኢኳዶርና ቭንዝዌላ መንግስታት ፕሬዝዳንቶችም ልክ እንደወያኔ በመንግስት ሚዲያ በቀጥታ ስርጭት ቀርበው ለረጅም ሰአታት የተቃዋሚ ፖለቲከኞችንና የህብረተሰቡን ህጋዊ ሰላማዊ ሰልፍና ጥያቄ ሲያወግዙበት ታይተዋል፡፡
ባጠቃላይ እንደ ወያኔ አይነት ፈላጭ ቆራጭ አምባገነን ፍሽስት ዘረኛ መንግስት አሁን በኢቢሲ ያቀረበውን የአማራ ክልልን ከሱዳንና ኤርትራ ድምበር የሚነጥልና ትግራይንም ከቤንሻንጉል የሚያዋስን ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ከላይ እንደገለጽኩት እንደ ወያኔ አይነት አምባገነን መንግስት የያዙትን የግል ሚዲያ በመጠቀም የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳውን መስራት የሚዲያው ተቀዳሚ አላማ ነው፡፡ ይህ ዋነኛ ማሳያውም ካርታው ከወር በፊት ታይቶ ይቅርታ ሲጠየቅበት ስህተት ቢሆን ኑሮ አሁን ባልተደገመ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ይህ ካርታ ሲቀርብም ከክልሉ መንግስት ተላላኪው ብአዴን በኩል ምንም ጥያቄ አለመቅረቡ ቢያሳዝንም የተሳሳተው አካልም የተወሰደበት ህጋዊ እርምጃ የለም፡፡እንግዲህ ይህ የሚያሳየን ደግሞ የተከዜ ማዶ ሰዎችን ትቢትና ተንኮል እንዲሁም የውስጥ ጉዞና የህዝባችን ቸልተኝነት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ርስቱን አጦ በማንነቱና በባህሉ ተከብሮ የሚኖር ህዝብ ላለማጣት በዚህ መርዘኛና የእፍኝት ልጆች ጥርቅም ማፊያዎች ላይ የማንተኛበት የመጨረሻው ሰአት ላይ እንገኛለን፡፡ሁላችንም በየአካባቢያችን ያለውን ሁኔታ ተቆጣጥረን በወያኔ ላይ በጋራ ዘምቶ ይሄን መርዘኛ መንግስት ከስሩ ካልነቀልነው የረጅም ጊዜ ችግራችን ማስወገድ አንችልም፡፡

Tuesday, October 10, 2017

በአዳማ ከተማ ሁለት ህፃናት በዱር እንስሣት ተበልተው ተገኙ፡፡

በአዳማ ከተማ ሁለት ህፃናት በዱር እንስሣት ተበልተው ተገኙ፡፡
አንደኛዋን የሁለት ዓመት ህፃን ከእናትና አባቷ እቅፍ ነጥቆ የበላት ጅብ መሆኑን የአዳማ ከተማ ፖሊስ ሪፖርተር ዋና ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ ነግረውናል፡፡
የህፃኗ ወላጆች በመድኃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ጥግ ሁለት ልጆቻቸውን ይዘው በተኙበት ጅቡ ትንሿን እየጐተተ ሲወስዳት በእንቅልፍ ውስጥ ነበሩ ተብሏል፡፡
በድንጋጤ ከእንቅልፋቸው ባነው ጅቡን የተከተሉት ወላጆች ሊደርሱበት እንዳልቻሉ ዋና ሳጅን ወርቅነሽ ነግረውናል፡፡
በተመሣሣይ ማንነቱ ሊለይ ያልቻለ እድሜው 7 ወር የሚገመት ህፃንም በዱር እንስሣት ተበልቶ ትናንት ጠዋት በአዳማ ከተማ ወረዳ ሁለት መገኘቱን ሰምተናል፡፡
ከመበላት የተረፈው የሁለቱ ህፃናት አካል በፖሊስ ተሰብስቦ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል ብለዋል ሳጅን ወርቅነሽ፡፡
በአዳማ እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች ተደጋግመው እየተከሰቱ መሆኑን የነገሩን ሳጅን ወርቅነሽ ህፃናትን ይዘው ለልመና ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ ሰዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ Read more here

የኦሮሚያና የሶማሌ ግጭት ሙሉ በሙሉ እንዳልቆመ መንግሥት አስታወቀ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል ከወር በፊት ተቀስቅሶ የነበረው ግጭት እስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዳልቆመ መንግሥት አስታወቀ፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ዓርብ መስከረም 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል የከፋ ግጭት ባይኖርም በየቀኑ አልፎ አልፎ ግጭት መከሰቱ ቀጥሏል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በኩል እስካሁን ድረስ እየሞቱና እየተፈናቀሉ ያሉ ሰዎች በየቀኑ ሪፖርት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ድረስም ጉዳቶች እንዳሉ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ደግሞ የታጠቀ ኃይል ሰርጎ እየገባና ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ነው ብለዋል፡፡
በሁለቱ ክልሎች መካከል ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት በተመለከተ ለመገምገምና አዳዲስ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ሲባል ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሁለቱን ክልሎች አመራሮች አግኝተው እንዳነጋገሯቸው ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ውይይት ላይ ከኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከሶማሌ ክልል ደግሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ግጭቱ የዜጎችን በሕይወት የመኖርና ንብረት የማፍራት መብቶች የጣሰ እንደሆነ መግለጻቸውን ጠቁመዋል፡፡ የኦሮሞና የሶማሌ ሕዝቦችን የማይወክሉ ኃይሎች ባደረሱት ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሕይወት መጥፋት ተገቢ እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ማስተላለፋቸውንም ተናግረዋል፡፡
ጉዳት ከደረሰባቸው ዜጎች ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ ክልል ባቀረበው ሪፖርት መሠረት ከ75 ሺሕ በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያ ተወላጆች ከሶማሌ ክልል መፈናቀላቸውን፣ ከኦሮሚያ ክልል ግን 392 የሶማሌ ተወላጆች መፈናቀላቸውን እንዳስታወቀ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ከአወዳይ አካባቢ ምሥራቅ ሐረርጌ የተፈናቀሉና ወደ ጅግጅጋ የሄዱ እንዳሉም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ኦሮሞዎች የሶማሌ ሕዝብ እንዳላፈናቀላቸው፣ አንዳንዶቹ በተለያዩ አካላት ተገፍተው፣ ሌሎቹ ደግሞ በአመራሩና በፀጥታ አካሉ ላይ እምነት ስላልነበራቸው ከሶማሌ ክልል መፈናቀላቸውን እንደገለጹም ጠቅሰዋል፡፡
‹‹ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉት ምናልባት 400 ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ በኦሮሚያ በኩል የተገለጸው ይህ ነው፡፡ እንዲያውም አወዳይ አካባቢ የደረሰውን ጥቃት የከፋ እንዳይሆን ያደረገው የኦሮሞ ሕዝብ እነዚህን ተፈናቃዮች ደብቋቸው ወደ ሐረር እንዲሄዱ በማድረጉ ነው፤›› ብለዋል፡፡
በሕዝቡ መሀል ችግር ከሌለ ይህ ግጭት ለምንድነው የተከሰተው ለሚባለው አመራሩ ራሱን እንዲፈትሽ የሚያስገድድ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸውንም ተናግረዋል፡፡
‹‹በዚህ ግጭት እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰው እንደሞተ ሁለቱም ክልሎች የሚገልጹት እንዳለ ሆኖ፣ በአሁኑ ወቅት እየተጠና ስለሆነ ወደፊት ለሕዝቡ ይፋ ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም በግጭቱ ምክንያት የደረሰውን ጉዳትና የሞተውን የሰው ቁጥር ለማወቅ በአሁኑ ወቅት እያጠና መሆኑን ጠቁመው፣ ‹‹በቅርብ ጊዜ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ያቀርባል፤›› ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ከሁለቱ ክልሎች ወንጀል የፈጸሙትንና ለግጭቱ መንስዔ የሆኑትን የፌዴራል ፖሊስ እያጣራና በቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ግጭቱን ለማስቆም ሲባልም የሁለቱ ክልሎች የፀጥታ አካላት ከአዋሳኝ አካባቢዎች እንዲርቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አቅጣጫ መስጠታቸውን አስታውሰዋል፡፡ በዚህ መሠረትም የሁለቱም ክልሎች ሚሊሻዎች ከወሰን አካባቢ አምስት ኪሎ ሜትር እንዲርቁ፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እየተባለ የሚጠራው ፖሊስና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስም ከአዋሳኝ አካባቢዎች ከአሥር እስከ 20 ኪሎ ሜትሮች መራቅ እንዳለበት አቅጣጫ መቀመጡን አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት መንግሥት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ታጣቂዎችን ትጥቅ እያስፈታ ነው እየተባለ በተለያዩ ሚዲያዎች እየተገለጸ እንደሆነ ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ ይህ ውሸት እንደሆነና የተከለከለውን ዞን ጥሰው የሚገቡ አካላት በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራ ግን እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሁለቱ ክልሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የወጪ ንግድ መስተጓጎል እያስከተለ እንደሆነ መንግሥት መገምገሙን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በምሥራቅ በኩል ጫትና ሌሎች ምርቶች እንዲቆሙና እንዲቃጠሉ በመደረጉ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ይህ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት ያስቀመጡትን አቅጣጫና መመርያ የጣሰ መሆኑ ታውቆ ለወደፊቱ እንዲስተካከል አቅጣጫ መስጠታቸውን አስረድተዋል፡፡
ለጫትና ለሌሎች ሸቀጣ ሸቀጦች መስተጓጎል ምክንያቱ ደግሞ በሁለቱ ክልሎች ውስጥ ያለው ኬላ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱም ክልሎች በገቢና በወጪ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ኬላ ማቆም እንደሌለባቸው፣ ወደፊት በፌዴራል መንግሥት ሥር ሆነው መሥራት እንደሚገባቸው መናገራቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከሁለቱም ክልሎች የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በተመለከተም በጊዜያዊነት የሚያስፈልጋቸው ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲደረግላቸው፣ የተጎዱት ንብረታቸው የሚመለስበትና ለወደመባቸው ደግሞ ካሳ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል፡፡
የሶማሌ ክልል መንግሥትና የአገር ሽማግሌዎች ባለፈው ሳምንት ያወጡትን መግለጫ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አይተው እንዳዘኑና እንደዚህ ዓይነት መግለጫ ለወደፊት መውጣት እንደሌለበት ጥብቅ ማሳሰቢያ መስጠታቸውን አስረድተዋል፡፡
የሶማሌ ክልል መንግሥትና የአገር ሽማግሌዎች ማክሰኞ መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋራ መግለጫ ያወጡ ሲሆን፣ መግለጫው የሶማሌ ሕዝብ የቀድሞውን የደርግ ሥርዓት ለማስወገድ በተደረገው ትግል ሕዝቡ መስዋዕትነት እንደከፈለ አስታውሷል፡፡ መግለጫው በሁለቱ ክልሎች መካከል ለተቀሰቀሰው ግጭት ዋነኛ ተጠያቂ የኦሮሚያ ክልልን አድርጓል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

