Showing posts with label Amharic. Show all posts
Showing posts with label Amharic. Show all posts

Thursday, September 21, 2017

የአማራ ገበሬ ግብር ይከፍላል የወያኔ ገበሬ ይከብርበታል

የአማራ ገበሬ ግብር ይከፍላል የወያኔ ገበሬ ይከብርበታል
====================

ሰሞኑን አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ከጎንደር ከተማ ትንሽ ኪሎ ሜትር ራቅ ብለው ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ጉብኝት ለማድረግ ወጣ ብየ ነበረ።ሆሌም እንደማደርገው ክረምቱ እዳለቀ በተለይ ደሞ በጥቅምት ወር ወጣ ብይ በአደይ አበባ ያጌጠውን ተራራ እና የገበሬውን ማሳ ማየት ያስደስተኛል። ወደሶስት ገበሬዎች ማሳ ስንዞር ውለን በስተመጨረሻ ወደ አንድ ገበሬ ቤት (ዘመድ ነው - የእናቴ ወንድም) ለማደር ሄድን። ከሁሉም ቀልቤን የሳበው ነገር ማታ የጎረቤት ሰወች ተጠራርተው ቡና እና ጠላ እየጠጡ የሚያወሩት ወሬ ነው። ሰፋ ያለው መወያያ ነጥብ የነበረው ስለ ቅማንት ማንነት ምርጫ ነበር። በግምት ወደ ስድስት የሚሆኑ ገበሬዎች እስከ ሚስቶቻቸው እና እንዳዶች እስከ ልጆቻቸው ነበሩ።እየተሳሳቁ ከሚያወሩት እንደተረዳሁት ሁለቱ ገበሬዎች አማራ ሲሆኑ ሌሎች ግን ቅማንት ናቸው። ሁለቱም አማራዎችም ሚስቶቻቸው ቅማንት እደሆኑ ነው የተረዳሁት።

ሁሉም ስለወያኔ መሰሪ ተግባር ጠንቅቀው ሚያውቁ ይመስላሉ። "መጀመሪያ አፋጀ እና አሁን ደሞ ምረጡ ይለናል" አለ አንዱ ገበሬ። "ተውው አሁን እማ ተነቅቶበታል" ሲል ሌላው መለሰለት። እንደዚህ እያሉ ብዙ ተወያዩ። ስለዚህ ወይይት በሌላ ቀን በሰፊው እመለስበታለሁ። ነገር ግን አሁን ገበሬዎች ሌላ ሲወያዩበት የነበረውን እና በጣም እረፍት የነሳኝን ነገር ላክፍላቹህ። ከመካከላቸው አንድ ገበሬ ነው ስሙን ባውቀውም ባልጠቅሰው ሚሻል ይመስለኛል። በግምት ከአንድ ስድስት አመት በፊት የተደረገ ድርጊት ነው። በሰሜን ጎንደር ከሚገኙ አርሶአደሮች የተወጣጡ 37 ገበሬዎች በዞኑ የግብርና አመራር አማካኝነት ትግራይ ክልል የስራ ለምድ ልውውጥ ለማድረግ ተመርጠው እንደሄዱ እና ያየውን ነገር ለሰዎች እያወራ ነበር።የሰሜን ጎንደር የግብርና አመራሯ የትግራይ ተወላጅ ሴት እንደሆነች እና በስራ ለምድ ልውውጥ በጣም ከፍተኛ ተዋናይት እንደነበረች እና በስሟ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይዛ እንደነበር እና ይህን ገንዘብ ለትግራይ ገበሬዎች አድላ እደተመለሰች አርሶአደሩ በቁጭት ይናግራል። በእያንዳንዱ የትግራይ አርሶአደር የስራ ልውውጥ ለማድረግ ስንገባ ያለምንም ምክንያት 50 እስከ 70 000 ብር ሰታ አጨብጭቡለት ትለናለች አለ። "እረ እትየ ለምን ይህን ያክል ገዘብ" ስንላት " እንዴ አታይቱም ከቤቱ ተለብዠን አስገብቶ፣ አታዩም እንዴ የውሃ ጉድጓድ ቆፍሮ፣ አልጋውን አታዩትም" ትለናለች አለ። ይህ ገበሬ በጣም ተናዶ በወሬው ሲቀጥል አኛ 37ታችን በተዘጋጀልን አንድ አውቶብስ እሷ በሌላ መኪና ፊት ከፊታቸው ወደሌላ የትግራይ ወረዳ ስንሄድ በሁላችን አንድ ወጣት ሳይክል እዬጋለበ ሲመጣ አየች እና ወረዱ ተባልን እና "አያቹህት ይህን ወጣት ከእኛ ጋር እኩል ሳይክል እዬጋለበ አለማጣ ሊገባ ነው" አለችን እና 60 000 ብር አውጥታ ሰታ አጨብጭቡለት አለችን አለ።

ከራስ እስክ እግሬ የሆነ ነገር ሲወረኘ ይሰመኛል። ነገር ግን ወሬውን ላለማቋረጥ ዝም አልኩ። ገበሬው ያለማቋረጥ ያየውን ነገረ በተለይ ደሞ የትግራይ ገበሬዎች በዛ ገደል እና ደረቅ መሬት የሠሩትን መልካም ነገር ያወራል። ነገር ግን ሴትየዋ የምትዘራውን ገንዘብ ግን አልተዋጠለትም። ለእነሱ እንኳ እለታዊ ለሆነ ምግብ፣ አልጋ እና ትራንስፖርት በቀር አንድ ብር ፍክች ያላላት ሴትዮ ያን ሁሉ ብር እረጭታ ስትመለስ በግዜው ገበሬዎች በጣም ግራ ተጋብተው ነበር ይላል። ትንሽ እየቆየ "የገባኘ አሁን ነው" ይላል። "አሁን ምንድን ነው የገባሀ?" ስለው "ተው ባክህ የአማራ ገበሬ ግብር ይፍላል የወያኔ ገበሬ ይከብርበታል" አለ እና የገባውን ያክል ዝክዝክ አድርጎ አወራኝ። እኔም በድርጊቱ ብቻ ሳይሆን በገበሬዎች ንቃተ ህሊና በጣም ተገረምኩ። እኔም የሴትዩዋን ስም ጠይቄ በሀሳቤ ይችን ሴትዮ አገቸ ለምን እደዛ እዳረገች ጠይቄ ብረዳ የተሻለ እንደሚሆን አሰብኩ እና ውይይቱን ቋጨን። ውድ ተከታታዩች ሴትዩዋ አሁንም ከቦታዋ ካለች እና ፍቃደኛ ከሆነች መረጃውን ላካፈረላቹህ ፍቃደኛ ነኝ። እስከዛው ቸር እንሰብት።

Wednesday, September 20, 2017

የአማራ ወጣቶች እና የወያኔ ኢሕአዴግ መንግሥት

የአማራ ወጣቶች እና የወያኔ ኢሕአዴግ መንግሥት 
===============================
Image may contain: one or more people and people standing
በአማራ ክልል እንደ ባህርዳር እና ጎንደር ያሉ ወጣቶች አስደንጋጭ በሆነ መልኩ የጫት ሱሰኛ እየሆኑ መምጣታቸው ብዙዎችን አሳስቧል። ይህ ደሞ የመንግሥት እጅ እዳለበት ብዙዎች ያምናሉ። ወያኔ ኢህአዴግ ሲገባ በምስራቅ ኢትዮጵያ ተወስኖ የነበረው የጫት ተጠቃሚ አሁን ግን በአስደንጋጭ ሁኔታ ወደሰሜኑ በተለይም ደግሞ በእማራ ክልል የወጣቱን አእምሮ እየተፈታተነው መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደ አሸን የፈላው ቢራ ፋብሪካ እና በመንግሥት ሚዲያ ቢራ ጠጡልኝ ማስታወቂያ የዚህን ክልል ወጣቶች ሆን ተብሎ አምራች ዜጋ እንዳይሆኑ እየተደረገ መሆኑን ያምናሉ። ወደትግራይ ከልል እደዚህ አይነት ነገር እንደለለ እና ጫትም በሕጋዊ በክልሉ እንደማይቃም ይነገራል። በቅርቡም በአለም መንግሥት የትግራይ ክልል ሰወች ከሰው ፌት ሲጋራ ባለማጨስ ተምሳሌት ክልል ተብላ እንደተመረጠች ብዙዎቻችን የምናውቀው ነው። 

ታዲያ ወደሌሎች ክልሎች በተለይ ደሞ አማራ ክልል ይህ ወጣቱን የማደዘዝ ተግባር በወያኔ መንግሥት አለመታቀዱ ምን ዋስትና አለ? በቅርቡ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተነሳው የወጣቶች ተቃውሞም አንድ ማሳያ ነው። ልማቶች እና የወጣቶች ስራ ፈጠራ ወደ አንድ ክልል ሆን ተብሎ በመንግሥት ትኩረት መሰጠቱ ባንፃሩ ግን ለሌሎች ክልሎች በተለይ ደም ለአማራ ክልል ሆን ተብሎ ወጣቱ አልባሌ ቦታ እንዲውል እየተደረገ ነው። በቅርቡ እንኳን በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ አመት ለሽገላ ያከወል ለወጣቶች 10 ቢሊዮን ብር የስራ ፈጠራ ተመድቧል ተብሎ በመንግሥትሚዲያ ሲለፈፍ የነበረው ብር የት እንደገባ እንደማይታወቅ ብዙ ለለውጥ የተዘጋጁ ወጣቶችን አሳዝኗል። ጎንደር አንድ ካፍቴሪያ ተደርድረው ሲጫወቱ ከነበሩት ወጣቶች አንድኛው ወጣት "ይሄኔ 10 ቢሊዮን ብር ትግራይ ውስጥ 10 ፋብሪካዎችን እየገነባ ነው" ብሎ በምሬት ሲያወራ ሌላኛው ደሞ "ወይኔ ወያኔ ከእናቴ ጋር አጣላኘወ" ይላል። 

ወጣቱ የወያኔ የይስሙላ ተደራጁ ልፍለፋ እና በየግዜው የሚደረገው ስብሰባ ያችን ያለችውን ስራም በመተው እና እናቱ እና ታናናሽ ወንድሞቹ እንደተቸገሩ እና በዚህም ምክንያት ከእናቱ ጋር መጣላቱን ለጓደኞቹ ቴብሉን በንዴት እየደበደበ ያወራል።"ከአንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም" ይላል ያገሬ ሰው። ወያኔ ኢሕአዴግ በሚዲያ ሚለፍፈውን ከልቡ ቢያደርገው ይህ ሁሉ ወጣት የሱስ ተገዢ ባልሆነ ነበር?

Monday, September 18, 2017

መንግሥት እና ሕዝቧ በተቃራኒው እየሄዱ ያሉ ብቸኛ ሀገር - ኢትዮጵያ

(Ethiopia Today) - መንግሥት እና ሕዝቧ በተቃራኒው እየሄዱ ያሉ ብቸኛ ሀገር - ኢትዮጵያ
==============================
መንግስት እደግመል ሽንት አንድ አቅጣጫ ብቻ ከማየት ዞር ብሎ ሁሉንም የመፍትሔ ሐሳቦችን ቢመለከት የተሻለ ነው ። አማራው፣ ኦሮሞውም፣ ኮንሶውም እንዲሁም ሌላው ኢትዮጵያዊ በመንግሥት ላይ ተቃውሞ ማንሳታቸው ስር የሰደደ ችግር ቢኖር ነው ። የሕዝብን ችግር ተቀብሎ ማስተናገድ ወይም ደሞ ሥፍራውን ለሌላ መልቀቅ። ከፋም ለማም እዋህት ኢሕአዴግ 25 ገዝተዋል። በ25 አመት አንዳንድ ጡሩ ነገር እደሰሩ ሁሉ፣ ነገር ግን መጥፎው ነገር እያየለ መምጣቱ ግን የማይታበይ ሐቅ ነው።
ትልቁ እና ዋነኛው ችግር በሁሉም ያገራችን ቦታዎች የጎሰኝነት እና የጠባብነት ስሜት ማበብ ነው። ይህ ደም የኢህአዴግ ያገዛዝ ውጤት ነው እናም ይሄን አምኖ መቀበል እና የመፍትሔ ሐሳቦችን ከሙህራን ተቀብሎ ማሻሻል ይጠበቅባቸዋል።
ሁለተኛው እና ሌላኛው ችግር አድሏዊ እና ኢፍታዊ አገዛዝ ያመጣው ውጤት ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በኢኮኖሚው፣ በፓለቲካው፣ በሚልተሪው እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ በበላይነት ሚቆጣጠሩት ያንድ ጎሳ ተወላጅ ብቻ ነው። ኢሕአዴግ ስልጣን ይዠ እቆያለሁ ካለ ይህ ችግር መወገድ አለበት። በበአዲን ውስጥ ያሉ የአማራውን ህዝብ እወክላለሁ የሚሉ ነገር ግን የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ስፍራው ለአማራ ልጆች መልቀቅ አለባቸው። ከክፍተኛ እስከ ቀበሌ አመራር የትግራይ ተወላጆች ችግር እየፈጠሩ እንዳሉ ማንም የሚያውቀው ሐቅ ነው። ይህ ችግር በበአዲን ይብዛ እንጂ በኦሮሞም በደቡብ ህዝቦችም የሚታይ ነው።
ሦስተኛው እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ያለው ስር የሰደደ ችግር ሙስና ነው። ኢሕአዴግ ዛሬ ከሚቆጣጠረው በላይ ስርአቱ በሙስና መበላሸቱ እና ይህን አምኖ ስር ነቀል ለውጥ ካላደረገ ስልጣን ላይ እቆያለሁ ማለቱ እማያዋጣው ነው። የኢህአዴግን ፓለቲካ እስከ ደገፍክ ድረስ ምንም ብታደርግ ዝም እንልህአለን የሚለው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ፕሪስፕል ማቆም አለበት። ያጠፋ፣ የሰረቀ፣ አገርን ያዋረደ በአደባባይ መቀጣት አለበት። ዛሬ የአማራን የኦሮሞን ህዝብ እወክላለሁ ብለው ከከፍተኛ እስክ ዝቅተኛ አመራር ላይ ያሉ ነገር ግን የድሀውን ሀብት እየመዘበሩ ያሉ እድር ባዮች ያማራ እና የኦሮሞ ባለሥልጣናት ባስቸኳይ እርምጃ ቢወሰድባቸው እና መንግሥት ባዲስ መልክ ቢያዋቅር የተሻለ ነው። ለወደፊቱም መንግሥት ለፖለቲካወው ካልተስማሙ ሙሰኛ ወይም አሸባሪ ብሎ እስር ቤት ከመወርወር በሕጉ መስረት ያጠፍ እዲቀጣ ቢደርግ የተሻለ ነው።
አራተኛው እና ኢሕአዴግ ማስተካከል ያለበት ችግር አድሎአዊ ኢኮኖሚ ነው። ዛሬ ያአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ሆ ብሎ ቢነሳ አይፈረድበትም። በ25 አመት ወስጥ ዛሬ ባአማራ ምድር ላይ አንድ እንኳን ላይን የሚይዝ ፋብሪካ የለም። ትግራይ ውስጥ ሚሰራውን ነገር ግን ሁላችንም ምናውቀው ነው። ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ እቆያለሁ ካለ እሄን ማስተካከል ይጠበቅበታል።
አምስተኛው እና ዋነኛው ችግር አፈና ጭቆና እስራት እና እግልት ናቸው። ኢህአዴግ ሰው ባገሩ የፈለገውን ተናግሮ የትም ቦታ ህዶ የመስራት መብት ማክበር አለበት። ሰው በሶሻል ሚዲያ በጋዜጣ እንዲሁም በብሎገር ሐሳቡን ስላሰፈረ ብቻ አሸባሪ፣ አክራሪ ወይም አገር አተራማሸ መባል ይቁም። ይልቁንስ እነዚህ ፃሀፌያን የሚቀርቡትን ቀና ሀሳብ ወይም የመንግሥት ደካማ ጎኖች መንግስት በቀና ልቦና ወስዶ ማሻሻያ ቢደርግ የተሻለ ነው። ዛሬ አብዛኛው የአማራ አና የኦሮሞ ግዛቶች ሶሻል ሚዲያ አፕስ አይሰሩም። አማራ ክልል በተለይም ጎንደር ስለመብታቸዉ ሰለጠየቁ ብቻ ቡዙ ሰወች እስር ቤት ነቸው። ።
እሄም ባስቸኳይ መስተካከል አለበት። የሰው የመናገር እና መንግሥትን መተቸት መብት መከበር አለበት። ዛሬ ሙህራን ሀሳባቸውን ወይም ፅህፎቻቸዉን ለአለም ሚያቀርቡበት እንደ ብሎገር ወርድ ፕረስ ያሉ በሎጎች ወይም ደግሞ ስለኢትዮጵያ እለታዊ መረጃዎችን ሚያቀርቡ ድረገፆች ልቅም ተደርገዉ በእያንዳንዱ ዮንቨርስቲ ተዘግተዋል። መረጃን በማፈን ወይም የመናገር መብትን በመክልከል እድሜን ማራዘም አይቻልም። የታፈነ ህዝብ እንዳየነው አንድ ቀን መፈዳቱ አይቀርም። ያኔም ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ያደርገዋል። ይልቁንስ መንግሥት ህዝቡ የሚያነሶቸውን ቅራኔዎች በሰከነ እና በተረጋጋ መፈስ አይቶ በወቅቱ መልስ መስጠት ያሻል። የወልቃይትን ጉዳይ በወቁቱ መልስ ቢሰጠው ኑሮ ዛሬ እሱን ስበብ አድርጎ እሂ ሁሉ ችግር ባልመጣ ነበር። የወልቃይት ማንነት ጉዳይ ኮምቴ እስከ ፌዴሬሽን ምክርቤት ለዓመታት ላቀረቡት ጥያቄ ቀና መልስ ከመስጠት ይልቅ ህዝብ ወይም ሚድያ እያወቃቸው አሸባሪ ወይም ፀረ ሰላም ብሎ መሰየም ውጤቱን ያየነው ነው ።
ለማጠቃለል ያክል መንግስት ከላይ የተዘረዘሩትን መክረ ሐሳቦች እምኖ እና ተቀብሎ አቅም ካለው ማስተካከል ከቻለ ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ ማይቆይበት ምክንያት የለም። የብዙ ሰው ፍላጎትም ይመስለኛል። የዜጎች ጥያቄ በወቅቱ ከተመለሰ የመናገር እና የመፃፍ መብት ከተከበረ አድሎአዊ ኢኮኖሚ እና ፓለቲካ ከለለ ሙስና ከቀነሰ ያላግባብ አፈና እስራት እና እንግልት ከለለ፣ የዘር መድሎ ከለለ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ ምን ይፈልጋል?
ነገር ግን ኢህአዴግ እነዚህን መክረ ሐሳቦች አምኖ እና ተቀብሎ መተርጎም ካልቻለ ወይም አቅም ከልለው ሌላ ጡሩ ነገር ለኢትዮጵያ ህዝብ የመስራት አቅም አንዳለው አምናለሁ። እሂም የኢህአዴግ አመራሮች በ11ኛው ስአት ከተጠያቂነት ሊያመልጡ ይችላሉ ። ነገር ግን አነሱ እደሚያወሩት እኛ ከለለን ኢትዮጵያ ትበታተናለች እና ምናምን እያሉ ከቀጠሉ እና እነሱ እዳሉት ከቀጠለ ኢትዮጵያ አትበታተንም እነሱም ከተጠያቂነት አያመልጡም። የኢትዮጵያ ህዝብም አይምራቸዉም። ይልቁንስ ከእነሱ ሌላ ኢትዮጵያን ማስተዳደር የሚችል አቅም እና እውቀት ያላቸው ምሁራን እዳሉ አምኖ እና ተቀብሉ የፓለቲካ ምህዳሩን ሰፋ አድርጎ ለእነሱ እድሉን መስጠት ያስፈልጋል። እሂንም ካደረገ ኢህአዴግ እስከ ዛሬ ከሰራቸው ስራዎች የበለጠ ያደርገዋል መጥፎ ስራዎችን ይሸፈንለታል ከተጠያቂነትም ያመልጣሉ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ባሁኑ ስአት ኢህአዴግ ስልጣን ይልቀቅ ማለትም አይደለም። የብዙ ሰው ፍላጎትም እሱ አይመስለኝም። ነገር ግን በህገ መንግሥቱ መሰረተ ምርጫ ለማካሄድ ሦስት አመት ይቀራል። በነዚህ አመታት ኢሕአዴግ ብዙ ስራዎችን መስራት ይጠበቅበታል። የፓለቲካ ምህዳሩ መስፋት አለበት። የምርጫ አዋጅ መሻሻል እና ገለልተኛ ማድረግ ያስፈልጋል። የዳኝነቱን ህግም ገለልተኛ እዲሆን ማድረግ እና ኢሕአዴግ ሁሉንም ነገር ይቅር ብሎ ከሐገር ውጭ እና ከሐገር ውስጥ ያሉትን የፓለቲካ ፓሪቲዎችን በሃገራቸው ጉዳይ ላይ እንዲሁም በምርጫው እዲሳተፉ ማድረግ ይጠበቅበታል። ከሐገር ውጭ በአሸባሪነት የፈረጃቸው የፓለቲካ ፓሪቲዎች ብዙ ህዝብ ደጋፊ እዳላቸው አውቆ እና አምኖ ሐገር ውስጥ ገብተው እኩል እዲሳተፉ ማድረግ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ በፓለቲካ ምክንያት ዛሬ ወደ ሐገረ ውስጥ መግባት እየፈለጉ ነገር ግን መግባት ያልቻሉ ስለ ሃገራቸው ጉዳይ የእግር እሳት የሆነባቸው ለኢህአዴግም ለእራሱ የእግር እሳት የሆኑበት በርካታ ኢትዮጵያን መህረት ተደርጎላቸው ስለሀገራቸዉ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና እና ፓለቲካዊ ተሳትፎ ኢዲያደርጉ ማድረግ። ኢህአዴግ እነዚህን ምክረ ሀሳብ ተቀብሎ ለሚቀጥለው ምርጫ እራሱን እና ህዝቡን ቢያዘጋጅ እኔው እራሴ አንደኛ ምርጫዬ እሱ እራሱ ወያኔ ኢሕአዴግ ነው ሚሆነው።
Image may contain: 8 people, crowd and outdoor

