Sunday, August 5, 2018

ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ። ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነች አንስታል።
ለውጡም መላ የኢትየጵያ ህዝቦችን ባሳተፈ እና ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል ያለው ሚኒስቴሩ፥ እየተካሄደ ካለው የለውጥ እንቅስቃሴም መላው የሀገሪቱ ህዝቦች ተጠቃሚ በመሆናቸው ተሳትፏቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ ብሏል።
ሆኖም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች አልፎ አልፎ የብጥብጥና የሁከት ድርጊቶች እንደሚስተዋሉ አስታውቋል።
እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች በሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ሃይሉ ከህዝቡ ጋር ሆኖ የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ነው የገለፀው።
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ፣ ቀጥሎም ወደ ሌሎች አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በፍጥነት ሊገታ እና ሊታረም የሚገባው ድርጊት መሆኑን አስታውቋል።
የአገር መከላከያ ሠራዊታችን ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የተከሰተውን ሁከት በቅርበት ሲከታተል፣ ሁኔታውን ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም ብጥብጡ በተፈለገው ፍጥነት ሊቆም አልቻለም ብሏል።
በመሆኑም በክልሉ የህዝቦቻችን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ውስጥ እየገባ ያለበት ሁኔታ በመፈጠሩ የመከላከያ ሃይላችን ሁከትና ብጥብጡን በዝምታ የማይመለከት መሆኑንና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ እንደሚያሳስብ ነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫው ያስታወቀው።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል
ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ
አገራችን ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነች ይታወቃል። ለውጡም መላ የኢትየጵያ ህዝቦችን ባሳተፈ እና ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል። እየተካሄደ ካለው የለውጥ እንቅስቃሴም መላው የአገራችን ህዝቦች ተጠቃሚ በመሆናቸው ተሳትፏቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ።
ሆኖም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች አልፎ አልፎ የብጥብጥና የሁከት ድርጊቶች ይስተዋላሉ። እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች በሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ሃይሉ ከህዝቡ ጋር ሆኖ የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ፣ ቀጥሎም ወደ ሌሎች አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በፍጥነት ሊገታ እና ሊታረም የሚገባው ድርጊት ነው።
የአገር መከላከያ ሠራዊታችን ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የተከሰተውን ሁከት በቅርበት ሲከታተል፣ ሁኔታውን ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም ብጥብጡ በተፈለገው ፍጥነት ሊቆም አልቻለም።
በመሆኑም በክልሉ የህዝቦቻችን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ውስጥ እየገባ ያለበት ሁኔታ በመፈጠሩ የመከላከያ ሃይላችን ሁከትና ብጥብጡን በዝምታ የማይመለከት መሆኑንና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር
ሃምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም.