የኤድስ ወረርሽኝ ሥርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

Image result for aids

-    በየዓመቱ 21ሺ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ፡፡ 60 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው
-    ዓምና ብቻ 20 ሺ የሚጠጉ ሰዎች በበሽታው ህይወታቸውን ማጣታቸው ይገመታል 
-    በአዲስ አበባ ብቻ በየዓመቱ 4ሺ243 አዳዲስ ሰዎች በኤችይቪ ይያዛሉ
-    718ሺ500  ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ
በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሄዱና አገሪቱ በበሽታው ወረርሽኝ ውስጥ እንደምትገኝ ተጠቆመ፡፡ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከበደ ወርቁ፣ ከትናንት በስቲያ፣ በባለድርሻ አካላት መካከል በተደረገው የምክክር ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት፤ የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በአሁኑ ወቅት 718ሺ500 የሚሆኑ ዜጎች ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሲሆን መድኃኒቱን የሚወስዱት ግን ከ400 ሺ አይበልጡም፡፡ በቫይረሱ ከተያዙት ዜጎች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡
 በወሲብ ንግድ ሥራ ላይ ከተሰማሩት ሴቶች መካከል 25 በመቶ ያህሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኝ የገለፁት ዶ/ር ከበደ፤አራት በመቶ የሚሆኑት በአገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚሰሩ ሾፌሮች የቫይረሱ ተጠቂዎች እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡ በየዓመቱ 21 ሺ አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚያዙ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ከእነዚህ መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውንና ከ15 እስከ 24 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙም ተናግረዋል፡፡ ለበሽታው ይሰጥ የነበረው ትኩረት በመቀዛቀዙ፣ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ወገኖች የፀረ ኤችአይቪ መድሃኒት ተጠቃሚ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ፣ከተወሰኑ አመታት በፊት ሲታይ የነበረው ከኤድስ ጋር የተያያዘው ህመምና ሞት በከፍተኛ ደረጃ በመቀነሱ ምክንያት፣ህብረተሰቡ ለበሽታው ይወስድ የነበረው ጥንቃቄ በመቀነሱ፣የቫይረሱ ስርጭት እንዲያገረሽ ምክንያት መሆኑን ዶ/ር ከበደ ገልፀዋል፡፡ ሁኔታው አሣሣቢ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑም ህብረተሰቡ፣በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ 
በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽ/ቤት፣ የዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ምትኩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ በሽታው በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ከሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመው፣ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይደረጉ የነበሩት የተለያዩ የውጪ ድርጅቶች እርዳታና ድጋፍ በመቋረጡ ምክንያት ስራው ተቀዛቅዞ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገው የውጪ እርዳታ መቋረጡን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ለመድኃኒት ግዥ የሚውለውም እርዳታ እየቀነሰ በመምጣቱ መጪውን ጊዜ እጅግ አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡ 
በምክክር መድረኩ ላይ ከቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፎች አብዛኛዎቹ በሽታው በአሁኑ ወቅት ያለበትን አሳሳቢ ደረጃ የሚጠቁሙ ናቸው፡፡ በአገሪቱ ካሉት ክልሎች ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ክልልና አዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው፣ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ወገኖች የሚኖሩባቸው ክልሎች መሆናቸውን ያመለከቱት ጥናቶቹ፤ በአራቱ ክልሎች ብቻ የሚገኙት የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ወገኖች በአጠቃላይ በአገሪቱ የሚገኙትን ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ወገኖች 82 በመቶ ያህሉን እንደሚሸፍኑ ጠቁመዋል፡፡  
በ2009 ዓ.ም ብቻ ከአጠቃላይ 19ሺ743 ሰዎች በኤድስ ሳቢያ እንደሞቱ እንደሚገመት የገለፀው ጥናቱ፤ ከእነዚህ መካከል 58 በመቶ ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም 3ሺ173 የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ0-14 ዓመት የሆናቸው ህፃናት መሆናቸውን በምክክር መድረኩ ላይ የቀረበው ጥናት ያመለክታል፡፡
በተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ለበሽታው ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት እነዚሁ ጥናቶች፤ የኤችአይቪ ስርጭቱም በዛው መጠን እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል፡፡ በሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ላይ በተካሄደ ጥናት፤ከአንድ ሺ ሴት ተማሪዎች ስልሣ አምስት (65) ያህሉ  ውርጃ መፈጸማቸውንና ይህም የበሽታው ስርጭት እጅግ አሣሣቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለአብነትም በአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ላይ በተካሄደ ጥናት፤አማካይ የስርጭት መጠኑ 3.8 በመቶ (በሴቶች 5.6%፣ በወንዶች 3%) መሆኑ ተገልጿል፡፡
ትላልቅ የልማት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ዜጎች፤ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸው እየጨመረ መምጣቱን ያመለከቱት ጥናቶች፤ በአበባ እርሻ ልማት ውስጥ የሚሰሩ ሴቶች፣ ጥንቃቄ ለጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት በመጋለጣቸው፣25.6 በመቶ ውርጃ መፈጸማቸውን ጠቁመዋል፡፡  
በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት መካከል ሲካሄድ የዋለው የምክክር መድረክ፤ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባና ህብረተሰቡ ለበሽታው ያለውን ግንዛቤ በማሳደጉ ረገድ ከፍተኛ ጥረት መደረግ እንዳለበት አቋም ተይዞ ተጠናቋል፡፡
በዓለማችን እስካሁን ከ70 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውና 35 ሚሊዮን የሚሆኑት በዚሁ በሽታ ሣቢያ ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወቃል፡፡  Read more here