Wednesday, August 30, 2017

ለካርታውስ ይቅርታ ተጠየቀ! ሕገ መንግሥቱ እንዴት ይስተባበል?

Image may contain: text
ለካርታውስ ይቅርታ ተጠየቀ! ሕገ መንግሥቱ እንዴት ይስተባበል?

ሰሞኑን በኢቢሲ የተላለፈውን ካርታ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ብዙ አነጋግሯል፤ ከዚያም አልፎ ‹‹ይቅርታ›› ተጠይቆበታል- ማዘናጊያ ቢሆንም፡፡ 
ግን የአማራ ‹‹ክልል›› ከሱዳን ጋር እንደማይዋሰን የሚያሳየው ካርታ በሕግ የጸና መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን? ቤኒሻንጉል ጉምዝና የትግራይ ክልሎች ጎረቤት መሆናቸውን በሕግ የተደነገገ መሆኑን ስንቶቻችን ተገንዝበናል? 

ከሽግግሩ መንግሥት በኋላ የተቋቋሙ ‹‹ክልሎች›› የራሳቸውን ሕገ መንግሥት አጽድቀዋል፡፡ ከነዚህም አንዱ የጎጃም ለም መሬቶችን ይዞ የተቋቋመው ‹‹ክልል›› ቤኒሻንጉል ጉምዝ ነው፡፡ በዚህ ክልል ሕገ መንግሥት መሠረት የአማራ ‹‹ክልል›› ከሱዳን ጋር አይጎራበትም፡፡ በ1988 ዓም በጸደቀው በክልሉ ሕገ መንግሥት መሠረት ክልሉን በሰሜን በኩል የሚያዋስነው የትግራይ ክልል እንደሆነ ቁጭ አድርጎ በአንቀጽ ሁለት ይናገራል፡፡ በዚህ መሠረት እነ ጃዊ፣ ቋራና መተማ የቤኒሻንጉል ሲሆኑ እነ አርማጭሆ ደግሞ ከወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ጋር የትግሬ ሆነዋል ማለት ነው፡፡ ትግርኛ ስለማልችል የታላቋ አዲ ትግራይ ሕገ መንግሥት ምን እንደሚል አላውቅም፡፡ 

አሁን ጥያቄው የካርታውስ ጉዳይ በይስሙላ ይቅርታ ታለፈ! የተሰረቀው ተራራና የተሰረቀው ቤተ መቅደስም አፉ በሉን ተብሎ ተመለሠ፡፡ ይህ ሕገ መንግሥት ምን ዓይነት ማስተካከያ ሊደረግበት ነው? የሚለው ነው፡፡ 
ይህን የያዘውን የቤኒሻንጉል ክልል ሕገ መንግሥት ክፍል በፎቶው ላይ ይመልከቱ፡፡ Read more here
No automatic alt text available.

Friday, August 18, 2017

ምንሊክን ልትጠላው ይገባል!