የሶማሌ ክልል ከኢትዮጵያ ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው

የሶማሌ ክልል (ክልል 5) ከኢትዮጵያ ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። ዋና ከተማው ጅጅጋ ነው። 279,252 ካሬ ኪ.ሜ. ቦታ ሲሸፍን በ1991 የሕዝብ ብዛቱ 3,602,000 ነበር። ባሁኑ ስአት የሕዝብ ብዛት በአጠቃላይ 5,148,989 በላይ ተብሎ ይገመታል። ክልሉ በጣም ብዙ የሶማሌ ብሔረሰቦች ይገኙበታል። በ1970ዎቹ እ.ኤ.አ. ሶማሊያ ቦታውን በወውረር ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት አስነስታ ነበር። ከነዚህም ዋነኛው የኦጋዴን ጦርነት ነው። ርዕሰ ከተማ ጅጅጋ ሲሆን ጅጅጋ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኝ ከተማ ነው። ከተማው ከሐረር 80 ኪ.ሜ. ይርቃል። በቀድሞው ሐረርጌ ክፍለ-ሀገር የሚገኝ ከተማ ሲሆን አሁን የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ነው። በ1994 እ.ኤ.አ. ከተማው 56,821 ሰዎች ነበሩት። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲችስ ባለስልጣን እንደተመነው ጅጅጋ የ98,076 ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም 50,355 ወንዶችና 47,721 ሴቶች ይገኙበታል። ከተማው በ9°10' ሰሜን ኬክሮስ እና 42°48' ምስራቅ ኬክሮስ ይገኛል። የሶማሌ ፕሬዚዳንት ሞሐሙድ አብዲ ኦማር («አብዲ ኢለይ») ይባላሉ። በክልሉ የሱማሌ ብሔር ሲገኙ የሶማሌ ብሔር ከኢትዮጵያ ሱማሎ ውጭም በአፍሪካ ቀንድ ይገኛሉ። ሱማሊኛ ቋንቋቸው ነው። ጠቅላላ ብዛታቸው ከ10 እስከ 20 ሚሊዮን የሚገመት ሲሆን እነዚህም በሶማሊያ (ከ8 ሚሊዮን በላይ)፣ ኢትዮጵያ ሱማሌ (ከ3 እስከ 5 ሚሊዮን)፣ ጅቡቲ (250,000)፣ ሰሜን-ምስራቅ ኬንያ (240,000)፣ እና በሌሎች ውጭ ሀገሮች ይገኛሉ። ዋና ሃይማኖታቸው ሱኒ እስልምና ነው።

ሶማልኛ ቋንቋ ኩሺቲክ ተብሎ በሚታወቀው የቋንቋ መደብ የአፍሮ-እስያ ቤተሰብ የሚካለል ቋንቋ ነው። በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙ አገሮች፥ በኢትዮጵያ ፥ ጅቡቲ፥ ሶማሌና ኬንያ፥ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተናጋሪዎች አሉት። በ1964፥ በዚአድ ባሬ መንግስት አነሳሽነት፥ ለመጀመሪያ ጊዜ በ ላቲን ፊደል መጻፍ ጀመረ።

Saturday, August 4, 2018

በጂግጂጋና ሌሎች የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በፍጥነት ሊገታ ይገባል:- ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ ሌሎች አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በፍጥነት ሊገታ እና ሊታረም የሚገባው መሆኑን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

መከላከያ ሠራዊቱ ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የተከሰተውን ሁከት በቅርበት ሲከታተልና ሁኔታውን ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን ለማረጋጋት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጅ እንደሚወስድ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ከመንግስት ኮሙኒከረሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ደርሶናል እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነች ይታወቃል።
ለውጡም መላ የኢትየጵያ ህዝቦችን ባሳተፈ እና ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል።
እየተካሄደ ካለው የለውጥ እንቅስቃሴም መላው የአገራችን ህዝባችን ተጠቃሚ በመሆናቸው ተሳትፏቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ።

ሆኖም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች አልፎ አልፎ የብጥብጥና የሁከት ድርጊቶች ይስተዋላሉ።
እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች በሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ሃይሉ ከህዝቡ ጋር ሆኖ የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ፣ ቀጥሎም ወደ ሌሎች አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በፍጥነት ሊገታ እና ሊታረም የሚገባው ድርጊት ነው።

የአገር መከላከያ ሠራዊታችን ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የተከሰተውን ሁከት በቅርበት ሲከታተልና ሁኔታውን ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም ብጥብጡ በተፈለገው ፍጥነት ሊቆም አልቻለም።

በመሆኑም በክልሉ የሚኖሩ ህዝቦቻችን ደህንነት እና ሰላም አደጋ ውስጥ እየገባ ያለበት ሁኔታ በመፈጠሩ የመከላከያ ሃይላችን ሁከትና ብጥብጡን በዝምታ የማይመለከት መሆኑንና ችግሩንም ለመቅረፍ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ ማሳሰቡን የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የአብዲ ዒሌ እብደት

