Monday, September 25, 2017

ከEBC - ESAT ማን ይዋሻል?

ውድ ተከታታዩቸ ካሁን በፊት መጣጥፌ መረጃን በማፈን የሚመጣ ችግርን ለማንሳት ሞክሬ ነበር። ቃል በገባሁት መሰረት አሁን ደሞ መንግስት ምን ማድረግ አለበት የሚለውን ጠቃሚ ሐሳብ ለማንሳት እሞክራለሁ።
መረጃ ላንድ አገር እድገት በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ሁሉም ሚያውቀው ነው። በመረጃ ፍሰት የፈረሰ አገር የለም በመረጃ እጦት እንጂ። እርግጥ ነው አምባገነን መንግሥታት ለሥልጣናቸው ሲሉ መረጃን ያፍናል፣ እውነቱን አውጥተው ለህዝብ ለማድረስ ይፈራሉ። የተደበቀ እውነትም ፈልፍሎ የሚያወጣ ሁሉ ለእነሱ ጠላት ነው። ምክንያቱም አላማቸው መረጃን በማፈን ሥልጣንን ማራዘም ነውእና። ትክክለኛው አካሄድ ግን እንደዚህ አይደለም። እውነትም ሆነ ሀሰት መረጃ መረጃ ነው። መረጃው ሐሰት ሆነ እውነት ፈራጅ ተጠቃሚው ነው እንጂ ሌላ ማንም አካል አይደለም። ሀሰት እየከሰመ ይሄዳል እውነት ግን እያደር እየጎለበተች ትሄዳለች። ይህን ማንም የሚያውቀው ሐቅ ነው።
No automatic alt text available.
በሶሻል ሚዲያው እውነትን አፈንፍኖ ለተጠቃሚው የሚያደርስ ብዙ ተከታይ አለው። ውሸትን ሚናገር ግን እያደር ይከስማል። የወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት ግን ለሁሉም ነገር የመረጃው ምንጭ እኔ ብቻ ነኝ እኔን ስሙኝ እያለ ሌላውን ግን ውሽት ነው እያለ ድፍን 25 አመት አብረን ቆየን። በአለም ላይ ስለፖለቲካ እውነትን ደፍሮ የሚናገር የግል ሚዲያ የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች። በወያኔ ኢህአዴግ አመለካከት ለወደፊቱም እዲኖር አይፈለግም።
መሠረታቸውን በውጭ ሐገረ አድርገው ስለኢትዮጵያ መረጃን የሚያቀብሉ እንደ ቨኦኤ፣ ጀርመን ያሉ ትልቅ የሚዲያ ተቋማት እንኳን በወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት ሚደርስባቸው አፈና ሁሉም ሚያውቀው ነው። ወያኔ እንደ እሳት፣ OMN እና ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ አክትብስቶችን አሸባሪ ናቸው ይለናል። ያ ሁሉ የእነሱ ተከታይ ታዲያ አሸባሪ ወዶ ነው? አሸባሪ ሆኑ አልሆኑ፣ እውነትን ተናገሩ ውሸትን ፈራጅ ተጠቃሚው ህዝብ ቢሆንስ? አሸባሪ ወይም ሀሰትን ተናጋሪ ከሆኑ ህዝቡ አንቅሮ እንደሚተፋቸው አሙን ነው። እውነታው ግን እንደዛ አይደለም። እውነቱን እንነጋገር ካልን ከ EBC እና ከእሳት ወይም OMN በሶሻል ሚዲያ ማነው ብዙ ተከታይ ያለው?
መልሱን ለአንባቢያን እንተው እና በጣም ሚገርመው ደሞ የድረ ገጾች አፈና ነው። የወያኔ መንግሥት ስለኢትዮጵያ የሚዘግቡ ኢትዮጵዊያን ድረ ገጾች ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ በጣም ታዋቂ እና ተነባቢ የሁኑ እንደ ዋሽግተን ፖስት፣ 24 ኒውስ፣ እና ሌሎችን በተለያዩ ተቋማት እና በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጥርቅም አድርጎ መዝጋቱ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን በአለም ብዙ ተጠቃሚ ያለው የGoogle ንብረት የሆነው ብዙ ፃሃፊያንሐሳባቸውን ወይም የምርምር ግኝታቸውን ለአንባቢያን የሚያጋሩበት በሎገር blogger.com ከብዙ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች እዳይሰሩ ተደርገዋል።ዩኒቨርሲቲዎች ደሞ ለዚህ አይነቱ ቁጥጥር በጣም ቀላል ናቸው። ሰርቨር ኮምፒውተራቸው ላይ የማይፈለጉ ድረ ገጾች ራውት ወይም ብሎክ ማድረግ ብቻ ነው።