Image may contain: one or more people and text

ምንሊክን ልትጠላው ይገባል!…
~~~~~ ~~~~~ ~~~~~
የእርሱ፤ "ሙሉ ሠው" የመሆን ግርማና የማይሸነፍ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ያንተን ውሽልሽል አናሳ ልቦና እራቁቱን ስለሚያስቀርብህ ልትጠላው ይገባል። የእርሱ፤ ከፍ ብሎና ደምቆ ዝንታለም የሚንቦገቦገው አስገራሚ የሠውነት ልዕልና ያንተን ጨለማ ትርክት መና ያስቀረዋልና ምንሊክን ልትጠላው ይገባል።
ከመቶ አመታት በፊት የነበረው የእርሱ ብልህ አዕምሮ፤ ያንተን እንጭጭነት። የእርሱ አመዛዛኝ ህሊና ያንተን ግልብነት። የእርሱ ሠፊ ልብ፣ ያንተን ጠባብና ጉልህ ድንቁርና፤ በድምቀት ያስተጋባልና ምንሊክን ልትጠላው ይገባል።
ምንሊክን ልትጠላው ይገባል። የእርሱ መሃሪ ልብ ያንተን የማይነፃ ሴረኛ ልብ ያኮስሰዋል። የእርሱ ለጋስነትና ቸርነት ያንተን ንፉግነትና ስስታምነት ያጐላዋል። የእርሱ አስገራሚ ብሩህነት፤ ያንተን አሳፋሪ ጨለምተኝነት ያጋልጥብሃልና እምዬ ምንሊክን ልትጠላው ይገባል።
የታሪክ መዝገብ ጠቅሠህ፣ መፃህፍትን መርምረህ፣ አዕምሮ እንዳለው እንደ ሠው ልጅ በምክንያት ተከራክረህ እምዬ ምንሊክን የምትንቅበት ሠበብ የለህምና የጨለምተኝነት ለቅሶህ በህዝብ ዘንድ ዋጋ እንዲኖረው እንደ ማገርነት የቸነከርከው፤ በተከታታይ ተግቶ የማልቀስና አጋፋሪዎችህን የማስለቀስ ፀጋህ ላይ ነው። ማን በምክንያት ሊረታህ ይቻለዋል!?
በድንቁርናህ ብርታት በልብህ ያፀናኸውን ጥላቻ፤ በልዕልና ሃይል ለመመከት አዳጋች ነውና ከጭለማህ ጋር ትሠነብት ዘንድ አድዮስ!!
እኛ ግን በብዙ ምክንያት እምዬ ምንሊክን እንኳን ተወለድክ እንለዋለን። አንተ ባትወለድ፤ ከዳር እስከ ዳር የተዘረጋውን ኢትዮጵያዊ አስተባብሮ ባርነትን ማን ይመክትልን ነበር!!?
እምዬ ምንሊክ እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆነህ ተወለድክ።
#ኢትዮጵያዊ መንፈስ
ለዘላለም በክብር ይንገስ!!
(ዳዊት ዘሚካኤል)
Image may contain: 2 people, hat

እቴጌ ጣይቱ ብጡል

Image may contain: 1 person
እቴጌ ጣይቱ ብጡል
«ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ»

«ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብዳር በነሐሴ12ቀን1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ በ 80 ቀናቸው ጥቅምት 23 ቀን1833 ዓ.ም በደብረ ታቦር እየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሱ። በልጅነት ዘመናቸው በዚሁ ደብር ውስጥ ዳዊት ደገሙ። ከዚያም በጊዜው ይሰጡ የነበሩትን ሌሎች የሃይማኖት ትምህርቶች በየታላላቅ አድባራት በመዘዋወር ያጠናቀቁ ስለመሆናቸው ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።
የተማሩባቸውም መጻሕፍት የተጻፉት በግዕዝ ቋንቋ ስለነበር ቋንቋውን አጣርተው ያውቁ ነበር። እናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ባለቤታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ከሞቱ በኋላ በጅሮንድ መዩ የተባሉትን የአፄ ቴዎድሮስ ባለሟልን አግብተው ነበር። እርሳቸውም ጣይቱ ብጡል ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ ልዩ መምህር ቀጥረውላቸዋል። እቴጌ ጣይቱ በማኅደረ ማርያም ሆነው ይማሩና መፃሕፍትን ይቀጽሉ በነበሩበት ጊዜ ለቤተክርስቲያን መጋረጃ መሥሪያ በትርፍ ጊዜያቸው ፈትል እየፈተሉ ያቀርቡ ነበር። በበገና ቅኝትና ድርደራም በኩል የታወቁ ባለሙያ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል።

የጣይቱና የምኒልክ ጋብቻ
-----------------------
የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የአፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ 17 ቀን 1857 ዓ.ም በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገቡ። በነሐሴ 24 ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው የፋሲካን በዓል በባሕር ዳር አቅራቢያ ሱሉልታ ላይ ዋሉና ደብረ መይ በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከዚያም ዋና ከተማቸው ወደነበረችው ደብረ ብርሃን ተመለሱ።
ከተጫጩ ከሁለት ዓመት በኋላ ወይዘሮ ጣይቱን ለማስመጣት በቤተ መንግሥቱ በተደረገው ምክር መሠረት አለቃ ተክለማርያም ወልደ ሚካኤል ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ተላኩ። በዚያም አስፈላጊው ሁሉ በተፋጠነ ሁኔታ ተሟልቶ በጐጃም በኩል ደንገጡሮችና አሽከሮች አስከትለው ጉዞውን ጀመሩ። ደብረ ብርሃንም በገቡ ጊዜ ንጉሡ ምኒልክ ታላቅ አቀባበል አደረጉላቸው። ከዚያም ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌ ብጡል ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የጋብቻቸው ሥነ-ሥርዓት የፋሲካ ዕለት ሚያዝያ 25 ቀን1875 ዓ.ም በአንኮበር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ተጋቡ።
አፈወርቅ ገብረ ጊዮርጊስ «ዳግማዊ አጤ ምኒልክ» በተባለው መጽሐፋቸው ከገጽ39 እስከ 41ላይ «ከልጅነት ጀምረው ሲመኟት እንደ ህልም ሲአልሟት ትኖር የነብረችው ጣይቱ ብጡል በ18 75ዓ.ም ደብረ ብርሃን ገባች። ንግሥተ ሸዋ ሆነች ወዲያው የፋሲካ ዕለት አንኮበር መድኃኔዓለም ቆርበው ተጋቡ። … ፀሐይቱ ለማለት ጣይቱ ተባለች ነገር ግን ከጣይቱ እጣይቱ ለመባል ይገባታል» ይላሉ።
«ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ»
ንጉሡ «አፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» የሚለውን ስም በተቀዳጁ በማግሥቱ ጥቅምት 27 ቀን 1882ዓ.ም ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ተብለው ተሰየሙ። የሥርዓተ ዘውዱ አፈፃፀም በከፍተኛ መሰናዶ የተጠናቀቀ በመሆኑ እጅግ ደማቅ እንደነበር ከተፃፉ ጽሑፎች ለማወቅ ይቻላል። እቴጌ ጣይቱም ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ከንጉሠ ነገሥቱ እጅ የተቀበሉትን ዘውድ ደፉላቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በታወቁበት «እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል የክብር ስም ማኅተም ተቀረፀላቸው። እነዚሁ ታሪካዊ ሂደቶች እቴጌዪቱን በኢትዮጵያ ዱኛዊ፣ ወታደራዊና ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ከፍተኛና ብሩህ ሚና ለመጫወት የቻሉ አድርጓቸዋል።

ፖለቲካዊ ተግባራት
--------------------
እቴጌ ጣይቱ በዱኛ አስተዳደር አንፃር የነበራቸው ችሎታና ተግባራዊ እንቅስቃሴ በታሪክ አዋቂዎች ዘንድ ተደናቂነትን አትርፎላቸዋል። በየጊዜው ይነሱ በነበሩ የሀገር ጉዳዮች ላይ ይይዙት የነበረው አቋም፣ ይሰጡት የነበረው ውሳኔና ያስተላልፉ የነበረው ትዕዛዝ ተሰሚነትና ተቀባይነት እያገኘ እንደመሄዱ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይሄድ ለነበረው የዱኛ ሥልጣናቸው ዓይነተኛ ምክንያት ነበር።
እቴጌ ጣይቱ በኢትዮጵያ ዱኛ ተሳትፏቸው የገነነውና በአገር አስተዳደርም ውስጥ ከፍተኛ ሚና መጫወት የጀመሩት፤ ኢትዮጵያ ሚያዝያ 25ቀን 1981ዓ.ም በውጫሌ ላይ ከኢጣሊያ ጋር በተፈራረመችው ውል ውስጥ በኢጣሊያንኛው ትርጉም ሀገሪቷን ነፃነት እንደሌላት ጥገኛ በማስመሰል ዓላማ ላይ የተመረኮዘ ውንብድና መኖሩ ከታወቀ ወዲህ ነው።
ይህ ለአድዋ ጦርነት መነሳት ምክንያትና ዋነኛ መንስዔ የሆነው ጉዳይ ሊታወቅ የቻለው እቴጌ ጣይቱ የውጫሌ ውል አንቀፅ 17ላይ አለቃ ዓፅመ ጊዮርጊስ የተባሉት ቋንቋ አዋቂ አፄ ምኒልክ በሰጧቸው ትዕዛዝ መሠረት ነው። ያኔ የውሉን ሰነድ በመመርመር የውሉ 17ኛ አንቀፅ የያዘውን የትርጉም መዛባት ያለበት መሆኑን አሳወቁ። ጉዳዩ ኢትዮጵያ የምትጐዳበት ስለመለሆኑ ጭምር በማስረዳት በሰጡት ቃል እቴጌ ጣይቱ በጥንቃቄ ተመለከቱት።
ጉዳዩን አፄ ምኒልክ በመጀመሪያ ሳይረዱ አለቃ ዓፅመ ጊዮርጊስ እንዲታሰሩ ቢያደርጉም እቴጌ ጣይቱ ግን እኚህ ሰው ትክክለኛ የኢትዮጵያ ወዳጅ መሆናቸውን ለአፄ ምኒልክ በማስረዳት ከሦስት ዓመታት እስራት በኋላ ማስፈታታቸው ይታወቃል። በዚህ በኩል ሲታይ እቴጌ ጣይቱ የምኒልክ የቅርብ አማካሪ በመሆን በፖለቲካ ተግባሮች ምን ያህል አስተዋፅኦ እንዳበረከቱ መገንዘብ ይቻላል። እቴጌ እንደተናገሩትም «ዓፅመ ጊዮርጊስ ቢታሰር ቢፈታም ለሀገሩ የሚገባውን ሠርቶ ነው። ኧረ ለመሆኑ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው ዮሴፍ፣ ኢጣሊያኖች በተንኮል ገብተው በማታለል ይህን የመሰለ ሥራ ሲሠሩ አነጋጋሪ ሆኖ ሳለ እንዴት ሳያስጠነቅቅዎ ቀረ?» በማለት የእቴጌ ጣይቱ የቁጣ መዓት ወደ ዮሴፍ ዞረ።

ከዚያም ጨምረው «ከእንግዲህ ወዲህ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚነካ፣ ሥር የሚነቅል፣ መሠረት የሚያፈርስ ጉዳዩን ሁሉ እኔ ሳላየው እንዳያልፍ ይፍቀዱልኝ» ብለው ለንጉሡ ባመለከቱት መሠረት «አንቺ ሳታይው ሳትመረምሪው አያልፍም» በማለት ፈቀዱላቸው። ይህ ሁኔታ የሚያመለክተው እቴጌ ጣይቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበራቸው ቦታ ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ነው። ውሉንም ለማስተካከል አፄ ምኒልክ ያደረጉት የዲፕሎማሲ ጥረት ውጤታማ ሊሆን ባለመቻሉ ሚኒስትሮች የጦር አለቆችና መኳንንት የሚገኙበት ጉባዔ እንዲጠራ አደረጉ።
እያንዳንዱ ሰው ስለተነሳው ችግር ያለውን አስተያየት የሀገር ፍቅር በተሞላበት አንደበትና የጋለ መንፈስ ሲገለፅ ቆየ። እቴጌ ጣይቱም «እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም። ሆኖም ይህን ኢትዮጵያን የኢጣሊያ ጥገኛ የሚያድርግ ውል ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ» የሚል አቋማቸው በታሪክ ቅርስነቱ ለትውልድ ትተውት ያለፉት አባባል ዘመን ተለውጦ ዘመን እየተተካ በሄደ ቁጥር የሚነገር ሆነ። ስለዚህ የእቴጌን ጀግንነት የቁርጠኛ ኢትዮጵያዊ ልጅ ለመሆናቸው ሌላ ማረጋገጫ ማቅረብ አያስፈልግም። እቴጌ ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌን አተኩረው በማየት በታወቀው ጀግና አንደበታቸው የተሰበሰበውን ሕዝብ ስሜት ለመቀስቀስ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ማድረጋቸው ይነገራል።

«መልኩ ከመልካችን የማይመሳሰል እግዚአብሔር በባህር ከልሎ የሰጠንን አገራችንን የሚቀማ ጠላት መጥቶ እንዴት ዝም እንላለን? እንዋጋለን እንጂ!» በማለት የሀገሪቱን ውበትና ልምላሜ የምታፈራውን እህልና የከብት ዓይነት እየጠቃቀሱ በማንሳት ተናገሩ። ቀጥለውም «ኧረ ለመሆኑ ተራራው ሸለቆው ወንዛወዙ ጨፌው ሜዳው ማነው ቢሉት የማነው ብሎ ሊመልስ ነው እንገጥመዋለን እንጂ!» በማለትም የተሰበሰበውን ሕዝብ ልብ የሚነካና ወኔ የሚቀሰቅስ ንግግር አደረጉ። በዚህ የተዋጣ የቅስቀሳ ችሎታቸውም ባገኙት መድረክና አጋጣሚ የሚጠቀሙ አንደበተ ርቱዕ መሆናቸው ይነገራል።
ስለ እቴጌ ጣይቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በምሳሌነት ሊቀርብ የሚችል ሌላ ዓይነተኛ ታሪክ አለ። ይኸውም አፄ ዮሐንስ በሞቱ በአንድ ዓመታቸው በመጋቢት 1882 ዓ.ም አፄ ምኒልክ አገሩን ለማረጋጋት ሲሉ መሃል ትግራይን ለመጐብኘት ሄዱ። ይህ የሆነው እቴጌ ጣይቱ ለሸዋም፣ ለወሎም፣ ለበጌምድርም፣ ለየጁም መካከል በሆነችው ደሴ ከተማ ሆነው አገሩን እንዲጠብቁ በማለት ነው። እዚያ ሆነው ያከናወኑት ተግባር የረጋ አስተዋይና የተዋጣላቸው ዲፕሎማት አሰኝቷቸዋል። በተለይም በሁለት የጦር አበጋዞች መሃል የሚፈጠር አለመግባባትን አግባብቶ በመፍታት በኩል ተወዳዳሪ አልነበራቸውም።

እቴጌ ጣይቱ ከሕዝቡ ጋር በነበራቸው ግንኙነት በተለይም ያሳዩት በነበረው ርህራሄና ልግስና በጣም የተወደዱና የተመሰገኑ አድርጓቸዋል። ግልፅ የሆነው የፖለቲካ አስተያየታቸውና ጽኑ የሆነው ተግባራዊ ውሳኔያቸው፣ ዘዴንና ሥልጣንን እንዲሁም ምክርን ኃይልን ምን ጊዜ በእንዴት ያለ መጠን መጠቀም እንዳለባቸው በትክክል የመገመት ችሎታቸው ሲታይ በዓለም ከታወቁት የፖለቲካ አርበኞች ውስጥ ሊወሳ የሚገባ ታሪካዊ ስፍራ እንዳላቸው አጠራጣሪ አይሆንም። መልካም ስማቸውን ለማትረፍ ካስቻላቸው ጉዳዮች ጽኑ በሆነ መንፈሳዊ ኑሯቸው አኳያ የሚታየው የልግስናና የቤተ ክርስቲያን ነፃ ተግባሮች አንዱና ዓይነተኛው ነው። ይህ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ልዩ ግንኙነት ለመመስረት ያስቻላቸው ከመሆኑም በላይ የፖለቲካ ሥልጣናቸውን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳደረገ ከሌሎች ታላላቅ የፖለቲካ ሰዎች ታሪካዊ አነሳስ ለመገንዘብ ይቻላል።

በዚህ በኩልም እቴጌ ጣይቱ ብጡል በማህበራዊ ህይወት ሲያደርጉ የነበሩት በጐ ተግባር በመንፈሳዊ ኑሯቸው በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት እጅግ የጐላ ነበር። ከነዚህም ውስጥ ለየካ ቅዱስ ሚካኤል ሰላሳ ጋሻ መሬት፣ ለሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት አሥራ ስድስት ጋሻ መሬት የሰጡ መሆኑ ለአብነት ያህል የሚጠቀሱ ናቸው።
እቴጌ ጣይቱ ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መረጋጋት የሚያረጋግጥ የሀገር ግንባታ ተግባሮች በማከናወን ረገድና የአዲስ አበባ ከተማ መቆርቆር በእቴጌ ጣይቱ ከተጠናቀቁት የግንባታ ተግባሮች አንዱ ነው። ስለ እቴጌ ጣይቱ ሲወሳ በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው የከተማዋ የመጀመሪያው ሆቴል «ጣይቱ ሆቴል» አብሮ ይነሳል። ምንም እንኳን እቴጌ ጣይቱ የተቀረፀላቸው ሐውልትና ለትውልድ የሚተላለፍ ስማቸውን የሚያስጠራ ከአብራካቸው የወጣ ልጅ ባይኖራቸውም፤ የአፄ ምኒልክን ልጆች አክብሮታዊ ፍቅር ሳይለያቸው ቤተሰባዊ ፍቅርን እየተላበሱ እንደኖሩ ከተለያዩ መጻህፍት ለመረዳት ይቻላል።

የሥልጣን ፍጻሜ
-----------------
እቴጌ ጣይቱ ከደንገ ጡራቸውና የእንጀራ ልጅ ልጃቸው ጋር ባላቸው ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከሞቱ በኋላ በልጅ እያሱና በደጃዝማች ተፈሪ መኮንን መካከል የሥልጣን ሽኩቻ ተፈጠረ። በጦሩ መካከልም መከፋፈል በመታየቱ አገራዊ ችግሩ የከፋ ሆነ። በልጅ እያሱ አስተዳደር ዘመንም እቴጌዪቱ ከቤተ መንግሥት ተወግደው በግዞት ላይ ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ከሃያ ሁለት ቀናት ተቀመጡ። ሆኖም ታማኝ አሽከሮቻቸውና መላው ሠራዊት የእቴጌነታቸውን ልዕልና አላጐደለባቸውም። መሳፍንቱ መኳንንቱና ወይዛዝርቱም ቢሆኑ ተገቢውን አክብሮት ሳይነፍጓቸው ዕለት በዕለት ይጠይቋቸው ነበር። አቤቶ እያሱም ቢሆኑ የተለያዩ ስጦታዎችን ይዘው በመሄድ ይጠይቋቸው ነበር። የጦር ሚኒስትሩ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴም የተለያዩ እጅ መንሻ ይዘው ይጠይቋቸው ነበር።
የልጅ እያሱ ሥልጣን ብዙም ሳይቆይ ከላይ በተገለጸው ‘የሥልጣን ክርክር’ ተሸንፈው መስከረም 17 ቀን 1909ዓ..ም የሚኒስትሮች ካቢኔ ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ ንግሥተ ነገሥታት ተብለው መንግሥቱን በመምራት እንዲተኳቸው መደረጉ ለእቴጌ ጣይቱ ታላቅ ድል ሆነ። በመሆኑም የእቴጌም የእስራት ቀንበር ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ሊወድቅላቸው ቻለ። ንግሥት ዘውዲቱ ሥልጣናቸው ተዳክሞ ትዕዛዛቸው እንዳይዛባ በማለት ከተጓዙበት ከእንጦጦ ሳይቀር ምክር መለገሳቸውን አላቋረጡም ነበር።

