Wednesday, October 4, 2017

ስለ ኢሬቻና ኦዳ አመጣጥ ከመሰረቱ

ስለ ኢሬቻና ኦዳ አመጣጥ ከመሰረቱ 🌻
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን እንደ ከተበው 
« ... አቴቴ ፈጣሪ ሰላም እንዲያወርድ ተማፅና የመታሰቢያ ዋርካ ተከለች። አምላክም ዝናብ አዝንቦ ዋርካውን አሳደገው፣ ልጆቿም የሚዳኙበት አዲስ ስርዓት ነገራት። ያንንም የሰላም ትንሣኤ ሕይወት ገዳ ስርዓት አለው። ጥንታዊ ና መሰረታዊ እምነቱ ደግሞ ዋቄፈና ተባለ። ኢሬቻ ይህ ስርዓት የሚከበርበት በዓል ነው።
የእሬቻ አከባበርና ለኦሮሞ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት ...
በኢትዮጵያ በኩሽ ምድር ፥ እሬቻ በኦሮሞ ዘንድ በገዳ ስርዓት ህዝቡ ተሰብስቦ ለምለም ቄጠማ፤ አረንጓዴ ቅጠል፤ አበባ ይዞ ፤ ፈጣሪን በወንዝ/በሀይቅ ዳርቻ ወይም በተራራ ላይ የማመስገን፤ የማክበር ፤የማምለክ በአል ነው። ገዳ ስርዓት በውሰጡ የፖለቲካ፣ የሐይማኖት፣ የባህል እና የምጣኔ ሀብት ሰንሰለቶችን የያዘ ነው። በክረመት ወቅት ወነዞቸ ስለሚሞሉ ሰዎች አይገናኙም፤ ማህበራዊ ግነኙነቶችም ይቀነሳሉ፤ መስከረም ሲጠባ የክረምት ወቀት አልቆ፣ የሞሉ ወንዞች ቀንሰው ፣ የተዘራው ያብባል፣ ጨለማው በብርን ይተካል፣ ምድር በልምላሜ ታጌጣለች። የዚህ ሁሉ መልካም ነገር ባለቤት ደግሞ ዋቃ/ ፈጣሪ/ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ለዋቃ ከፍተኛ የሆነውን ምስጋና ወደ ወነዞችና ሐይቆች በመውረድ ያቀርባል። ወንዞች ወይም ሐይቆች የተመረጡበት ምክንያት ውሃ ፈጣሪ/ዋቃ/ በጥበቡ ለሰውና ለሌሎች ፍጡራን ከለገሳቸው ስጦታዎች ውስጥ ዋነኛው በመሆኑና የዋቃ ሐይል የሚንፀባረቅበት ስለሆነ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ እና አባ ገዳዎች በተገኙበት መሬዮ መሬዮ መሬዮ….ኦያ መሬዮ በማለት ለምለም ቄጤማ እና አደይ አበባ በመያዝ ውሀውን እየነኩ አምላክ ተመስገን ክበርልን እያሉ ምስጋናቸውን ለዋቃ ያቀርባሉ። የኦሮሞ ሕዝብ በወንዝም ሆነ በዛፍ አያመልክም። በእሬቻ እነሱን ለፈጠረ አምላክ፤ የተፈጥሮን ኡደት ሳያዛባ ያስቀጠለ ዋቃ ይመሰገናል። ዋቃ ይከበራል። ዋቃ /ፈጣሪ/ ይመለካል። እሬቻ የእርቅ ቀን የሰላም ይሁንልን።«
ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ቀዌሳ፤ ገዳ መፅሔት
14462915_1106559772755417_5071182939573984887_n
