Thursday, December 28, 2017

በጦርነት እየታመሰች ባለችው የመን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የሚደርስልን አጣን እያሉ ነው።

በቅርቡ በነበረው ጦርነት በሰንዓ ከተማ ሁለት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጥይት ተመተው እግራቸው ተቆርጧል
በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የሚደርስልን አጥተን ለእንግልት ተዳርገናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
እነዚህ ስደተኞች አብዛኞቹ ሰንዓ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን በጦርነቱ ምክንያት ወደ ተለያዩ የገጠር አካባቢዎች እየተሰደዱ እንደሆነ እና መፍትሄም እንዳጡ ይናገራሉ።
ጀማል ጄይላን ከ16 ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ወጥቶ በየመን መኖር የጀመረ ሲሆን "ሀገሪቱ በጦርነት እየታመሰች ስለሆነ የሚደርስልን አጥተናል" ይላል።
"ስለዚህ ችግራችንን የምንነግረው አንድም አካል የለም፤ ስንታመም የምንታከምበት ቦታ የለም፤ ብዙ ልጆች ያሏቸው ሰዎች አሉ። ከፍተኛ እንግልት እየደረሰብን ነው" በማለት ያሉበትን ሁኔታ አስረድቷል።
ከዚህ በተጨማሪ "በጦርነቱ ምክንያት ሥራ የለም። ለሰራንበትም ደሞዝ አይከፈለንም፤ ቢከፈለንም ዝቅተኛ ነው። የምግብ ዋጋ ደግሞ እጅጉን ንሯል" ሲል ሁኔታቸውን ይገልፃል።
ሌላኛው ለ17 ዓመት የመን ውስጥ የኖረው ኤርትራዊ እና ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቀን ግለሰብ ደግሞ በየመን መንግሥት እና በአማፅያን መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች እየተጎዱ መሆኑን ተናግሯል።
"ሀገሪቱ በጦርነቱ ምክንያት አዲስ ስደተኛ መመዝገብ ካቆመችም ሁለት ዓመት ሆኗታል።"
ስለዚህ ወደ የመን የሚሄዱ ስደተኞች መታወቂያ ከማጣታቸውም በላይ ቀድመው እንኳ መታወቂያውን ያገኙ ማሳደስ አለመቻላቸውን ይናገራል።
አማፅያኑ መግቢያና መውጫ መንገዶችን የዘጉ ሲሆን ጦርነቱን በመሸሽ ለማምለጥ የሚሞክሩ ስደተኞች ለወታደሮች ጥቃት እየተጋለጡ እንደሆነም ይገልፃል።
በቅርቡ በነበረው ጦርነት እንኳ በሰንዓ ከተማ ጎዳናዎች ሁለት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጥይት ተመተው በደረሰባቸው ጉዳት እግራቸው ተቆርጦ አሁን ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ እንደሆነ ጀማል ይናገራል።
መንገድ ላይ መዘረፍ፣ መታሰር፣ ገንዘብ ከቤተሰብ እንድናስልክ መገደድ እና የመሳሰሉትን ቀድሞም ቢሆን ለምደነዋል፤ የሚለው ኤርትራዊው ስደተኛ በሀገሪቱ ያለው ጦርነት ከመባባሱ ጋር ተያይዞ ግን አንዳንዶች ተገደው ወደ ውትድርና እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ተናግሯል።
ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ማለዳ ላይ በዘጠኝ የሁቲ ፖሊሶች ተደብድቤያለሁ፤ የሚለው አማን መሀመድ መታወቂያውን ቤት ውስጥ ረስቶ መውጣቱን ቢናገርም እንኳ ከከተማዋ ወጣ ባለች የገጠር አካባቢ ወስደው እንደደበደቡት ይናገራል። ከድብደባው በተጨማሪም 330ሺህ የየመን ሪያል መዘረፉንም ይገልፃል።
"ለአንድ ሰው 9 ወታደር ማለት ከባድ ነው። እንደ እባብ ነው የቀጠቀጡኝ። ራሴን እንድስት ከመኪና ጋር አጋጩኝ። ከዚያም ወደ ጦር ሜዳ ሊወስዱኝ ነበር። በኋላም ሁቲዎችን በሚቃወም አንድ ወታደር ነው ነፍሴ ለመትረፍ የቻለው" ይላል አማን።
ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ሶማሌያዊያን የስደተኞች ማህበረሰብ አባላት በጋራ በመሆን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የየመኑን ቅርንጫፍ ሄደው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ይናገራሉ።
የመንImage copyrightMOHAMMED HUWAIS
አጭር የምስል መግለጫየመን ሰነዓ
የቀድሞው ፕሬዝዳንት አሊ አብዱላህ ሳላህ በተገደሉበት ወቅት በሀገሪቱ ያለው ውጥረት ተባብሶ እንደነበር የሚናገሩት እነዚህ ስደተኞች፤ በዚህም ምክንያት የከፋ ችግር ገጥሟቸዋል።
እየደረሰባቸው ያለውንም ችግር ጠቅሰው ኮሚሽኑን እርዳታ ቢጠይቁም አልተዘጋጀንበትም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው እና በድጋሚ ጥያቄውን አቅርበው ምንም የምናግዛችሁ ነገር የለም የአካል ጉዳት ያለበት ስደተኛ ካልሆነ በቀር በጀት የለንም መባላቸውን ገልፀዋል።
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅትም ''የእኛ ድርሻ ጦርነት በተነሳ ወቅት ከጦርነቱ ቀጠና መውጣት ያልቻሉ ሰዎችን ወደ ሰላማዊ ስፍራ መውሰድ ነው'' ማለቱን እነዚሁ ስደተኞች ተናግረዋል።
ስደተኞቹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የሚገኙበትን ሁኔታ ለዓለም እንዲያሳውቅ ካልሆነ ደግሞ ከየመን መውጣት የሚችሉበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።
የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባይ ሊዮናርዶ ዶይል፤ ቀድሞም ቢሆን ፍልሰት መኖሩን ጠቅሰው ከአፍሪካ ቀንድ የሚሰደዱ ግለሰቦች ቀውስ ውስጥ በምትገኝ ሀገር ውስጥ በጦርነት መሃል ይገኛሉ ብለዋል።
"ሰዎችን አትሰደዱ አንልም ነገር ግን በተቻለ መጠን ከወንጀለኛ እና ደላሎች ራሳቸውን ጠብቀው ደህንነቱ የተጠበቀ ስደት እንዲያደርጉ እንፈልጋለን"ብለዋል። Read more here

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time