የአብዲ ዒሌ እብደት

ሰበር ዜናውን ኢሳት ላይ እንዳየሁ ነው ወደዚህ የመጣሁት። የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጂጂጋ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሰራዊት እጅ ገብታለች። የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ዋና ዋና የከተማዋ ክፍሎች በፌደራሉ መንግስት ቁጥጥር ስር ገብተው ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው። ጂጂጋ ያለው ነገር ግልጽ አይደለም።
አብዲ ዒሌ እያበደ ነው። እንደሰማሁት የሶማሌ ክልልን ከእናት ሀገሩ እገነጥላለሁ ብሎ ሊያውጅ አፉን በልቶታል። ካቢኔውን ለዚሁ ጉዳይ ትላንት ምሽት እንደሰበሰበው መረጃውን አግኝቼአለሁ። የፌደራል መንግስቱ ቁንጥጫ ሲጠነክርበትና ህዝቡም አይንህን ለአፈር ሲለው የፈረደበትን ''እንገነጠላለን'' ቀረርቶ እያሰማ ነው። የጡት አባቱ ጄነራል ኳርተር ያስጠናው አንድ ነገር ቢኖር ይህቺው አንቀጽ 39 ናት። አርጩሜ በቀመሰ ቁጥር የሚመዛት የተለመደች ዲስኩር። ለአብዲ ዒሌ ህግ ከቃል ያለፈ ትርጉም የለውም። አንቀጽ 39ኝን እየጠቀሰ ማስፈራራት ለዘመናት የተጠቀመው ስትራቴጂ ነው። ዘንድሮም አልቀቀም።
አብዲ ዒሌ አፍንጫው ስር የሚያሸተው ውድቀቱ ደም እንዳስከረው ውሻ እያቅበዘበዘው ነው። የሶማሌ ኢትዮጵያውያንን ሰብዓዊ ጋሻ በማድረግ የአብይን አስተዳደር ለማስጨነቅ መዘጋጀቱን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት። ትላንት ምሽት የሰበሰበው ካቢኔው ምን ውሳኔ እንዳስተላለፈ ባይታወቅም የአብዲ ዒሊን ቅዥት ይቀበላል ተብሎ የሚገመት አይደለም። አዝማሚያው ያላማራቸው ዶ/ር አብይ ዛሬ መከላከያ ሰራዊቱ ጂጂጋን እንዲይዝ አድርገዋል::
አዎን!ሶማሌ ክልል ተቃውሞው አገርሽቷል። ህዝቡ ቆርጧል። የአብዲ ዒሌን አስተዳደር ፈንቅሎ ለመጣል የመጨረሻውን ምዕራፍ ተጥግቷል። አብዲ ዒሌ ህወሀት ላይ ጣቱን ከቀሰረና የቀድሞውን ደህንነት ሃላፊ ጌታቸው አሰፋ ላይ ሃጢያቱን ከደፈደፈ በኋላም ከተጣባው የመግደል አመል አልተላቀቀም። ጄል ኦጋዴንን ዘጋሁ በሚል ዕለም ዓቀፉን ማህብረሰብ ለማደናገር የሄደበት ርቀት ከእዚያ ከጂጂጋ የሚያስወጣው አልነበረም።
አብዲ ዒሌ ለዶ/ር አብይ ብርቱ ፈተና መሆኑ ሲጠበቅ ነበር:። ህወሀት ይሄን ሰው በመጠቀም የጥፋት ሚናውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ሲገለጽ ቆይቷል። በእርግጥም ያኮረፈውና መቀሌ የመሸገው የህወሀት ቡድን እጅና እግሩ ቢቆረጥም ምላስና ገንዘቡ ግን አልተነካም። ለውጡን ለመቀልበስ እንቅልፍ አጥተው ማደር ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። ከሰሜን እስከደቡብ: በምስራቅም በምዕራብ እሳት በመጫር ኢትዮጵያን የቀውስ ሀገር በማድረግ የዶ/ር አብይ መንግስት ያልተረጋጋ: ሰላም የራቀው አድርጎ ማሳየት የህወሀት የሽንፈት ፓለቲካ መገለጫ ሆኗል። በሰሜን ጎንደርም የቅማንትን ካርድ በመሳብ አደገኛ ጨዋታ ጀምራል:: በረከት ስምዖን በሰው ደም እድሜውን ለማርዘም ጭልጋ እየተመላለሰ መሆኑ ተስምቷል። ህወሀት በአንዳንድ የሀገሪቱ አከባቢዎችም ተመሳሳይ ግጭት በመፍጠር ላይ ተጠምዷል።