ኢሬቻ ማለት ማምለክ እና ማመስገን ማለት ነው፡፡ ይሄን ስላደረግህልኝ፣ከክረምት ወደ በጋ (ብራ) ስላሸጋገርከኝ አመሠግናለሁ እየተባለ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ነው፡፡ ኢሬቻ ሠፊ አገልግሎቶች አሉት፡፡ መነሻውም በጣም የራቀ ነው፡፡ ሠው ማምለክ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የመጣ ነው።በተለይ የኦሮሞን ብሔር ጨምሮ በኩሽቲክ የቋንቋ ክፍል ውስጥ የሚጠቃለሉ ብሄሮች ሃይማኖቶች ከመምጣታቸው በፊት ኢሬቻ (እርጥብ ሣር) ይዘው ነው ፈጣሪያቸውን የሚለማመኑት፡፡ ኢሬቻ በእርጥብ ሣር ይወከላል፡፡ለጋብቻ ጥያቄ በራሱ (ኢሬቻ) እርጥብ ሣር አገልግል ውስጥ ተጨምሮ ነውየሚላከው፡፡ እንግዲህ እነዚህን ነገሮች በምናይበት ጊዜ ኢሬቻ ሃይማኖታዊ ዳራ ያለው መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ድሮ ሠዎች መልዕክተኛ ሲልኩ እርጥብ ሣርቆርጠው በመስጠት፣ “አደራህን በፈጣሪ ስም ይህን መልዕክት አድርስልኝ”ብለው ይልኩታል፡፡ እንግዲህ ቃል በቃል ሲገለፅ፤ ኢሬቻ ሣር ወይም የተመረጡ ዛፎች ቅጠል ማለት ነው፡፡

ኢሬቻ በአመት ሁለት ጊዜ ነው የሚደረገው የመጀመሪያው ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ እስከ ጥቅምት መጨረሻ ይካሄዳል፤ ሁለተኛው ደግሞ በበልግ ወራቶች ግንቦትና ሠኔ ውስጥ የሚደረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ግን አሁን እየተረሣና እየተዳከመ ነው ያለው፡፡ ሠዎች መገንዘብ ያለባቸው ኢሬቻ ሃይማኖት አይደለም። ነገር ግን ሃይማኖታዊ ክብረ በአል ነው፡፡ ለምሣሌ ጥምቀት ሃይማኖታዊ በአልነው እንጂ ሃይማኖት አይደለም፡፡ ኢሬቻም እንዲሁ ነው፡፡
እምነቱ ምንድን ነዉ?
የሃይማኖቱ ስም ዋቄፈና ነው፡፡ የእምነቱ ተከታይ ዋቄፈታ ነው የሚባለው፡፡ከዋቄፈና ሃይማኖታዊ በአላት አንዱ ኢሬቻ ነው፤ ሌሎችም ብዙ በአላት አሉ፡፡ሌላው ከዚህ ሃይማኖታዊ በአል ጋር በልማድ አብሮ ተቀላቅሎ የሚከወን ነገር አለ፡፡ ለምሣሌ ቡና ማፍላት፣ ዛፍ ቅቤ መቀባት፣ ስለት ማግባት፣ ሽቶ ውሃ ውስጥ መወርወር የመሣሠሉ አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ልማዶች ናቸው እንጂ የሃይማኖቱ መርሆች የሚያዛቸው አይደሉም፡፡ ሃይማኖቱ በጭራሽ እነዚህን ነገሮች አይፈቅድም። የኦሮሞ ህዝብ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታይ ነው፡፡ በክርስትናውም በእስልምናውም ሃይማኖት ውስጥ ያሉ አሉ፡፡ እነዚህ እንዴት ነው የዚህ በአል ተሣታፊ የሚሆኑት?
የበዓሉ አከባበር ምን ይመስላል?
