Saturday, November 12, 2016

የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኛ በፍቃዱ ኃይሉ ዳግም እስር

በፈቃዱ ኃይሉ
የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኛ በፍቃዱ ኃይሉ ዛሬ ማለዳ በድጋሚ ታሰረ። በሽብር ወንጀል ከሌሎች የኢንተርኔት አምደኞች ጋር ታስሮ የነበረውና በ20 ሺሕ ብር ዋስ ተፈቶ ጉዳዩን በውጭ ሲከታተል የቆየ የኢንተርኔት አምደኛው በፍቃዱ ኃይሉ ዛሬ ማለዳ ሲቪል በለበሱ ሰዎች ልዩ ስሙ "ፈረንሳይ" ከተባለው መኖሪያ ቤቱ በኮማንድ ፖስት እንደሚፈለግ ተነግሮት መታሰሩ ታውቋል። አሁኑ በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ እንደሚገኝ ጣቢያው አረጋግጦልናል።
የዛሬ ዓመት ከእስር የተለቀቀው የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት የጡመራ መድርክ አምደኛና የውይይት መጽሔት አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ ዛሬ በድጋሚ መታሰሩን ሌላዋ የኢንተርኔት አምደኛ ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጸች። የመታሰሩ ምክንያት ምን እንደሆነ እስክካሁን በግልጽ አለመታወቁን የገለጸችው ወ/ት ሶሊያና ከቤት የተወሰደው ግን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ለማስፈፀም በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ትፈለጋለህ በሚል እንደሆን መረጃ እንዳላት ትናገራች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ
በፍቃዱ ኃይሉ በአዲስ አበባ በተለምዶ ፈረንሳይ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በሚገኘው የቤተሰቦቹ መኖሪያ ቤት የሚኖር ሲሆን በአቅራቢያው ወደነበረው ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ ማቆያ ክፍል ለሰዓታት እንደቆየና እዚያ በነበረበት ወቅት ከቤተሰቦቹ ጋር እየተነጋገረ እንደነበረና እስከዛ ድረስ ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳልቀረበለት ወ/ት ሶሊያና ገልፃለች።
ወ/ት ሶሊያና ምንጮቿን ዋቢ አድርጋ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገረችው በፍቃዱ ማምሻውን በተደረገለት አጠር ያለ የምርመራ መጠይቅ ስሙ ለተጠቀሰለት ብዙሃን መገናኛ ቃለ ምልልስ ሰጥተሃል የሚል ክስ በቃል እንደቀረበለት ነው።
የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የበፍቃዱ የቅርብ ወዳጆችም በተመሳሳይ ለምን ቃለ ምልልስ ሰጠህ በሚል እንደተጠየቀ ጠቁመዋል። ነገር ግን ወ/ት ሶሊያና እንደምትለው እስካሁን በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ላይ በክልከላ ከተቀመጡት ውስጥ በግልጽ ይህን ጥሰሃል ተብሎ የተነገረው ነገር እንደሌለ ነው።
በፍቃዱ ኃይሉ ዞን ዘጠኝ በተባለው የኢንተርኔት የጡመራ መድርክ ላይ በኢንተርኔት አምደኛነቱ ይታወቃል። በሚያዚያ ወር በ2007 እርሱና አምስት የኢንተርኔት አምደኞች ባሉበት ሌላዋ የኢንተርኔት አምደኛ ወ/ት ሶሊያና ሽመለስ በሌለችበት እንዲሁም ሦስት ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሽብር ወንጀል ተከሰው ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ በመጀመሪያ አምስቱ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ሲለቀቁ ጥቂት ቆይቶ ደግሞ ሦስቱን እና ወ/ት ሶሊያና በሌለችበት ፍርድ ቤት በነፃ አሰናብቷቸው እንደነበር ይታወሳል።
የዞን ዘጠኝ አምደኞችና ጋዜጠኞች
የዞን ዘጠኝ አምደኞችና ጋዜጠኞች
በፍቃዱ ኃይሉን ግን አመጽ በጹሑፍ በማነሳሳት ክስ እዲከላከል ተበይኖበት በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የ20,000 ብር ዋስትና አሲዞ ከእስር እንዲፈታ ከሀገር እንዳይወጣ እገዳ ጥሎበት ነበር፡፡
በተጨማሪም በነፃ ከተሰናበቱት ሊሎች አራት አምደኞች አቤል ዋበላ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃነ እና ሶሊያና ሽመልስ(በሌለችበት)ጋር ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ስለጠየቀባቸው ማክሰኞ ህዳር 6፣2009 ለአምስተኛ ግዜ ለብይን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በፍቃዱ ኃይሉ ዛሬ ስለታሰረበት ሁኔታ ከቤተሰቦቹ መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርገን በፍቃዱ የታሰረው ለብዙሃን መገናኛ ቃለ ምልልስ ሰጥተሃል በሚል መሆኑን መስማታቸውን ገልጸው መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ጠበቃ እንዳለው ጠይቀን በዐአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መሰረት ጠበቃ ማቆም ስለማይፈቀድ ለጊዜው ጠበቃ የለውም ስትል ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ ገልፃልናለች።
