Saturday, September 3, 2016

የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በመቻቻልና ንግግር እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ


የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ኒኮሳዛና ላሚኒ ዙማ ባለፉት ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉትን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ደላሚና ዙማ
በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የእርሻ መሬት ለልማት ከተመደበበት ዕቅዶች በተያያዘ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መከሰታቸውን ተከትሎ የብዙ ሰው ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል ያለው የአፍሪካው ህብረት መግለጫ የመንግስትና የግል የንግድ ሥራዎች አልፎ አልፎም የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች የተቋረጡበት ሁኔታ መፈጠሩን አመልክቷል።
የህብረቱ ሊቀ-መንበር ዙማ ለሞቱት ሰዎች ቤተሰቦች ሃዘናቸውን በመግለጽ የቆሰሉትም በቶሎ ጤናቸውን እንዲያገኙ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ለተቃውሞዎቹ መነሾ የሆኑት ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ሰላማዊ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት እንዲቻል የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ እንዲነጋገሩ የተማጸኑት ዙማ በሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ ቁጥብነትና መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ አድርገዋል።
አያይዘውም የአፍሪካ ህብረት ለዲሞክራሲ ባህልና መርሆች ወሳኝ የሆኑት የህግ የበላይነት እና በሰላማዊ መንገድ የመሰለፍ መብት እንዲከበር የሚደግፍ መሆኑን የህብረቱ ሊቀመንበር አረጋግጠዋል። Read more here

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time