እቴጌ ጣይቱ የደረሰባቸውን ፈተና ሁሉ በትዕግስት ተቀብለው ጥቂት እፎይ ካሉ በኋላ ከአፄ ምኒልክ ጐን ሆነው የኢትዮጵያን አንድነትና ጥንካሬ ለማረጋገጥ ሲታገሉ ያለፉት ዘመን ከዕለታት አንድ ቀን ትዝ ስላላቸው ከሰገነት ላይ ብቅ ብለው «ያ ቤት የትኛው ነው?» ብለው ሲጠይቁ ከደንገጡሮቹ አንዷ «የእመቤቴ እልፍኝ ግምጃ ቤት ነበር» አለች። እሳቸውም ትንሽ ተከዝ ብለው ከቆዩ በኋላ ቀበል በማድረግ «ነበር ለካስ እንዲህ ቅርብ ኖሯል» አሉ ይባላል።
እቴጌ ጣይቱ ሰኞ የካቲት አራት ቀን 1910ዓ.ም በመንፈቀ ሌሊት ህመም ፀንቶባቸው ከሚወዱትና ከሚወዳቸው ሕዝብ በሞት ተለዩ። የዕረፍታቸውን ዜና የኀዘኑንም ሥነ ሥርዓት ለማወጅ የቤተ መንግሥቱ መድፍ ሃያ አምስት ጊዜ ድምፁን አሰማ። በኀዘኑ ሥርዓትም ላይ እቴጌ በአድዋ ጦር ሜዳ ላይ ያሳዩትን የቆራጥነትና የጀግንነት ሙያቸውን እየጠቀሱ በግጥም እየገለጡ በማሞገስ ይሸልሉ ይፎክሩና ያቅራሩ ነበር። የእቴጌም አስክሬን በወርቅ ሐረግ በተከበበ የእንጨት ሳጥን ተደርጐ በብረት ሳጥን ውስጥ ከገባ በኋላ በቀድሞ ቤተ ፀሎታቸው ውስጥ ሸራ ቤት እየተባለ ይጠራ በነበረው መንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም ቤት ውስጥ በታላቅ ክብር አረፉ። ለተሰበሰበው ሕዝብ ትልቅ ግብዣ ተደርጐ የቀብሩ ፍፃሜ ሆነ።

እቴጌ ጣይቱ ከማረፋቸው አስቀድመው ለንግሥት ዘውዲቱ «ልጄ ማሚቴ ሆይ አደራዬን ሰጥቼሻለሁ» ብለው መናዘዛቸው በታሪክ ይወሳል። በዚሁ መሠረት ንግሥት ዘውዲቱ በታኅሣሥ ወር1920 ዓ.ም የአፄ ምኒልክን ዓፅም ከቤተ መንግሥቱ አስወጥተው ለማረፊያው በታዕካ ነገሥት በአታ ቤተ ክርስቲያን አሳንፀው በነበረ ጊዜ የእቴጌንም ዓጽም እዚሁ እንዲያርፍ ቢፈልጉም የእንጦጦ ማርያም ካህናት እቴጌ ጣይቱ ለኛም እናታችን ናቸውና መታሰቢያነታቸውን እንሻለን በማለት የተቃውሞ ድምፅ አሰሙ። ቢሆንም የኑዛዜውን ቃል አብራርተው በማስረዳታቸው ፈቅደውላቸዋል። በመጨረሻም የእቴጌ ጣይቱ፣ የአፄ ምኒልክና የንግሥት ዘውዲቱ መካነ መቃብር በታዕካ ነገሥት በዓታ ቤተ ክርስቲያን ምድር ቤት ውስጥ በመንበሩ ትይዩ ሳጥኖች ተፈልፍለው በተሰሩ እብነ በረድ ታሽገው እንደቆዩ በወለሉ ላይ መደዳውን ተቀምጠው ይገኛሉ።

እቴጌ ጣይቱ በሞት የተለዩዋቸውን የሕይወት ጓደኛቸውን ጥለው በግዞት እንዲቆዩ በተገደዱበት በእንጦጦ አፋፍ ላይ ሆነው አዲስ አበባ ብለው የሰየሟትን መዲና በዓይን በመቃኘት «ያ ቤት የትኛው ነው?» ብለው የጠየቁት የምኒልክን መቃብር በዓይናቸው ሲፈልጉ ይሆን? የሰው ሕይወት ኃላፊ ነው፤ ታሪክ ግን ሠሪዋን ለዘላለም ታስታውሳለች። በዚያች ደቂቃ እቴጌ ጣይቱ ስማቸውን የሚያስጠራ ታሪካቸውን የሚያስታውስ አንድ የምኒልክ የደም ቋጠሮ ሀረግ ሳያሠሩ ማለፋቸው ሳያሳዝናቸው እንዳልቀረ መገመቱ ቀላል ነው። ይህንም ሀዘን ለግዞት ወደ እንጦጦ ከመውጣታቸው ጥቂት ጊዜ በፊት ሊሸኟቸው በተሰበሰቡት መኳንንትና ወይዛዝርት ፊት የገጠሙት ግጥም አንጀት የሚበላ ነበር።እኛም በዚሁ ተሰናበትን።
«ተወዶ ከመኖር ተጠልቶ መውለድ
ማን ያይብኝ ነበር ይህን ሁሉ ጉድ»

ፀሐፊ ዳንኤል ወ/ኪዳን
እቴጌ ጣይቱ ብጡል
«ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ»

«ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ...

Monday, July 10, 2017

እንጦጦን የቱሪስት መስህብ የማድረግ ውጥን

ባቡር መንገድ (የመኪና መንገድ) አዲስ አበባ ላይ የተጀመረው በ1894 ዓ.ም. ቢሆንም፣ በእንጦጦ ዳገት ላይ ባቡር መንገድ የተሠራው በ1897 ዓ.ም. ነው፡፡ መንገዱ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በእንጦጦ ዳገት ላይ እየተጥመዘመዘ እስከ ማርያም ቤተክርስቲያን ድረስ በመሐንዲሱ በሙሴ ካስተኛ ተቀይሶ ዳገቱ እየተቆፈረ መደልደሉን ብላታ መርስኤ ሐዘን ወልደቂርቆስ ‹‹የዘመን ታሪክ ትዝታዬ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ›› በሚለው መጽሐፋቸው አስፍረውታል፡፡ ‹‹ባቡር መንገድ›› የሚባለው ለመኪና ማስኬጃ እንደሚስማማ ተደርጎ ከመሠራቱ ባለፈ ባህር ዛፍም ተተክሏል፡፡ ከዚህ ቀደም በ1878 ዓ.ም. እንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን የታነፀች ሲሆን፣ አፄ ምኒልክም በሥራዎቹ ላይ ይገኙ ነበር፡፡
አፄ ምኒልክ እንጦጦን ከተማ ካደረጉበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ሃይማኖታዊና መንግሥታዊ እንዲሁም የግል ተቋማት ሥፍራውን ለማልማት ቢረባረቡም፣ እንጦጦ ከአዲስ አበባ ቀድማ የመቆርቆሯን ያህል አልለማችም፡፡ ከቱሪስት የምታስገኘው ገቢም እንደ ጥንታዊነቷ አይደለም፡፡ በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእንጦጦ አረንጓዴ መቀነት የሚያርፍ፣ የጉለሌና የየካን ተራሮች የሚያካትትና ለአዲስ አበባ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚቆጠር ትልቅ ፕሮጀክት ለእንጦጦ ልማት አቅዷል፡፡ ዕቅዱም የእንጦጦ፣ የጉለሌና የየካ ሰንሰለታማ ተራራዎችን ያከተተ 4,200 ሔክታር መሬትን የቱሪስት መዳረሻ ማድረግ ነው፡፡
እንጦጦና አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ስትራቴጂ ዕቅድ ተዘጋጅቶም ሰኔ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በሰኔ 2009 ዓ.ም. አጋማሽ መገባደጃ ላይ የእጦጦና አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻ ፕሮጀክት አስመልክቶ ወደ ትግበራ ከመገባቱ በፊት፣ ከታሪክ ምሁራን፣ ከሥነ ሕንፃ ባለሙያዎች በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ከተሰማሩ ተቋማትና ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተደርጎ ሐሳቦች እንዲካተቱ እንደሚደረግ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባና የከተማዋ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሸን ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ድሪባ ኩማ ተናግረው ነበር፡፡ በዚህም መሠረት አዲስ አበባ ከቱሪስት መስህብ የምታገኘውን ገቢ ያሳድጋል የተባለውንና በእንጦጦ ጥብቅ ደን፣ በየካ ዋሻ ሚካኤልና ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን ይዞ በተራራማው 4,200 ሔክታር መሬት ላይ በሚያርፈው ፕሮጀክት ረቂቅ ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችና ግብዓቶች ተሰጥተዋል፡፡
በአረንጓዴው የእንጦጦ ሰንሰለት የሚያርፍ የፈረስ መጋለቢያ ሥፍራ፣ የቱሪስት ማረፊያ ቦታዎች፣ የቱሪስት መረጃ መስጫ ማዕከል፣ የአዕዋፋት ዕይታ ሥፍራዎች፣ አፀደ እንስሳት፣ የአየር ላይ የኬብል መኪና ኢኮሎጂና ሪዞርቶች በስፍራው የሚገነቡ የቱሪስት አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ናቸው፡፡
የባህል ማዕከል ግንባታ ከዕቅዶቹ አንዱ ሲሆን፣ በዚህ ሥር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዕውቅና የሰጣቸውን 76 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚወክል የባህል ማዕከል ይኖራል፡፡ የዕደ ጥበባት ማሠልጠኛ፣ ማሳያና መሸጫ ማዕከል እንዲሁም የአዲስ አበባ ማማ ይገነባል፡፡
ፕሮጀክቱ የስፖርቱን ዘርፍ ያካተተ ሲሆን፣ የመሮጫ መም፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የአትሌቶች ዌልነስ ማዕከልና ካምፕም ይኖሩታል፡፡
የአካባቢን ተፈጥሯዊ ሀብት በመጠቀም፣ የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ ቅርሶችን በመጠበቅና በማልማት መካከልም ሚዛናዊ መስተጋብርን የሚፈጥር ፕሮጀክት መሆኑ ተነግሯል፡፡
አዲስ አበባ ከያዘቻቸው ስድስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነውን እንጦጦና አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻ የማድረግ ፕሮጀክት፣ በረቂቅ ደረጃ በተቀመጠው መሠረት 4.8 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር የሚፈጅ ሲሆን፣ ግንባታውም ከአምስት እስከ አሥር ዓመት ይወስዳል፡፡ ሥራ በጀመረ በስድስት ዓመት ውስጥ ወጪውን ይሸፍናል ተብሎ የተገመተ ሲሆን፣ በአሥር ዓመት ውስጥ ደግሞ 63 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በእንጦጦ አረንጓዴ ሰንሰለት ውስጥ በሚገኙት ጉለሌና የካ ክፍለ ከተሞች፣ በስተሰሜን ሴፕቴምበር 11፣ በስተደቡብ አዲስ አበባ ከተማ፣ በስተምዕራብ ፍተሻ በስተምሥራቅ የካ አባዶ ወሰኑን አድርጎ የሚሠራው የቱሪዝም ልማት፣ ለቱሪዝም ዘርፍ ቅድሚያና ትኩረት በመስጠት ከዓለም በ118ኛ፣ በመሠረተ ልማት 134ኛ፣ በተወዳዳሪነት 118ኛ፣ (ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም 2016) የምትገኘውን ኢትዮጵያ፣ ደረጃ ያሻሽላል፣ በአፍሪካም በ2013 ዓ.ም. ከአምስቱ የቱሪስት መዳረሻ አገሮች አንዷ ለማድረግ ለተጀመረው ሥራ ግብዓት ይሆናል፡፡
የእንጦጦና አካባቢው የቱሪስት መዳረሻ ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በ2009 ዓ.ም. ባደረገው ዳሰሳ፣ በፕሮጀክቱ በተያዙ ሥፍራዎች ጥንቸል፣ ቀበሮ፣ ሚዳቋ፣ ጦጣ፣ ጅብና ጃርት የሚገኙ ሲሆን፣ ከአዕዋፋት አቢሲኒያን ካትበርድና የሎው ፍሮንትድ ፓሮት (ብርቅዬ ዝርያዎች ናቸው)፣ 11 ብርቅዬ ሊሆኑ የተቃረቡ እንዲሁም አራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሥጋት ውስጥ ያሉ አዕዋፋት ይገኛሉ፡፡
ከአዕዋፋትና ከዱር እንስሳት በተጨማሪ የእንጦጦ አብዛኛው ክፍል በባህር ዛፍ ቢሸፈንም፣ የፕሮጀክት ሥፍራው በሚያርፍባቸው ስፍራዎች የአበሻ ጥድ፣ ወይራ ዛፍ፣ አልፎ አልፎ የኮሶ ዛፍ፣ የዝግባ ዛፍ፣ ባዝራ ግራር፣ አጋምና ቀጋም ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ስፍራው ዛፍ የሞላበት ቢመስልም ውስጡ የተራቆተ በመሆኑ ፕሮጀክቱ የተጎዱ ስፍራዎችን መልሶ የማልማት፣ ባህር ዛፎችን በአገር በቀል የመተካትና አካባቢውን በደን የማልበስ ዕቅድ አለው፡፡ 
በአረጓዴ ሰንሰለት (በፕሮጀክቱ) ውስጥ የሚገኙት ክፍለ ከተሞች ጉለሌና የካ ሲሆኑ፣ በጉለሌ ሦስት፣ በየካ ስምንት ወረዳዎች ላይ ፕሮጀክቱ ያርፋል፡፡ በየካ 8,291 የግል ይዞታ (አባዎራ) 99 መንግሥታዊና ሃይማኖታዊ ተቋማት እንዲሁም 38 የቀበሌ ቤቶች በአጠቃላይም 8,428 ስፍራዎች በይዞታ ሥር ያሉ ሲሆን፣ በጉለሌ የግል 388፣ መንግሥታዊና ሃይማኖታዊ ተቋማት አራት እንዲሁም የቀበሌ ቤቶች 85 በአጠቃላይ 477 ይዞታዎች አሉ፡፡ ፕሮጀክቱም ይህንን ታሳቢ አድርጎ የሚተገበርና በመልሶ ልማቱ የሚነሱ ይዞታዎችንና ነዋሪዎን ጥቅም የሚያስጠብቅ ይሆናል፡፡
ከ12 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል የተባለው ፕሮጀክት፣ ለልማት ተነሺዎች ቅድሚያ የሥራ ዕድሎች የሚያስገኝ ሲሆን፣ በተራራው ዙሪያ ያሉ አጎራባች ማኅበረሰቦች በሁለተኛ ደረጃ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ የፕሮጀክቱን ማኅበራዊ ዘላቂነት ለማረጋገጥም ልማቱ ከአካባቢው እሴቶች ጋር ተስማሚ ይደረጋል፡፡
አምፊቲያትርን ጨምሮ የተለያዩ ሙዚየሞችን በሚያካትተው በዚህ ፕሮጀክት፣  ከተለያዩ ተቋማት የተሰባሰቡ ባለሙያዎች በቢሾፍቱ በተካሄደው ውይይት ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፕሮጀክቱ መልካም መሆኑን ገልጸው፣ ፕሮጀክቱ ከመነሻው የሚያካትታቸው ስፍራዎች እንጦጦና አካባቢው የሚል እንደነበር በማስታወስ የኦሮሚያን ወሰን መካለሎች ታሳቢ ያደረገ እንደማይመስልና ግልጽ ያልሆኑ የኦሮሚያና አዲስ አበባ ግንኙነት ባለበት ፕሮጀክቱ መፈጸሙ ችግር እንዳይፈጥር ዳግም ቢታይ የሚል ሐሳብ አቅርበዋል፡፡
አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ጋር ያለው የወሰን ግንኙነት ሰፊ በመሆኑም ይህን ቢያገናዝብ፣ ቱሪዝም ለፍትሐዊነት ሀብት ክፍፍል ጥሩ ሚና ቢኖረውም፣ በግልጽ ፍትሐዊ የሚያስብለው የቱ ጋር ነው? ብዙ ነገሩ ከባለሀብት ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ይህ ማኅበረሰቡን በሰፊው የሚነካ ስለሆነ በዚህ መልኩ ብናየውም ብለዋል፡፡
ባህላዊ ሙዚየሙ የታሰበው የብሔር ብሔሰቦች መንደር ነው፡፡ ነገር ግን የፌዴራል ድርሻ ምንድነው? ይህ ቢታይ የሚል ሐሳብም አቅርበዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የፕሮጀክቱ የቦርድ አባል ዶ/ር ሙሉጌታ ፍሰሃ፣ በተራራው ዙሪያ በአጎራባች አካባቢዎች የአካባቢ ማኅበረሰብ በልማቱ ተሳታፊ እንዲሆንና በፕሮጀክቱ ዕቅድ ከተካተቱት ኢንቫይሮመንትና ኢኮኖሚ ቀጣይነት ጎን ለጎን የባህል ቀጣይነት ወሳኝ ስለሆነ ይህ እንዲታሰብ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበርን ወክለው የተገኙት ዶ/ር ቴድሮስ አጥላባቸው፣ ዕቅዱን ወደ ተግባር መወለጥ መልካም ቢሆንም፣ ሥራው ትልቅ ከመሆኑ አንፃር አንዴ ከመተግበሩ በፊት ኢኮሎጂውን እያዩ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በአንድ ጊዜ ስንት ሰው ያስተናግዳል? ምን ዓይነትን አገልግሎት ይሰጣል? ሆቴል ከሆነ ይህን ያህል መኝታ፣ መዋኛ ከሆነ መተንተን አለበት ብለዋል፡፡
አካባቢውን እንደ አንድ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግም በስፍራው የፖሊስ፣ የጤና ፖስት፣ የባንክ አገልግሎትና ሌሎችም ከማስፈለጋቸው በተጨማሪ የሙዚቃ ጋለሪ አምፊቲያትሩ ውስጥ ሊኖር ቢችልም፣ የሙዚቃ ጋለሪ ለብቻ ያስፈልጋል፣ ቴሌስኮፕ ተደርጎ ከዋከብት የሚታይበት ስፍራም ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡
በአካባቢ ያሉት ፕሮጀክቶች ማለትም ሔሪቴጂ ትረስት ሴቴምበር 11፣ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከልና ሌሎቹም ስፍራውን ለማልማት እየሞከሩ መሆኑ ተገልጾም፣ የአዲስ አበባው ፕሮጀክት ከነዚህም ጋር ተጣምሮ መሥራት እንዳለበት ሐሳብ ተሰንዝሯል፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተገኙት ቀሲስ ሰለሞን ቶልቻ፣ ቤተክርስቲያኒቷ በፕሮጀክቱ አካባቢ አራት ቤተክርስቲያናት እንዳሏት፣ ቤተክርስቲያኒቷ ከምትሰጠው አገልግሎት ውስጥ በእንጦጦ ማርያም ምዕመኑ ከመቶ ዓመት በፊት አገልግሎት የሚያገኝበት የፀበል ቦታና የቀብር ስፍራ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ ቦታው የቱሪስት መዳረሻ ሲደረግ ዘመናዊ የቀብር ቦታ እንዲገነባና በፀበል ቦታውም የመፀዳጃ አገልግሎት ታሳቢ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ በደርግ ጊዜ የተሠራው የእንጦጦ ሙዚየም ጠባብ ቢሆንም ብዙ ቅርሶች እንዳሉት ጠቁመው፣ እንጦጦ ማሪያም ሙዚየም በአንዴ 50 ሰው መያዝ እንደማይችል፣ የቱሪስት መስህቦችም በመጋዘን ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ እነዚህ መኖራቸውንም አውቆ ከቤተክርስቲያኒቷ ጋር ቢሠራ፣ ቤተክርስቲያኒቷ ለመተባበር ፍላጎት እንዳላትም አክለዋል፡፡
