በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ውጥረት መቀጠሉን ክልሉ በወታደሮች ቁጥጥር ሥር መዋሉንና፣ ከሰኞ ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ ምን ያህል የሰው ሕይወት እንደጠፋ ፣ ምን ያህል እንደቆሰለ ፣ምን ያህል እንደታሰረ ፣ ምን ያህል ንብረት እንደወደመ የተጣራ መረጃ ለማግኘት ሁኔታዎች ዝግ እንደሆኑበት መኢአድ አስታውቋል።
ዋሽንግተን —
አረና ትግራይ በበኩሉ የትግራይ ሕዝብ ያለበትን ሁኔታ ባለመረዳት በአማራ ክልልና በኦሮሚያ እየተገደሉ ለሚገኙ ወገኖች አጋር አላሳያችሁም በሚል የትግራይ ተወላጆች ላይ ጫና ማሳደር ንብረት ማቃጣል እና ማሰደድ እንዳለ ሕዝብ ግንኙነቱ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል በወገራ፣ በመተማ፣ በደባርቅ የሚገኙ ነዋሪዎች ውጥረቱ መቀጠሉን እና ሰዎች እየተገደሉ መሆኑን ይናገራሉ።
የአማራ ክልል መንግሥት ነገሮችን ለማረጋጋት ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
በጎንደር የሚገኙ የሃይማኖት አባት ዛሬ ፤ በጎንደር የተደረገው ውይይት ባለመግባባት የተበተነ መሆኑን ልጆቻችን እየተገደሉ ነገር ተረጋግቷል እንድንል እየተጠየቅን ነው ይላሉ።
የተለያዩ ወገኖችን በማናገር የተጠናከረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ። Read more here
No comments:
Post a Comment