Saturday, May 25, 2013
ፍቅር
ፍቅር፣ ፍቅር፣
አቤት ሲያመናቅር፤
ምንቅር፣ ምንቅር፣
ምንቅርቅርቅርቅር፤
ደንገጥ፣ ደንገጥ፣
ፈራ፣ ተባ ሲል፤
ወይኔ ታየ
የልቡ መዝለል፤
እፍር፣ እፍር፣
እፍርፍር እሷም፤
እይዋት ቆንጂት
ስትሽኮረመም፤
ኮስተር፣ ኮስተር፣
አቤት ኮስተርተር፤
ፈካ፣ በራ፣
ትንፋሽ እጥርጥር፤
ሰከን፣ ሰከን፣
ሰከንከንከንከን፤
አቤት ለሱ
ያላት ሰቀቀን፤
እዩት፣ እዩት፣
አፉ ሲታሰር፤
ኮልተፍ፣ ኮልተፍ፣
ወይ መቀባጠር፤
ደንበር፣ ደንበር፣
ደንበርበርበርበር፤
እይዋት ውቢት
ስትደናበር፤
ማፍቀር፣ ማፍቀር፣
በስሜት መስከር፤
ለልብ ህመም፣
ትርምስ መፍጠር፤
አዲስ ማዕበል፣
አዲስ ውዥንብር፣
አዲስ ቀውጢ፣
የፎንቃ ነገር፤
ውድድ፣ ውድድ፣
ልጅቷን ውድድ፤
በፍቅሯ ምክንያት
እብድ፣ እብድብድ፤
ውድድ፣ ውድድ፣
ልጅቷ ውድድ፤
ልጁን ስታይ
ረሳች መራመድ፤
አቤት ደስታ፣
አቤት ፍስሐ፤
ኧረ በለው፣
የምን ንስሐ?!
ፍቅር፣ ፍቅር፣
ፍቅር ነፃነት፤
ለተፋቀሩ
ደስ የሚል ሂወት፤
ፍቅር ፣ ፍቅር፣
የኔዋ ፍቅር፤
ነይ፣ ነይ፣ ኮቱ፣
የኔ ምንታምር፤
ፍቅር፣ ፍቅር፣
የኔ አፋሪ፤
ፈታዊተይ
የኔ ፊዮሪ!
***
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Recent Articles
Recent Video Uploads
Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube
Ethiopia Today
- Active a minute ago with many
- videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies, Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time
No comments:
Post a Comment