የአብይ አስተዳደር ከያቅጣጫው ጫና እየበረታ መጥቶበታል። እርምጃ እንዲወስዱ እየተጠየቀ ነው።ከኢንጅነር ስመኘው ግድያ በሃላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ እየገፋ የመጣውና ህግን እንዲያስከብሩ እየተደረገ ያለው ግፊት ተጠናክሯል። አፋጣኝ ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች በደህንነት መስሪያ ቤቱ መዝገብ ቤት ተከማችተው እንደሚገኙም ይነገራል። በሀገር ላይ ከፍተኛ በደልና ወንጀል የሰሩ በተለይ የህወሀት መሪዎችን ለማሰር የሚያስችል በቂ መረጃና ማስረጃ ተጠናቅሮ ማለቁ ተሰምቷል። እነዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፊርማ የሚጠብቁ ትልልቅ ጉዳዮች በቶሎ ተግባራዊ ካልተደረጉ በእሳቸው ላይ መልሶ ከመባረቅ አንስቶ ሀገሪቱን ወደ ትርምስ እንዳይከታት ስጋቱ ከአፍንጫ በር ስር የሚሰነፍጥ ሆኗል።
በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ማረጋጋቱና የበለጠ ቀውስን ከሚፈጥሩ ውሳኔዎች ለጊዜው መራቃቸውን የሚደግፉ ሰዎች አሉ። መቀሌ መሽጎ የሚያለቃቅሰው የህወሀቱ ቡድን እጅ ባልሰጠበትና የመረበሽ አቅሙ ባልሟሸሸበት: አሁንም ከጥፋት መንገዱ ላይ የቆመው የትላንቱ መንግስት የዛሬው ሽፍታ ቡድን እያለ ከበድ ያሉ እርምጃዎችን ባይወስዱ ይመረጣል የሚሉ በርክተዋል። ህወሀት ከቤተመንግስት ተባረረ እንጂ አልሞተም። ከእንግዲህ ቤተመንግስት የመግባት እድሉ የማይታሰብ ቢሆንም የጥፋት ሃይል ሆኖ ለጥቂት ጊዜያት መቀጠል የሚያስችል አቅም እንዳለው ይታወቃል።
ህወሀት አረናዎችን ከጎኑ በማሰለፍ መቀሌ ላይ እየመከረ ነው። ብዙ ሚስጢራዊ ስብሰባዎች በመካሄድ ላይ ናቸው። ወይ እንከባበር አልያም እንበታተን የሚል መፈክር ከመቀሌ ክፍ ብሎ ይታያል። ህወሀቶች እርምጃው ወደ እነሱ ከመምጣቱ በፊት ሌላው ጋ ቀውስ መፍጠርን እንደስትራቴጂ እየተጠቀሙ ነው። ጂጂጋ ጥሩ ቤንዚን ናት። ትንሽ እሳት ካየች ትቀጣጠላለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጂጂጋ ላይ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ ከሚመጣው አደጋ አንጻር ተገቢ ይመስላል። አብዲ ዒሌ የመጨረሻ ጥይቱን ሊተኩስ መዘጋጀቱን የሰሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቀድመው መከላከያ ሰራዊታቸውን አስገብተዋል። ምንም እንኳን በህገመንግስቱ የመገንጠል መብት ውስብስብና ዓመታትን በሚፈጅ ሂደት የሚከናወን ቢሆንም ህዝቡን ውዥንብር ውስጥ ለመክተትና ሰላም ለማደፍረስ በቂ ሰበብ መሆኑ አይቀርም። የህወሀት ስትራቴጂ ሰላም ማሳጣት ነው። መንግስትን መረበሽ ነው። ለውጡን ማደናቀፍ ነው። ለዚህ እንደአብዲ ዒሌ ጥሩ መሳሪያ ቢፈለግ አይገኝም።
እናም ጂጂጋ ውጥረት ውስጥ ናት። መረጃዎች በየሰዓቱ እየተቀያየሩ ነው። ሰሞኑን አብዲ ዒሌ በከፈተው መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያት በ10ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ወደ ጅቡቲ ሸሽተዋል። የአብዲ ዒሌ ጸሀይ እየጠለቀች ቢሆንም በቀላሉ እጅ አልሰጥም እያለ ነው። መቀሌ የመሸገው የህውሀት ቡድን በገንዘብና በፕሮፖጋንዳ ከአብዲ ዒሌ ጎን መሰለፉም ይነገራል። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የዛሬው እርምጃ የአብዲ ዒሌን ፍጻሜ ያቃርበው ይሆን?
Mesay Mekonnen

