ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ጋር መሠረታዊ በሆኑ ፖለቲካዊ ችግሮች ላይ ለመነጋገር መወያየታቸው ተነገረ፤ እስካሁን ግን ከገዢው ግንባር ተጨባጭ እርምጃ እንዳልተወሰደ የመድረክ መሪ አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ —
ኢሕአዴግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኩል ወደ ቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ የፈለገ እንደሚመስልም ግምታቸውን ገልፀዋል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በኮንሶ ብቻ ከ5መቶ በላይ ሰዎች መታሠራቸው በጋሙጎፋ ዞን የፓርቲ አመራር አባላት መያዛቸው ተሰማ።
የአትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ትናንት አመሻሹ ላይ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከአንድ ወር በፊት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ከዚያም ወዲህ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለፓርላማ ያደረጓቸውን ንግግሮች በመንተራስ መድረክ ለጠቅላይም ሚኒስተሩ ደብዳቤ መፃፉን ገልፀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ። Read more here
No comments:
Post a Comment