አረንጓዴውን የተፈጥሮ ሀብት ከመጠበቅ አኳያ የከተማውን መሬት ያጥለቀለቀው የፌስታልና የፕላስቲክ ውኃ መያዣ አደብ ሊበጅለት ይገባል ያሉት ቀሲስ ሰለሞን፣ ኬንያ ፌስታል ምርት ለአገር ጠንቅ ነው በሚል ማገዷን በማስታወስ፣ በአገራችን የውኃ ፕላስቲኮች ተመልሰው ጥቅም ላይ ካልዋሉ በስተቀር ፕሮጀክቱ ቢሠራ በፌስታልና በውኃ ፕላስቲክ ይበከላል፣ ለዚህ ምን ታስቧል? ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ቤተክርሰቲያኒቷ ለፕሮጀክቱ ድጋፏን እንደምትሰጥ፣ ፕሮጀክቱም ቤተክርስቲያኒቷ ከምትሰጠው አገልግሎት ጋር ተጣጥሞ እንዲሄድ እንጠይቃለንም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የስፔስ ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብነት እዝራ በበኩላቸው፣ የስፔስ ሶሳይቲው ያለውን ኦብዘርቫቶሪ ቱሪስቶች ለመጎብኘት እንደሚመጡ በማስታወስ፣ አዲሱ ፕሮጀክት የተረሳውን ሳይንስና ቴክኖሎጂ በተለይ ስፔስ ሳይንስን እንደ ቱሪስት መዳረሻ ቢጠቀመውና ሳይንስና ቴክኖሎጂን የሚወክል ሙዚየም ቢሠራ መልካም ነው ብለዋል፡፡
የቱሪስት መስህብ ባህል ብቻ ከሚሆንና ዓለምም ሳይንስና ቴክኖሎጂን እየተጠየቀመው ስለሆነ፣ ፕሮጀክቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም ቢኖረው፣ ገቢውን በ40 እና 50 በመቶ ይጨምረዋል የሚል አስተያየትም ሰንዝረዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወንዞች ጽሕፈት ቤት የተገኙት አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ ፕሮጀክቱ የቀረው ነገር እንዳለ ነው የተገለጹት፡፡ የፕሮጀክት አዋጭነት መልካም መሆኑን ገልጸው፣  ከከተማ ፕላንና ከኢንቫይሮመንት አንፃር ፕሮጀክቱ ምን ማለት ነው? የሚሉት እንዲታዩ የሚከተሉትን አንስተዋል፡፡
እንደ አቶ ዋለልኝ አዲሱ የከተማ መዋቅራዊ ፕላን 22 ሺሕ ሔክታር መሬት ለኢንቫይሮመንት ብሎ ትቷል፡፡ በዚህ ውስጥ ለአረንጓዴ ብቻ ሳይሆን ወንዝና ሌሎችም አሉ፡፡ አሁን ፕሮጀክቱ የሚያርፍበት በፕላኑ ከሰው ንክኪ ጥብቅ ተብሎ የተቀመጠ ነው፡፡ የቀረበው ፕሮፖዛል ደግሞ ጥብቅ ከተባለው ሥፍራ ሁለት በመቶ ያህል ይሸፍናል፡፡  ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ የሚዘልቀው የእንጦጦ አረንጓዴ ቀበቶ ተራራ በብዛት ከኢንቫይሮመንት አገልግሎት ውጪ እየዋለ ነው፡፡
ቦታው የከተማዋ መተንፈሻና ከተማዋን ከጎርፍ ለመጠበቅ የሚውል መሆኑን፣ መለስ ፋውንዴሽን፣ ሔሪቴጅ ትረስትና ሌሎችም፣ ከ8,000 በላይ ነዋሪዎች በውስጡ መኖራቸውን በመጥቀስ ‹‹ይህ ፕሮጀክትና ሌሎችም ለምን እንጦጦ ላይ ብቻ ይሆናሉ? ከተማዋ በተራራ የተከበበች ነች፡፡ ለምን ሌሎች ተራሮች አይታዩም? የእንጦጦ ተራራ ለምን በፕሮጀክቶች ይታጠራል?›› የሚል አስተያየትም ሰጥተዋል፡፡
በፕሮጀክቱ የተለያዩ ዓይነት የመኝታ ክፍሎ ያሏቸው ሞቴል ወይም ሆቴልስ፣ የተራራ ሪዞርትና ኢኮ ሎጅ እንደሚኖሩ የተቀመጠ ሲሆን፣ አቶ ዋለልኝ መኝታ ክፍሎች እዚያው መኖራቸውን አልደገፉትም፡፡ በሰጡት አስተያየትም፣ ቱሪስቶች ተራራው ላይ ደርሰው፣ መስህቦችን ዓይተው መመለስ አለባቸው እንጂ አዚያው ማደር የለባቸውም፣ ሌሎች አገሮችም ይህንን ይከተላሉ ብለዋል፡፡
በአካባቢው ከዚህ ቀደም ያሉ ፕሮጀክቶች ከአዲስ አበባው ጋር እንዲተሳሰሩ፣ ሱሉልታ የአትሌቲክስ መንደር እያለ በሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት እጦጦ ላይ መገንባቱ አዋጭ ያደርገናል ወይ? የሚልም ተነስቷ፡፡ ጎልፍ የለንም፣ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች የሚፈልጉት ነው፡፡ ከዓለም አቀፍ ደረጃ አንፃር አንድ ያለንም በቂ አይደለም፡፡ ይህ ቢታይም ተብሏል፡፡ ከኦሮሚያ ባህል ማዕከል የተወከሉት ባለሙያ ደግሞ፣ አዲስ አበባ እንደ ከተማ መስተዳደር ክልሎችን ወክሎ ነው የባህል ማዕከልን የሚሠራው? ወይስ ከክልል ጋር ተቀናጅቶ? የፌዴራል ሚና ውስጥ የገባ ይመስላል ብለዋል፡፡
በፕሮጀክቱ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶች ይገነባሉ የሚለውንም፣ በየክልሉ ቅርሶቹ በአካል እያሉ የክልሎችን ሀብት አይሻማም ወይ? ለምሳሌ ኮንሶን፣ አክሱምንና ፋሲልን እዚህም ማምጣት መገንባት ምን ያህል አዋጭ ነው? ቱሪስቱ ቦታው ድረስ ሄዶ ማየት የለበትም ወይ? እንዴት ታዩታላችሁ?ም ብለዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፂያን ማኅበር የተወከሉ ባለሙያም፣ አዲስ አበባ የኢትዮጵያና የአፍሪካ መዲና ከመሆኗ አንፃር በፕሮጀክቱ የሚሠሩ ሪዞርቶችና ሌሎችም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሉ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡ አብዛኛዎቹ የአገሪቱ ሆቴሎች ኢትዮጵያዊነት ስለማይታይባቸው ቱሪስቶቹ የሚገኙት በመሸታ ቤቶችና በዝቅተኛ ስፍራ መሆኑን መታዘባቸውን በመግለጽ፣ የእንጦጦው ፕሮጀክት ፈጠራ በተሞላበት እንዲሠራ፣ ተቆርቋሪነት እንዲፈጠርና ኅብረተሰቡ ለቱሪስቱ የሚናገረው ወግ መኖር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከ200 በላይ ባህላዊ ስፖርቶች እንዳሏት በማስታወስም፤ ከእነዚህ ለፕሮጀክቱ አመቺ የሆኑ እንዲካተቱ፣ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክም ቢቃኝ የሚል ሐሳብ ተሰንዝሯል፡፡
በፕሮጀክቱ እንደ ፈረንሣዩ ኤፍል ታወር ያለ የአዲስ አበባ ማማ ተራራው ላይ ለመገንባት የታቀደ ሲሆን፣ ይህ ለገሃር አካባቢ ቢሆን የሚል አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
ከጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞችና ጀግኖች ማኅበር የተገኙት ሻምበል ዋኘው ዓባይ፣ ‹‹የአርበኞች ታሪክ የታሪክ ማኅደር ነው፡፡ ይህ በፕሮጀክቱ በሚሠራው ሙዚየም ላይ አልተካተተም፡፡ አንድ አገር ከመነሻው ማሰብ አለበት፡፡ ለቱሪዝም መስክ ገቢ የሚያስገኙ መሣሪያዎችም አሉ፤›› በማለት የጀግኖች አርበኞች ታሪክ ያለበት ሙዚየም በፕሮጀክቱ እንዲካተት ጠይቀዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው፣ ‹‹ረቂቅ ስትራቴጂ ዕቅዱ ላይ የተለያዩ አካላትን ጨምረን ያወያየነው ያላየነውን እንድታሳዩን፣ የረሳነውን እንድታስታውሱንና ማካተት ያለብንን እንድትነግሩን ነው፤› ብለዋል፡፡ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች መልስ የሰጡት የእንጦጦና አካባቢው የቱሪስት መዳረሻ ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ህያብ ገብረፃዲቅ፣ ፕሮጀክቱ አዲስ አበባ ክልል ውስጥ ብቻ እንደሚያርፍ እስከ ሱሉልታ የሚደርሰውን የኦሮሚያ ቱሪዝም ቢሮ ቢያለማው የሚል ሐሳብ እንዳለ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር እንጦጦ፣ የካና ጉለሌ ላይ እንደሚሠራና ኃላፊነቱም በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሥፍራዎች መሆኑን አክለዋል፡፡
የባህል ማዕከሉን በተመለከተም፣ አዲስ አበባ ቢሠራውም የሚያለሙት ክልሎች መሆናቸውንና በዚህ ላይ ከክልሎች ጋር ውይይት እንደሚኖር አክለዋል፡፡
በአካባቢው ላይ እየሠሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችም ወደ ልማቱ እንደሚገቡ፣ አብረው እንደሚሠሩና ከአካባቢ ጥበቃ ጋርም የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም ዝግጅት መኖሩን ተናግረዋል፡፡
በአካባቢው ያሉ ሃይማኖታዊ ተቋማት ሀብቶች በመሆናቸው፣ በስፍራው ዘመናዊ መቃብር ለማድረግ ውይይት ላይ መሆናቸውን ከቤተክርስቲያን ጋር አብረው እንደሚሠሩም አክለዋል፡፡  
የሳይንስ ሙዚየም እንዲኖር ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ አቃቂ አካባቢ ዘመናዊ የሳይንስ ሙዚየም ስላለ ተደጋጋሚ እንዳይሆን መተውን፣ ጎልፍ በቦሌ አካባቢ ለመሥራት በከተማዋ ማስተር ፕላን ስላለም በእንጦጦው የታሰበው መሰረዙን ተናግረዋል፡፡
የአትሌቲክስ ልዩ ሙዚየም፣ ዓባይ ልዩ ሙዚየምና ቡና ልዩ ሙዚየም እንደሚኖር፣ ተረስቶ የነበረው የአርበኞች ሙዚየምም በጥናት እንደሚገባ፣ በፕሮጀክቱ ላሊበላ፣ ጢያና ሌሎችን ቅርሶች የሚመስል መሠራቱ  ታሪኩን ለማሳየትና የቱሪስቱን ፍላጎት ለማነሳሳት እንጂ የክልሎችን ድርሻ ለመሻማት ወይም ቅርሶችን ደግሞ ለመሥራትና ለመተካት እንዳልሆነ፣ ፕሮጀክቱም ሌሎችን የመተካት ሳይሆን እንደ ማነሳሻ የማሳየት እንደሆነ አክለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ልዩ መለያ የሚሆን 500 ሜትር ርዝመት ያለው ማማ የሚገነባ ሲሆን፣ አናቱም የኦዳ ቅርፅ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ በኦዳና በገዳ መካከል ልዩነት መኖሩ በውይይቱ በመነሳቱ፣ ይህን ባለሙያዎች አይተውት የሚስተካከል ይሆናል ተብሏል፡፡
የመጀመሪያ ዙር ዲዛይን ሲቀርብና ሲተች፣ የጎደሉ ሙሉ እንደሚሆኑ ለዲዛይን ሥራውና ጥናቱ ብዙ ጊዜ እንደሚሰጥና የማያዳግም ሥራ እንደሚሠራም ታክሏል፡፡
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረፃዲቅ ሐጎስ፣ በበኩላቸው፣ ከኦሮሚያ ድንበር ጋር ያለውን ሁኔታ አስመልክተው፣ ጥናቱ በዓለም ባንክ ድጋፍ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር መጠናቱን፣ ለዚህም በቱሪዝም ዙሪያ ለውጥ ለማምጣት በተመረጡ አካባቢዎች ማለትም ላሊበላ፣ አክሱም፣ አዲስ አበባና አካባቢዋ በሚል መጠናቱን፣ ቢሮውም አዲስ አበባ ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ብሎ የተነሳበትን እንጦጦን እንደሚያለማና በቀጣይ ሌላ ሠርተው ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ጥናቱ በአገር ደረጃ ሲሠራ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያ ጋር የሚገናኙ የእንጦጦ አካባቢዎች ተያይዘው ተሠርተው የነበረ ቢሆንም፣ ረቂቅ ስትራቴጂክ ዕቅዱ የተዘጋጀው በጥናቱ መሠረት ሳይሆን እንጦጦ ዋሻ ሚካኤል፣ የካ አካባቢና ከጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል አካባቢ ያሉትና አዲስ አበባ ክልል ውጥስ ብቻ የሚገኙ መደረጋቸውን፣ ገልጸዋል፡፡ ወደፊት ከወሰን ጋር ያለው መስመር ሲይዝ በሱሉልታና በሌላም በኩል ያለውን ከኦሮሚያ ክልል ጋር በጋራ ለማልማት የሚከለክል ነገር እንደሌለ በመጥቀስም፣ ከአዲስ አበባ ጀምረን ወደፊት ከኦሮሚያ የሚዋሰኑት ላይ አብሮ ለመሥራት ይቻላል ብለዋል፡፡
ከማስተር ፕላኑና ከአካባቢ ጥበቃ አንፃርም ፕሮጀክቱ የአካባቢውን ደን የሚጋፉ እንደማይሆን፣ 98 በመቶውን ደን በጠበቀ መልኩ የሚሠራ እንደሆነና በጥንቃቄ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡
ዲዛይኑን በሚመለከት ከህዳሴ ግድብ ተለይቶ እንደማይታይ፣ ብዙ መታየት የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉና ለዲዛይኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጨረታ እንደሚወጣ ተናገረዋል፡፡
የባህል ማዕከሉን በተመለከተ አዲስ አበባ የብሔር ብሔረሰቦች መቀመጫ፣ ትንሿ ኢትዮጵያ እንደመሆኗ ይህንን የሚያሳይ የባህል ማዕከል በአገሪቱ አለመኖሩ፣ ከተማዋ በየቦታውም ለምን የባህል ማዕከል የላትም? ከተማዋ ያስፈልጋታል የሚል አስተያየት ሲሰጥ በመክረሙ የፕሮጀክቱ አንዱ አካል ተደርጓል፡፡
በማዕከሉ የሚሠሩት የቅርስ ናሙናዎች ክልሎችን የሚሸፍኑ ሳይሆኑ፣ ወደ ከተማዋ የሚገባ ቱሪስት የባህል ማዕከሉን ሲጎበኝ ሌሎች ክልሎች ያለውን ፀጋ ዓይቶ ስፍራው ለመሄድ እንዲነሳሳ የሚያደርግና የክልሎችን ተጠቃሚነት የሚደግፍ እንጂ የሚሻማ አይሆንምም ብለዋል፡፡
ይዘቱን በሚመለከት ከክልሎች ጋር በጋራ የሚመከርበት ሲሆን፣ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር ምክክር ተጀምሯል፡፡ ፕሮጀክቱ የሁሉም ኅብረተሰብ የጋራ አጀንዳ ከተደረገ በኋላም ወደ ትግበራ እንደሚገባ አክለዋል፡፡
ኬብል ካር ውድ ነው፣ ለውጭ ሰው ነው የታሰበው፣ አገሬውስ ውድ አይሆንበትም ወይ? ተብሎ ለቀረበው ጥያቄም፣ አገሬውም የውጭውም የተሻለ መዝናኛ አካባቢ እንዲያገኝ ታስቦ የሚሠራው ነው ተብሏል፡፡
አቶ አባተ በበኩላቸው፣ ቱሪዝም ሲታሰብ ተባብሮና ተመጋግቦ እንደሆነ ገልጸው፣ ሲንጋፖር ላይ የኢትዮጵያ መስህብ እንዳለ በመጠቆም፣ ፕሮጀክቱ ለአንድ አገር ለአንድ ዓላማ ተብሎ የሚሠራ መሆኑን፣ ከወሰን ጋር ያለውን አዲስ አበባና ኦሮሚያ ተነጋግረው በጋራ እንደሚፈቱት፣ በዋናነት ተደጋግፈን ብናለማው ምንኛ አካባቢውንና አገራችንን ይጠቅማል፣ ውብ ብናደርገው መልካም ነው ብሎ ማሰብ እንደሚገባና ወሰኑ እንደማያስጨንቅ፣ ሊያስጨንቅ የሚገባው በጋራ እንዴት አልምተን፣ አካባቢውን ውብ እናድርገው፣ እንዴትስ ሕዝቡንና አገሪቷን ተጠቃሚ እናደርግ? ለሚለው መሆን እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
እንጦጦ በደን የተሸፈነ ቢመስልም ውስጡ ሲገባ 60 በመቶው የተራቆተ መሆኑን በመናገርም፣ ሥፍራውን በአረንጓዴ መሸፈን፣ የተራቆተውን ማልማት የፕሮጀክቱ አካል እንደሆነ፣ ግንባታው በሙሉ ባህላዊ እንደሚሆንና ዲዛይኑ በጥልቀት እንደሚሠራና ውይይት እንደሚደረግበት ተናግረዋል፡፡
ውይይቱን የዘጉት ከንቲባ ድሪባ ኩማ፣ ‹‹ፕሮጀክቱ ተፈጥሮ የለገሰችንን ፀጋ ወደ ተጨባጭ ጥቅም ለመቀየር የተጀመረ ነው፤›› በማለት፣ አዲስ አበባ በተራሮች የተከበበች ብትሆንም ተራሮቿና ወንዞቿ የውበትና የሥልጣኔ ምንጭ መሆን ሲገባቸው ተበክለው ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱንም ይህንን የሚቀለብስ፣ አዲስ አበባንና ኢትዮጵያን የቱሪስት መዳረሻ የሚያደርግና ለውጥ የሚታይበት ብለውታል፡፡  Read more here

የታክስ ግምቱና የአነስተኛ ነጋዴዎች እሮሮ

በብርሃኑ ፈቃደና በዳዊት እንደሻው
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በደረጃ ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች ላይ ባስቀመጠው አዲስ የታክስ ምጣኔ ሳቢያ በአዲስ አበባ ከተማ አራቱም ማዕዘናት ከፍተኛ እሮሮ እየተደመጠ ይገኛል፡፡ በርካቶች በቀን ገቢ ግምት ስሌት እንዲሁም በዓመታዊ ሽያጫቸው መሠረት የተጣለው ታክስ  በየተጋነነ ነው በማለት፣ ቅሬታውን ለማቅረብ የክፍለ ከተማና የወረዳ ጽሕፈት ቤቶችን ሲያጨናንቁ ታይተዋል፡፡
ሰሞኑን በተፈጠረው በዚሁ የታክስ ግርግር ሳቢያ በርካታ ክስተቶች ተስተናግደዋል፡፡ በርካቶች ሲላቀሱ ታይተዋል፡፡ በየቀበሌው በድንጋጤ አቅላቸውን ስተው የሚዘረሩ ሰዎችም አልታጡም፡፡ ሪፖርተር በተጨባጭ ለማረጋገጥ ባይቻለውም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ በቀን ግምት የሦስት ሺሕ ብር ታክስ ተጥሎባቸው ከድንጋጤ ብዛት መፀዳጃ ቤት ውስጥ ሞተው እንደተገኙ የአካባቢ ሰዎች ሲናገሩ የተመደጠ፣ የሰሞኑ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል፡፡
ወ/ሮ ራሔል ስጦታው 24 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በምግብ ንግድ ሥራ የምትተዳደር ስትሆን፣ አምስት ጠረጴዛዎችና 17 ወንበሮችን በምትይዘው ‹‹ቁርስ ቤቷ›› በቀን ከ15 እስከ 20 እንጀራ በመሸጥ ላለፉት ሦስት ዓመታት ስትሠራ እንደቆየች ለሪፖርተር ገልፃለች፡፡ ወ/ሮ ራሔል እንደጠቀሰችው፣ እነዚህን ዓመታት ከሰዎች በመደበር የጀመረችውን ሥራ ለማደራጀትና ቤተሰቧን ለማስተዳደር ስትጣጣር ቆይታለች፡፡ እስካሁንም ገንዘብ ላበደሯት ሰዎች ዕዳዋን ለመመለስ በምትሯሯጥበት ወቅት፣ የቤት ኪራይ ስለተጨመረባት የንግድ ፈቃዷን በመመለስ ምግብ ቤቷን ለመዝጋት እየተዘጋጅ ባለችበት ወቅት አዲሱ የታክስ ዱብ ዕዳ እንደመጣባት ትናገራለች፡፡ በወር ስምንት ሺሕ ብር ኪራይ የምትከፍልበት ንግድ ቤት፣ ወደ 15 ሺሕ ብር ብር ጨምሯል በመባሏ ነበር ሥራውን ለማቆም የወሰነችው፡፡  
ወትሮውንም በወር ይህን ያህል የቤት ኪራይ እየከፈለች ስትሠራ የቆየችው የተበደረችውን ዕዳ መክፈል ግድ ስለሆነባት እንጂ፣ አቅሙ ኖሯት ሥራውን እንዳልገባችበት ገልፃለች፡፡ ከሰዎች 40 ሺሕ ብር ያህል ተበድራ፣ ሥራውን ስትጀምር የስድስት ወር ቅድሚያ ክፍያ መጠየቋ ነበር የመጀመሪያው ችግር፡፡ በብድር ካገኘችው ገንዘብ ላይ ቀናንሳ ብትከፍልም ሥራው የታሰበውን ያህል አልሆነም፡፡