Friday, August 3, 2018

ተስፋ ሰጭው የሳይንስ ትግበራ -የሮኬት ሙከራ

ተስፋ ሰጭው የሳይንስ ትግበራ፡፡

‹‹የማዕከሉ ሙከራዎች ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ለመድረስ ላሰበችው እቅድ አቅም ይሆናል።››
‹‹የተማሪዎችን ፈጠራ በእውቀት እና በገንዘብ የምንደግፍበት ወቅት ነው›› የባሕርዳር ሳይንስ ማበልፀግያ ማዕከል፡፡

ሳይንስ ለችግሮች መፍትሄ ለማምጣት የምንጥርበት የእውቀት እና ክህሎት መድረሻ ነው። የሁሉም ስኬታማ ሳይንስ መነሻው ችግር ፣ ትንንሽ ሙከራዎች እና የሚያድጉ ፍላጎቶች ናቸው።
በባሕርዳር ሳይንስ ማበልፀግያ ማዕከል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ሮኪቶችን ማምጠቅ የሚቻልበትን ሳይንሳዊ ትግበራ እየሰሩ ነው።
የ11ኛ ክፍል ተማሪዎቹ ናሆም ፈረጃ እና ኑር አህመድ አባይ በውሃ ሃይል እምቅታ እና በኬሜካል የሚመጥቁ ሮኪቶችን ሰርተዋል።
የተማሪዎቹ ግኝት ከሶስት ዓመታት በላይ የወሰደ ሳይንሳዊ ግኝት ነው የሚሉት የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋየ ሽፈራው ሳይንስን መተግበር እንደተጀመረ ማሳያ ነው ይላሉ።
ዶክተር ተስፋየ እውነታው ግን ተማሪዎቹ በውሃ እምቅታና በኬሜካል ሊያመጥቁ የሚችሉ ትግበራዎችን በግሃድ ማሳየት የሚችሉበት አቅም ፈጥረዋል።
የሚሰሩት ቁሳቁስ በአከባቢው ከሚገኙት በመሆኑ የሚወነጨፈው ሮኪት ለሃገራዊ ጥቅም የሚውል አይደለም። እንደነዚህ አይነት ሙከራዎችን ግን ከትንሽ እስከ ትልቅ ችግር ለመፍታት እንዲያስችል ወደ ምርት ለማስገባት እገዛዎች ያስፈልጉናል ብለዋል።
የተማሪዎችን ፈጠራ ጥቅም ላይ ለማዋል ተጨማሪ እውቀት ማበልፀግ እና በገንዘብ የምንደግፍበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ለመድረስ ላሰበችው እቅድም አቅም የሚያጎለብቱ በመሆኑ ተማሪዎቹ የተሻለ ስልጠና እንዲያገኙ በገንዘብ እንዲደገፉ መስራት እንደሚያስፈልግ ዶክተር ተስፋየ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ






Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time