Monday, May 30, 2016

ፈተናው የወጣው በኦሮሞ ልጆች ወይስ በከፍተኛ ባለስልጣናት ልጆች ?


የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና  መቋረጡን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ:፡

ከሰኞ አስከ ሐሙስ ሊሰጥ የነበረው የ12 ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እንዲቋረጥ የተደረገው የእንግሊዝኛ እና ማትስ ፈተናዎች መውጣቱ ስለተረጋገጠ እና ቀድሞ በኢተርኔት በመሰራጨቱ ነው ።ያሁኑ መግለጫ ከመሰጠቱ በፊት ትምህርት ሚንስትር ከተማሪዎች እና ከህብረተሰቡ በተነሱ ፈተናው ወቷል በሚለው ሹክሹክታ ላይ ፈተናው እንዳልወጣ እና ተማሪዎች በተረጋጋ መፈስ ፈተናውን እዲፈተኑ መገለጫ አውጥቶ ነበር።

 ፈተናው እሁድ ማታ በፌስቡክ እንደተሰራጨ እና የተለያዩ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የፈተናውን ቡከሌት እስከ መልሶቻቸው ለጓደኞቻቸው ሲጋሩ ታይተዋል። ፈተናው እንዴት ወጣ ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ መላምቶች ሲኖሩ ነገር ግን ጁሀር መሐመድ የሚባል በቡዙ ሽህ የሚቆጠር የፌስቡክ ተከታዮች ያሉት አንድ ሰው  እንዳለው አንድ በተበሳጨ የኦሮሞ ፈተና አስተባባሪ አማካኝነት ነው ይላል። ጁሀር ለመጀመሪያ ግዜ እስካን የተደረገውን ፈተና ፖስት ሲደረግ ባለፈው በኦሮሞ ተማሪዎቹ በተነሣው ተቃውሞ ምክንያት ተማሪዎች በደንብ እዳልተዘጋጁ እና መንግሥት ፈተናውን እዲያራዝምላቸው ጥያቄ ጠይቀው  መንግሥት አይቻልም በማለቱ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል ደም አንዳንድ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ፈተናው የወጣው የክፍተኛ ባለሥልጣናትን ልጆች ለመጥቀም ነው ይላሉ ። ነገር ግን ፈተናው ባልታወቀ ምክንያት አፈትልኮ ከልጆች እጅ ወቷል ብለዋል ።

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time