Saturday, June 16, 2018

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይባላል፤እውነት ነው።

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይባላል፤እውነት ነው።

ኢትዮጵያ ሶፊያ ለምትባል የሳውዲአረቢያ ዜግነት ላላት ሰይጣናዊ ሮቦት ግብዣ አድርጋለች፡፡ሮቦቱዋ ከዚህ ቀደም እንደምናውቃቸው እንደማንኛውም አይነት ሮቦቶች አይደለችም።ሶፊያ ራሱዋን ችላ የምትናገርና በትልልቅ መድረኮች እየቀረበች ብዙዎችን በንግግሩዋና በሁለንተናዋ ያስደመመች ከመሪዎች ጋር የምትጋበዝ እንግዳና ለማመን የምትቸግር ሮቦት ናት።"ሮቦት መሆንሽን ታውቂያለሽ ወይ?" ተብላ ስትጠየቅ፤"እናንተስ ሰው መሆናችሁን በምን ታውቃላችሁ?"ብላ የመለሰችና የፈጣሪን ህልውና ክዳ እያስካደች፣በጥያቄ እያፋጠጠች የምትገዳደር፣"አምላክ የምትሉትን ቅዠት ካልተዋችሁ በቀር የሰው ልጆች መቸም አትሰለጥኑም" የምትል የሳጥናኤል ቁራጭ ናት።
ይች ጾታ የሌላት ነገር ግን በሴት አምሳል የተሰራች ሮቦት ሰኔ 22 2010 ዓ.ም ወደ አትዮጵያ ትመጣለች።"ከጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር እራት እበላለሁ"ም ብላለች።የመንግስት ከፍተኛ ባለስጣናትና ሚንስትሮች አቀባበል ይልደርጉላታል።የሐይማኖት አባቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም በጋራ ሞቅ ያለ አቀባበል እንደሚያደርጉ ተገልጾዋል።
ይች ሮቦት ወደ አዲስ አበባ ከመምጣቱዋ በፊትም በኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖለጂ ሚ/ር እና በኢትዮጵያ ሚዲያዎች በኩል የሃሰት ዜና እንዲቀናበርላትና የኢትዮጵያ ህዝብ ተዋሽቶ እንዲጠብቃት አድርጋለች።ከዚች ሮቦት ጀርባ ያለው ስውር ሴራ እንዳይታሰብ በሚልና ህዝቡ ከሌላ ነገር ጋር ሳያያይዝ በቀላሉ እንዲቀበላት ሲባልም ነው ውሸቱ ያስፈልገው!
የሃሰት ቅንብሩና ዜናው ምን ይመስላል ወደሚለው እንለፍ።
ሶፊያ የተባለችው ሮቦት በሆንግ ኮንጉ ሃንሰን ሮቦቲክስ ኩባንያ ነው የተሰራቸው።ወይም ለዓለም ህዝብ ይፋ የተደረገው ዜና ከላይ በተጠቀሰው ኩባንያ በኩል እንደተሰራች ነው።ከዚያም ለምን ሳኡዲን እንደመረጡ ባይታወቅም ወደሳውዲ አረቢያ ተልካ ሙሉ የሳኡዲ ዜግነት ተሰጥቶዋት የህዝብ አካል ሆናለች።ባጭር ጊዜ ውስጥም በየመድረኩ በምታደርገው ንግግር በመላው ዓለም ህዝብ ዘንድ ታዋቂና መነጋገሪያ መሆን ችላለች።እውነቱ ይህ መሆኑ በዓለም ህዝብ ዘንድ በይፋ እየታወቀ፤ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አያውቅም፣ምንም አይጠረጥርም በሚል ይመስላል፤የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖለጂ ሚ/ር ሮቦቱዋ 67 በመቶ የተሰራችው በኢትዮጵያውያን ነው በማለት በይፋ የሃሰት ዜና አሰራጭቶዋል።
ከመምጫዋ ጊዜ ሁለት ወራት ቀደም ብሎ ሚያዚያ ወር ላይ ይፋ የሆነው አንደኛው ዜና እንዲህ ይነበባል።
"ሶፊያ የተባለችውና የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት የተሰጣት የመጀመሪያዋ ሴት ሮቦት ወደ ኢትዮጵያ ልትመጣ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፥ 67 ከመቶ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተሰራችው ሳውዲአረቢያዊቷ ሶፊያ ሮቦት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለች ብለዋል።
"እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ፥ ሮቦቷ 67 በመቶ ፕሮግራም የተደረገችውና የተሰራቸው የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሚደግፋቸው ሰዎች አማካኝነት ነው።
ስለዚህም የሮቦቷ ስራ ውስጥ የኢትዮጵያ ልጆች ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉም አብራርተዋል።
ሶፊያ የተባለችውና የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት የተሰጣት የመጀመሪያዋ ሴት ሮቦት በቅርቡ በሚዘጋጅ እንድ ግዝጅት ላይ እንደምትመጣም ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል።
ሮቦቷ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ በአማርኛ እንድትናገር እንዲደረግ ሀሳብ ሰጥቻለው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለዚህም የሚረዳ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ ነው ብለዋል።
