የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ባሳለፍነው ሳምንት 14 ሰዎች መግደሉን ተከትሎ አምንስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ አወጣ። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራክረው አምንስቲ ኢንተርናሽናል የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ካልታገደ በሰዎች ላይ የሚደርሰው ግፍና ሰቆቃ ማቋረጫ የለውም ብሏል። የሶማሌ ልዩ ፖሊስ በጭናቅሰን ወረዳ በፈጸመው ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አረጋግጧል። ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚል በሶማሌ ክልል የተቋቋመው ልዩ ፖሊስ እርሱ ራሱ ሰዎችን አሸባሪ ከሆነ ሰነባብቷል። የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ከተቋቋመ ወዲህ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው ነው የሚነገረው። በተለይ ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በተፈጠረ የአዋሳኝ ድንበር ግጭት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሲሰደዱ ብዙዎቹም ተገድለዋል፤ የአካል ጉዳትም ደርሶባቸዋል። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት የከራካሪ ዓምንስቲ ኢንተርናሽናል ታድያ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ካልታገደ በስተቀር ግድያው ሊቆም እንደማይችል ሲያስጠነቅቅ ነበር። እንዳለውም አልቀረ በሰሞኑ ብቻ በጭናቅሰን ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች በሶማሌ ልዩ ሃይል በተፈጸመ ጥቃት 14 ሰዎች ተገድለዋል ነው ያለው። ቆቦ ቢካ፣ ኡላን ኡላ እና ዋሌንሱ በተባሉት ሶስት አካባቢዎች ብቻ 3 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል። ዳርቢጋ እና ጎሎቻ በተባሉ ሌሎች ሁለት አካባቢዎችም 7 ሰዎች ተገድለው ተጨማሪ 17 ሰዎችም እንደቆሰሉም ነው የተነገረው። እናም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ደጋግሞ እንደገለጸው የሶማሌ ልዩ ሃይል በመንግስት እንደፈረሰ ካልተደረገ ሰቆቃውና ግፍ ይቀጥላል ሲል አስጠንቅቋል። የአምንስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ እና የታላላቅ ሃይቆች ዳይሬክተር ጁምን ኒያንዮኪ እንዳሉት በሶማሌ ልዩ ፖሊስ በሚፈጸመው ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱ ካልቆመ ችግሩ አሳሳቢ መሆኑ ይቀጥላል። ስለሆነም መፍትሄው የሶማሌ ልዩ ሃይልን ማገዱና ለማፍረስ ብቻ ነው ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል
Tuesday, June 12, 2018
ህልም ሁኖ የቀረው የሁለቱን ብሔር የማጋጨት አላማ - ታዬ ደንደኣ
ባለፈዉ ዓመት ኢሉ አባቦር ላይ በኦሮሞ እና በአማራ መሀከል ግጭት ተቀስቅሶ ነበር። ያ ግጭት ግብ ነበረዉ። ግቡ በሁለቱ ታላላቅ የኢትዮጵያ ብሔሮች መሀከል የነበረዉን ምናባዊ መጠራጠር ይበልጥ በማጠናከር በኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ እና ባርነት መበልፀግ ነዉ። ግን ህልም ሆኖ ቀርቷል። ግጭቱ ኦሮማራን ወልዶ የሴራኞችን ጉልበት እንዳልነበረ አድርጓል። ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሩ ተስፋ ማየት እንደ ጀመረ ለማሳየት ምስክር መጥራት አያስፈልግም።
ዛሬም ሴራኞች አልተኙም። የተሸነፉበትን ስልታዊ ቦታ ስለሚያዉቁ በአሮሞ እና በአማራ መሀከል ጥርጣሬ ለመፍጠር የሞት ሽረት ትግል ላይ ናቸዉ። በራሳቸዉ ባጀት መድበዉ ትንሽ ችግር ከፈጠሩ በኀላ ነገሩን ከሚገባዉ በላይ በሚዲያ ያራግባሉ። ኦሮሞ አማራን አፈናቀለ እያሉ የአዞ እምባ እያነቡ “ኦሮማራ ፈርሷል!” እያሉ ይጮሀሉ። ግን ከንቱ ልፋት ነዉ። ኦሮማራ ፈፅሞ አይፈርስም። ሌሎች ብሔሮችን ጨምሮ በማቀፍ የኢትዮጵያን አንድነት ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካን አንድነት በማይነቃነቅ መሠረት ላይ የገነባል!