Saturday, October 7, 2017

አይቀሬው የለውጥ ማዕበል በኢትዮጵያ እና የህወሀት/ኢህአዴግ የቁልቁለት መንገድ

<<< ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት >>>>
Image may contain: 1 person, eyeglasses
" አይቀሬው የለውጥ ማዕበል በኢትዮጵያ እና የህወሀት/ኢህአዴግ የቁልቁለት መንገድ!!! – ከይልቃል ጌትነት (ኢ/ር)
ከይልቃል ጌትነት (ኢ/ር)
ሰሞኑን ከሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ የመቀሌ ስብሰባ ምን ይመጣ ይሆን?የሚል አስተያየትና በተቃዋሚዎች በኩል ደግሞ እነ ዶ/ር በዛብህ ደምሴ የ2010 ዓ.ም የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምርጫ እንደሚሳተፉና እንደሚያሸንፉ ሲናገሩ ሰማሁ። ምርጫንና ሕወሐትን እንዲሁም ተያያዝ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከአምስት ወራት በፊት የፃፍኩትን ግምገማ ለወቅቱ ውይይት መነሻ እንዲሆን በድጋሜ ለጥፌዋለሁ።
አይቀሬው የለውጥ ማዕበል በኢትዮጵያ እና የህወሀት/ኢህአዴግ የቁልቁለት መንገድ!!!
ኢትዮጵያ ሐገራችን አሁን ላለችበት ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መፍትፌው ምን መሆን አለበት በሚለው አስተሳሰብ ላይ በገዥው ቡድንና በለውጥ ኃይሉ ያለው ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ ችግሮቹ በተጨባጭ መኖራቸውን በመረዳት በኩል ግን በገዥውም ሆነ በለውጥ ፈላጊዎች መካከል ብዙም ልዩነት ስለሌለ ስለሚደርሰው ግፍ፣ ግድያ፣ አፈናና ሌሎች ቀውሶችን መተንተን አሁን ላይ ብዙም አስፈላጊ ሆኖ ስላልታዬኝ በለውጥ አይቀሬነት፣ የለውጥ ስልቶችና ውጤቱ ላይ አተኩራለሁ፡፡
ለውጥ ተፈጥሯዊ ነው፣ማንኛውም ነገር ይለወጣል፡፡ የሰው ልጅም ይወለዳል ያድጋል ይሞታል፡፡ስልጣኔም ይፈጠራል፣ያብባል ከዚያም ያረጅና በሌላ ስልጣኔ ይተካል፡፡ አገዛዝም የተለያዩ ማደናገሪያዎችንና አስተሳሰቦችን ይዞ በስልጣን ላይ ይቆያል፡፡ ያለውን አመለካከትና አገዛዝ የማይሸከም ህሊናዊና ነባራዊ ሁኔታ ሲፈጠር በስብሶ ይወድቃል፣ በሌላ ሰርዓት ይተካል፡፡
ስለዚህም ህወሀት/ኢህአዴግ ወደደም ጠላም እኛ ተንቀረፈፍንም ፈጠንም በራሱ በተፈጥሮ ህግም ቢሆን ለውጥ አይቀሬ ነው፡፡ የእኛ ሚና ሊሆን የሚችለው ለውጡን በራሱ በተፈጥሮ ከሚሆነው ይልቅ እግዚዓብሄር በሰጠን አዕምሮ ተጠቅመን በታቀደና በተጠና መልኩ በአነስተኛ ወጭና ጊዜ ወደ ተሻለና አስቀድሞ ውጤቱ ወደታወቀ መንገድ መምራት ነው፡፡ ይህንን ካለደረግን ተፈጥሮ በራሱ ለውጥ የሚያደርግብን እንጅ በራሳችን ነገሮችን የምንለውጥ ወይም የመጡ ለውጦችን የምንቆጣጠር ሰብዓዊ ፍጡሮች መሆናችን ይቀርና ደመነፍሳዊ እንስሳ ወደ መሆን እንጠጋለን፡፡ ይህንን ካልኩ በኋል አሁን በሃገራች ያለውን የለውጥ ማዕበል በተመለከተ በሶስት ክፍሎች በአጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡
1. የለውጡ ሁኔታና የህወሀት/ኢህአዴግ የሁኔታዎች ትንተና
2. ለውጡ ሊመጣ/ሊፋጠን/ የሚችልባቸው አመራጮች
3. የሚመጣውን ለውጥ እንዴት ወደ ተሻለ ሁኔታ መምራት እንቻላለን በሚሉ መሰረታዊ ሃሳቦች እይታዬን አቀርባለሁ፡፡
1. የለውጡ ሁኔታና የህወሀት/ኢህአዴግ የሁኔታዎች ትንተና
ህወሀት/ኢህአዴግ አሁን ያለውን የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ሲገመግም “የጠባብና የትምክህት አመለካከቶች ለስርዓቱ አደጋ መሆናቸውንና ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር ተጨምሮበት የጀመርናቸውን ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ባለማጠናቀቃችን የህዝብ ቅሬታ ተፈጥሯል፡፡በዚህ ቅሬታ ምክንያት ሁከትና ብጥብጥ ተፈጥሮ ሌሎች ሃይሎች ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድርገውታል” የሚል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፈራ ተባ እያለም ቢሆን የልማትና የዲሞክራሲ ጥያቄ የብሄራዊ ደህንነት አጀንዳ መሆኑን ይገልፃል፡፡ ህወሀት/ኢህአዴግ የተፈጠረውን ችግር ከላይ በተገለፀው ሁኔታ ከተነተነ በኋላ ችግሮቹን ለማስወገድ እንደ መፍትሔ ያቀረበው ሐሳብ “በመጀመሪያ የተፈጠረውን ተቃውሞ በቁጥጥር ስር ማዋል፤ ለዚህም የእስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ ማንኛውንም እርምጃ መውሰድ፤ ቀጥሎም በጥልቅ የድርጅት ግምገማ የትምክህትና የጠባብ ሃይሎችን መምታት፣የድርጅትን የማስፈፀም አቅም በማሳደግ ለህዝብ ቅሬታዎች ምላሽ መስጠት ከዚህም በተጨማሪ የፓርላማ ወንበሮችን ሙሉ በሙሉ በማሸነፋችን ተቃዋሚ ሃይሎች ባለመደመጣቸው ስለሆነ የምርጫ አዋጁን ከተቃዋሚዎች ጋር በማሻሻል በቀጣዩ ዙር ምርጫ ተቃዋሚዎች መጠነኛ ወንበር እንዲያገኙ በማድረግ የህወሀት/ኢህአዴግን የተራዘመ የስልጣን ባለቤትነት ማረጋገጥ” የሚል ነው፡፡
ህወሀት/ኢህአዴግ የወቅቱ የሀገሪቱ ችግሮች እነዚህ ናቸው ይበል እንጅ የነገሮችን እድገትና የችግሮችን ዋና ምንጭ በውል ለመገንዘብ አልቻለም/አልፈለገም፡፡ ህወሀት/ኢህአዴግ እንደ ችግር የተቀበላቸውን ሀሳቦች እንደመነሻ ብንወስድ ትምክህትና ጥበት እንዴት ሊፈጠር ይችላል? ወቅታዊ ችግር ነው ወይስ በየደረጃው እያደገ የመጣ ችግር? ትምክህትና ጠባብነት እንደ ችግር እዚህ ደረጃ ከደረሰ በኋላ የችግሩን ምንጭ ሳይገነዘቡ እና የመፍትሄ ሃሳብ ሳያስቀምጡ በድርጅታዊ ግምገማ እንዴት ማጥፋት እንደሚቻል በግልፅ አላስቀመጠም ወይም ለማስቀመጥ አልፈገም፡፡ በተጨማሪም ዴሞክራሲና ልማት ጥያቄ አለመመለስ የብሔራዊ ደህንነት አደጋዎች ናቸው ብሎ ቢናገርም የዴሞክራሲና የልማት ጥያቄ በኢትዮጵያ እንዴት የህዝቡን ፍላጎት በሚመጥን ሁኔታ እውን ማድረግ እንደሚቻል ሳያሳይ የዴሞክራሲ መሰረታዊ ተቋማት እንዴት እንደሚገነቡ እና የዴሞክራሲና የልማት ጥልቅ ትስስርን ሳይገነዘብ ችግሩን ለማለፍ ብቻ በማድበስበስ እነደ ጊዜ መግዣ መንገድ እየተተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ስለሆነም በሕወሀት/ኢሕአዴግ የተሳሳተ የነባራዊ ሁኔታዎች ግምገማ ላይ ተመርኩዞ የሚሰጥ የመፍትሄ ሀሳብ ውጤታማ ስለማይሆን የለውጡን አይቀሬነት ያመላክታል፡፡
በእኔ እምነት ህወሀት/ኢህአዴግ እንደሚለው ሀገሪቱ አሁን ላለችበት ችግር መሰረቱ ጠባብነትና ትምክት ያመጣው ነው የሚለውን ብንቀበል እልኳን ጠባብነትና ትምክህት ላለፉት 26 ዓመታት ሕወሀት/ኢህአዴግ ውሃ እያጠጣና እየኮተኮተ በየደረጃው እያሳደጋቸው የመጡ ችግሮች እንጅ በድንገት የተፈጠሩ ስላልሆኑ የተፈጥሮ እድገታቸውን ጨርሰው የሚያደርሱትን ጥፋት አድርሰው ይከስማሉ እንጅ በድርጅት ግምገማ ሊጠፉ አይችሉም፡፡ ስለሆነም ህወሀት በባህሪውና የተመሰረተበትን የቆመበትን የማነነት ፖለቲካ እስካልቀየረ ድረስ የራሱ የችግር መገለጫ የሆኑትን ጠባብነትና ትምክህትን መዋጋት አይችልም፡፡ በሌላ አነጋገር ለማታለልም ቢሆን በማንነት ላይ ተመርኩዞ ራስን ለማስተዳደር በህገ መንግስት የተፈቀደው መብት በክልሎች ዘንድ እያደገ ስለሚሄድና ከህወሃት ተፈጥሯዊ የጠቅላይነት ባህሪ ጋር በፅኑ ስለሚቃረን የውስጥ ሽኩቻውን ከጊዜ ጋር እያጠናከረው ይሄዳል፡፡ ጠቅለል ባለ አነጋገር ህወሃት አሁን በያዘወ የችግር አፈታት ዘዴ ከጊዜ ጋር በተቃራኒው መንገድ ስለሚሄድ ጊዜ በጨመረ ቁጥር የማንነት ጥያቄዎችና ሽኩቻዎች እያደጉ ድርጅቱ እራሱን በራሱ እየበላ ወደማይቀረው ሞት አፋፍ ይሄዳል፡፡ ስለሆነም ለውጥ አይቀሬ ይሆናል፡፡
ዴሞክራሲ በመሰረቱ ለአብላጫ ድምፅ በመገዛት የአናሳውን መብት ማክበር ሲሆን በዚህ መሰረት ከህዝብ መካከል በህዝብ የተመረጠ እና ለህዝብ የሚሰራ ማለት ነው፡፡ ከዚህ መሰረታዊ የዴሞክራሲ አስተሳሰብ አንፃር ህወሃት/ኢህአዴግን ስናየው ድርጅቱ እጅግ የጠበቀ ማዕከላዊነት ያለውና ጥቂቶቹ ብዙኃኑን እንደፈለጉ የሚገዙበት ስልጣንና ተዕዛዝ ከላይ ወደ ታች የሚወርድብት ከዴሞክራሲ ፅንሰ ሀሳብ በተፃራሪ የተፈጠረ ድርጅት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ህወሃትና ዴሞክራሲ አይተዋወቁ ወይም በአንድ ላይ ሊገኙ አይችሉም፡፡ የህወሃትና የዴሞክራሲን ዝምድና በጨለማና በብርሃን መመሰል ይቻላል፡፡ ብርሃን ካለ ጨለማ የለም፤ ጨለማ ካለ ብርሃን የለም፡፡ ጨለማና ብርሃን አንዱ ሌላውን ካላጠፋ በስተቀር በአንድ ላይ ሊገኙ አይችሉም፡፡ ህወሃትና ዴሞክራሲም እንዲሁ ናቸው፡፡ ህወሃት ካለ ዴሞክራሲ የለም፤ ዴሞክራሲ ካለ ህወሃት የለም፡፡ በተፈጥሮ ባህሪያቸው አንዱ ሌላውን ካላጠፋ በስተቀር በአንድ ላይ ሊገኙ አይችሉም፡፡
በአጠቃላይ ህወሃት/ኢህአዴግ አሁን በያዘው የችግር መፍቻ መንገድና ከላይ በተነሱት ትንተናዎች መሰረት ትምክህትንና ጠባብነትን ታግሎ አመጣዋለሁ የሚለው ዴሚክራሲ እንደ ጊዜ መግዣና ማታለያ አድርጎ ስልጣኑን ለማስቀጠል የያዘው የመፍትሔ መንገድ በመሰረቱ የተሳሳተ የችግር ግምገማና መፍትሄ ላይ የተንጠለጠለ ስለሆነ የለውጡን ሂደት በእጅጉ ያፋጥነዋል፡፡ ለውጡንም አይቀሬ ያደርገዋል፡፡
2. ለውጡ ሊመጣ/ሊፋጠን/ የሚችልባቸው አማራጮች
ለውጥ መምጣቱ አይቀሬ መሆኑን ከላይ ያነሳኋቸው መሰረታዊ ምክንያቶች የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ገዥውም ቡድን ቢሆን ለውጥ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው በማለት ጥገናዊም ቢሆን ለውጥ ሳያደርግ ሊቀጥል እንደማይቻል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ ለውጡ በምን ይመጣል በሚለው ላይ ግን የተለያዩ ወገኖች የተለያዩ እይታዎች እንዷላቸው በማሰብ የለውጡን ማዕበል ሊያፋጥኑ ለለውጥም ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉ አማራጭ የትግል ስልቶች መካከል፡-
ምርጫ
የትጥቅ ትግል
በውጭ ሃይሎች ተፅዕኖ
በህወሃት/ኢህአዴግ የሚወሰድ የማሻሸያ እርምጃ
መፈንቅለ መንግስት
ህዝባዊ እምቢተኝነት
የእርስ በእርስ ጦርነት እና የሐገር መፍረስ አደጋ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የለውጥ አማራጭ መንገዶች ለውጡን ለማምጣት ያላቸውን እድል ለመለየት እያንዳንዱን መንገድ ያለውን መልካም ዕድል ወይም ችግር በዝርዝር ማየት ያስፈልጋል፡፡