ታሰረበት የተባለው የላምበረት አካባቢ የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ደውለን ስልኩን ያነሱት መሰረት የተባሉ ሴት በፍቃዱ ሃይሉ ተጫኔ ዛሬ የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩንና የታሰረበትን ዝርዝር በተመለከተ ግን በአካል ቀርበን መርማሪውን ካልጠየቅን የሚነግሩን መረጃ እንደሌለ ገልጸዋል።
የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞችና ጋዜጠኞች ከእስር ከተፈቱ በኋላ
የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞችና ጋዜጠኞች ከእስር ከተፈቱ በኋላ
በፍቃዱ ኃይሉ ከእስር ከተፈታ በኋላ ውይይት የተሰኘ መጽሔት ከጓደኞቹ ጋራ በማዘጋጀት በማሳተም ላይ ይገኝ ነበር። በፍቃዱ ከባልደረቦቹ የዞን ዘጠኝ የድረ ገጽ አምደኞች ጋር በጋራ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሽልማቶችን አግኝቷል። ችልድረንስ ኦፍ ዜር ፓረንትስ (የወላጆቻቸዉ ልጆች) በሚል ርእስ በጻፈዉ ልብ ወለድ መጽሐፍም በግሉ ከአራት ዓመታት በፊት የአፍሪካ የስነጽሑፍ ሽልማት ውድድር ተወዳደሮ ሦስተኛ በመውጣቱ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድመጡ Read more here

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

  • Ethiopia: 75-Year-Old Civilian Brutally Murdered in Church by Abiy Ahmed Regime’s Forces
     In a shocking and disturbing incident, 75-year-old Mr. Fentaw Derbew, a civilian, was brutally murdered while attending a mass at Kobo Michael Church in Raya Kobo Woreda, North Wollo Zone in Ethiopia. According to eyewitnesses and sources, Mr. Fentaw Derbew was killed by the Abiy Ahmed...
    July-27 - 2025 | More »
  • Ethiopian Health Professionals Association Urges Govt to Promptly Respond to Health Workers' Demands Amid Pre-Strike Demonstrations
     Dagmawi Melnilik Hospital, which was later upgraded to a referral hospital, is the nation’s first hospital, built in 1909.Addis Standard (Addis Ababa)As health professionals across Ethiopia stage pre-strike demonstrations demanding improved salaries, benefits, and working conditions, the...
    May-13 - 2025 | More »
  • Commentary: Why Ethiopian university lecturers' strike failed: A cautionary tale for health professionals
     The moment of release of the detained teachers’ coordinators, greeted by fellow teachers awaiting their return. Photo: Provided by the writerIn 2022, Ethiopian university lecturers launched a year-long social media campaign  and subsequent threat for indefinite...
    May-13 - 2025 | More »
  • ሰባት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ባሕሩ ጣሏቸው'፡ ትኩረት ያላገኘው የስደት መንገድ
     መሐመድ አብዱላሂ ሞሐሙድ 35 ዓመቱ ነው።ከጂቡቲ ወደ የመን በጀልባ ያደረገውን የስደት ጉዞ አይረሳውም። በ20ዎቹ ዕድሜ ሳለ ነበር የተሰደደው።ሶማሊያን ጥሎ የወጣው የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ነበር።ከአፍሪካ ወደ የመን የሚደረገው ስደተኞች የሚጓዙበት መንገድ 'ምሥራቃዊው ኮሪደር' በሚል ይታወቃል።በብዛት ስደተኞች ከሚጓዙባቸው መንገዶች አንደኛው ነው። እምብዛም ግን ትኩረት አላገኘም።ይህ መንገድ በጣም አደገኛው እንደሆነም መሐመድ ይናገራል።"መንገድ ጀምረን 30 ደቂቃ...
