Sunday, December 25, 2016

የግብፅ ክፍተኛ ባለስልጣን በህዳሴው ግድብ ላይ የተደረሰው ስምምነት ውድቅ እንዲሆን ጠየቁ

የግብፅ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ኢብራሂም ዮስሪ፤ በህዳሴው ግደብ ላይ ሀገራቸው ከኢትዮጵያና ከሱዳን ጋር  የደረሰችበት ስምምነት ውድቅ እንዲሆን ለሀገሪቱ የመንግስት ም/ቤት የህግ መሟገቻ አቀረቡ፡፡ አምባሳደሩ፤ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በአባይ ጉዳይና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የተፈራረሙት ስምምነት የግብፅን ህገ መንግስት የሚቃረንና የሀገራቸውን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን እንደገለፁ “ዘ ሚድል ኢስት ሞኒተር” ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ የቀረበው የመሟገቻ ሀሳብ ስምምነቱ ግብፅን የሚጎዳ መሆኑን ጠቁሞ፤ “ይህ ስምምነት በግብፅ ፕሬዚዳንት ዙሪያ ያሉ የህግና አለማቀፍ አማካሪዎች ደካማና ለሀገራቸው ጥቅም የቆሙ አለመሆናቸውን ያመለክታል” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡ ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለቱ ሀገራት ጋር የተለያዩ ውይይቶችን እያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ግድቡ በሁለቱ ሀገራት ላይ ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረው በተደጋጋሚ መግለፁ አይዘነጋም፡፡  Read more here

No comments:

Post a Comment