1ኛ. በምርጫ ለውጥ ማምጣት፡-
ምርጫ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥን ሊያመጣ ይችላል ወይም አይችልም ከማለቴ በፊት ምርጫ በባሕሪው ከምንም አስቀድሞ ነፃነትን የሚሻና መራጩ የሚፈልገውን ለመምረጥ አማራጮች በእኩልነት የሚቀርቡበት መንገድ ነው፡፡ ለኢህአዴግ ምርጫ ማለት ዛሬ የሰው ልጅ ከደረሰበት የአስተሳሰብ ልዕልና አንፃር ቢያንስ ቢያንስ ያለማስመሰያ ምረጫ በገዥነት መቀመጥ ጊዜው ያለፈበት አስተሳሰብና የኢህአዴግ ቁንጮ የሆነው ሕወሃት የአናሳ ቡድን ተወካይ በመሆኑ ብዙሃኑን ሁልጊዜ በኃይል አፍኖ ለመግዛት የማይችል መሆኑን ስለተረዳ የሚጠቀምበት የማታለያ ስልት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አድርገው ወደስልጣን ያመጡትን ምዕራባውያን አሁን በደረሱበት የስነ መንግስት አወቃቀር ስልጣንን በምርጫ መለወጥ መርህአቸው እያደረጉት በመምጣታቸው ድጋፍ የሚደርጉላቸው አናሳ ቡድኖች ምርጫ እንዲያደርጉ ስለሚያስገድዱ የእነሱን ፍላጎት ለሟሟላት ብቻ ለይስሙላ የሚጠቀምበት ስልት እንጅ ዜጎች በነፃ ምርጫ የሚፈልጉት የሚያወጡበትና ያልፈለጉትን የሚያወርዱበት መንገድ እንዲሆን ስለሚፈልግ አይደለም፡፡ በነፃ ምርጫ የሚወለድ ዲሞክራሲ መሰረታዊ ባህሪው በብዙሃን ድምፅ መገዛትን እና የአናሳዎችን መብት ማክበር ነው፡፡ ሁለቱም መሰረታዊ ሃሳቦች ማለትም ነፃነትና ዲሞክራሲ ስለሌሉና የሕወሃት አፈጣጠር ከነዚህ በተቃርኖ የቆመ ስለሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ ለውጥ ማምጣት አይቻልም፡፡ ነፃነት ለዲሞክራሲዊ አስተዳደር ቅድመ ሁኔታ ነው፤ነፃነትና ዲሞክራሲ በሌሉባት ኢትዮጵያ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ አይቻልም፡፡
2ኛ. በትጥቅ ትግል ለውጥ ማምጣት፡-
ዓለም በካፒታሊዝምና ኮሚዩኒዝም ርዕዮተ ዓለም ጎራ ተከፍላ ስትናጥበት የነበረው ዘመን የኮሚንይዝሙ ጎራ ተዳክሞ ከተፈረካከሰ በኋላ ዓለም በብቸኝነት በምዕራቡ የካፒታሊዝም ተፅዕኖ ስር ወድቃለች፡፡ የሁለቱ ጎራዎች ፉክክር በተመጣጣኝ ደረጃ በነበረት ወቅት በአንድ ጎራ የተቀመጠን ስርዓት ማውረድ የፈለጉ አካላት ከተቃራኒው ጎራ በሚያገኙት ድጋፍ መንግስታትን በትጥቅ ትግል ሲለዋውጡ አይተናል፡፡ ነገር ግን የኮሚንይዝሙ ጎራ ተዳክሞ ከተፈረካከሰ በኋላና ዓለም በምዕራቡ ዓለም የአስተሳሰብ ዕዝ ስር ከወደቀ በኋላ በስልጣን ላይ የተቀመጡ አምባገነኖችን በትጥቅ ለማውረድ የሚሞክሩ ለውጥ ፈላጊዎች በበቂ ሁኔታ ድጋፍ የሚሰጣቸው ኃይል ባለመኖሩ በዚህ ስልት አምባገነኖችን ለመቀየር እየከበደ እንደመጣ የኮምኒይዝሙ ዓለም ከፈረሰበት ካለፉት 28 ዓመታት ወዲህ በጠመንጃ የተቀየረ አምባገነን ስርዓት ዓለሞኖሩ ግልፅ ማሳያ ነው፡፡ እዚህ ላይ የኮንጎንና የሊቢያ አምባገነኖች ከኮምኒዝም ጎራ መፈረካከስ በኋላ በጠመንጃ ኃይል የተገረሰሱ አምባገነኖች በመሆናቸው እንደመከራከሪያ ሊቀርቡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በሁለቱ ሐገራት ላይ በትጥቅ ትግል ለውጥ የመጣበትን መንገድ በጥንቃቄ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ኮንጎ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት መዝረፍ የፈለጉ ኃይሎች ያለ ኃፍረት የካቢላን ኃይሎች በቀጥታ በማስታቅና በመርዳት ስድስት ወር ባልሞለ ጊዜ ውስጥ ወትሮም ደካማና በሙስና የላሸቀውን የዛየር መንግስት ማውረዳቸው ከጀርባው የሚፈልጉትን ቡድን ወደስልጣን በማውጣት እሱን ተጠግተው የተፈጥሮ ሐብቷን ለመዝረፍ የፈለጉ ሰፍሳፋ የውጭ ኃይሎች የነበራቸውን ሚና በተለዬ ሁኔታ ማየት ይኖርብናል፡፡ የሊቢያውን አምባገነን ኮሌኔል ሞአመር ጋዳፊን ለማውረድ ምዕራባውያን በቀጥታ በዓየርና በምድር ጥቃት በማድረስ የሊቢያ ለውጥ ፈላጊዎች ጋዳፊን ለማውረድ ካደረጉት እንቅስቃሴ ጀርባ ምዕራባውያን የነበራቸው ጣልቃ ገብነት እጅግ ያፈጠጠ ስለነበረ በትጥቅ ትግል ለውጥ መጥቶበታል ለሚባል መከራከሪያ ማሳያ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም፡፡ በዚህም መሰረት በኮንጎና በሊቢያ በትጥቅ የተደረጉ ለውጦች ምን ያህል በውጭ ኃይሎች ፍላጎት የተመሩ እንደነበሩ በማሰብ ባሁኑ ዘመን በትጥቅ ትግል ከሚደረጉ ትግሎች ጋር በተለዬ ሁኔታ መታየት አለባቸው እላለሁ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በቅርብ ጊዜ የትጥቅ ትግል የጀመሩት ይቅርና ዓለም በሁለት ጎራ በተከፈለችበት ወቅት ጀምረው የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነቡሩት ለአብነት ያህል የኮሎምቢያው ፋርክ፤ የኩርዶቹ ፒኬኬ፣ የስፔኑ ኤታ፤ የዩጋንዳው ሎርድ ሬስታንስ እና ሌሎችም የትጥቅ ትግል አራማጆች እየተዳከሙ እንደመጡና አሁን ለውጥን በድርድና በሰላማዊ መንገድ ለማምጣት ጥረት ላይ እንዳሉ ስናይ አሁን ባለንበት ዘመን በትጥቅ ትግል ለውጥ ለማምጣት እየከበደ መምጣቱን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያም በትጥቅ ትግል ለውጥ እናመጣለን የሚሉ ኃይሎች ዓለም ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ሰለባ በመሆናቸው እስካሁን ተጨባጭ ለውጦችን ማምጣት አልቻሉም፡፡ ወደፊም ቢሆን ለምዕራባውያንም ሆነ ለኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ጥቅም መከበር ተቃዋሚዎች ከገዥው ቡድን የበለጠ ምቹ ሆነው ስለማይገኙ ድጋፍና እርዳታ አግኝተው ገዥውን ቡድን በትጥቅ ትግል የማውረዳቸው እድል እጅግ የመነመነ ይመስለኛል፡፡
3ኛ. በውጭ ኃይሎች ተፅዕኖ ለውጥ ማምጣት
በሐገሮች መካከል የሚደረጉ ዲፕሎማሲዊም ይሁን ሌላ ዓይነት ግንኙነት መሰረታዊ መነሻው ሁሉም የየራሱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በመሆኑ እያንዳንዷ የሚያደርጓት እንቅስቃሴ ከጥቅማቸው መከበር ወይም ማጣት ጋር ያለውን ተፅዕኖ በማስላት ነው፡፡ እንደ መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ ዛሬ በመላው ዓለም በስልጣን ላይ የተቀመጡ አምባገነኖች ዜጎቻቸውን ቀጥቅጠው እየገዙ ቢሆንም በመሸጦነታቸው የውጭ ኃይሎችን ጥቅም በማስከበር ለለውጥ ከሚታገሉ የዲሞክራሲና የነፃነት ኃይሎች በላይ እጅግ የተመቹ በመሆኑ አገልጋይነታቸውን በማሳየት ከውጭ ኃይሎች የሚደርስባቸውን ተፅዕኖ እያሳነሱ መጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የውጭ ኃይሎች የራሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም እስካስከበሩ ድረስ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀመው በደልና ግፍ ብዙም ግድ ስለማይሰጣቸው በበደል ሰለባዎች ላይ የተፈፀመው ድርጊት ያሳስበናል እያሉ ሲቀልዱ ከመኖር አልፈው የእነሱን ጥቅም ያልነካን አምባገነል እንዲያውም በተቃራኒ በስውርና በግልፅ ድጋፍ ከማድረግ አልፈው ተፅዕኖ በመፍጠር ለለውጥ አስተዋፅዖ ሊያደርጉ አይችሉም፡፡ ወትሮም ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት መከበር ደንታ የሌላቸው ራሳቸውም በአምባገነኖች ስር ያሉና የወደቀው የኮሚንስት ርዕዮተ ዓለም ትራፊ የሆኑ የምስራቁ ዓለም ሐገሮች ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ የሚታገሉ ኃይሎችን ትግል ደግፈው ተፅዕኖ ይፈጥራሉ ተብሎም አይታሰብም፡፡ እንግዲህ የዲሞክራሲና የነፃነት ኃይሎች መሸጦነታቸው በስልጣን ላይ ካሉት አምባገነኖች በላይ ሆኖ የውጭ ኃይሎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን የበለጠ የሚያስጠብቁበትን መንገድ ካላሳዩ በስተቀር የውጭ ኃይሎች በአምባገነኖች ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር ለውጥ ለማምጣት ያላቸው ሚና በተለይ በኢትዮጵያ ሁኔታ የማይታሰብ ነው፡፡
4ኛ. በህወሃት/ኢህአዴግ በሚወሰዱ የየማሻሸያ እርምጃዎች ለውጥ ማምጣት
ከዲምክራሲያዊ ስርዓት በተቃርኖ የተቀመጠው የሕወሀት/ኢህአዴግ ገዥ ቡድን ህዝባዊ አመፅ ባናወጠው ሰሞን አክራሪ ጠባብ ኃይሎችና የትምክህት ኃይሎች ለስልጣኑ አደጋ እንደሆኑበት በመግለፅ እነዚህን ጠባብና የትምክህት ኃይሎች በጥልቅ ተሃድሶ አጥፍቶ ለውጥ አመጣለሁ በማለት ሲንደፋደፍ ታይቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመልካም አስተዳደር እጦትና አንዳንድ መሰረታዊ የሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን ከተቃዋሚዎች ጋር በመነጋገር አንዳንድ ህጎችንና የህገ መንግስት ማሻሻያ በማድረግ ኢህአዴግ ራሱን ለውጦና አሻሽሎ በገዥነቱ ለመቀጠል ያለውን ፍላጎት ለማሳከት የሄደበትን የምኞት መንገድ ታዝበናል፡፡ ከላይ በመግቢያው እንደተጠቀሰው ኢህአዲግን በህዝባዊ አመፅ ጭንቅ ውስጥ አስገብቶት ዛሬ ሐገራችንን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም በወታደራዊ አገዛዝ ሥር እንድትወድቅ ያደረጋት ጠባብነትና ትምክህት ነው የሚለው የሕወሀት/ኢህአዴግ የግምገማ ግንዛቤ እወነት ነው እንኳ ብንል ጠባብነትና ትምክህትን ገዥው ቡድን ላለፉት 26 ዓመታት ውሃ እያጠጣና እየኮተኮተ በየደረጃው እያሳደጋቸው የመጡ ችግሮች እንጅ በድንገት የተፈጠሩ ስላልሆኑ የተፈጥሮ እድገታቸውን ጨርሰው የሚያደርሱትን ጥፋት አድርሰው ይከስማሉ እንጅ በሕወሀት/ኢህአዴግ የድርጅት ግምገማ ሊጠፉ አይችሉም፡፡ ስለሆነም ህወሀት በባህሪውና የተመሰረተበትን የማነነት ፖለቲካ እስካልቀየረ ድረስ የራሱ የችግር መገለጫ የሆኑትን ጠባብነትና ትምክህትን መዋጋት አይችልም፡፡ በሌላ አነጋገር ለማታለልም ቢሆን በማንነት ላይ ተመርኩዞ ራስን ለማስተዳደር በህገ መንግስት የተፈቀደው መብት በክልሎች ዘንድ እያደገ ስለሚሄድና ከህወሃት ተፈጥሯዊ የጠቅላይነት ባህሪ ጋር በፅኑ ስለሚቃረን የውስጥ ሽኩቻውን ከጊዜ ጋር እያጠናከረው ይሄዳል፡፡ ጠቅለል ባለ አነጋገር ህወሃት አሁን በያዘወ የችግር አፈታት ዘዴ ከጊዜ ጋር በተቃራኒው መንገድ ስለሚሄድ ጊዜ በጨመረ ቁጥር የማንነት ጥያቄዎችና ሽኩቻዎች እያደጉ ድርጅቱ እራሱን በራሱ እየበላ ወደማይቀረው ሞት አፋፍ ይሄዳል፡፡ ስለሆነም በህወሃት/ኢህአዴግ በሚወሰዱ የየማሻሸያ እርምጃዎች ለውጥ ማምጣት አይቻላቸውም፡፡