በዚያም ላይ የኩላሊት በሽተኛ በመሆኗ እና እንደልቧ ጎንበስ ቀና ብላ መሥራት ባለመቻሏ፣ ሥራውን በአግባቡ ለማስኬድ መቸገሯን ጠቅሳለች፡፡ እንዲህ እየተፈተነች ባለችበት ወቅት፣ በዓመት 49 ሺሕ ብር የታክስ ዕዳ ሲመጣባት የምትጨብጠው፣ የምትይዝ የምትሆነው እንዳጣች እንባዋን እያዘራች ገልጻለች፡፡ በየዓመቱ 5,700 ብር ያህል ስትከፍል ብትቆይም ይህም ቢሆን ከአቅሟ በላይ ሆኖባት ስትፍጨረጨር መቆየቷን አስታውሳ፣ አዲስ የተጠየቀችውን የምትከፍልበት የሥራ እንቅስቃሴ እንደሌለ በመግለጽ አቤቱታ ማስገባቷንም ገልጻለች፡፡
‹‹እኔ ይህንን ያህል መክፈል አልችልም፡፡ ተቀጥሬም ሆነ እንደሌሎች ጓደኞቼ ስደት ሄጄ መሥራት አልችልም፡፡ በሽተኛ ነኝ ስላቸው እጄን ይዘው አስወጡኝ፡፡ የሚሰማን ሰው የለም፡፡ አታፍሪም ብትችይ አይደል እንዴ ይህን ያህል ጊዜ ስትሠሪ የቆየሽው? ካልቻልሽ ለምን በስድስት ወር ውስጥ አትዘጊውም ነበር፤›› እንዳሏት እሷም ‹‹ነገ የተሻለ እሠራለሁ በማለት የተሸጠው ተሽጦ የተረፈውን በልቼ ማደሬን እንጂ ትርፍ እስካሁን አላገኘሁም፡፡ እስካሁን የተሳካልኝ ነገር ቢኖር የነበረብኝን ብድር መመለስ መቻሌ ነው፤›› ያለችው ራሔል፣ ኑሮ ይባስ እየተወደደ፣ በመጣበት ወቅት ሁለት መንታ ልጆቿን ጨምሮ እናትና አባት የሌላቸው እህት ወንድሞቿን ለማስተዳደር ቀና ደፋ በምትልበት ወቅት እንዲህ ያለው ጉድ ያውም ከመንግሥት መምጣቱ ቅስሟን ከመስበር አልፎ፣ በሕይወት ተስፋ እንዳይኖራት ማድረጉን ጠቅሳለች፡፡ 
እንዲህ ያሉ ታሪኮች የተደመጡበት የዚህ ዓመት የታክስ ጉዳይ የሁሉም ሰው መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በርካቶች በመንግሥት ላይ ብሶታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡ ከስድስት ዓመታት በፊትም እንዲሁ ተመሳሳይ ቅሬታዎች በመንግሥት ላይ ሲሰነዘሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአሁኑን ይበልጥ አሳሳቢ ያደረገው ግን መንግሥት ባሻሻለው የታክስ ምጣኔ መሠረት ከታችኛው ክፍል ወደ ላይ መሔድ የሚገባቸው በርካታ ግብር ከፋዮችን ለማግኘት በማሰብ፣ የታክስ መሠረቱን የማስፋት ዕርምጃው አካል እንደሆነ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም የደረጃ ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች ዓመታዊ የሽያጭ መጠን እስከ 500 ሺሕ ብር እንዲሆን በመደረጉ፣ በዚህ መደብ ውስጥ የሚገቡት ነጋዴዎች ምንም እንኳ የገቢ መጠናቸው ዝቅተኛ ነው ቢባልም መክፈል የሚገባቸው የታክስ መጠን ላይ የተደረገው ማሻሻያ ግን ከአቅማቸው በላይ መሆኑን በምሬት እያስተጋቡ ይገኛሉ፡፡
ሪፖርተር ስለዚሁ ጉዳይ ተዘዋውሮ መረጃ ካጠናቀረባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ቦሌ ቡልቡላ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ የሚገኙ አነስተኛ ነጋዴዎችም እንደሌሎቹ አካባቢዎች ሁሉ ‹‹ታክስ አንፈልም አላለንም፡፡ ለዓመታት ስንከፈል ኖረናል፡፡ የአሁኑ ግን ከሚታሰበው በላይ ቅጥ ያጣና ከምናገኘው ገቢ ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ነው፤›› ያሉት በቦሌ ቡልቡላ በአነስተኛ መደብር ውስጥ ነጠላ ጫማና ሌሎችም የፕላስቲክ ውጤቶችን የሚሸጡት አቶ አበራ ተሰማ ናቸው፡፡  አቶ አበራም ሆኑ በርካታ የእሳቸው ብጤ ነጋዴዎች የጋራ ቋንቋቸው የተጣለው የገቢ ግምት የአካባቢውን እንቅስቃሴ ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በዓመት 450 ብር ሲከፍሉ የነበረው የታክስ መጠን በአዲሱ ተመን መሠረት ከፍተኛ ጭማሪ እንዲኖረው በመደረጉ ተማረዋል፡፡
ጌሾና ብቅል የሚሸጡ፣ ጉልት የሚቸረችሩ፣ የ‹‹አርከበ ሱቅ›› በሚባሉት አነስተኛ መደብሮች ልዩ ልዩ ሸቀጦችን የሚነግዱ በጠቅላላው የታክስ ግመታው ከተጣለባቸው ከ150 ሺሕ የሚጠጉ ነጋዴዎች ውስጥ አብዛኛው በመንግሥት ላይ እሮሮውን እያሰማ፣ በየወረዳው ማመልከቻ ለመስገባት ሲጣደፉ ታይተዋል፡፡ ሆኖም አብዛኞቹ ከሦስት ወር በፊት ምላሽ እንደማያገኙ እየተነገራቸው፣ ጥቂት የማይባሉትም በአግባቡ የሚያስረዳቸው በማጣት መንገላታታቸውን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
የምሁራን ምልከታ
መንግሥት አብዛኛው ከታክስ መረብ ውጭ የሆነውን ነጋዴ ብቻም ሳይሆን፣ በታክስ ሥርዓቱ ውስጥ ተካቶም ተገቢውን ታክስ አልከፈለም ብሎ ባሰበው ክፍል ላይ የተከተለው አካሔድ ከግልጽነት ጀምሮ የአተገባበር ወጣ ገባነት እንደሚታይበት ሲገለጽ ይታያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕዝቡ እንዲዘጋጅበት የሚመጣው የታክስ ምጣኔ ድንገተኛ ከሚሆን ይልቅ ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር እየተገናዘበ የሚጣል መሆን ሲገባው፣ በአንድ ጊዜ ያውም ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ እንዲህ ከፍተኛ ጭማሪ አስከትሎ መምጣቱ ተቀባይነት እንደሌለው ከሚገልጹት ባለሙያዎች መካከል አንዱ ዶ/ር ታደሰ ሌንጮ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ታክስ ሥርዓት ውስጥ የዳበረ ልምድ ያላቸው ዶ/ር ታደሰ በኢትዮጵያ የታክስ ግመታ የሚካሔደበትን ሥርዓትና የሚጣለውን የግምት ታክስ መጠን ኮንነዋል፡፡
እንዲህ ያለው ሒደት በአንድ ጀምበር እንደማይከናወን፣ ይልቁንም የታክስ ግምቱ ከመቀመጡ በፊት ሰፊ የማጣራት ሥራዎች መከናወን እንደነበረባቸው አብራርተዋል፡፡ ለታክስ ግመታው የሚረዱ ሳይንሳዊ ዘዴዎች ቢተገበሩ ኑሮ የስህተት ደረጃውን ሊቀንሱት ይችሉ እንደነበር በመግለጽ፣ የታክስ ግመታው ከመደረጉ ቀደም ብሎም ከነጋዴው ማኅበሰረብ ጋር በመነጋገርና መግባባት ላይ በመድረስ ለግምት ስለሚጠቀምባቸው ዘዴዎችና የአተማመን ሒደቶች አመላካች ነጥቦችን ማብራራት ይጠበቅበት እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹በትክክል ሠርተውት ቢሆን ኑሮ ይህ ሁሉ ሰው አይቃወማቸውም ነበር፤›› ብለዋል፡፡ ይልቁንም የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋናው ዓላማ የታክስ ገቢውን ማሳደግ ብቻ እንዳስመሰለውም ከመግለጽ አልተቆጠቡም፡፡ በመሆኑም የተከተሉት የትመና ሥርዓት ሳይንሳዊ እስካልሆነ ድረስ፣ የሕዝቡም ተቃውሞ እስከቀጠለ ድረስ ፖለቲካዊ ሚና ሊኖረው እንደሚችልም አሳስበዋል፡፡ በመሆኑም የታክስ አስተዳደሩ ባለሥልጣናት ከበላይ ስልክ ተደውሎላቸው ተዉ ሊባሉ እንደሚችሉም ከሚታየው የሕዝቡ ቅሬታና ተቃውሞ በመነሳት ግምታቸውን በማስቀመጥ መንግሥት የተመነውን የታክስ መጠን ሊያነሳ እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡
የተቃማዊ ፓርቲዎች መግለጫ
ሆኖም ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታክስ ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ነፃነት አበራ፣ ሰዎች ቅሬታ ካላቸው በተናጠል እንደሚስተናገዱ ተናግረዋል፡፡ በቡድን ለሚቀርብ የትኛውም ዓይነት ጥያቄ ምላሽ እንደማይሰጥ የጠቀሱት ወ/ሮ ነፃነት፣ ታክስ ከፋዮችን በተናጠል በመገምገም የታክስ ግምቱ እንደተጣለባቸው በማስታወቅ የሚቀርብ ቅሬታ ካለም በዚሁ አግባብ ብቻ እንደሚስተናገድ ገልጸዋል፡፡
እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ በተናጠልም ቢሆን የሚቀርበው ቅሬታ ተገቢውን ምላሽ እንደማያገኝ ታክስ ከፋዮች እየተናገሩ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር አሁን ታክስ ከፋዮቹ አሁን የተጠየቁት የታክስ መጠን ሙሉውን እንዳልሆነና በመጪው በጀት ዓመት ሙሉውን መጠን መክፈል እንደሚጠበቅባቸው እየተነገራቸው በመሆኑ፣ ቅሬታቸውን እያባባሰው እንደሚገኝ ሲገልጹ ይደመጣል፡፡
የሰሞኑን የታክስ ግርግር በመንተራስ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) ሰኔ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. ባወጡት መግለጫ፣ ‹‹በአዲስ አበባ ነጋዴዎች ላይ የተተመነው ከአቅም በላይ የሆነ የግብር ዕዳ እንዲሻሻል አጥብቀን እንጠይቃለን፤›› ብለዋል፡፡ በፓርቲዎቹ መግለጫ መሠረት ይህ የግብር ዕዳ ዜጎች በአገራቸው ነግደው ለማደር ያላቸውን ተስፋ የሚያሟጥጥና ለስደት የሚዳርግ ከመሆኑም በላይ በስደት የሚገኙ ወገኖችም ወደ አገር ቤት ለመመለስ ፈቃደኛ እንዳይሆኑ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ዋነኛው እንደሚሆን እና መንግሥትም ልብ ሊለው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በተጣለባቸው ከፍተኛ የግብር ጫና ምክንያት የንግድ ፈቃድ ለመመለስና ከሥራ ለመውጣት የጠየቁ ነጋዴዎች እስከ ጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም. ድረስ መመለስ እንዳይችሉ መከልከላቸውን ፓርቲዎቹ ተቃውመው፣ መመለስ ቢችሉ እንኳ ሥራ ካቆሙበት ጊዜ ጀምሮ ንግድ ፈቃዳቸውን እስከመለሱበት ጊዜ ድረስ ያለውን የገቢ ግብር በአዲሱ ተመን መሠረት መክፈል እንዳለባቸው መቀመጡንም ኮንነዋል፡፡ በመሆኑም መኢአድና ሰማያዊ የመንግሥትን ድርጊት በማውገዝ ባለአራት ነጥብ የአቋም መግለጫውን ይፋ አድርገዋል፡፡
ምንም እንኳ ነጋዴዎቹም ሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ምሁራንም ጭምር የመንግሥትን የግምት ታክስ አሠራር ቢቃወሙም፣ መንግሥት ግን ሊከፈለው የሚገባ በርካታ ገንዘብ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. በፓርላማ መዝጊያ ንግግራቸው፣ ይህ የታክስ አሠራር እንደሚቀጥል ቆፍጠን ባለመንገድ አስታውቀዋል፡፡
በሚቀጥለው በጀት ዓመት መንግሥት ከከተማው ታክስ ከፋዮች እንደሚሰበስብ ያስታወቀው የታክስ መጠን 26 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት ባለሥልጣኑ የሰበሰበው መጠን 129.6 ቢሊን ብር ሲሆን ከዕቅዱ የ18 ቢሊን ብር ያህል ቅናሽ ያሳየ መጠን እንደሆነም አስታውቋል፡፡ አብዛኛውን አገሪቱን የልማት ወጪዎች በራስ አቅም ለመሸፈን ባለው አቋም መሠረት 80 በመቶ ያህል ወጪዎቹን በዚሁ አግባብ ከአገር ውስጥ ምንጮች ለመሸን እንደቻለም ሲገልጽ ይደመጣል፡፡ ይሁንና አሁንም ድረስ በታክስ መረብ ውስጥ ያልተካተተ ሰፊ የንግድ ማኅበሰረብ እንደሚገኝ ሲገልጽ ዋናው መደበቂያ ደግሞ የደረጃ ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች ውስጥ የሚገኙት እንደሆኑ አስታውቋል፡፡ ከዘጠኝ ሺሕ ያላነሱ ነገር ግን ከፍተኛ ግብር ከፋይ መሆን የሚገባቸው ነጋዴዎች እንደሚገኙ መንግሥት ያምናል፡፡
በሌላ በኩል ከተቀጣሪዎች የሚሰበሰበው የታክስ መጠን ከፍተኛ የመሆኑን ያህል ከነጋዴው የሚገኘው ከሚጠበቀው ይልቅ አነስተኛ መሆኑ ብቻም ሳይሆን አብዛኛው ኅብረሰተብ ታክስ የመክፈል ልማድ ባለማዳበሩ ችግሮች እንደሚከሰቱ ይገልጻል፡፡ ምንም እንኳ መንግሥት በግምት የሚጣለውን የታክስ ሥርዓት እንደማያምንበት ከዚህ ቀደም ቢያስታውቅም፣ አማራጭ ስሌለው ግን ይህንኑ መንገድ እንደተከተለም ይጠቅሳል፡፡
ይህም ሆኖ ባለሥልጣኑ ታክስ ከፋዩ ‹‹ባመነው ልክ ይክፈል፤›› የሚል አሠራር እንደሚከተል በዚሁ አግባብም ታክስ እንደሚያስከፍል ቢናገርም፣ በተግባር ግን ልምድ የሌላቸው ገማቾችን በየመደብሩ በማሰማራት ግምት ማውጣቱ ሲኮነን ቆይቷል፡፡ ከስድስት ዓመታት በፊት እንደተደረገው ዘንድሮም ተመሳሳዩ አካሔድ የተተገበረ ሲሆን፣ የዘንድሮው ግን ሁለት ጊዜ እንደተካሔደ ይታወቃል፡፡ በመጀመሪያው ዙር የተደረገው ግመታ ተቀባይነት በማጣቱ በድጋሚ እንዲገመት የተደረገበት አግባብም በአብዛኛው ነጋዴ እሮሮ እንዲነሳበት ምክንያት ሆኗል፡፡ Read more here

ቴዲ አፍሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ለሚያዘጋጀው ኮንሰርት የመንግሥትን ይሁንታ እየጠበቀ ነው

ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ‹‹ኢትዮጵያ›› የተሰኘውን አልበም ካወጣ በኋላ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ የመጀመርያውን ኮንሰርት ለማቅረብ የመንግሥትን ይሁንታ እየጠበቀ ነው፡፡
ድምፃዊው ጳጉሜን 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ መዘጋጀቱን፣ ማኔጀሩ አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ኮንሰርቱን አልበሙን ያከፋፈለው ኩባንያ ጆይ ኤቨንትና ፕሮሞሽን ኩባንያ ከኤፕላስ ኤቨንትና ፕሮሞሽን ኩባንያ ጋር በጥምረት የሚያዘጋጁት መሆኑን፣ ጆይ ኤቨንት የሚሊኒየም አዳራሽን ከሚያስተዳድረው አዲስ ፓርክ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ጆይ ኤቨንት ኮንሰርቱን ለማዘጋጀት የሚያስችል ዕውቅና ለማግኘት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ለሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ፈቃድ ማሳወቂያ ክፍል ጥያቄ ማቅረቡም ታውቋል፡፡
የአዲስ ፓርክ ዴቨሎፕመንትና ማኔጅመንት ኩባንያ የማርኬቲንግና የሰው ኃይል መምርያ ኃላፊ አቶ ስለሺ ለማ፣ ሰኔ 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት በጻፉት ደብዳቤ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ኮንሰርት በሚሊኒየም አዳራሽ ለማካሄድ ፕሮግራም መያዙን ገልጿል፡፡ ‹‹ለፕሮግራሙ ተገቢው ትብብር ይደረግለት ዘንድ እንጠይቃለን፤›› በማለት አቶ ስለሺ በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው የኮንሰርት ጥያቄ መቅረቡን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ነገር ግን ከሚመለከተው አካል ጋር ንግግር ከተደረገ በኋላ ምላሽ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡
ለዚህ ኮንሰርት ቴዲ አፍሮ 1.8 ሚሊዮን ብር እንደሚከፈለው፣ ለሚሊኒየም አዳራሽ የዕለቱ ዝግጅት ኪራይ 1.2 ሚሊዮን ብር ክፍያ ለመፈጸም ስምምነት ላይ መደረሱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ቴዲ አፍሮ የአዲስ አበባውን ኮንሰርት ካካሄደ በኋላ በሐዋሳ፣ በጎንደርና በመቀሌ ተጨማሪ ኮንሰርቶችን እንደሚያካሂድ ከስምምነት ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
‹‹ኢትዮጵያ›› የተሰኘውን አልበም ጨምሮ አራት አልበሞቹን ለአድማጮች አቅርቧል፡፡ ከአልበም በተጨማሪ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን በተለያዩ ጊዜያት ያቀረበ ሲሆን፣ ሥራዎቹ በአድናቂዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እንደነበራቸው ይታወቃል፡፡    Read more here

ጥቂት ዕውነቶች ስለጣና ሐይቅ፤

Captureq
ጥቂት ዕውነቶች ስለጣና ሐይቅ፤

1. ከ10% እስከ 15% ወይም ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የዐማራ ሕዝብ ኑሮው የተመሠረተው በጣና ሐይቅ ላይ ነው፡፡ የባሕር ዳር ከተማን ጨምሮ በምዕራብ ጎጃም፣ በደቡብና በሰሜን ጎንደር ዞኖች የሚገኙ 54 ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት ኢኮኖሚያዊ መሠረታቸው ከጣና ሐይቅ በሚገኝ የአሣ ምርትና መስኖ ነው፡፡ 
2. የኢትዮጵያን 50% የንጹህ ውኃ ክምችት የያዘ ጣና ነው፡፡ 
3. ከ40 በላይ ወንዞችና ጅረቶች ወደ ጣና ሐይቅ ይፈሳሉ፤ የዓለማችን በርዝመቱ ትልቁ ወንዝ ዓባይ ከጣና ሐይቅ ይነሳል፡፡ ወደ ሐይቁ ከሚገቡ ወንዞችና ጅረቶች መካከል ግልገል ዓባይ፣ ርብ፣ ጉማራ፣ እንፍራንዝና መገጭ ይገኙበታል፡፡