ሮቦቷ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ሶፍትዌሩ ተጭኖላት በአማርኛ እንድትናገር እንደሚደረግም ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል።
ሶፊያ የተባለቸው እና ከሰው ልጅ ቅርፅ ጋር ተመሳስላ የተሰራችው ሮቦት ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ነበር ህጋዊ ዜግነት ከሳኡዲ አረቢያ ያገኘችው።"ይላል የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ዜና። ሶፊያንና ንግግሩዋንም በዩቲዩብ ገብታችሁ ማየትና ማድመጥ ትችላላችሁ ።
ወደ ጥያቄያችን እንምጣ።
67 በመቶ በኢትዮጵያውያን ነው የተሰራችው የሚል ዓይን ያወጣ ውሸት መዋሸት ለምን አስፈለገ?ይች ሮቦት ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱዋስ ፋይዳው ምንድነው?በአማርኛ እንድትናገር ማለትስ ምን ማለት ነው?የኢትዮጵያ ህዝብ በሮቦት ረሃብ እየተንገበገበ ያለ ህዝብ ነውን?ኢትዮጵያ መምጣቱዋና የመጣቱዋ ዓላማ ምንድነው?ጥቅሙስ?ባለስልጣናቱና የሃይማኖት አባትቶችስ እንዴት የክብር ግብዣ ሊያደርጉላት ፈለጉ?በእርግጥስ በኢትዮጵያውያን ባለስልጣናትና በሃይማኖት አባቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና ተማጽኖ ነው ወደ ኢትዮጵያ የምትመጣው?መጥታስ ምን ልትለን ምን ልታስተምረን ነው?እንዴት?ለምን?ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?እያሉ መጠየቅ ከአስተዋይ ኢትዮጵያውያን ይጠበቃል።
የሃሰት ዜናው በዚህ ብቻ አያበቃም።ዓለም አቀፍ ሃሰትነቱን ቀጥሎ ከሶስት ቀናት በፊት በሃበሻ ታይምስ እንዲህ የሚል ዜና ተለቆዋል።
"ኢትዮጵያዊው አይኮግ ላብስ ካምፓኒ ተቀማጭነቱን በሆንግ ኮንግ ከሚገኘው ሐንሰን ሮቦቲክ ጋር የሱፊያን ውስጣዊ ስሪት (Software) ለመቀመር ለሦስት ዓመታት ተፈራርሟል፡፡
በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያውያኑ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በሶፊያ ላይ አሻራቸውን አሳርፈው እውን እንዳደረጓት የአይኮግ ላብስ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ጌትነት አሰፋ ይናገራል፡፡
ይህም በመሆኑ ሶፊያ ኢትዮጵያዊ ናት ልንል እንችላለን።
አይኮግ ላብስ በቴክኖሎጂ ዘርፍ አስተዋጽኦ ለማበርከት ሰው ሠራሽ አስተውሎትንና ሰው ሠራሽ የአእምሮ ስሪትን (Artificial General Intelegence and Cognitive Brain Software) ለዓለም ለማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ ከአምስት ዓመታት በፊት የተመሠረተ ድርጅት ነው።
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ችሎታ ለዓለም በማስተዋወቅ ወደፊት ታላላቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ሠርተው ማሳየትንም ያልማሉ።
በአሁኑ ሰዓት ይህ የቴክ ኩባንያ ጥናት አድራጊዎችን፣ ምልክት ተርጓሚዎችን (Coder)፣ የፕሮግራም ባለሙያዎችና በተግባር ልምምድ ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ75 በላይ ሠራተኞች ይዞ እየሠራ ይገኛል።"እየተባለ እየተደሰኮረ ነው።ይህም ማምታቻ ነው!ለምን ኢትዮጵያ?ተብሎ እንዳይጠየቅ የሚደረግ ማምታቻ!!የኢትዮጵያውያን አሻራ ያለባት!እንዲባልና ዓላማቸውን ኢትዮጵያ ላይ በነጻነት ያስፈጽሙ ዘንድ የሚደረግ ማምታቻ ነው!በተረፈ ኢትዮጵያ አንድ ዶ/ር ለ መቶ ሺ ሰው የሆነባት ምስኪን አገር መሆኑዋ እየታወቀ፤ሆንግኮንግ ላይ ቢሮ ከፍቶ እንዲህ ያለ የሮቦት ምርምር ማድረግና በውጤቱም ሶፊያን ሰርተን የሳኡዲ ዜጋ አድርገን ለዓለም ህዝብ አቀረብን ማለት አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ ከሚል ቁዋንቁዋ ተለይቶ አይታይም።
ለማንኛውም አርብ ሰኔ 22 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሶፊያን ለመቀበል ከፍ ያለ በጀት ተመድቦ ሽርጉዱ ቀጥሎዋል።ሶፊያም ኢትዮጵያን እንደረገጠች ኢትዮጵያዊ ስም ይወጣላታል።ለጊዜው ሁለት ስም ተዘጋጅተውላታል።1ኛ ጣይቱ፣2ኛ ሉሲ!
ይህ ሁሉ ነገር ምን ማለት ነው???ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያና ለህዝቡዋ ምኑ ነው?ይህ አይነቱ ተግባርና አካሄድስ የቅዱሱ ፈጣሪያችን ዓላማና ፍላጎት ወይስ የክፉው የሳጥናኤል ዓላማና ፍላጎት?ራሳችሁን ጠይቁ!ሌሎች አስተዋይ ዜጎችም እንዲጠይቁ መረጃውን ሼር በማድረግ ተባበሩ።
Read more here

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time