ነገሮች ግልፅ መሆን አለባቸዉ። በኦሮሚያ ክልል ማንንም የማፈናቀል ፖሊሲ የለም። አላማችን ሁሉንም ብሔሮች አቅፈን በፍቅር እና በትብብር ለዘመናት የተንሰራፋዉን ሰቆቃ ከክልላችን እና ከሀገራችን ጫንቃ ላይ ማዉረድ ነዉ። በትብብር የከበደንን ሸክም ለብቻችን እንደማንወጣዉ ጠንቅቄን እናዉቃለን። ከተባበርን ደግሞ የትኛዉንም ተራራ መናድ እንደምንችል በተጨባጭ አይተናል። ስለዚህ ኦሮሚያ እንደ ክልልም ሆነ እነደ ህዝብ ሁሉንም በእኩልነት ይዞ ሀገርን ማሸገር እንጂ ወንድሞቻችንን የማግለል ህልም የለዉም። ነገር ግን ሜዳ ሁሉ ወለል አይደለም። እዝያም እዝህም ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ግጭት በስጋ ወንድሞች መሀከልም ይከሰታል። ችግሩ ግጭቶችን የሚናይበት መነፅር ነዉ። ቶሎሣ እና ገመቹ ወይም ኩራባቸዉ እና ወርቁ ቢገዳደሉ ነገሩ ምንም ነዉ። ነገር ግን ገመቹ እና ኩራባቸዉ ትንሽ ቢጋጩ ጉዳዪ ይከራል። ይህ እጅግ አደገኛ ነዉ። በዝህ ላይ የጠላት ሴራ አለ።
ይህን ችግር ለመፍታት መስራት ያስፈልጋል። የመጀመሪያዉ ስራ መነፅሩን ማስተካከል ነዉ። የግለሰቦች ጉዳይ እንደ ጠቅላላ ህዝብ መታየት የለበትም። ሚዲያዎቻችን በዝህ ጉዳይ ላይ ስልጡን መሆን አለባቸዉ።
ሁለተኛዉ የራስን ፖሊሲ ግልፅ ማድረግ ነዉ። ክልላችን በኦሮሚያ የሚኖሩ ብሔር-ብሔረሰቦችን ከኦሮሞ ለይቶ አይመለከትም። ይህን የሚያደረገዉ ከምንም በላይ ለኦሮሞ ህዝብ ዘላቂ ጥቅም በማሰብ ነዉ። በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ኦሮሞዎች በነፃነት ተከብረዉ ይኖሩ ዘንድ በኦሮሚያ የሚኖሩ ብሔሮች መከበር አለባቸዉ። ከላከበሩ መከበር እንደማይኖር ይታወቃል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ወንድሞቹን አቅፎ በፍቅር አብሮ መኖር የኦሮሞ ህዝብ መሠረታዊ ባህል ነዉ። ስለዝህ በክልላችን በሚኖር የትኛዉም ብሔር ላይ ጥቃት የሚፈፅም ግለሰብ ወይም ቡድን የኦሮሞ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነዉ። ይህ የክልሉ እና ክልሉን የሚመራዉ ድርጅት ግልፅ አቋም ነዉ።
ግን ነገሮች መልክ መያዝ አለባቸዉ። የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። አማራ ክልል የሚኖር ኦሮሞ የክልሉን ህግና ደንብ ማክበር አለበት። ህግ ከጣሰ ተጠያቂ ነዉ። ጥፋቱን በብሔር ካባ መሸፈን የለበትም። ለሱ ብቻ የሚወጣ ልዪ ህግ የለም። የአማራ ክልል ግዴታ ባለዉ ህግ ሁሉንም እኩል ማስተናገድ ብቻ ነዉ። በአዳማ ወይም በአምቦ የሚኖር አማራም እንደዚሁ ነዉ። የኦሮሚያን ህግ እና ደንብ አክብሮ መኖር አለበት። ካላከበረ ይጠየቃል። በዝህ ላይ ድርድር የለም። የእኩልነት እንጂ የተለየ መብት አንሰጥም። ለእኛም እንድሰጠን አንፈልግም። ግልፅ መነጋገር ያስፈልጋል።
Monday, June 11, 2018
የለውጥ መሪው ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ-በዓለም አቀፉ ዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት እይታ
የለውጥ መሪው ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ-በዓለም አቀፉ ዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት እይታ። የለውጥ መሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዓለም አቀፉ ዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት እይታ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ በተሰኘው አምዱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን በተመለከተ እና በአጭር ጊዜያት ውስጥ ስላከናወኗቸው ተግባራት ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዞ ወጥቷል፡፡