በስራ ምክንያት ብዙ ዩኒቨርሲቲዎችን እንደ ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ አርባምንጭ ባየሁ ግዜ እንደ ብሎገር እና ወርድ ፕረስ አይሰሩም። ይህ ደሞ አካዳሚክ ነፃነትን መጋፋት ነው። በጣም የሚገርመው ዩኒቨርስቲ ያለ ሰው የተማረ ክፉውን እና በጎውን፣ ውሸት እና እውነቱን አመዛዝኖ መለየት የሚችል ያለበት የሙህራን ጥርቅም ነው። እነ እሳት እና OMNስ የወያኔ ተቀናቃኝ ነቸው ብየ ልፈርጅ፣ ታዲያ በምን አስተሳሰብ ነው ስለኢትዮጵያ ሚዘግቡ እነ ዋሽግተን ፖስት፣ ABC ኒውስ፣ ሌሎች እና ብሎገሮች ጥርቅም ብለው በነዚህ ተቋማት ላይ ሚዘጉት? ሕዝብን መናቅ መረጃን ማፈን የትም አያደርስም። ከዚህ ጋር በተያያዘ በጣም የሚገርመው ደም የሃገርን ባህል፣ ሐይማኖት፣ ቅርስን የሚበርዙ አደገኛ የሆኑ እንደ ፖኖግራፌ ፣ ተመሳሳይ የፆታ ጋብቻ እና ሌሎች ድረ ገፆች በወያኔ ምንግስት ምንም ደንታ የላቸውም። መታገድ ሚኖርባቸውስ እነዚህ ነበሩ።
የወያኔ መንግሥት ሰለማይችል ነው እንጂ ማይፍልጋቸውን ድረ ገጾች በእያንዳንዱ ሰው ሞባይል ላይም ሳንሱር ቢያደር ምንኛ ደስ ባለው። ነገር ግን አሁን ዘመኑ ተቀይሯል። የወያኔ መንግሥት በዚህ መልኩ ወደፊት መቀጠል አይችልም። ሁሉም ቴክኖሎጂው በኪሱ አለው። ከላይ ለመጥቀስ እደሞከርኩት ወያኔ አቅም ኑሮት ወይም አቅም ያለውን በብዙ ገንዘብ ቀጥሮ በእያንዳንዱ ኪስ ካለው ቴክኖሎጂ ላይ ድረ ገፆችን ራውት ወይም ብሎክ ካላደረገ (ሳስበው ሚሞክሩት ይመስለኛል) መረጃን እንደወትሮው ማፈን አይችልም። ይልቁንስ የወያኔ ኢሕአዴግ መንግሥት በመረጃ ፍሰት የሚመጣውን ፍርሀት እርግፈ አርጎ ትቶ የኢትዮጵያን ህዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን ማከበር ይገባዋል። እውነት መጋፈጥ መልመድ ይኖርበታል። "እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር" አደል የሚለው ያገሬ ሰው።
ለዚህም ደሞ የግል ሜዳውን ሆነ ሶሻል ሚዲያዎችን ያለምንም ሳንሱር መፈቀድ ይኖርበታል። ያለምንም ምክንያት በኢትዮጵያ ቴሌ ሰርቪስ ፕሮባደር (IP) ሆነ በተለያዩ ተቋማት ሰርበር ኮፒተራቸው የሚደረግ የድረ ገፅ አፈና መቆም አለበት። ማንም ሚዲያ ህጉን እና ደቡን ተከትየ ስለሀገሬ አወራለሁ፣ እዘግባለሁ ብሎ ቢመጣ መፈቀድ አለበት። ምክንያቱም ባሌቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ነውእና። የኢትዮጵያን ህዝብ ለቀቅ አርጉት። ሚያዳምጠውን እሱ ያውቃል። እኔን ብቻ አዳምጡኝ ሌላው አሸባሪ እና ሀገር አተራማሽ ነው ሚለው መብቃት አለበት። ማን እውሸት ተናጋሪ፣ ማን አሸባሪ እና ማን ሐገረ አተራማሽ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ያላቹህን የቴክኖሎጂ እውቀት እና ይህን ለማፈን የምታወጡትን ገንዘብ ለጡሩ ነገር አውሉት። ዛሬ እነ ኮሪያን እያየን ነው። የዜጎቿን የቴክኖሎጂ እውቀት ተጠቅመው ሃገራቸውን ማስከበር የቻሉ ሐገሮች ናቸው። ዛሬ world cyber war ቢነሳ ኮሪያ ውስጥ ተቀምጠው የአሜሪካን ሰርበር ድባቅ የሚመቱ ልጆቿ ተፈጥረዋል። ከኛ ሐገረ ግን ተቃራኒው ነው ያለው። መንግስት አለኝ ያለውን አቅም አሟጦ ሆነ በከፍተኛ ገንዘብ ወጭ ከነቻይና በቀጠራቸው ሰወች የራሱን ዘጋ መብት ያፍንበታል።
ውድ ተከታታዩቸ በሚቀጥለው ወያኔ ኢሕአዴግ እንዴት አድርጎ ደረ ገፆዎችን ሳንሱር እንደሚያደርግ፣ ውጭ ሚተላለፉ እንደ እኦሳት ያሉ ሜዳዎች እዴት ጃም እደሚያደርግ፣ ምን ሶፍትዌሮች እደሚጠቀም፣ ማን እና ምን አይነት ባለሙያ እደሚጠቀም እና ምን ያህል ወጪ እንደሚያወጣ በሰፊው ይዤ እደምቀርብ ቃል እገባለሁለት። እስከዛው ግነ ቸር እንሰብት።

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time