Monday, May 21, 2018

በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶምን ለማስፋፋት ፕሮቴስታንት አዋጇን በይፋ ጀምራለች

በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶምን ለማስፋፋት ፕሮቴስታንት አዋጇን በይፋ ጀምራለች


Michal Fattal
Image result

"ሰው መንፈስ ነው" የሚለው የፕሮቴስታንቱ ትምህርት የሰዶማውያን አስተምህሮ ነው። በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሥር እየሰደደ የመጣውና ብዙ ክርስቲያኖችን እያወዛገበ ያለው የእምነት ቃል እንቅስቃሴ/ Word faith movement / አስተምህሮ በአሁን ሰዓት በፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቶት ታላላቅ በሚባሉ ፓስተሮች ሳይቀር ይህ እንግዳ የሆነ አጋንንታዊ ትምህርት በየመድረኮቻቸው በስፋት እየተሰበከ ነው።የእምነት ቃል እንቅስቃሴ በርካታ ክህደትና ኑፋቄ ያለው አስተምህሮ ሲሆን በዋነኛነት "ሰው መንፈስ ነው ነፍስ አለው በሥጋ ውስጥ ያድራል"የሚለው ትምህርት ግን ግብረ ሰዶማውያን የፈጠሩትና ሰዶማዊነትን በሃይማኖት ሽፋን ለማስፋፋት ሆን ተብሎ የታቀደ አጋንንታዊ አስተምህሮ ነው። ሰው መንፈስ ነው በሥጋ ውስጥ ያድራል የሚሉት የፕሮቴስታንት ሰባኪዎች በሥጋችን የምንሰራው ማናቸውም ዓይነት ኃጢአት እና ነውር ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ኅብረት አያቋርጠውም፤ እኛም የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችን ላይ የሚያመጣብን አንዳችም ዓይነት ተጽኅኖ የለውም የሚልና ትውልዱን መረን የለሽ የሚያደርግ በድፍረት ኃጢአት ክርስቲያኖች እንዲመላለሱ የሚያበረታታ በማር የተለወሰ መርዝ ነው። ሰው መንፈስ ነው በሥጋ ውስጥ ያድራል ማለት ልክ እንደ ዳዊትና ማኅደር ወይም እንደ መጽሐፍና ቦርሳ ማለት ነው መጽሐፍ ቦርሳ ውስጥ ይቀመጣል ቦርሳው ቢቆሽሽና ቢጨቀይም መጽሐፋ ላይ የሚያመጣው ተጽኅኖ የለም የሚለው የፕሮቴስታንቱ ፍልስፍና በሥጋችን ምንም ነገር ብንፈጽም ሰው የሚባለው ዋነኛው መንፈሳችንን አያረክሰውም አያቆሽሸውም ባዮች ናቸው። ወገኖቼ መጽሐፍ ቅዱስ "ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች ፍጻሜዋ ግን ሞት ነው" ብሎ እንደ ሚነግረን ይህ ትክክለኛ የሚመስለውና የሰዎችን ልቡና በቀላሉ ለማሳመን በሰይጣናዊ ጥበብ የተወጠነው ትምህርት ክርስቲያኖችን ሙሉ ለሙሉ ከእግዚአብሔር የሚለይና ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያራቁት የድፍረት ኃጢአትን የሚያለማምድ ክህደት ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን ሥጋችንም መንፈሳችንም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ እንዲሆን ነው እንጂ በመንፈስ ስለ መቀደስ ብቻ አያስተምረንም ። " እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:1)::

ሰዶማውያን በአሁን ሰዓት በየሀገሩ እየተስፋፋ የመጡትና በፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ውስጥ ሕጋዊ ጋብቻ እስከ መፈጸም የደረሱት በዚህ አጋንንታዊ አስተምህሮ ላይ በመመስረት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ግብረ ሰዶምን ለማስፋፋት "ሰው መንፈስ ነው በሥጋ ውስጥ ያድራል"የሚለውን አስተምህሮ እያወጁና እየሰበኩ ያሉ ፓስተሮች የዲያብሎስ መንገድ ጠራጊዎች ናቸውና በጣም ልንጠነቀቃቸው ይገባል። ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል " የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።" (1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:23) የተከበራችሁ ወገኖቼ በተለያዩ ሀገራት ፕሮቴስታንት ግብረ ሰዶምን በአዋጅ ማጽደቋን በይፋ እያየን ነው ቀጥሎ ያለው ጽሑፍ የእነርሱ የአቋም ነው።

መግለጫ

Evangelical Lutheran Church in America

The Evangelical Lutheran Church in America defines marriage as “a lifelong covenant of faithfulness between a man and a woman.” However, at its 2009 church-wide assembly, it voted to allow congregations that choose to do so to recognize and bless same-sex unions. At the same assembly, the church also adopted a social statement on human sexuality that supports a wide variety of families, including those headed by same-gender couples.

ሰዶማውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸው ዕቅድ ምንድን ነው ? 

በ1908 አከባቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያንን የወንጌል ስርጨት ለመደገፍ በሚሉ የዴንሽ/የዴንማርክ/ ሚሽነሪዎች ምንፍቅናን ወደ ሀገራችን ያስገቡት የዴንማርክ ፕሮቴስታንቶች ዛሬ ከ100 ዓመት የእምነት ኢንቨስትመንት ልፋት በኋላ ዛሬም እንዳሰቡት ሳይሆን እንደተገኘ የሚያምኑት ሀቅ ነው ፤ከኢትዮጽያ ሚሽነሪዎች በኋላ ወደ ኬንያ የገቡት አካላት መሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የኬንያውያንን ዕሴት ፣እምነት እና ባህል ከኢንግሊዛውያን ጋር በመተባበር በርዘው ህዝቡን ሞራል እና ስብዕና አጥ አድርገውታል። እንግዲህ ዛሬ ላይ ላለው የኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት ወይም ወንጌላውያን አማኞች ህብረት ትልቅ የአስተምህሮ እና የአርዓያ ምልክት የሚደረጉት የዴንማርክ ሚሽነሪዎች ናቸው ። ዛሬም ይህቺ ሀገር ማለትም ዴንማርክ ለህብረቱ እና ለአንዳንድ የፕሮቴስታንት ዓብያተክርስትያናት የትምህርት የሎጀስቲክ እና የፋይናንስ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ናት ።


የዴንማርክ የዕምነት እና የግብረ ሰዶማዊነት ፕሮፋይል

ዴንማርክ ምንም እንኳን ላይ ላዩን ቅዱስ የምትመስል ሀገር ብትሆንም ውስጧ ግን እጅግ በጣም በክፋት እና በኃጢአት የደረጀ ነው ። ከሀገሪቷ 5.7 ሚልዬን ህዝብ መካከል በዋናነት ፕሮቴስታንት 75.2% ማለትም 4,275,000፣ በትንሳኤ ሙታን የማያምኑ agnostic 9.1% ማለትም 518,700፣ በእግዚአብሄር የማያምኑ Atheist 10.6 % ማለትም 604,000 ናቸው። ዴንማርክ የፕሮቴስታንት የበላይነት ስላለ የዴንማርክ ሕገ መንግስት እና የሀገሪቱ መንግስት የፕሮቴስታንት ተልዕኮን፣ ወንጌልን እና ስርዓትን የመደገፍ ብሄራዊ ግዴታ አለበት ። በእዚህ መሰረት ዴንማርካውያን እና የዴንማርክ መንግስት በሥሩ በአፍሪካ ብቻ 259 የዓብያተክርስቲያናትን ህብረት እና ቤተክርስትያን ይደግፋል፣ ስኮላር ሺፕ ይሰጣል፣ ከእዛም ከፍ ሲል የመኖርያ ፍቃድ ይሸልማል

ዴንማርክ እና ግብረሶዳማውያን

ዴንማርክ ከዓለም ሀገራት መካከል ግብረሶዶማዊነትን በማስፋፋት እና እውቅና በመስጠት እጅግ በጣም ቀዳሚዋ ናት ። ይህም የሚያሳዩው ከ1925 ዓ.ም ጀምሮ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ህጋዊ አድርጋለች፣ 1981 ጀምሮ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ፈቅዳለች፣ 2005 ጀምሮ ግብረሰዶማውያን በጉድፈቻ ልጅ የማሳደግ መብት ተሰጥቷቸዋል፣ በ2006 ዓ.ም ግብረሰዶማውያን ፆታቸውን በሰርጀሪ የመቀየር መብት ተሰጥቷቸዋል፣ ከእዚህ በተቃራኒው ግብረሶዶማውያንን ማግለል፣ ልክ እንደእኛው ሀገር ሰዶማውያን በሚሰደቡበት ቃል መስደብ፣ ልዩ በሆነ እንቅስቃሴ እና አትኩሮት መመልከት፣ አገልግሎትን ( ለምሳሌ የአልጋ የመጠጥ የምግብ ፣ወዘተ) መከልከል ዘብጥያ የሚያስወርድ ወንጀል ነው።