እንደ መጽሄቱ ትንታኔ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከወራት በፊት ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መጥተዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት እና ህዝባዊ ተቃውሞች እንዲሁም ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በሰፈነበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ በመያዛቸው በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ እንዳልታመነ ዘ ኢኮኖሚኒስት አትቷል፡፡
ሆኖም በሹመት በአላቸው ለሀገራዊ አንድነት ጥሪ ማቅረባቸው እና በተቃውሞ ሰልፍ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎችን አስመልክቶ ይቅርታ መጠየቃቸው ግርምትና አድናቆትን አጭሯል፡፡
በቀጣይም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመዘዋወር ብዙ ህዝብ በተገኘባቸው መድረኮች የትውውቅ ንግግሮችን እና ውይይቶችን አካሂደዋል፡፡ ከህዝቡ ጋር በአንድነት ለመስራት እንደሚፈልጉም ገልፀው ነበር ይላል የዘኢኮኖሚስት ትንታኔ፡፡
በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሀገር የተባረሩ ተቃዋሚዎች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ እና በውጪ ሀገራት የሚገኙ እና በተቃዋሚነት የተፈረጁ መገናኛ ብዙኃን በአዲስ አበባ ማዕከላቸውን እንዲከፍቱ ጥሪ ቀርቧል፡፡
አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ሌሎች አያሌ የፖለቲካ እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ በነፃ ተለቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህገ-መንግስቱን በማሻሻል የስልጣን ዘመንን ገደብ ለማበጀት ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ካቢኔያቸው በወሰነው መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ተነስቷል፡፡ በድንበር ውዝግብ ከኤርትራ ጋር ተፈጥሮ የቆየውን ውጥረት ለመፍታት እና ኢትዮጵያን የወደብ ተጠቃሚ ለማድረግ የአልጀርሱን ስምምነት እንደሚቀበል ካቢኔያቸው ይፋ ማድረጉን ዘኢኮኖሚስት አስፍሯል፡፡
የአልጀርሱ ውሳኔ በብዙ ዜጎች ዘንድ ጥርጣሬ እና ተቃውሞ ማስነሳቱንም ጠቅሷል፡፡ በስራ ተወጥረው የቆዩት ዶ/ር አብይ ችግር ላይ ለወደቀው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብዙም ትኩረት የሰጡት አይመስልም ነበር ይላል ዘገባው፡፡
ሆኖም በመንግስት ሙሉ ቁጥጥር ስር የቆዩ ቁልፍ የመሰረተ ልማት ፣ ባንክ፣ ባቡር፣ ቴሌኮም፣ እና የበረራ ዘርፎችን ለግሉ ዘርፍ በሙሉ እና በከፊል በማዘዋወር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚያጠናክሩ መናገራቸው ለኢኮኖሚው ዘርፍ ትኩረት መስጠታቸውን ያሳያል፡፡
ከጥቂት ወራ በፊት ሚኒስትሩ ከባለ ሀብቶች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኙ ዘርፎች ከመንግስት እጅ እንደማይወጡ በመግለጻቸዉ የአሁኑ ውሳኔ ግርምትን ፈጥሯል ብሎም ኢኮኖሚክ ሊብራል ወይም የነፃ ኢኮኖሚ ርዬተ-ዓለም ተከታይ ናቸው የሚል እምነትን አሳድሯል ይላል የዘ ኢኮኖሚስት ዘገባ፡፡
ዘኢኮኖሚስት በትንታኔው እንዳሰፈረዉ መንግስት አነዚህን ውሳኔዎች ያሳለፈው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አንጻራዊ በሆነ መልኩ መዳከም በማሳየቱ ነው፡፡ ባለፉት አስር አመታት የሀገሪቱ አጠቃላይ አመታዊ እድገት በአማካኝ 10 በመቶ የነበረ ሲሆን በያዝነው አመት ከ2 በመቶ በላይ ቅናሽ እንደሚኖረው የዓለም የገንዘብ ድርጅትን (IMF) ዋቢ አድርጎ ትንታኔውን አስቀምጧል፡፡
የውጪ ምንዛሬ እጥረት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ መጉዳቱን እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እቃዎች እጥረት ማጋጠሙን ጠቅሶ በዚህ ሳቢያ የዋጋ ውድነቱ በ 15 በመቶ ማሻቀቡን ጠቁሟል፡፡
መንግስት ያሳለፋቸዉ ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎች ለኢኮኖሚያዊ ለውጥ ትኩረት መስጠቱን አመላካች ቢሆኑም ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በጥልቅ ካልተሰራ የባለቤትነት ለውጥ ብቻ እንደሚሆን እና ለሙስና የተጋለጠ አሰራርን ሊፈጥር እንደሚችል የኢኮኖሚ ምሁራንን ጠቅሶ ዘኢኮኖሚስት አስፍሯል፡፡
