የግብፅ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ኢብራሂም ዮስሪ፤ በህዳሴው ግደብ ላይ ሀገራቸው ከኢትዮጵያና ከሱዳን ጋር የደረሰችበት ስምምነት ውድቅ እንዲሆን ለሀገሪቱ የመንግስት ም/ቤት የህግ መሟገቻ አቀረቡ፡፡ አምባሳደሩ፤ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በአባይ ጉዳይና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የተፈራረሙት ስምምነት የግብፅን ህገ መንግስት የሚቃረንና የሀገራቸውን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን እንደገለፁ “ዘ ሚድል ኢስት ሞኒተር” ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ የቀረበው የመሟገቻ ሀሳብ ስምምነቱ ግብፅን የሚጎዳ መሆኑን ጠቁሞ፤ “ይህ ስምምነት በግብፅ ፕሬዚዳንት ዙሪያ ያሉ የህግና አለማቀፍ አማካሪዎች ደካማና ለሀገራቸው ጥቅም የቆሙ አለመሆናቸውን ያመለክታል” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡ ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለቱ ሀገራት ጋር የተለያዩ ውይይቶችን እያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ግድቡ በሁለቱ ሀገራት ላይ ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረው በተደጋጋሚ መግለፁ አይዘነጋም፡፡ Read more here
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Recent Articles
Recent Video Uploads
Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube
Ethiopia Today
- Active a minute ago with many
- videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies, Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time
No comments:
Post a Comment