5ኛ. በመፈንቅለ መንግስት ለውጥ ማምጣት
በመሰረቱ መፈንቅለ መንግስት ሊደረግ የሚችለው የፖለቲካውና የወታደራዊ ኃይል አንደኛው ከሌላው ገለልተኛ ሆኖ የተዋቀረ ሲሆንና አምባገነኖች ባሉበት ሐገር ወታደራዊ ኃይሉ የህዝብ ወገንተኝነት ያለው ከሆነ ወይም ወታደራዊ ኃይሉ ከሲቪል አስተዳደሩ የተለየ አመለካከት ሲኖረው ነው፡፡ በግልፅ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማትና የደህንነት ኃይሎች እና ገዥው የሕወሀት/ኢህአዴግ በዘርም ሆነ በአመለካከት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች በመሆናቸው እንደ ሁለት የተለያዩ አካላት ሊታዩ አይችሉም፡፡ አመራሩ መቶ በመቶ በአንድ ሰፈር ልጆች የተያዘው የኢትዮጵያ የወታደራዊ ኃይል የሰፈሩ ልጆችና የጥቅም ተጋሪው የሆኑ የሲቪል አስተዳደሩን መሪዎች አውርዶ በጠላትነትና እንደ ባዕድ በሚቆጥራቸው የዲሞክራሲ ኃይሎች እንዲተካ የራሱን ሚና ይጫወታል ብሎ መጠበቅ ሲበዛ የዋህነት ይሆናል፡፡ ስለዚህም በሕወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመን ለውጥ በመፈንቅለ መንግስት ይመጣል ተብሎ አይታሰብም፡፡
6ኛ. በህዝባዊ እምቢተኝነት ለውጥ ማምጣት
የሕወሀት/ኢህአዴግ የማስመሰያ የሲቪል አስተዳደር ኢትዮጵያን የማስተዳደር አቅሙ ተዳክሞ ዛሬ ሐገራችንን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም በወታደራዊ አገዛዝ ሥር እንድትወድቅ አድርጓታል፡፡ ለውጥ የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው፡፡ ባለፉት 26 ዓመታት ለውጥን በሰላማዊ መንገድ ለማምጣት ብዙ ዋጋ የከፈሉና እየከፈሉ ያሉ የፖለቲካ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የኃይማኖትና የሞራል ሰዎች፣ የኪነጥበብና የስነ ጥበብ ባለሙያዎች ያደረጉአቸው አስተዋፅዖዎች ስርዓቱ ዛሬ ለወደቀበት የጭንቅ መንገድ የራሰቸውን ሚና አበርክተዋል፡፡ በሕወሀት/ኢህአዴግ አስተሳሰብም ዛሬ ላጋጠመኝ ፈተና መነሻው ጠባብነትና ትምክህት ነው የሚለው አስተሳሰብም ለማታለያነት ታስቦ በሰነድና በሕግ የተቀመጠ የመብትና የአስተሳሰብ መሰረትም እያደገ መጥቶ ጥቂቶች ብዙሃኑን እየገዙ የሚኖሩበት ስርዓት በህዝባዊ እምቢተኝነት ወደ ለውጥ እየተገፋ መምጣቱን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ዛሬ ሕወሀት/ኢህአዴግ ደረሸበታለሁ በሚለው ግምገማም ሆነ አማካሪዎቹ በአደባባይ የሚሰጡት ምክር ለውጥ ማድረግ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ አከራካሪነቱ አክትሟል፡፡ ነገር ግን የሕወሀት/ኢህአዲግ የችግር ግምገማና የመፍትሔ መንገድ ችግሮችን የመፍታት አቅም ስለሌላቸው የትንሽ ጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ሕዝባዊ ተቃውሞውን አያቆመውም፡፡ ሕወሀት/ኢህአዴግ በጥገናዊ ለውጥ ሊያቆመው የፈለገው ስርዓትም መፈራረሱ አይቀሬ ነው፡፡ በሰላማዊ መንገድ የታገሉ ዜጎች በፈጠሩት የፖለቱካ ጫና ያስከተለው ህዝባዊ እምቢተኝነትም ሆነ በሕወሀት/ኢህአዴግ የግምገማ ድምዳሜ ጠባብና የትምክህት ኃሎች የፈፀሙት ሕዝባዊ አመፅ ስርዓቱን ወደ ከፍተኛ ጭንቅ በመክተት ባለፉት 25 አመታት ካጋጠሙት ፈተናዎች በላይ ወደ መፍረስ ጫፍ ስላመጣው የሲቪል አስተዳደሩን አፍርሶ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም ሐገራችንን በወታደራዊ አገዛዝ ስር እንድትወድቅ በማድረግ የሲቪል አስተዳደሩን ለመመለስ ፍርሃትና ጥርጣሬ ውስጥ ከቶት ይገኛል፡፡ ከላይ ከተነተንናቸው የትግልና የለውጥ አማራጮች መካከል ሕዝባዊ እምቢተኝነት በስርዓቱ ላይ ተጨበጭ ጫና በመፍጠር ከሌሎች ስልቶች የተሻለ ለውጥ የማምጣትም አቅም ያለው ስልት መሆኑን አሳይቷል፡፡ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታና አሁን ባለው የዓለም የኃይል ሚዛን አሰላለፍ አንፃር ሲታይ በገዥው ቡድን ላይ የመጨረሻውን ለውጥ ለማምጣት የተሻለ እድል ያለው የትግል አማራጭ ስልት ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
7ኛ. የእርስ በእርስ ፍጅት እና የሐገር መፍረስ አደጋ
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ እንደምንገነዘበው ወደ ዲሞክራሲ ለመሸጋገር መልካም አጋጣሚ የነበሩ በርካታ የለውጥ ሙከራዎች በእርስ በእርስ ሽኩቻና በአመራር ድክመት ምክንያት በትክክል ሳንጠቀምባቸው በማለፋችን አሁን ሐገራችን ላለችበት ምስቅቅል አድረሰናታል፡፡ አሁንም ሊመጣ ያለውን ለውጥ በተጠናና በምክንያታዊ አስተሳሰብ ካልገራነው በስተቀር አሁን እያቆጠቆጡ የመጡት የአመለካከት ጫፎች በኢትዮጵያ ውስጥ የእርስ በርስ ፍጅትና የሐገር መፍረስ አደጋ ያንዣበበ መሆኑ ብዞዎቻችን ባንወደውም አፍጥጦ እየመጣ ያለ ሐቅ ነው፡፡ ሐገር መፍረስ በዜጎች ላይ የሚያመጣውን ስቃይ፣ በአጎራባች አካባቢዎች የሚፈጥረውን ትርመስ ግምት ውስጥ በማስገባት በሌሎች ሐገሮች የደረሰው መከራ በእኛም ላይ ከመድረሱ በፊት ሁላችንም ለመፍትሔው የበኩላችንን መልካም አስተዋፅዖ ማድረግ ይኖርብናል እላለሁ፡፡
3. የሚመጣውን ለውጥ እንዴት ወደ ተሻለ ሁኔታ መምራት እንቻላለን
በሁለቱ ዋና ርዕሶች ለማሳየት እንደሞከርኩት ሕወሀት/ኢህአዴግ ችግሮችን የሚገመግመው በተሳሰተ መንገድ መሆኑና የሚያቀርባቸው የምፍትሔ ሐሳቦችም ችግሮች አሁን ያሉበትን ደረጃ የማይመጥኑ በእውነትም መፍትሔ የማያመጡ በሙሆኑ በእኔ አስተያዬት በኢትዮጵያ የለውጥ ማዕበል አይቀሬ ነው፡፡ አሁን ባለው የኢትዮጵያና አለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሕዝባዊ እምቢተኝነት በተግባር ውጤት ያመጣና የወደፊቱንም የሐገራችንን የለውጥ ሂደት በመወሰን ከሌሎች አማራጮች የተሻለ እድል እንዳለው ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡ ነገር ግን ይህን በህዝባዊ እምቢተኝነት የሚመጣ ለውጥ በአግባቡ ካልያዝነው የእርስ በእርስ ፍጅትና የሐገር መፍረስ አደጋም ሊያመጣ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ይህንን አደጋ በመገንዘብና ካለፈ ታሪካችን ትምህርት በመውሰድ ለዉጡ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በአወንታዊነት የሚቀበሉትና ለውጤታመነቱም የሚሰሩለት የጋራ አጀንዳ መፍጠር ይኖርብናል፡፡
እዚህ ላይ የታሪካችን አካል የሆነውን የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴና የመሬት ላራሹ አጀንዳን መጥቀስ አሁን ላለንበት ሁኔታ ትምህርት ሰጭ ይመስለኛል፡፡ የመሬት ላራሹ ጥያቄ በአፈፃፀሙና በውጤታማነቱ ላይ አከራካሪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በወቅቱ ግን በኢትዮጵያ የለውጥ ኃይሎችን ለማሰባሰብና ለማስተባበር በብዙዎቹ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ትልቅ የጋራ አጀንዳ ነበር፡፡ ከዚህ ትምህርት በመውሰድ በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ ኃይሎች መካከል ያለውን ያለመተማመን የሚቀንስ የኢትዮጵያን የሽግግር ወቅት የሚመጥን ሁሉን አቀፍ የሆነና በጊዜ የተገደበ “የባለ አደራ መንግስት መቋቋም አለበት” የሚል አጀንዳ ከፍ ብሎ መውጣትና መሰባሰቢያ የለውጥ ግብ ሆኖ መቀረፅ አለበት፡፡ የባለ አደራ መንግስቱ ይዘት፣ ስልጣንና ኃላፊነት ውክልናና አሳታፊነት በሂደት በዝርዝር በድርድርና በውይይት ቅርፅ ሊይዝ የሚችል ጉዳይ ይሆናል የሚል እምነትም አለኝ፡፡
ከትውልድ ተጠያቂነት ለማምለጥ የተሻለውን ነገር ለመስራት ከአሁን የተሸለ ጊዜ የለንም!!!!
አመሰግናለሁ!!!
እስካሁን ከተከታተልኳቸው የኢትዮጵያን የፖለታካ ትኩሳት በትክክል የለካ ቴርሞ ሜትር (ቴርሞ ፖለቲክስ) ነው ህውሃት ከመሻሻልና ለለውጥ እራሱን ከማዘጋጀት ይልቅ እለወጣለሁ እያለ አሳምሞ ይናከሳል አንድ ሰው አካሉ ከተነከሰ የበለጠ መጮሁ አይቀርም ሲኮተኩትና ውሃ ሲያጠጣቸው የነበሩት የኤትኒክስ ፓለቲክስ እሳቤዎች ጥቂቶች የስልጣንና የሃብት ማማ ላይ እንደሚያስቀምጣቸው ስለሚያውቁ ለመጡበት ጎሣ ሽንጣቸውን ገትረው ይጮሃሉ ሺ ቢታለብ ያው በገሌ ነው እንዳለችው ድመት ለጎሣው አባላት የተረፈላቸው ያው በቋንቋቸው መናገርና የማያውቁትን የክልል ሰንደቅ አላማ ማውለብለብ ነው
ከክልል አንዱ አንዱን ጎሳ ማባረሩይቀጥላል ከጉረፈርዳ የተባረሩት ተመልሰዋል ?አልተመልእሱም አይደል ? አንድን ነገር ወደ ነበረብት ሁኔታ እስታተስኮ state es coup ሳይመለስ ተመሳሳዩን ማረም እንዴት ይቻላል? ህውሃት በስብሰባ ተወጥሮአል ግን ምንም ለውጥ ለማምጣት አይችልም እንደውም የበለጠ ጨካኝ ለመሆን ይዘጋጃል ምንአልባትም የአዴጋ ጌዜ መንግስት መሆኑን በድጋሚ ሊያውጅ ይችላል ምንአልባት የውጭ መንግስታት ተፅእኖ በማድረግ የተረጋጋ መንግስት እንዲሆን ጣልቃ ሊገቡ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊከሰት ይችል ይሆንምክንያቱም ኢትዪጵያ ከተበተነች ምስራቅ አፍሪካ መበተኑ እይቀርም ለምእራቡ አለም ኢትዪጵያ የተሻለች አስፈላጊ አገር ናት ደቡብ ሱዳን ያልተረጋጋ ነው ሱማሌ ያልተረጋጋና አዲስ መንግስት ነው ኤርትራ የተገለለ እና ዝግ ነው ሰሜን ሱዳንም ደካማ ነው ኬንያ በምርጫ ቅራኔ ውስጥ ያለ አገር ሲሆን እንደጨረቃ የፖለቲካ ብርሃኑን ከሌሎች ነው የሚያገኘው ጂቡቲ ተፅእኖ ፈጣሪ ያልሆነች አገር ነች ግብፅ ጠንካራ ቢሆንም ጥቁሩን ፓርት አፍሪካ ለመምራት ስነልቡናው እይፈቅድለትም ::እና ምእራባውያን ለጥገናዊ ለውጥ ሸምጋይ ሆነው ብቅ ሊሉ ይችላሉ ለአስራ አንድ አምስት ጉዳይ ከመሆኑ በፊት ቢሆን እዴት ጥሩ ነበር ከዛ የተረፈውን ላነሳው እልፈልግም የምፅአት ቀን በሉት:: "  Read more here