ይሁንና ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸዉ ከወራት በፊት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በአልጀርሱ ስምምነት እና በተወሰኑት ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ዙሪያ ዉይይት ሲያካሂድ መቆየቱን ብሎም ዉሳኔዉ ቀደም ብሎ የታሰበ እንደነበር አንድ ኢትዮጵያዊ ተንታኝ መግለጹን አስፍሮ ትንታኔዉን ደምድሟል፡፡ በቢኒያም መስፍን
ምንጭ፡- ዘ ኢኮኖሚስት
Sunday, June 10, 2018
የዐማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ
የዐማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ፡ለሁለት ቀናት በባሕር ዳር ከተማ በሙሉዓለም የባህል ማዕከል ሲካሄድ የነበረው የዐማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) መስራች ጉባኤ ተጠናቋል።
‹‹አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፤ ሁሉም ዐማራ ለአንድ ዐማራ›› የሚል መርህ ያለው ድርጅቱ በሁለት ቀን ቆይታው የድርጅቱን ሊቀመንበርና የውስጠ ድርጅት ተግባራትን ከአባላትና ደጋፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
ዐብን በመሥራች ጉባኤው ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን ሊቀመንበር ፣ አቶ በለጠ ሞላን ደግሞ ም/ሊቀመንበርና የድርጅቱ የምርጫ ጉዳይ ሃላፊ አድርጎ መርጧል፡፡ በተጨማሪም ንቅናቂው የስራ አስፈፃሚ አባላትና የምክር ቤት አባላትን ሰይሟል ።
በሁለተኛው ቀን ውሎ ከአባላት እና ደጋፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል ። በምስረታው የተገኙ አባላትም የአማራ ምሁራን በባለፉት ዓመታት በፍርሀት ሁነው የአማራውን መብትና ተጠቃሚነት እንዲከበር ባለመስራታችው ድርጅቱ በምሁራን እንዲዋቀር መነሻ ሆኗል ብለዋል ።
የአማራው እንደብሔር መደራጀት በአማራው ላይ በባለፉት ጊዚያት ሲፈጠሩ የነበሩ የፓለቲካና የዘር ጥቃቶችን ለስማቆም ከሌሎች ህዝቦች እና ድርጅቶች ጋር አብሮ ይሰራልም ተብሏል ።
የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በምስረታው እለት በሰጡት መግለጫ ከባለፉት 50 ዓመታት ወዲህ የአማራው ህዝብ ህልውና ወድቆ ነበር ። በ1960ዎቹ የተፈጠረው የተማሪዎች አብዮት አማራውን የበላይ አድርጎ ሌሎችን ተጨቋኝ አድርጎ አማራውን የማሳደድ እና በትጥቅ ትግሎች ጣት እንዲቀሰርበት ተደርጓል ። በዚህም አማራው ከፍተኛ መሰደድና ጭቆና እንዲሁም የፓለቲካ የበላይነት ተወስዶበታል ብለዋል።
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የዐማራ ብሔር ንቅናቄም ለዘብተኛ ሊብራሊዝምን በመጠቀም የዐማራን ህዝብ ታሪክ ባህልና ትውፊት ተከብሮ በምጣኔ ሃብት ደረጃ ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተጠቃሚ ማድረግ ነው ። በቀጣይ ፓርቲው ዲሞክራስያዊ በሆነ መንገድ ህገ መንግስታዊ ለውጦች እንዲኖሩ፤ የአማራ ህዝብ የጸረ ጭቆናና የልማት ተጠቃሚነቶች እንዲረጋገጡ በክልሉና በሃገራዊ መድረኮች ተሳታፊ ይሆናል ብለዋል ።
ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ
Friday, June 8, 2018
At least 20 Amharas had been killed in these attacks by April 2018
“The Ethiopian government must take action to prevent these brutal attacks on the Amhara community, who have been targeted due to their ethnicity and now face being made homeless,” said Joan Nyanyuki, Amnesty International’s Director for East Africa, the Horn and the Great Lakes. An estimated 1,400 Amhara families remain in the besieged Siyo District, but residents told Amnesty International they would soon be forced to flee their homes of more than three decades after being repeatedly targeted by the Qerro and Folle Oromo youth groups. Frustrated Amhara villager