4. በጣና ሐይቅ ውስጥ ከ31 በላይ ደሴቶች አሉ፡፡ ትልቁ ደሴት የደቅ ደሴት ሲሆን 16 ካሬ ኪሎ ሜትር አለው፤ 4,816 ሰዎች በደሴቱ ላይ ይኖራሉ፡፡ ደሴቶቹ በጥንታዊ ገዳማትና ታሪክ የታጨቁ ናቸው፡፡ ረዥም እድሜ ያለው ገዳም የጣና ቂርቆስ ሲሆን በብሉይ ዘመን የኦሪት መስዋት ሲሰዋባቸው ከነበሩት ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ እንደ አንቀጸ ብርሃን፣ ዚቅና የዜማ ድርሰቶች የደረሰው በዚሁ ደሴት ገድሞ ነው፡፡
5. የጣና ሐይቅ በትንሹ 19 ዓይነት ገበሎ አስተኔዎች፣ 35 ዓይነት ተሳቢዎች፣ 28 ዓይነት አጥቢዎችንና 437 ዓይነት የተለያዩ አእዋፋትን የያዘ ነው፡፡
6. የጣና ሐይቅ ምድቡ በከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኝ ሲሆን ከባሕር ወለል በላይ 1800 ሜትር ከፍ ያለ ነው፡፡
7. ሐይቁ 90 ኪሎ ሜትር የዲያሜትር ርዝመትና የ385 ኪሎ ሜትር የጠርዝ ርዝመት አለው፡፡ የሐይቁ ጥልቀት ከ4 እስከ 14 ሜትር ጥልቀት ሲኖረው አማካይ ጥልቀቱ 8 ሜትር አካባቢ ነው፡፡ ቀደም ሲል 9.8 ሜትር አማካይ ጥልቀት እንደነበረው ይገመታል፡፡
8. የሐይቁ ስፋት 3672 ካሬ ኪሎ ሜትር የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ 3000 ብቻ ቀርቷል፡፡ 672 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሆነው ውኃ ደርቋል ወይም ወደ የብስነት ተቀይሯል፡፡
9. የጣና ሐይቅን አደጋ ላይ የጣሉ አራት ምክንያቶች እስካሁን በውል ተለይተው ታውቀዋል፡፡ እንደጥፋት መጠናቸው ቅደም ተከተል የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ፣ የእንቦጭ አረም፣ የከተሞች ፍሳሽና በደለል መሞላት ናቸው፡፡ የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ የሐይቁ ጥልቀት ከ50 ሣ.ሜ በላይ ጥልቀት ቀንሷል፡፡ ከጎንደርና ከባሕር ዳር ከተማዎች የሚወጣ ወደ ሐይቁ የሚለቀቅ ቆሻሻ ሐይቁን እየበከሉት ነው፡፡
10. ከእምቦጭ አረም ውጭ ሌሎች ሁለት የተለያዩ መጥፎ አረሞች ጣናን እንደወረሩት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እንቦጭ በጣና ላይ የተከሠተው በፈረንጆች አቆጣጠር በ2011 ሲሆን እንቦጭ ቆቃን ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ ሐይቆች ውስጥ እንደነበረ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡
11. በ2014 እና 15 በጣና ሐይቅ ላይ በእንቦጭ ተሸፍኖ የነበረው የጣና ክፍል 20 ሺህ ሔክታር ቢሆንም በ2017 ወደ 24 ሺህ ሔክታር ከፍ ብሏል፡፡
12. እምቦጭ 50 በመቶ የሚሆነውን የሐይቁን ጠርዝ ወሮታል፡፡ እምቦጭ ወደ ጣና የገባው በመገጭ ወንዝ ጫፍ አካባቢ እንደሆነ ሲገመት በፎገራ በኩል ከሩዝ ምርት ጋር ሌሎች ሁለት መጥፎ አረሞች እንደገቡ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ሁለቱ ሌሎች መጤ አረሞች Azolla እና water lettuce በመባል ይታወቃሉ፡፡ Read from the source here

Monday, July 3, 2017

አምስት አርቲስቶች በወንጀልና በሽብርተኝነት ተከሰሱ

Image result for ኦነግ ባንዲራ
ሁከትና አመፅን የሚያነሳሱ ዜናዎች፣ ግጭቶችና ሙዚቃ በማዘጋጀት፣ ከኦነግ ባንዲራና ወታደሮች ጋር በማቀናበርና ወደ ውጪ በመላክ በዩቲዮብ ላይ እንዲጫን አድርገዋል የተባሉ 5 የኦሮሞ አርቲስቶችን ጨምሮ 7 ግለሰቦች ትናንት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ የሽብርና የወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ 

በክስ መዝገቡ ስር የተካተቱት 7 ተከሳሾ አርቲስት መሆናቸው የተመለከተ ሲሆን አሊያድ በቀለ፣ ኢፋ ገመቹ፣ ሃይሉ ነጨ፣ ሴና ሰለሞን፣ ኤልያስ ክፍሉና በግል ስራ እንተዳደራለን ያሉት ሞይቡሊ ሞስጋኑና ቀነኒ ታምሩ ናቸው፡፡ 

በግለሰቦቹ ላይ ሁለት ክሶች የቀረቡ ሲሆን በአጠቃላይ የክሶቹ ጭብጥ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የወጣቶች “ሰገሌ ቄሮ” ድምፅ ዜና አዘጋጆችና ዜና አንባቢዎች በሚል ቡድን ራሳቸውን በማደራጀት፣ ዜና በማዘጋጀት ውጪ ላሉት የኦነግ አባሎችና አመራሮች በመላክ፣ በነሱ አማካኝነት ለተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች እንዲሰራጩ በማድረግ ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳት ስራ ላይ የቆዩ ሲሆኑ በፈፀሙት የሽብር ድርጅት ውስጥ በመሳተፍና የሽብር ተግባር በማሴር፣ በማዘጋጀትና በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸው ተመልክቷል፡፡ 

ተከሳሾቹ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ስለ ሀገሪቱ ፖለቲካ ቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ ሁከትና አመፅ የሚያነሳሱ ዜናዎችን በኦሮሚኛና በአማርኛ ቋንቋ አዘጋጅተው በድምፅ በመቅረፅ ማሰራጨታቸውም በክስ መዝገቡ ተጠቅሷል፡፡ 

ትናንት አርብ ሰኔ 23 በፍ/ቤቱ ክሳቸው በንባብ የተገለፀላቸው ተከሳሾቹ፣ የክስ መቃወሚያቸውን እንዲቀርቡ ለሐምሌ 7 ቀን 2009 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡ Read more here

የበቀለ ሞላ ሆቴል ለሁለት ገዢዎች መሸጡ ውዝግብ ፈጥሯል


በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከሚገኙ የታዋቂው በቀለ ሞላ ሆቴሎች መካከል አንዱ የሆነውና በባሌ ዞን በሲናና ወረዳ ሮቤ ከተማ የሚገኘው ሆቴል ለሁለት መሸጡ በፍ/ቤት እያከራከረ ነው፡፡ 

የሆቴሉ ባለቤቶች ሆቴሉን ለሁለት ገዢዎች እንደሸጡት መሆኑን ከክስ መዝገቦቹ መረዳት የተቻለ ሲሆን 4 ግለሰቦች በጋራ በ24 ሚሊዮን ብር ሲገዙት፣ ሳናቴ ትሬዲንግ ደግሞ በ33 ሚሊዮን ብር እንደገዛው ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

ሰኔ 18 ቀን 2008 ዓ.ም ሆቴሉን በጋራ የገዙት አቶ ንዋይ ከበደ፣ አቶ አብርሃም ጌታሁን፣ አቶ አለሙ ንጉሴና አቶ ደምስ አበበ የተባሉ ግለሰቦች ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የፍ/ብሔር ቢፒአር ችሎት ባቀረቡት ክስ፤ ሆቴሉን በ24 ሚሊዮን ብር ለመግዛት ተስማምተው የነበረ ቢሆንም በውላቸው መሰረት ሆቴሉን የራሳቸው ማድረግ አለመቻላቸውን አስረድተዋል፡፡ 
የግዥ ውሉን በተፈራረሙበት ቀን ቅድመ ክፍያ 4 ሚሊዮን ብር ከፍለው ቀሪውን 20 ሚሊዮን ብር ደግሞ እስከ ህዳር 30 ቀን 2009 ዓ.ም ለማስረከብና ሆቴሉም በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ዝውውሩን እንዲያደርግላቸው ተዋውለው የነበረ ቢሆንም ተፈፃሚ ሳይሆንላቸው መቅረቱን ከክስ አቤቱታው መረዳት ተችሏል፡፡ 

ከሳሾች በውላቸው መሰረት፤ ሆቴሉን ባለመረከባቸው ውሉን ያፈረሰው የሆቴሉ ባለቤት የቅድመ ክፍያውን 4 ሚሊዮን ሁለት እጥፍ ማለትም 8 ሚሊዮን ብር እንዲከፍላቸው እንዲሁም ቀደም ሲል በገቡት ውል መሰረት የሀብት ዝውውር እንዲከናወንላቸውና ድርጅቱን መረከብ እንዲችሉ ይደረግላቸው ዘንድ አመልክተዋል፡፡ 

ተከሳሽ በቀለ ሞላ ሆቴሎች በበኩሉ፤ ለቀረበበት ክስ በሰጠው ምላሽ፤ በ24 ሚሊዮን ብር ለመሸጥ የተደረሰ ስምምነት መኖሩን በመግለፅ የተፈረመው የስምምነት ሰነድ “የውል ረቂቅ” እንጂ “ውል” ባለመሆኑ፣ ገዥዎች በረቂቅ ውሉ መሰረት በተቀመጠላቸው ቀነ ገደብ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው የተፈጠረ ችግር መሆኑን ጠቁሟል፡፡  ከሳሾች በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ቀሪ ክፍያ 20 ሚሊዮን ብር በመክፈል ግዴታቸውን አለመፈፀማቸውን የጠቀሰው ተከሳሽ፤ “የገዙትን ሆቴል ዋጋ በሙሉ እስከ ህዳር 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ መክፈል ነበረባቸው፤ ይህን ግዴታቸውን ሳይወጡ ሻጩ ግዴታውን አልተወጣም የሚል ጥያቄ ወይም ክስ ሊያቀርቡ አይችሉም” ብሏል፡፡ 

ከሳሾች የራሳቸውን ግዴታ ሳይወጡ ተከሳሹ ድርጅቱን ያስረክብ የሚል ክስ ማቅረብ አይችሉም ያሉት የበቀለ ሞላ ሆቴሎች፤ 8 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው የጠየቁትም ህጋዊ መሰረት ስለሌለው ውድቅ እንዲሆን ፍ/ቤቱ ጠይቋል፡፡ 
በሁለቱ ወገኖች ክርክር መሃል የገባው ሳናቴ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በበኩሉ፤ ሆቴሉን በ33 ሚሊዮን ብር እንደገዛው፤ ክፍያውንም ሙሉ ለሙሉ ከፍሎ የቤቱን አስፈላጊ ሰነዶች መቀበሉንና በቦታው ላይም G+2 ህንፃ ለማሰራት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የዲዛይን ስራ ውል መግባቱን የክስ መዝገቡ ያመለክታል፡፡ 

ኩባንያው ለፍ/ቤቱ የዳኝነት ጥያቄ ባቀረበው ማመልከቻ፤ ከአራቱ ከሳሾች በበለጠ በንብረቱ ላይ የተሻለ መብት እንዳለው ጠቅሶ፤ ከሳሾች ያቀረቡት ክስ ውድቅ ተደርጎ የተጣለበት የእግድ ትዕዛዝ እንዲነሳለት ጠይቋል፡፡ ኩባንያው በክርክሩ ምክንያት ለጠበቃ አበል፣ ለቴምብር ቀረጥ፣ ለፎቶ ኮፒና ለመሳሰሉ ያወጣውን ወጪ እንዲተኩለት ይወሰንለት ዘንድም ፍ/ቤቱን ጠይቋል፡፡ 
የግራ ቀኙን ክርክሮች እያዳመጠ የሚገኘው ፍ/ቤቱ፤ መዝገቡን ለህዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም ቀጥሮታል፡፡ Read more here

Sunday, June 25, 2017

የፕሮፌሰር አስራት ወልደዬስ አጭር የህይዎት ታሪክ

Image may contain: 5 people, people standing
አስራት ወልደዬስ ከአባታቸው ከአቶ ወልደዬስ አልታዬና ከእናታቸው ከወይዘሮ በሰልፍይዋሉ ጽጌ ሰኔ 12 ቀን 1920 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአስራት አባት አቶ ወልደዬስ አልታዬ በጸሓፊ ትዕዛዝ ኃይሌ ወልደ-ስላሴ አስተዳደር ውስጥ በጸሃፊነትና በአስተዳደር ተግባር የተሰማሩ ነበሩ፡፡ እናታቸውም በአነስተኛ ንግድ የተሰማሩ ነበሩ፡፡ ፕሮፌሰር አሥራት የሶስት ዓመት ህጻን እያሉ ወላጆቻቸው በፍች ምክንያት ስለተለያዩ ከእናታቸው ጋር ወደ ድሬዳዋ አቀኑ፡፡ አስራት ድሬዳዋ በነበሩበት ወቅት ጣሊያን ኢትዮጵያን ትወራለች፡፡ በዚህ ወቅት በእነ ሞገስ አስግዶምና አብርሃም ደቦጭ ግራዚያኒ ላይ የተደረገ የግድያ ሙከራን ለመበቀል ከግራዚያኒ በተላለፈ በቀል በሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ33 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በዶማ፤ በአካፋና በገጀራ ተጨፍጭፈው ተገደሉ፡፡ የአስራት አባት አቶ ወልደዬስ አልታዬም እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተጨፍጭፈው በአርበኝነት ሞቱ፡፡ እናቱ ወይዘሮ በሰልፍይዋሉ ጽጌም የባለቤታቸው ሞት ተጨምሮበት ብዙም ሳይቆዩ ታመው በሞት ተለዩ፡፡
ወላጆቹን በሞት የተነጠቀው ታዳጊ ከአያቱ ከወይዘሮ ባንቺወሰን ይፍሩ-ለሱሲሉ ጋር መኖር ጀመረ፡፡ አጎቱ አቶ ዘውዴ ወረደወርቅ እዚያው ድሬዳዋ ይኖሩ ነበርና ታዳጊውን የቄስ ትምህርት እንዲማር አስገቡት፡፡ የቄስ ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት በቀለም አቀባበሉ ጎበዝ ነበር ይላሉ አስተማሪው አለቃ ለማ፡፡ ምስክርነታቸውን ሲሰጡ ‹‹አስራት በልጅነት በጣም ጎበዝ በመሆኑ ዓመት ሳይሞላው ወንጌሉን ከቁጥሩ አንበልብሎ፤ ከፍካሬ እስከ ነቢያት ደግሞ ድቁና ተቀበለ›› ይላሉ፡፡ ከቄስ ትምህርቱ ጎን ለጎን ድሬዳዋ ይገኝ ከነበረው ፈረንሳይ ሚሲዮን ገብቶ ቀለም መቁጠር ጀመሮም ነበር፡፡ የእናቱ አባት ቀኛዝማች ጽጌ ወረደወርቅ ታዋቂ አርበኛ ነበሩ፡፡ በመሆኑም ጣሊያን አርበኞችን ወደ ጣሊያን ሐገር ወስዶ በሚያስርበት ወቅት ቀኛዝማች ጽጌም አንዱ ታሳሪ ነበሩ፡፡ ቀኛዝማች ጽጌ ከሶስት ዓመት ተኩል እስር በኋላ ሐገራችን ነጻ ወጥታ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ አስራትን አዲስ አበባ አስመጥተው በ1934 ዓ.ም ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት አስገቡት፡፡ ትምህርት ቤት በገባ በአመቱ በ1935 ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ከአጠቃላይ ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት የካሜራ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ በወቅቱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል ላቅ ያለ ውጤት ያስመዘገቡትን ወደ ውጭ ሐገር ልኮ ማስተማር ተጀምሮ ነበርና አስራትም በዚሁ የትምህርት ዕድል ምክንያት ግብጽ ወደሚገኘው የእንግሊዞች ቪክቶሪያ ኮሌጅ ተላከ፡፡ በቪክቶሪያ ኮሌጅ ለአምስት ዓመታት ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በስኮላሽፕ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ እንግሊዝ ሐገር እስኮትላንድ ኤደንብራ ዩንቨርስቲ አቀና፡፡ በወቅቱ ህግ እንዲያጠና ከትምህርት ሚንስቴር ቢነገረውም አሻፈረኝ ብሎ ህክምና ኮሌጁን ተቀላቀለ፡፡
ትምህርቱን እንደጨረሰም ፈጥኖ ወደ ሐገሩ ተመለሰ፡፡ በወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚንስተር የነበሩት አውቁ አርበኛ ደጃዝማች ጸሐይ እንቁስላሴ አስጠርተው የጤና ሚንስትርነቱን ቦታ እንዲይዝ ይጠይቁታል፡፡ ዶክተር አስራት ግን አይሆንም ሲል ተቃወመ፡፡ በዚሁም የተነሳ የልዕልት ጸሃይ ሆስፒታልን ተቀላቀለ፡፡ ለአምስት ዓመታት በልዕልት ጸሐይ ሆስፒታል ካገለገለ በኋላ ለተጨማሪ ትምህርት ወደ እንግሊዝ ሐገር አቀና፡፡ አደንብራ ዩንቨርሲቲ ገብቶ ቀዶ ህክምናን አጠና፡፡ በቀዶ ህክምና ዘርፍ አስራት የመጀመሪያው ኢትየጵያዊ ሐኪም ነው፡፡ ከዚህ በኋላ አስራት በእድሜም በማዕረግም እያደገ ስለሆነ አንቱ አያልን አንናገራለን፡፡ እነ ዶክተር አስራት እስኪተኩት ድረስ የሀገራችን የህክምና ዘርፍ በነጮች የተያዘ ነበር፡፡ ዶክተር አስራት ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን የህክምና ማሰልጠኛ እንዲከፈት በመወትወታቸው ምክንያት የጥቁር አንበሳን ሆሰፒታል እውን አደረጉ፡፡ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሲቋቋም የቴክኒክ ኮሚቴውን የመሩት ዶክተር አስራት ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ በ1965 ዓ.ም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እውን ሲሆን ፕሮፌሰር አስራት ተባባሪ ፕሮፌሰር በመሆን የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ዲን ሆኑ፡፡
በደርግ ወቅትም በካድሬዎች ይደረግባቸው የነበረውን ከፍተኛ ጫና ተቋቁመው ሐገራቸውን ሳይለቁ ህዝባቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በወቅቱ በተደጋጋሚ ዘመቻ የተላኩ ሲሆን የሄዱበትን ዘመቻ በክብር ለመወጣት በቅተዋል፡፡ በዚህም መሰረት በ1968 ዓ.ም በቀዳጅ ሐኪምነት በቃኘው ሆስፒታል አስመራ፤ በ1969 ዓ.ም እንደገና በቃኘው ሆስፒታል አስመራ፤ በ1970 ዓ.ም በራዛ ዘመቻ በቀዳጅ ሐኪምነት እና ቡድን መሪነት በመቀሌ ሆስፒታል፤ እንዲሁም በሰኔ 1971 ዓ.ም በቀዳጅ ሐኪምነት ምጽዋ ዘምተው ግዳጃቸውን ተወጥተዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም በህክምናው ዘርፍ ‹‹አስራት የተባለ ጸበል ፈልቋል›› እስከመባል የደረሰ አንቱታን ያተረፉ ብቁ ሐኪም ነበሩ፡፡ ኢህአዴግ ከሌሎች 42 ምሁራን ጋር ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በ1985 ዓ.ም እስከሚያባርራቸው ድረስ በትጋት ያገለገሉ የሐገር ባለውለታ ነበሩ፡፡ በሙያቸው የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን ጥቂቶቹን ለመዘርዘር ያክል የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የፈረሰኛ ደረጃ፤ የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን የፈረሰኛ ደረጃ፤ የአብዮታዊ ዘመቻ አርማ ፤ አለም አቀፍ የወርቅ ሜርኩሪ (በግል አስተዋጽኦ)፤ የቀይ ባህር ኒሻን አንደኛ ደረጃ ይገኙበታል፡፡