ክፍት ስራ ማስታወቂያ

Image may contain: text
ክፍት ስራ ማስታወቂያ
===================
Ethiopia Today ከዚህ በታች የተቀመጠውን የሥራ መደብ የምታሟላ ሴት አመልካች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
1• የስራ መደቡ:  የመረጃ ቴክኖሎጂ / information technology
2• የሥራው አይነት: መረጃ ሰብሳቢ፣ አቀናባሪ እና መረጃ አሰራጭ
3• ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ። ድፕሎማ/ ድግሪ በሙያ ቴክኒክ ወይም በእንፎርሞሽን ቴክኖሎጂ ወይም በእንፎርመሽን
ሲስተም ወይም በኮፒተር ሳይንስ።
4. ተፈላጊ የስራ ልምድ: ለድፕሎማ አራት አመት እና ከዛ በላይ ለድግሪ ሁለት አመት እና ከዛ በላይ በሶሻል
ኔትዎርኪግ፣ በሶሻል ሚዲያ ማነጅግ፣ በብሎጊግ፣ መሰረታዊ HTML ኮዲግ፣ ቪዲዎ ኢዲቲግ እና መሰረታዊ የሆነ ዳታ
ቤዝ ማኔጂንግ።
5• ደሞዝ: 5000 የኢትዮጵያ ብር
6• የስራ ቦታ: አዲስ አበባ
7• የቅጥር ሁኔታ: በኩንትራት ሁኖ እንደአፈፃፀሙ በየአመቱ የሚታደስ
8• ፆታ: ሴት
9. ብዛት: ሁለት
ማሳሰቢያ: ከላይ የተጠቀሰውን የምታሟሉ አመልካቾች CV ፣ የድፕሎማ ወይም ድግሪ፣ ትራንስክሪፒት እና የስራ
ልምዳቹህን ፎቶ ኮፒ በአንድ PDF ፋይል ( የፋይል ስም ስማቹህን) በማድረግ  ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ለ10
ተከታታይ ቀናት  ለEthiopia Today at ethiop.Today@gmail.com ኢሜል በማድረግ መመዝገብ
እንደምትችሉ እናሳውቃለን። ለፈተና እና እንተርቢው ለምትቀርቡ ልጆች በአድራሻቹህ ይደወልላቹሀል። ለበለጠ መረጃ

Ethiopia Today
e-mail: ethiop.Today@gmail.com
Mobil: +251920233894
www. ethiopian-today.blogspot.com
www.facebook.com/ethiopToday

Wednesday, October 4, 2017

ስለ ኢሬቻና ኦዳ አመጣጥ ከመሰረቱ

ስለ ኢሬቻና ኦዳ አመጣጥ ከመሰረቱ 🌻
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን እንደ ከተበው 
« ... አቴቴ ፈጣሪ ሰላም እንዲያወርድ ተማፅና የመታሰቢያ ዋርካ ተከለች። አምላክም ዝናብ አዝንቦ ዋርካውን አሳደገው፣ ልጆቿም የሚዳኙበት አዲስ ስርዓት ነገራት። ያንንም የሰላም ትንሣኤ ሕይወት ገዳ ስርዓት አለው። ጥንታዊ ና መሰረታዊ እምነቱ ደግሞ ዋቄፈና ተባለ። ኢሬቻ ይህ ስርዓት የሚከበርበት በዓል ነው።
የእሬቻ አከባበርና ለኦሮሞ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት ...
በኢትዮጵያ በኩሽ ምድር ፥ እሬቻ በኦሮሞ ዘንድ በገዳ ስርዓት ህዝቡ ተሰብስቦ ለምለም ቄጠማ፤ አረንጓዴ ቅጠል፤ አበባ ይዞ ፤ ፈጣሪን በወንዝ/በሀይቅ ዳርቻ ወይም በተራራ ላይ የማመስገን፤ የማክበር ፤የማምለክ በአል ነው። ገዳ ስርዓት በውሰጡ የፖለቲካ፣ የሐይማኖት፣ የባህል እና የምጣኔ ሀብት ሰንሰለቶችን የያዘ ነው። በክረመት ወቅት ወነዞቸ ስለሚሞሉ ሰዎች አይገናኙም፤ ማህበራዊ ግነኙነቶችም ይቀነሳሉ፤ መስከረም ሲጠባ የክረምት ወቀት አልቆ፣ የሞሉ ወንዞች ቀንሰው ፣ የተዘራው ያብባል፣ ጨለማው በብርን ይተካል፣ ምድር በልምላሜ ታጌጣለች። የዚህ ሁሉ መልካም ነገር ባለቤት ደግሞ ዋቃ/ ፈጣሪ/ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ለዋቃ ከፍተኛ የሆነውን ምስጋና ወደ ወነዞችና ሐይቆች በመውረድ ያቀርባል። ወንዞች ወይም ሐይቆች የተመረጡበት ምክንያት ውሃ ፈጣሪ/ዋቃ/ በጥበቡ ለሰውና ለሌሎች ፍጡራን ከለገሳቸው ስጦታዎች ውስጥ ዋነኛው በመሆኑና የዋቃ ሐይል የሚንፀባረቅበት ስለሆነ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ እና አባ ገዳዎች በተገኙበት መሬዮ መሬዮ መሬዮ….ኦያ መሬዮ በማለት ለምለም ቄጤማ እና አደይ አበባ በመያዝ ውሀውን እየነኩ አምላክ ተመስገን ክበርልን እያሉ ምስጋናቸውን ለዋቃ ያቀርባሉ። የኦሮሞ ሕዝብ በወንዝም ሆነ በዛፍ አያመልክም። በእሬቻ እነሱን ለፈጠረ አምላክ፤ የተፈጥሮን ኡደት ሳያዛባ ያስቀጠለ ዋቃ ይመሰገናል። ዋቃ ይከበራል። ዋቃ /ፈጣሪ/ ይመለካል። እሬቻ የእርቅ ቀን የሰላም ይሁንልን።«
ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ቀዌሳ፤ ገዳ መፅሔት
14462915_1106559772755417_5071182939573984887_n
ኢሬቻ ማለት ማምለክ እና ማመስገን ማለት ነው፡፡ ይሄን ስላደረግህልኝ፣ከክረምት ወደ በጋ (ብራ) ስላሸጋገርከኝ አመሠግናለሁ እየተባለ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ነው፡፡ ኢሬቻ ሠፊ አገልግሎቶች አሉት፡፡ መነሻውም በጣም የራቀ ነው፡፡ ሠው ማምለክ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የመጣ ነው።በተለይ የኦሮሞን ብሔር ጨምሮ በኩሽቲክ የቋንቋ ክፍል ውስጥ የሚጠቃለሉ ብሄሮች ሃይማኖቶች ከመምጣታቸው በፊት ኢሬቻ (እርጥብ ሣር) ይዘው ነው ፈጣሪያቸውን የሚለማመኑት፡፡ ኢሬቻ በእርጥብ ሣር ይወከላል፡፡ለጋብቻ ጥያቄ በራሱ (ኢሬቻ) እርጥብ ሣር አገልግል ውስጥ ተጨምሮ ነውየሚላከው፡፡ እንግዲህ እነዚህን ነገሮች በምናይበት ጊዜ ኢሬቻ ሃይማኖታዊ ዳራ ያለው መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ድሮ ሠዎች መልዕክተኛ ሲልኩ እርጥብ ሣርቆርጠው በመስጠት፣ “አደራህን በፈጣሪ ስም ይህን መልዕክት አድርስልኝ”ብለው ይልኩታል፡፡ እንግዲህ ቃል በቃል ሲገለፅ፤ ኢሬቻ ሣር ወይም የተመረጡ ዛፎች ቅጠል ማለት ነው፡፡