የኦሮሞ ህዝብ በየቦታው ያለና ሠፊ ስለሆነ የበአሉ ትውፊታዊ አከባበር ወጥነትየለውም፡፡ የተለያዩ ክዋኔዎች ይንፀባረቃሉ፡፡ በአከባበርም ይለያያሉ፡፡ መሠረታዊ ስርአቱ ግን እሬቻ (እርጥብ ሣር) ይይዛሉ፣ በእለቱ የሚዘመሩ መዝሙሮች ይኖራሉ። ነገር ግን እነዚህ መዝሙሮች በቱለማ፣ በሜሜ እንዲሁም በቦረና የተለያዩ ናቸው፡፡ ዋናው ነገር ግን መዝሙሩን እየዘመሩ ወደ “መልካ” (ወንዝ)ይሄዳሉ፡፡ እዚያም ሲደርሡ “በክረምት ወቅት ያሉትን ተግዳሮቶች አሣልፈህ ለዚህ ላደረስከን በጣም እናመሠግናለን” ይላሉ፡፡ በዚያው ቀንም ግለሠቦችኢሬቻውን ይዘው የጐደለባቸውን ለፈጣሪያቸው በፀሎት እየነገሩ መለመን ይችላሉ፡፡ መልካው (ወንዙ) ምልክትነቱ ከዚህ በኋላ በጋ ሆኗል፣ ወንዙም ጎድሏል፤ ዘመድ ከዘመድ ወንዝ እየተሻገረ መጠያየቅ ይችላል ብሎ የሚገልፅነው፡፡ በእለቱ ሽማግሌዎች ሃይማኖታዊ ንግግሮች ያደርጉና በድሮው ባህልእርድ ይኖራል፣ ያ ይበላ ይጠጣና ፈጣሪን በተለያዩ ጨዋታዎች እያመሠገኑ ወደየ መጡበት ይመለሣሉ ማለት ነው፡፡
ሃይማኖቱን የሚመሩት እነማን ናቸው?
ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ይባላሉ፡፡ በገልማ (ቤተ-አምልኮ) ውስጥ በዝማሬ አገልግሎት የሚሠጡት ዋዩ ይባላሉ፡፡ አባ ከኩ የሚባሉት ደግሞ ፀሎት አድራሽናቸው፡፡ ሉባ የሚባለው የተለያዩ የአስተዳደር አመራር ቦታዎችን የሚያከፋፍል ነው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው ጉላነው፡፡ ጉላ ከተጠቀሡት በላይ ሆኖ በማዕከላዊ ደረጃ ሃይማኖቱን የሚመራ ነው፣ ይህ ግለሠብ በሃይማኖቱ ላይ ከ13 አመት በላይ ያገለገለ መሆን ይኖርበታል፡፡ በሌላ በኩል በገዳ ባህላዊ አስተዳደራዊ ስርአት በኩልም የሚመጣ የጐላ ደረጃ አለ፡፡ የመጨረሻው ደረጃአባ ኬና ይባላል፡፡ አባ ኬና የገዳ ስርአቱንም ሆነ ሃይማኖታዊ ስርአቱን ልቅም አድርጐ የሚያውቅ ሊቅ ነው፡፡ በዚህ የኢሬቻ በአልአያንቱዎች ተሣትፎ ያደርጋሉ፡፡
ከእነሡ ጋርስ ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?
እንግዲህ አያንቱ የሚባለው በሃይማኖታዊው ስርአት ውስጥ ያለ ነው፡፡ኢሬቻ ማለት የኦሮሞ ህዝብ የዋቄፈና ስርአት ነው፡፡ ዋቄፈና ማለት ሃይማኖታዊ ማለት ነው። ትልቁ ነገር የዋቄፈና በአል ነው ብንልም በባህል የተሞላ ነው፡፡ እንደ ሌላው ንፁህ ሃይማኖታዊ በአል ነው ማለት አይቻልም፡፡ በአብዛኛው ባህሉ ነው ጐልቶ የሚንፀባረቀው፡፡ “ኢሬቻ” የምትለዋ ቃል የምትወክለው ሣር ወይም አበባ ነው፡፡ ያንን የያዘ ሠው ኢሬቻ የሚሄድ ሠው ነው፡፡ ዋቄፈና ማለት ደግሞ ለአንድ አምላክ ብዙ ሆኖ ምስጋና ማቅረብ ማለት ነው፡፡
የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት ተሠብስቦ በፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት ነው፡ይህ ሃይማኖታዊ ሊያሠኘው ይችል ይሆናል፡፡
