Tuesday, June 19, 2018

ድብደባ እና እስር የመንግስት የሽብር ተግባር ነው -BBC

ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን የጠቅለይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን የፓርላማ ንግግር የዘገባቸዉ ትኩረት አድርገዋል፡፡
ቢቢሲ በአፍሪካ አምዱ ዶ/ር አብይ አህመድ ‹‹ድብደባ እና እስር የመንግስት የሽብር ተግባር ነው አሉ ›› በሚል ርዕስ ነዉ ዘገባውን ይዞ የወጣዉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ወሳኝ ለውጦችን አድርገዋል ነዉ ያለዉ ዘገባዉ፡፡
ለፓርላማ ደረጉትን ንግግር ተከትሎ ከአባላትም ስለቀረቡላቸዉ ጥያቄዎች እና ምላሾቻቸዉም አትቷል፡፡ በሽብር፣ሙስና እና ግድያ ወንጀሎች የተከሰሱ ግለሰቦች ለምን ከእስር ይለቀቃሉ? የሚል ጥያቄ መነሳቱንም የትንታኔዉ ቀዳሚ ትኩረት አደረገ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸዉ ጣታቸውን ወደ መንግስት ቀስረዋል ይላል ቢቢሲ፡፡
“ሽብርተኝነት በስልጣን ላይ ለመቆየት ህገ-መንግስቱን በመጣስ፣ ሀይል መጠቀም ነው!” ማለታቸውንም አስነበበ፡፡
“በመላ ሀገሪቱ ታስረው ድብደባ የተፈጸመባቸው እንዲሁም በጨለማ ክፍል የተወረወሩ ግለሰቦችም አሉ፤ ህገ-መንግስቱ ይህንን አድርጉ አይልም፤ ስለዚህ ይህ ተግባር ነው የሽብር ድርጊት” ማለታቸዉን ነዉ በማሳያነት ያቀረበዉ፡፡
በተያያዘ ዜናዉም ከወር በፊት ከፍተኛ የደህንነት እና ወታደራዊ ባለስልጣናት ከስልጣን መነሳታቸዉን ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ ጋር ሰላም ለመፍጠር የአልጀርሱን ስምምነት ቢቀበልም ከኤርትራ መንግስት እስካሁን ምላሽ አለመስጠቱንም አስነብቧል፡፡
የፕራይቬታይዜሽን ፖሊሲ ለውጣችው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማዘመን ይረዳቸዋል ሲልም ዘገባውን ደምድሟል፡፡
የቻይናዉ ዓለማቀፍ የቴሌዥን ኔትወርክ (CGTN) ደግሞ ቢቢሲን ምንጭ አድርጎ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ዘገባ አስነብቧል፡፡ ከዚህ ባሻገር ሲ ጂ ቲ ኤን የዓለም የገንዘብ ድርጅትን (IMF) ጠቅሶ ሲዘግብ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እስካሁን ሲያስመዘግብ የቆየውን የሁለት አሃዝ እድገት በዚህ ዓመት እንደሚያስመዘግብ ተንብይዋል፡፡ በውጭ ምንዛሬ እጥረት፣በሙስና እና በሌሎች ችግሮች ሳቢያ የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት የዶ/ር ዐብይ አስተዳደር ወሳኝ ኢኮኖሚያዊ እቅዶችን አስተዋውቋል ብሏል፤ ዘገባዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እርቅ እና ይቅር መባባል ለሀገሪቱ መረጋጋት እና ሰላም ትልቅ ፋይዳ አለው” ማለታቸውን ሲቲጂኤን ዘግቧል፡፡
ሽንዋ በበኩሉ እርቅ እና ይቅርታ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ ስለመሆናቸዉ ዶ/ር አብይ ትኩረት እንደሰጡ ነዉ በዋና ሃሳብነት የጻፈዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለፓርላማዉ ባደረጉት ንግግር እስካሁን የተደረጉት ምህረቶች እና ይቅረታዎች ለሀገሪቱ ሰላም መስፈን ጉልህ ሚና እንዳላቸዉ ማብራራታቸዉን ትልቅ ዋጋ የሚሰጠዉ ሃሳብ ብሎታል፡፡
አፍሪካ ኒዉስ ሌላዉ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ማብራሪያ የዘገበ የዜና ምንጭ ነዉ፡፡ “በኢትዮጵያ የእስራት እና የድብደባ ዘመን አከተመ” የሚለዉ ሀሳብ ደግሞ ቀዳሚዉ ነበር፡፡ ዶክተር አብይ በንግግራቸዉ ዜጎች ወንጀለኝነታቸዉ እስካልተረጋገጠ በእስራት መቀጣት እንደሌለባቸዉ እና ንጹሀንን ከማሰር ወንጀለኞችን መፍታት ይሻላል የሚል አቋማቸዉን አንጸባርቀዋል፤ ይላል ዘገባዉ፡፡
የአልጀርሱን ስምምነትን አስመልክቶ የተነሳዉ ተቃዉሞ ምክኒያታዊ አለመሆኑን እና ከዚህ ቀደም ፓርላማዉ ያጸደቀዉ ስምምነት እንጂ አዲስ ዉሳኔ አለመሆኑን አስረድተዋል በማለትም አስነብቧል ሽንዋ፡፡
በቢኒያም መስፍን

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time