ዴንማርክ በኢትዮጵያ

እንግዲህ ዴንማርክ እና ዴንማርካውያን ከኢትዮጵያውን ጋር የተዋወቁት በክርስትናዊ ምንፍቅና ነው ።ከእዛ ጊዜ ጀምሮ በመንፈሳዊ ጠላትነታቸው አንዱ ስኮናውን ሊመታ ሌላኛው አፈር ሊልልስ ተማምለው ርስት ላለማስነጠቅ ውጊያ ላይ ከሆኑ ሰነባብተዋል ። በፕሮቴስታንት ቤተእምነት በኩል የሸረበችው ህዝቡን ከሞራል እና ከግብረግብነት ሜዳ ለማውጣት የወጠነችው ውጥን ፍሬ እንደማያፈራ የገመተችው ዴንማርክ ዛሬ በተቀደሰችው ሀገራችን መዲና በሆነችው አዲስ አበበ ላይ የግብረሰዶማውያንን ባንዲሪ ከሀገሯ ሰንደቃላማ ከፍ አድርጋ በማውለብለብ በኤንባሲዋ በኩል ፍላጓቷን ገልፃለች ።

ኢትዮጵያውያን ሆይ ግብረሰዶማዊነት አጸያፊ ነውርና ወንጀል በሆነበት ሀገራችን ይህቺ ፕሮቴስታንታዊ መንግስት የሆነችው ዴንማርክ በሀገሪቷ ላይ የሰማይ መስኮት ልታስከፍት እና የዲን እሳት ልታዘንብ ዛሬ ግብረሰዶማዊነትን በምድራችን ላይ አውጃለች እያልኩሁ ነው ። መፃፍ ቅዱስ በቃሉ"" ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጻፍሁላችሁ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5 : 9"" እንዳለው በእምነት እና በእውነት ክርስቶስን የምትሹ ፕሮቴስታንታውያን እጃችሁን እና ወንጌላችሁን ከእነዚህ ወገኖች አርቁ ።ከሴሰኞች እና ከፀረ-ክርስቲያናዊ ቡድን ጋር ብትተባበሩ ግን ከክፋታችሁ በላይ እየከፋችሁ እንዳትሄዱ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ቃሉ ""ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3 : 13"" ይላል።

እንግዲህ ወዳጄ ሁላችንም ሀገራችንን እና እምነታችንን የመጠበቅ ግዴታ አለብን ።ይህም በፀሎት፣ ነቅቶ በመጠበቅ እና ሀሰተኛን በመለየት እንዲሁም ከሰው አስተሳሰብ ከሆነ ፍልስፍናዎች ወጥተን የክርስቶስ የፍቅሩን ትዕዛዛት በመጠበቅ ሀገራችንን በቅድስና ልናቆም ይገባል ። ቃሉም "" እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።" ይላል።የዮሐንስ ወንጌል 15 : 10

የተከበራችሁ ፕሮቴስታንት ወገኖቼ አብዛኛው ፓስተሮች ሃይማኖተኛ አትሁኑ የእምነት ሰዎች ብቻ ሁኑ ሃይማኖተኛነት የተቋም አጥር ነው የሚሉት ትውልዱን ከ ውጭ በመጣ እርኩሰት ውስጥ ለማስገባት ነው።ፓስተሮቹ ሃይማኖተኛነት አይድንም የሚለውን ስብከት ኮፒ አድርገው የሚሰብኩት ከነጮች ነው።ስለዚህ እስከዛሬ ድረስ የተታለላችሁት ይበቃል ወደ እናት ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ሃይማኖት ተመልሳችሁ በቅድስና ከእግዚአብሔር ጋር ቀሪ ዘመናችሁ ኑሩ።የመዳን ቀን ዛሬ ነው ልባችሁን መልሱ በፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ሰዶማዊነት፣ጥንቆላ፣ዝሙት እጅግ እየተስፋፋ መጥቷል ወደ ፊት ትውልዱን እግዚአብሔር የለም የሚል ክህደት ውስጥ የሚከቱት እነዚሁ የፕሮቴስታንት ነውረኛ አገልጋዮች ስለሆኑ እግዚአብሔር ይህችን ዕለት ለነስሐ ሰጥቷችኋልና በፍጥነት ተመለሱ።አውሮፓውያንን እምነት የለሽ ያደረጋቸው ከፕሮቴስታንት ቤተ እምነት የተነሳው የሐሰተኛ ነቢያት ውሸት፣የአጭበርባሪ ፓስተሮች ሌብነት እና በቤተ እምነቱ ውስጥ በየጊዜው የሚነሳው እንግዳ ትምህርት ነው። ወገኔ ሆይ ንቃ!!!

እባካችሁ ይህንን ጽሑፍ ሼር በማድረግ ትውልዱን ከእሳት ነጥቀን እናድን

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time