ኢሬቻ በአመት ሁለት ጊዜ ነው የሚደረገው የመጀመሪያው ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ እስከ ጥቅምት መጨረሻ ይካሄዳል፤ ሁለተኛው ደግሞ በበልግ ወራቶች ግንቦትና ሠኔ ውስጥ የሚደረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ግን አሁን እየተረሣና እየተዳከመ ነው ያለው፡፡ ሠዎች መገንዘብ ያለባቸው ኢሬቻ ሃይማኖት አይደለም። ነገር ግን ሃይማኖታዊ ክብረ በአል ነው፡፡ ለምሣሌ ጥምቀት ሃይማኖታዊ በአልነው እንጂ ሃይማኖት አይደለም፡፡ ኢሬቻም እንዲሁ ነው፡፡
እምነቱ ምንድን ነዉ?
የሃይማኖቱ ስም ዋቄፈና ነው፡፡ የእምነቱ ተከታይ ዋቄፈታ ነው የሚባለው፡፡ከዋቄፈና ሃይማኖታዊ በአላት አንዱ ኢሬቻ ነው፤ ሌሎችም ብዙ በአላት አሉ፡፡ሌላው ከዚህ ሃይማኖታዊ በአል ጋር በልማድ አብሮ ተቀላቅሎ የሚከወን ነገር አለ፡፡ ለምሣሌ ቡና ማፍላት፣ ዛፍ ቅቤ መቀባት፣ ስለት ማግባት፣ ሽቶ ውሃ ውስጥ መወርወር የመሣሠሉ አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ልማዶች ናቸው እንጂ የሃይማኖቱ መርሆች የሚያዛቸው አይደሉም፡፡ ሃይማኖቱ በጭራሽ እነዚህን ነገሮች አይፈቅድም። የኦሮሞ ህዝብ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታይ ነው፡፡ በክርስትናውም በእስልምናውም ሃይማኖት ውስጥ ያሉ አሉ፡፡ እነዚህ እንዴት ነው የዚህ በአል ተሣታፊ የሚሆኑት?
የበዓሉ አከባበር ምን ይመስላል?
የኦሮሞ ህዝብ በየቦታው ያለና ሠፊ ስለሆነ የበአሉ ትውፊታዊ አከባበር ወጥነትየለውም፡፡ የተለያዩ ክዋኔዎች ይንፀባረቃሉ፡፡ በአከባበርም ይለያያሉ፡፡ መሠረታዊ ስርአቱ ግን እሬቻ (እርጥብ ሣር) ይይዛሉ፣ በእለቱ የሚዘመሩ መዝሙሮች ይኖራሉ። ነገር ግን እነዚህ መዝሙሮች በቱለማ፣ በሜሜ እንዲሁም በቦረና የተለያዩ ናቸው፡፡ ዋናው ነገር ግን መዝሙሩን እየዘመሩ ወደ “መልካ” (ወንዝ)ይሄዳሉ፡፡ እዚያም ሲደርሡ “በክረምት ወቅት ያሉትን ተግዳሮቶች አሣልፈህ ለዚህ ላደረስከን በጣም እናመሠግናለን” ይላሉ፡፡ በዚያው ቀንም ግለሠቦችኢሬቻውን ይዘው የጐደለባቸውን ለፈጣሪያቸው በፀሎት እየነገሩ መለመን ይችላሉ፡፡ መልካው (ወንዙ) ምልክትነቱ ከዚህ በኋላ በጋ ሆኗል፣ ወንዙም ጎድሏል፤ ዘመድ ከዘመድ ወንዝ እየተሻገረ መጠያየቅ ይችላል ብሎ የሚገልፅነው፡፡ በእለቱ ሽማግሌዎች ሃይማኖታዊ ንግግሮች ያደርጉና በድሮው ባህልእርድ ይኖራል፣ ያ ይበላ ይጠጣና ፈጣሪን በተለያዩ ጨዋታዎች እያመሠገኑ ወደየ መጡበት ይመለሣሉ ማለት ነው፡፡
ሃይማኖቱን የሚመሩት እነማን ናቸው?
ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ይባላሉ፡፡ በገልማ (ቤተ-አምልኮ) ውስጥ በዝማሬ አገልግሎት የሚሠጡት ዋዩ ይባላሉ፡፡ አባ ከኩ የሚባሉት ደግሞ ፀሎት አድራሽናቸው፡፡ ሉባ የሚባለው የተለያዩ የአስተዳደር አመራር ቦታዎችን የሚያከፋፍል ነው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው ጉላነው፡፡ ጉላ ከተጠቀሡት በላይ ሆኖ በማዕከላዊ ደረጃ ሃይማኖቱን የሚመራ ነው፣ ይህ ግለሠብ በሃይማኖቱ ላይ ከ13 አመት በላይ ያገለገለ መሆን ይኖርበታል፡፡ በሌላ በኩል በገዳ ባህላዊ አስተዳደራዊ ስርአት በኩልም የሚመጣ የጐላ ደረጃ አለ፡፡ የመጨረሻው ደረጃአባ ኬና ይባላል፡፡ አባ ኬና የገዳ ስርአቱንም ሆነ ሃይማኖታዊ ስርአቱን ልቅም አድርጐ የሚያውቅ ሊቅ ነው፡፡ በዚህ የኢሬቻ በአልአያንቱዎች ተሣትፎ ያደርጋሉ፡፡
ከእነሡ ጋርስ ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?
እንግዲህ አያንቱ የሚባለው በሃይማኖታዊው ስርአት ውስጥ ያለ ነው፡፡ኢሬቻ ማለት የኦሮሞ ህዝብ የዋቄፈና ስርአት ነው፡፡ ዋቄፈና ማለት ሃይማኖታዊ ማለት ነው። ትልቁ ነገር የዋቄፈና በአል ነው ብንልም በባህል የተሞላ ነው፡፡ እንደ ሌላው ንፁህ ሃይማኖታዊ በአል ነው ማለት አይቻልም፡፡ በአብዛኛው ባህሉ ነው ጐልቶ የሚንፀባረቀው፡፡ “ኢሬቻ” የምትለዋ ቃል የምትወክለው ሣር ወይም አበባ ነው፡፡ ያንን የያዘ ሠው ኢሬቻ የሚሄድ ሠው ነው፡፡ ዋቄፈና ማለት ደግሞ ለአንድ አምላክ ብዙ ሆኖ ምስጋና ማቅረብ ማለት ነው፡፡
የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት ተሠብስቦ በፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት ነው፡ይህ ሃይማኖታዊ ሊያሠኘው ይችል ይሆናል፡፡
እድምተኞቹ “መሬሆ” የሚለውን የምስጋና መዝሙር በአንድነት እያሠሙ ለአምላካቸው ምስጋና ያቀርቡበታል፡፡ ባህላዊ የምንለው ደግሞ ህዝቡ የፈለገውን የባህል ጭፈራ እየጨፈረ ነው የሚመጣው። ወንዱም ሴቱም በልዩ አለባበስ ተውቦ በአሉ ወደ ሚከበርበት ስፍራ ይሄዳል፡፡
እንደ ኢሬቻ ባህልን በጉልህ የሚያሣይ በአል የለም፡፡ ለዚህ ነው ባህሉ ስለሚያመዝን ሃይማኖታዊነቱ ይሸፈናል፡፡ በኦሮሞ ባህሎች በእጅጉ የተሞላ ነው፡፡
የዋቄፈና  ሃይማኖት ተከታዮች የእምነቱን መሠረታዊ መርሆች በጠበቀ መልኩ እየተከበረ አይደለም የሚል ቅሬታ ያነሣሉ?አንዳንድ ፈሩን የለቀቁ ሠዎች የሚያደርጉት ድርጊት አለ፡፡ የኦሮሞ ህዝብም አባ ገዳዎችም የሚቃወሙት ድርጊቶች አሉ፡፡ የኦሮሞ ዋቄፈና በአንድ አምላክ ብቻ ነው የሚያምነው፡፡ እግዚአብሔር ተአምር የሠራበት ቦታብለው ነው እዚያ የሚሄዱት እንጂ ወንዝ ለማምለክ አይደለም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሰይጣን አለ ብሎ አያምንም፡፡ ሰው ሲያብድ በአንድ ጣሳ ውሃ የሚለቅ ሰይጣን እንደት ባህር ውስጥ ይተኛል ብሎ ነው የሚጠይቀው።
ስለዚህ ኦሮሞ በዛፍ እና በወንዝ አያምንም፡፡እዚያ ቦታ ግን መሰብሰቢያና ፈጣሪን የሚያገኝበት ቦታ ነው፡፡ ነገር ግን
አንዳንዶች በስለት ስም ውሃ ውስጥ ሽቶ መወርወራቸው የመሳሰለው ለባህሉም በእምነቱም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው፡፡
የቀለበት ቃልኪዳን ማህበር ከእምነት ጋር ይገናኛው፣ ጭፈራዎቹና ፌሽታዎች ደግሞ ባህል ናቸው ባህል ማለት የማንነት መግለጫ ነው፡፡ ሃይማኖት፣ታሪክ፣ቋንቋ ባህል ውስጥ የሚጠቀለሉ ናቸው ስንል ባህልና ሃይማኖትን ለያይቶ ሃይማኖት መመልከት ትክክል አይደለም፡፡ በእሬቻ ላይ ደግሞ የበለጠ የሚንፀባረቀው ባህላዊነቱ ነው።
የኦሮሞ ትልቁ ፀሎት የሚባለው ምረቃ ነው። ምረቃውን ደግሞ ሙስሊምም ክርስቲያንም ይመርቃል፡፡ ስለዚህ እሬቻ ሁሉንም የሚያሳትፍ ባህል ነው፡፡
እሬቻ በዓል የሚውልበት ቀን በምንድነው የሚታወቀው?
በእርግጥ አሁን የእሬቻ አቆጣጠር ከመስቀል ደመራ ጋር ይገናኛል፡፡ ድሮ ሌሎች ሃይማኖቶች ማይገቡ ቀኑ ከነሃሴ ጀምሮ ይከበር ነበር። ነገር ግን አሁን ከመስቀል ደመራ ማግስት ባለው እሁድ ቀን ነው የሚሆነው፡፡በመስቀል ደመራ ነው ቀኑ የሚታወቀው። ወቅቱ የአበባና የልምላሜ ወቅት ትልቅ ተስፋ የሚታይበት ስለሆነ ለዚህ በቅተናል ተብሎ ነው የሚታሰበው፡፡ Read more here
በቢሾፍቱ ኢሬቻ በዓል የሞቱት ቁጥር ማሻቀቡን ተገለፀ
Image result for ኢሬቻ
Related image

Monday, September 25, 2017

ከEBC - ESAT ማን ይዋሻል?