“It is no longer tenable to continue living here; we are afraid for the lives of our children. We have packed our belongings and are ready to run away unless the government intervenes,” one villager told Amnesty International. He added that, despite the community filing numerous reports and complaints to District and Zonal authorities in Oromia State about the ongoing attacks, the authorities had not addressed the violence. The attacks on Amharas living in Qellem Wollega and Illu-Ababora Zones of Oromia Regional State begun in October 2017. Also affected are Amharas in Shinasha Zone of Beninshangul Regional State. At least 20 Amharas had been killed in these attacks by April 2018. Joan Nyanyuki, Amnesty International Director for East Africa, the Horn and the Great Lakes
Thousands have fled to Bahir Dar, the capital of the neighbouring Amhara Regional State, but some have been forced to live on the streets due to a lack of proper accommodation facilities for displaced people. “Every citizen has the right to choose where they want to establish their homes, and no one should be allowed to restrict this freedom on the basis of ethnicity,” said Joan Nyanyuki. “Ethiopia’s new government has been making great strides to improve human rights in the country, but the pattern of ethnically motivated violent attacks and displacement is being shamefully ignored. They must be protected from further attacks, and those already displaced must be provided with adequate alternative accommodation.”
Background.These ethnically motivated attacks in Ethiopia have caused the displacement of more than 200,000 people from the West Guji Zone of Oromia Regional State and Gedeo Zone of Southern Nations, Nationalities and Peoples (SNNPR) Regional State, according to UN data. At least another 20 people were killed in the violence between the Gedeo and Guji communities.
Amnesty International is monitoring and documenting the impacts of these ethnically motivated attacks in other parts of Oromia, and the country in general.
Source: Amnesty International
Recent Articles
Recent Video Uploads
Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube
Ethiopia Today
- Active a minute ago with many
- videos