    May-08 - 2025 | More »
  • ሐኪም በመሆኔ ያተረፍኩት ድኅነትን ነው" የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች እሮሮ እና ጥያቄ
     የደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ያነሱ የጤና ባለሙያዎች መንግሥት ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ ተናገሩ።ባለሙያዎቹ ጥያቄዎቻቸውን ለመንግሥት ማቅረባቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ ምላሽ እንዲሰጣቸውም የ30 ቀናት ቀነ ገደብ ከሰጡ ሳምንታት ተቆጥረዋል።የጤና ባለሙያዎቹ "መኖር አቅቶናል" ያሉ ሲሆን፤ በተለያዩ መንገዶች ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።ሐኪም ለመሆን 23 ዓመታትን በትምህርት እንዳሳለፉ ለቢቢሲ የተናገሩት ዶ/ር ይማም እንድሪስ...
    May-08 - 2025 | More »
  • በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው ስለሚባለው 'አፈሳ' የነዋሪዎች ስጋት
     ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች ከመንገድ እየታፈሱመሆናቸውን ወላጆች፣ ወጣቶች እና ፖለቲከኞች በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየገለፁ ነው።ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማ ነዋሪዎችም በግዳጅ የታፈሱ ወጣቶችን እንደሚያውቁ እና እነርሱም ባለባቸው ስጋት የተነሳ ድንገት ከተያዝን በሚል "ገንዘብ ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ" ተናግረዋል።ቢቢሲ ከአዲስ አበባ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ በምትገኘው በአዳማ ከተማ የሚገኝ እና ከመንገድ ላይ...
    May-05 - 2025 | More »
  • ሰባት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ባሕሩ ጣሏቸው'፡ ትኩረት ያላገኘው የስደት መንገድ
     መሐመድ አብዱላሂ ሞሐሙድ 35 ዓመቱ ነው።ከጂቡቲ ወደ የመን በጀልባ ያደረገውን የስደት ጉዞ አይረሳውም። በ20ዎቹ ዕድሜ ሳለ ነበር የተሰደደው።ሶማሊያን ጥሎ የወጣው የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ነበር።ከአፍሪካ ወደ የመን የሚደረገው ስደተኞች የሚጓዙበት መንገድ 'ምሥራቃዊው ኮሪደር' በሚል ይታወቃል።በብዛት ስደተኞች ከሚጓዙባቸው መንገዶች አንደኛው ነው። እምብዛም ግን ትኩረት አላገኘም።ይህ መንገድ በጣም አደገኛው እንደሆነም መሐመድ ይናገራል።"መንገድ ጀምረን 30 ደቂቃ...
    May-05 - 2025 | More »
  • Ethiopia’s civil war: what’s behind the Amhara rebellion?
     Ethiopia is in the grip of a civil war between federal government forces and the Fano, a loose alliance of ethnic-based militia in the Amhara region.This conflict in Ethiopia’s north erupted less than a year after the devastating Tigray war, which ended in...
    Apr-28 - 2025 | More »
  • በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተመረተ ነው!
     በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተመረተ ነው!ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት የሚገኝበት አቅም መፈጠሩን በግብርና ሚኒስቴር ዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ሃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ገለጹ። ኢትዮጵያ እምቅ የዓሣ ሀብት ቢኖራትም በተለያዩ ተግዳሮቶች ምክንያት በዘርፉ ተጠቃሚ ሳትሆን መቆየቷን በግብርና ሚኒስቴር ዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ሃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ተናግረዋል። በሀገር ደረጃ...
    Mar-26 - 2025 | More »
  • የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ደፋር ማሻሻያዎችን እና አፍሪካን የሚመሩ መፍትሄዎችን ከፒአርሲ ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ አሳሰቡ!
     የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ደፋር ማሻሻያዎችን እና አፍሪካን የሚመሩ መፍትሄዎችን ከፒአርሲ ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ አሳሰቡ!የመጀመርያው የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) እና አዲስ የተሾሙት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አመራር አባላት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂደዋል። ስብሰባውን በኤች.ኢ. ማህሙድ አሊ የሱፍ፣ የAUC ሊቀመንበር እና ኤች.ኢ. በአፍሪካ ህብረት የአንጎላ ሪፐብሊክ ቋሚ ተወካይ እና የፒአርሲ ሊቀመንበር አምባሳደር ፕሮፌሰር ሚጌል ሴሳር...
    Mar-18 - 2025 | More »
  • ፀሐይ ባለበት የቫይታሚን D እጥረት ለምን?
     ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆነው ቫይታሚን ዲ የሚገኘው በፀሐይ ጨረር አማካኝነት በተፈጥሮ ሂደት ነው። ኢትዮጵያ ዓመቱን ሙሉ የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት የምታገኝ ሀገር ብትሆንም በቅርቡ የወጣ መረጃ ብዙዎች የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዳለባቸው  ያመለክታል። ለምን ይሆን?ቫይታሚን ዲየቫይታሚን ዲ እጥረት በመላው ዓለም ሰዎች ላይ ስለሚታይ አሳሳቢ መሆኑ ይነገራል። በተለይ በዓመት ውስጥ የፀሐይ ብርሃንም ሆነ ሙቀቷን በውስን ወራት ብቻ በሚያገኙ የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ...
    Mar-18 - 2025 | More »
  • "እንደ አሮጌ ምንጣፍ የተጣለ" - የቻይና መንግሥት ጋዜጣ የቪኦኤ በጀት እንዲቋረጥ መወሰኑን አወደሰ!
     የቻይና መንግሥት ጋዜጣ የአሜሪካው ፕሬዝንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) በጀት እንዲቋረጥ መወሰናቸውን አወደሰ።የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) እና ራድዮ ፍሪ እስያ (አርኤፍኤ) በቻይና መንግሥት ዙሪያ ለዓመታት ሲዘግቡ የቆዩ ሲሆን ትራምፕ የጣቢያዎቹ በጀት እንዲቀነስ ወስነዋል።ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው አርብ ነው። 1300 የቪኦኤ ሠራተኞች በግዴታ እረፍት እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።ተቺዎች ውሳኔው ዲሞክራሲን ወደኋላ የሚጎትት ነው ቢሉም ግሎባል ታይምስ...
    Mar-18 - 2025 | More »
  • Killings, abductions, funding shortfalls stifle WFP relief efforts across Ethiopia!
     Killings, abductions, funding shortfalls stifle WFP relief efforts across Ethiopia!Eight personnel dead as org. takes USD 30mln loan to sustain operationsThe World Food Program says security concerns are straining its ability to deliver crucial aid assistance in Ethiopia as no less than eight...
    Sept-15 - 2024 | More »
  • Ethiopia : Dialogue Commission wants gov’t to create “enabling condition
     Professor Mesfin Araya, Chief of the Dialogue Commission (Photo credit : DW Amharic)The National Dialogue Commission on Thursday presented its performance report to the parliament. Unusual about it was that this meeting took place in a hotel, not at the parliament building. The practice...
    June-30 - 2024 | More »
  • Struggles of High-Rise Living
     Located on the western outskirts of AddisAbaba, the Asko 40/60 condominium towers stand tall, promising a modern lifestyle but delivering a daily ordeal for its residents. Among them is Melat Kasa, a pregnant mother of two young children aged 4 and 6, who lives on the 13th floor. “I’ve been...
    June-30 - 2024 | More »
  • TPLF regains political legitimacy with Justice Ministry’s blessing
     NewsTPLF regains political legitimacy with Justice Ministry’s blessingThe Ministry of Justice has granted the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) the green light to register with the National Election Board of Ethiopia (NEBE) as a political party.Heads of the NEBE were informed of the...
    June-29 - 2024 | More »
  • A father who lost 2 sons in a Boeing Max crash waits to hear if the US will prosecute the company
     Ike Riffel fears that instead of putting Boeing on trial, the government will offer the company another shot at corporate probationPhoto by: Jim Young/APProtesters hold photographs of victims of the 2019 Boeing Ethiopian Airlines crash, including Melvin Riffel, left.By: AP via Scripps...
    June-29 - 2024 | More »
  • Ethiopia’s dam fills threaten Egypt’s lifeline: Calls for international intervention
     Adel Sadawi, a member of the Egyptian Council for Foreign Affairs and former Dean of the Institute for Research and Strategic Studies on Nile Basin Countries, commented on Ethiopia’s announcement of its readiness to carry out the fifth filling of the Grand Ethiopian Renaissance...
    June-29 - 2024 | More »
  • Fashion event brings Kanu, others to Ethiopia
     Former Nigerian national football team striker Nwankwo Kanu and other African former football players are in Addis Ababa to participate in the Shenen Africa Fashion Festival Week 2024Upon arrival at the Addis Ababa Bole International Airport, on Thursday Kanu was welcomed by Ethiopia’s...
    June-29 - 2024 | More »
  • Economic, conflict spurring human trafficking in Ethiopia: US State Department
     NewsEconomic, conflict spurring human trafficking in Ethiopia: US State DepartmentYemeni Houthis forcing Ethiopian migrants into military serviceThe US Department of State commends the Ethiopian government’s efforts to combat human trafficking but urges that more needs to be done to eliminate...
    June-29 - 2024 | More »

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time