እድምተኞቹ “መሬሆ” የሚለውን የምስጋና መዝሙር በአንድነት እያሠሙ ለአምላካቸው ምስጋና ያቀርቡበታል፡፡ ባህላዊ የምንለው ደግሞ ህዝቡ የፈለገውን የባህል ጭፈራ እየጨፈረ ነው የሚመጣው። ወንዱም ሴቱም በልዩ አለባበስ ተውቦ በአሉ ወደ ሚከበርበት ስፍራ ይሄዳል፡፡
እንደ ኢሬቻ ባህልን በጉልህ የሚያሣይ በአል የለም፡፡ ለዚህ ነው ባህሉ ስለሚያመዝን ሃይማኖታዊነቱ ይሸፈናል፡፡ በኦሮሞ ባህሎች በእጅጉ የተሞላ ነው፡፡
የዋቄፈና  ሃይማኖት ተከታዮች የእምነቱን መሠረታዊ መርሆች በጠበቀ መልኩ እየተከበረ አይደለም የሚል ቅሬታ ያነሣሉ?አንዳንድ ፈሩን የለቀቁ ሠዎች የሚያደርጉት ድርጊት አለ፡፡ የኦሮሞ ህዝብም አባ ገዳዎችም የሚቃወሙት ድርጊቶች አሉ፡፡ የኦሮሞ ዋቄፈና በአንድ አምላክ ብቻ ነው የሚያምነው፡፡ እግዚአብሔር ተአምር የሠራበት ቦታብለው ነው እዚያ የሚሄዱት እንጂ ወንዝ ለማምለክ አይደለም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሰይጣን አለ ብሎ አያምንም፡፡ ሰው ሲያብድ በአንድ ጣሳ ውሃ የሚለቅ ሰይጣን እንደት ባህር ውስጥ ይተኛል ብሎ ነው የሚጠይቀው።
ስለዚህ ኦሮሞ በዛፍ እና በወንዝ አያምንም፡፡እዚያ ቦታ ግን መሰብሰቢያና ፈጣሪን የሚያገኝበት ቦታ ነው፡፡ ነገር ግን
አንዳንዶች በስለት ስም ውሃ ውስጥ ሽቶ መወርወራቸው የመሳሰለው ለባህሉም በእምነቱም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው፡፡
የቀለበት ቃልኪዳን ማህበር ከእምነት ጋር ይገናኛው፣ ጭፈራዎቹና ፌሽታዎች ደግሞ ባህል ናቸው ባህል ማለት የማንነት መግለጫ ነው፡፡ ሃይማኖት፣ታሪክ፣ቋንቋ ባህል ውስጥ የሚጠቀለሉ ናቸው ስንል ባህልና ሃይማኖትን ለያይቶ ሃይማኖት መመልከት ትክክል አይደለም፡፡ በእሬቻ ላይ ደግሞ የበለጠ የሚንፀባረቀው ባህላዊነቱ ነው።
የኦሮሞ ትልቁ ፀሎት የሚባለው ምረቃ ነው። ምረቃውን ደግሞ ሙስሊምም ክርስቲያንም ይመርቃል፡፡ ስለዚህ እሬቻ ሁሉንም የሚያሳትፍ ባህል ነው፡፡
እሬቻ በዓል የሚውልበት ቀን በምንድነው የሚታወቀው?
በእርግጥ አሁን የእሬቻ አቆጣጠር ከመስቀል ደመራ ጋር ይገናኛል፡፡ ድሮ ሌሎች ሃይማኖቶች ማይገቡ ቀኑ ከነሃሴ ጀምሮ ይከበር ነበር። ነገር ግን አሁን ከመስቀል ደመራ ማግስት ባለው እሁድ ቀን ነው የሚሆነው፡፡በመስቀል ደመራ ነው ቀኑ የሚታወቀው። ወቅቱ የአበባና የልምላሜ ወቅት ትልቅ ተስፋ የሚታይበት ስለሆነ ለዚህ በቅተናል ተብሎ ነው የሚታሰበው፡፡ Read more here
በቢሾፍቱ ኢሬቻ በዓል የሞቱት ቁጥር ማሻቀቡን ተገለፀ
Image result for ኢሬቻ
Related image

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time