ውድ ተከታታዩቸ ካሁን በፊት መጣጥፌ መረጃን በማፈን የሚመጣ ችግርን ለማንሳት ሞክሬ ነበር። ቃል በገባሁት መሰረት አሁን ደሞ መንግስት ምን ማድረግ አለበት የሚለውን ጠቃሚ ሐሳብ ለማንሳት እሞክራለሁ።
መረጃ ላንድ አገር እድገት በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ሁሉም ሚያውቀው ነው። በመረጃ ፍሰት የፈረሰ አገር የለም በመረጃ እጦት እንጂ። እርግጥ ነው አምባገነን መንግሥታት ለሥልጣናቸው ሲሉ መረጃን ያፍናል፣ እውነቱን አውጥተው ለህዝብ ለማድረስ ይፈራሉ። የተደበቀ እውነትም ፈልፍሎ የሚያወጣ ሁሉ ለእነሱ ጠላት ነው። ምክንያቱም አላማቸው መረጃን በማፈን ሥልጣንን ማራዘም ነውእና። ትክክለኛው አካሄድ ግን እንደዚህ አይደለም። እውነትም ሆነ ሀሰት መረጃ መረጃ ነው። መረጃው ሐሰት ሆነ እውነት ፈራጅ ተጠቃሚው ነው እንጂ ሌላ ማንም አካል አይደለም። ሀሰት እየከሰመ ይሄዳል እውነት ግን እያደር እየጎለበተች ትሄዳለች። ይህን ማንም የሚያውቀው ሐቅ ነው።
No automatic alt text available.
በሶሻል ሚዲያው እውነትን አፈንፍኖ ለተጠቃሚው የሚያደርስ ብዙ ተከታይ አለው። ውሸትን ሚናገር ግን እያደር ይከስማል። የወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት ግን ለሁሉም ነገር የመረጃው ምንጭ እኔ ብቻ ነኝ እኔን ስሙኝ እያለ ሌላውን ግን ውሽት ነው እያለ ድፍን 25 አመት አብረን ቆየን። በአለም ላይ ስለፖለቲካ እውነትን ደፍሮ የሚናገር የግል ሚዲያ የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች። በወያኔ ኢህአዴግ አመለካከት ለወደፊቱም እዲኖር አይፈለግም።
መሠረታቸውን በውጭ ሐገረ አድርገው ስለኢትዮጵያ መረጃን የሚያቀብሉ እንደ ቨኦኤ፣ ጀርመን ያሉ ትልቅ የሚዲያ ተቋማት እንኳን በወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት ሚደርስባቸው አፈና ሁሉም ሚያውቀው ነው። ወያኔ እንደ እሳት፣ OMN እና ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ አክትብስቶችን አሸባሪ ናቸው ይለናል። ያ ሁሉ የእነሱ ተከታይ ታዲያ አሸባሪ ወዶ ነው? አሸባሪ ሆኑ አልሆኑ፣ እውነትን ተናገሩ ውሸትን ፈራጅ ተጠቃሚው ህዝብ ቢሆንስ? አሸባሪ ወይም ሀሰትን ተናጋሪ ከሆኑ ህዝቡ አንቅሮ እንደሚተፋቸው አሙን ነው። እውነታው ግን እንደዛ አይደለም። እውነቱን እንነጋገር ካልን ከ EBC እና ከእሳት ወይም OMN በሶሻል ሚዲያ ማነው ብዙ ተከታይ ያለው?
መልሱን ለአንባቢያን እንተው እና በጣም ሚገርመው ደሞ የድረ ገጾች አፈና ነው። የወያኔ መንግሥት ስለኢትዮጵያ የሚዘግቡ ኢትዮጵዊያን ድረ ገጾች ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ በጣም ታዋቂ እና ተነባቢ የሁኑ እንደ ዋሽግተን ፖስት፣ 24 ኒውስ፣ እና ሌሎችን በተለያዩ ተቋማት እና በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጥርቅም አድርጎ መዝጋቱ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን በአለም ብዙ ተጠቃሚ ያለው የGoogle ንብረት የሆነው ብዙ ፃሃፊያንሐሳባቸውን ወይም የምርምር ግኝታቸውን ለአንባቢያን የሚያጋሩበት በሎገር blogger.com ከብዙ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች እዳይሰሩ ተደርገዋል።ዩኒቨርሲቲዎች ደሞ ለዚህ አይነቱ ቁጥጥር በጣም ቀላል ናቸው። ሰርቨር ኮምፒውተራቸው ላይ የማይፈለጉ ድረ ገጾች ራውት ወይም ብሎክ ማድረግ ብቻ ነው።
በስራ ምክንያት ብዙ ዩኒቨርሲቲዎችን እንደ ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ አርባምንጭ ባየሁ ግዜ እንደ ብሎገር እና ወርድ ፕረስ አይሰሩም። ይህ ደሞ አካዳሚክ ነፃነትን መጋፋት ነው። በጣም የሚገርመው ዩኒቨርስቲ ያለ ሰው የተማረ ክፉውን እና በጎውን፣ ውሸት እና እውነቱን አመዛዝኖ መለየት የሚችል ያለበት የሙህራን ጥርቅም ነው። እነ እሳት እና OMNስ የወያኔ ተቀናቃኝ ነቸው ብየ ልፈርጅ፣ ታዲያ በምን አስተሳሰብ ነው ስለኢትዮጵያ ሚዘግቡ እነ ዋሽግተን ፖስት፣ ABC ኒውስ፣ ሌሎች እና ብሎገሮች ጥርቅም ብለው በነዚህ ተቋማት ላይ ሚዘጉት? ሕዝብን መናቅ መረጃን ማፈን የትም አያደርስም። ከዚህ ጋር በተያያዘ በጣም የሚገርመው ደም የሃገርን ባህል፣ ሐይማኖት፣ ቅርስን የሚበርዙ አደገኛ የሆኑ እንደ ፖኖግራፌ ፣ ተመሳሳይ የፆታ ጋብቻ እና ሌሎች ድረ ገፆች በወያኔ ምንግስት ምንም ደንታ የላቸውም። መታገድ ሚኖርባቸውስ እነዚህ ነበሩ።
የወያኔ መንግሥት ሰለማይችል ነው እንጂ ማይፍልጋቸውን ድረ ገጾች በእያንዳንዱ ሰው ሞባይል ላይም ሳንሱር ቢያደር ምንኛ ደስ ባለው። ነገር ግን አሁን ዘመኑ ተቀይሯል። የወያኔ መንግሥት በዚህ መልኩ ወደፊት መቀጠል አይችልም። ሁሉም ቴክኖሎጂው በኪሱ አለው። ከላይ ለመጥቀስ እደሞከርኩት ወያኔ አቅም ኑሮት ወይም አቅም ያለውን በብዙ ገንዘብ ቀጥሮ በእያንዳንዱ ኪስ ካለው ቴክኖሎጂ ላይ ድረ ገፆችን ራውት ወይም ብሎክ ካላደረገ (ሳስበው ሚሞክሩት ይመስለኛል) መረጃን እንደወትሮው ማፈን አይችልም። ይልቁንስ የወያኔ ኢሕአዴግ መንግሥት በመረጃ ፍሰት የሚመጣውን ፍርሀት እርግፈ አርጎ ትቶ የኢትዮጵያን ህዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን ማከበር ይገባዋል። እውነት መጋፈጥ መልመድ ይኖርበታል። "እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር" አደል የሚለው ያገሬ ሰው።
ለዚህም ደሞ የግል ሜዳውን ሆነ ሶሻል ሚዲያዎችን ያለምንም ሳንሱር መፈቀድ ይኖርበታል። ያለምንም ምክንያት በኢትዮጵያ ቴሌ ሰርቪስ ፕሮባደር (IP) ሆነ በተለያዩ ተቋማት ሰርበር ኮፒተራቸው የሚደረግ የድረ ገፅ አፈና መቆም አለበት። ማንም ሚዲያ ህጉን እና ደቡን ተከትየ ስለሀገሬ አወራለሁ፣ እዘግባለሁ ብሎ ቢመጣ መፈቀድ አለበት። ምክንያቱም ባሌቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ነውእና። የኢትዮጵያን ህዝብ ለቀቅ አርጉት። ሚያዳምጠውን እሱ ያውቃል። እኔን ብቻ አዳምጡኝ ሌላው አሸባሪ እና ሀገር አተራማሽ ነው ሚለው መብቃት አለበት። ማን እውሸት ተናጋሪ፣ ማን አሸባሪ እና ማን ሐገረ አተራማሽ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ያላቹህን የቴክኖሎጂ እውቀት እና ይህን ለማፈን የምታወጡትን ገንዘብ ለጡሩ ነገር አውሉት። ዛሬ እነ ኮሪያን እያየን ነው። የዜጎቿን የቴክኖሎጂ እውቀት ተጠቅመው ሃገራቸውን ማስከበር የቻሉ ሐገሮች ናቸው። ዛሬ world cyber war ቢነሳ ኮሪያ ውስጥ ተቀምጠው የአሜሪካን ሰርበር ድባቅ የሚመቱ ልጆቿ ተፈጥረዋል። ከኛ ሐገረ ግን ተቃራኒው ነው ያለው። መንግስት አለኝ ያለውን አቅም አሟጦ ሆነ በከፍተኛ ገንዘብ ወጭ ከነቻይና በቀጠራቸው ሰወች የራሱን ዘጋ መብት ያፍንበታል።
ውድ ተከታታዩቸ በሚቀጥለው ወያኔ ኢሕአዴግ እንዴት አድርጎ ደረ ገፆዎችን ሳንሱር እንደሚያደርግ፣ ውጭ ሚተላለፉ እንደ እኦሳት ያሉ ሜዳዎች እዴት ጃም እደሚያደርግ፣ ምን ሶፍትዌሮች እደሚጠቀም፣ ማን እና ምን አይነት ባለሙያ እደሚጠቀም እና ምን ያህል ወጪ እንደሚያወጣ በሰፊው ይዤ እደምቀርብ ቃል እገባለሁለት። እስከዛው ግነ ቸር እንሰብት።
Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time