የደርግ ስርዓት ተሸንፎ ኢህአዴግና ሻዕቢያ ስልጣኑን በተቆጣጠሩበት ወቅት ሰኔ 24 ቀን 1983 ዓ.ም በተደረገው የሽግግር መንግስት ቻርተር ውይይት ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ወክለው የተገኙት ፕሮፌሰር አስራት ‹‹ሐገር ላስገነጥል ተወክዬ አልመጣሁም›› በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ብቸኛው ሰው ነበሩ፡፡ ‹‹ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ምንም ጉዳይ ሊወስን፤ ሊያግድ ወይም ሊሰርዝ አይችልም›› በማለት ጉባኤው እያደረገው ያለው ውሳኔ ኢ-ዲሞክራሲያዊ መሆኑን አስረግጠው ሞገቱ፡፡ በዚህ ንግግራቸውም የተነሳ ከጉባኤው ሲወጡ ብዙ ማስፈራሪያና ዛቻ ያካሂዱባቸው ነበር፡፡
በወቅቱ በኮንፈረንሱም ሆነ በሽግግር መንግስቱ ምንም ውክልና ያልነበረው የአማራ ህዝብ በየአካባቢው ግፍና መከራን ማስተናገድ ጀመረ፡፡ ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸው ምሁራን በመነጋገር የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትን ታህሳስ 2 ቀን 1984 ዓ.ም መሰረቱ፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበርም ፕሮፌሰር አስራት ሆነው ተመረጡ፡፡ ፕሮፌሰር አስራት የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ ድርጅታቸውን ማስተዋወቅና የተቃጣውን የዘር ፍጅት ለመመከት ጥረት አደረጉ፡፡ ከሐገር ውጭ ጉዞ በማድረግ በስዊድን፤ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ፤በሎሳንጀለስና ኒዮርክ በመዟዟር የድጋፍ ቻፕተሮችን አቋቋሙ፡፡ በሐገር ውስጥ በነበረው የህዝብ ጥያቄ መሰረት በደብረ ብርሃን ዘርያዕቆብ አደባባይ ታህሳስ 11 ቀን 1985 ዓ.ም በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ታሪካዊ ንግግር አደረጉ፡፡ የድርጅታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቀባይነት ማግኘት እረፍት የነሳው የሽግግር መንግስት ፕሮፌሰሩን ‹‹ጦርነት ቀስቃሽ ንግግር›› አድርገዋል ሲል ከሰሳቸው፡፡ የዚህን ንግግር ጦርነት ቀስቃሽ መባል የሰማ የአካባቢው ህዝብም ‹‹እስካሁን አማርኛ እናውቃለን ስንል ኖረናል፡፡ አሁን ግን በሽግግር መንግስቱ በአዲስ መልክ መማር ሊገባን ነው›› ሲል ምጸቱን ገልጾ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተጠርተው በ50 ሺህ ብር ዋስና ከአገር እንዳይወጡ እገዳ ተጥሎባቸው ተለቀቁ፡፡ በዚያው ዓመት ከጎጃም ከመጡ አርሶ አደሮች ጋር አሲረዋል በሚል ‹‹ለጥያቄ ይፈለጋሉ›› ተብለው ሐምሌ 5 ቀን 1985 ዓ.ም ተጠርተው ለ24 ሰዓታት ከታሰሩ በኋላ በ20 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀቁ፡፡ ከዚያ በኋላ ሐምሌ 12 በነበረው ተለዋጭ ቀጠሮ ዋስተናቸው ተነስቶ ለ43 ቀናት ከታሰሩ በኋላ ነሐሴ 24 ቀን 1985 ዓ.ም ሊፈቱ ችለዋል፡፡ በወቅቱ በተደጋጋሚ እየተጠሩ ዋስትና ከመጠየቃቸው የተነሳ ‹‹የዋሶች ባንክ ማደራጀት ሳይኖርብኝ አይቀርም›› ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸው ነበር፡፡
ከተደጋጋሚና አሰልች የፍርድ ቤት ምልልስ በኋላ ሰኔ 20 ቀን 1986 ዓ.ም የዋለው ችሎት ከጎጃም ገበሬዎች ጋር አስረዋል በሚለው ክስ የሁለት ዓመት እስር ተፈረደባቸው፡፡ ሐገራቸውን በታማኝነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ ሽማግሌ በጡረታ እድሜያቸው ከርቸሌ ወረዱ፡፡ በወቅቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሰሩን ‹‹የህሊና እስረኛ›› ሲላቸው የፍርድ ሒደቱንም ‹‹መረጃ አልባ›› ሲል አጣጥሎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በእንጥልጥል የቆየው ደብረ ብርሃ ንግግር ክስ ተቀስቅሶ በሳምንት እስከ ሶስትና ሁለት ጊዜ ፍርድ ቤት እየተመላለሱ የሰላቻቸው ፕሮፌሰር አስራት ‹‹የምታውቁትን ውሳኔ የዛሬ 6 ወይም 9 ወር ከምትሰጡኝ ዛሬውኑ አሳውቁኝና እስር ቤት ቁጭ ብዬ መጽሐፍ ላንብብ›› ሲሉ ለችሎቱ በምሬት ተናግረው ነበር፡፡ ታህሳስ 18 ቀን 1987 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፕሮፌሰሩን የ3 አመት አስር በየነባቸው፡፡ በዚህ ሒደት ውስጥ ፕሮፌሰር አስራት ከ150 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል፡፡ ከርቸሌ ታስረው በነበረበት ወቅት ከፖለቲካ እስረኞች ተለይተው ከፍታብሔር እስረኞች ጋር እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን መጽሃፍትና ጠያቂም በፈለጉት መጠን አያገኙም ነበር፡፡
የእስር አያያዛቸው የከፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ1972 ዓ.ም የጀመራቸው የልብ ሕመም ተባብሶ እንዲሁም የስኳር መጠናቸው በመጨመሩ ከፍተኛ የጤና ችግር ላይ ወደቁ፡፡ ለብዙ በሽተኞች መድኀኒት የነበሩት አስራት ህክምና ተከልክለው የበሽታ መጫዎቻ ሆኑ፡፡ ከስኳራቸው ከፍ ማለት ጋር ተያያዞ አይናቸው ማዬት አልቻለም፡፡ ሰውነታቸውም እንደፈለጉ ሊታዘዛቸው አልቻለም፡፡ የልብ ድካማቸው ጨምሯል፡፡ ሕክምና እንዲያገኙ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ሳይቀር ደብዳቤ ጻፉ፡፡ መፍትሄ ግን አላገኙም፡፡ የኋላ ኋላ ሲዳከሙ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቢወሰዱም ህመማቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም እ.ኤአ ታህሳስ 27 ቀን 1988 ዓ.ም ወደ ውጭ ሐገር ሄደው እንዲታከሙ ተፈቀደ፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ በመድከማቸው አውሮፕላን ውስጥ በሐኪሞች እየታገዙ ወደ ለንደን ሆስፒታል በረሩ፡፡ ከ3 ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ አሜሪካ ሆስተን አመሩ፡፡ በአሜሪካ ቅዱስ ሉቃስ ኤጲስቆጳል ሆስፒታል በነበሩበት ወቅት እንደተሻላቸውና ከልቡ ሲያስባቸው ለነበረው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈው ነበር፡፡ ትንሽ እንደተሻላቸው ዘመዶቻቸው ወደሚገኙበት ፊላደልፊያ ከወር በፊት ተዛውረው በነበረበት ወቅት ባልታወቀ ምክንያት ህመማቸው ተባብሶ ተዳከሙ፡፡ ሞትን ድል ሲያደርጉት የኖሩት ሐኪም ግንቦት 6 ቀን 1991 ዓ.ም ፊላደልፊያ በሚገኘው ፔኒሲለቫኒያ ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዕለተ አርብ በተወለዱ በ71 ዓመታቸው አረፉ፡፡ በወቅቱ የፕሮፌሰሩን ሞት ትልልቅ የአለም መገናኛ አውታሮች ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ነበር፡፡
የፕሮፌሰሩ አስከሬን ታላላቅ እግንዶች፤ ቤተሰቦቻቸውና አድናቂቆቻቸው በተገኙበት ግንቦት 15 ቀን አሸኛኘት ተደርጎለት ከዋሽንግተን ዲሲ ጉዞ ጀመረ፡፡ ግንቦት 15 የተነሳው የፕሮፌሰሩ አስከሬን ሮም አርፎ ግንቦት 17 ቀን 1991 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሲሆን ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረሰ፡፡ በስፍራው ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ አስከሬኑን በከፍተኛ አጀብ ለገሐር ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አደረሰው፡፡ ግንቦት 17 ቀን ሌሊቱን ጸሎተ ፍትኃት ሲደረግ አድሮ በማግስቱ አስከሬናቸው በመሰረቱትና በኋላም በሞቱለት ድርጅታቸው (መአህድ) ጽ/ቤት ጥቂት ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ስላሴ ካቴድራል አመራ፡፡ በስላሴ ካቴድራል ፍትሃትና ጸሎት ከተደረገላቸው በኋላ ስላሴ እንዳይቀበሩ መንግስት በመከልከሉ ምክንያት በባለወልድ ቤተክርስቲያን እንዲያርፉ ተደረገ፡፡ ይኸው ላለፉት 18 ዓመታት በባለወልድ የቆየው አጽማቸው ዛሬ ወደሚገባው ቦታ ስላሴ ካቴድራል ሊዛወር ችሏል፡፡ ፕሮፌሰር አስራት ወልደዬስ የሁለት ወንዶች ልጆች አባትም ነበሩ፡፡
.
ይኸ ጽሁፍ ዛሬ ቀብራቸው ቦታ ላይ የተነበበ ሲሆን የፕሮፌሠሩን ሙሉ የህይዎት ውጣ ውረድ ማወቅ ለምትፈልጉ አንጸባራቂው ኮከብ በሚል ርዕሥ የጻፍኩትን ሥለ ፕሮፌሠር የህይዎት ታሪክ የሚያትት መጽሃፍ ማንበብ እንደምትችሉ እጋብዛለሁ።
©ጋሻው መርሻ read more here

Saturday, May 27, 2017

ግቦት 20 አንዴት ነው ሚከበረው?

Captureda

አውን ግቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነትን፣ እኩልነት፣ አንድነት እና ዲሞክራሲን አጎናፅፏል? የትም ሐገረ ተደርጎ ማይታወቅ አመት ሊሞላው ትንሽ ወር በቀረው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ህዝቡ ታፍኖ ባለበት፣ ሰው የመሰለውን የመፃፍ የመናገር ነፃነት ባጣበት፣ ፊስቡክ እንኳ ፖስት ባረገው ሰው እስር ቤት ሚወረወርበት፣ ኢትዮጵያ ከመቸው የበለጠ ላአድነቷ ፈተና ውስጥ ባለችበት፣ ከመቼውም የበለጠ ፓለቲካ እና ኢኮኖሚ በአንድ የፖለቲካ ድርጆት በወደቀበት፣  ከመቼውም የበለጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራው ችግር በገባበት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከእንድ ጨቋኝ መንግሥት ወደሌላ ጨቋኝ መግሥት በተጋለጠበት፣ ልማቶች ሁሉ ወደ አንድ ክልል ባተኮሩበት፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ህዝብ አያስፈልግም ተብሎ ወደተለየ አፈና እና ጭቆና መንግሥት በገባበት፣ 2/3ኛው የኢትዮጵያ ህዝብ (ኦሮሞ አና አማራ) ዲሞክራሲ፣ እኩልነት፣ ነጻነት እና ልማት) ተጠማሁ ብሎ እየጮኸ ባለበት ወቅት ወያኔ ኢህአዴግ ግቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነትን፣ እኩልነት፣ ዴሞክራሲን እና ልማትን አምጥቷል ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር አሁንም መንግሥት እሱ እንደሚለው ጥልቅ ታድሶ ሳይሆን ምን ያህል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፓለቲካ ቀማር እየተጫወተ መሆኑን በግልፅ አሳይቷል።

Friday, May 19, 2017

Amharic fidels (Amharic Alphabet)

Amharic fidels

ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ ሏ
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ ሗ
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ ሟ
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ ሧ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ ሯ
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ ሷ
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ ሿ
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ ቈ ቊ ቋ ቌ ቍ
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቧ
ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ ቯ
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ ቷ
ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ ቿ
ኀ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ ኈ ኊ ኋ ኌ ኍ
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ ኗ
ኘ ኙ ኚ ኛ ኜ ኝ ኞ ኟ
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ ኰ ኲ ኳ ኴ ኵ
ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ ዀ ዂ ዃ ዄ ዅ
ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ ዟ
ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ ዧ
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ ዷ
ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ ጇ
ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ ጐ ጒ ጓ ጔ ጕ
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ ጧ
ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ ጯ
ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ ጷ
ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ ጿ
ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ ፏ
ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ ፗ

Friday, May 12, 2017

“እስር ቤት ውስጥ ሞተ ተብሎ አስክሬን ተሰጠን” - የሟች እናት

አቶ ዘነበ ጫቅሌ
ዘነበ ጫቅሌ ዩሃንስ የተባለ የሁለት ልጆች አባትና የ32 ዓመት ወጣት ዳንሻ ከብት ገበያ ውስጥ ከብት በመነገድ ላይ እያለ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም በፖሊሶች ተይዞ ከተወሰደ ከሁለት ሳምንት በኋላ በእስር ቤት መሞቱን ቤተሰቡና በቅርብ የሚያውቁት ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በተለይ በወልቃይት ፀገዴ ለወራት የዘለቁ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ተከትሎ፤ በቁጥጥር የሚውሉና የደረሱበት የማይታወቅ ሰዎች መበራከታቸውን በሰሜን ምእራባዊው ግዛት የባህልና ማንነት ጥያቄ አንስተው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የማህበረሰብ ለውጥ አቀንቃኞች ይገልጻሉ።

ዘነበ ጫቅሌ ዩሃንስ የተባለ የሁለት ልጆች አባትና የ32 ዓመት ወጣት ዳንሻ ከብት ገበያ ውስጥ ከብት በመነገድ ላይ እያለ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም በፖሊሶች ተይዞ ከተወሰደ ከሁለት ሳምንት በኋላ በእስር ቤት መሞቱን ቤተሰቡና በቅርብ የሚያውቁት ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል። ሟች ለፋሲካ በዓል ለቤተሰቡ ደውሎ የቀረበበትን ክስ በፍርድ ቤት እንደሚሟገት ተናግሮ እንደነበል ወላጅ እናቱ ተናግረዋል።

እንዴት ሞተ? ቤተሰቦቹ የተሰጣቸው ምክንያት ለማመን የሚያስቸግር እንደሆነ ገልጸው፤ አስከሬኑ መመርመሩን ተነግሯቸው ውጤቱን ግን እንዳልሰሙ ተናግረዋል። በወልቃይት ፀገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ የተሳተፉ፤ ከመሪዎቹ ጨምሮ በእስር ላይ መሆናቸውንና ደብዛቸው የሚጠፋና ድንገት የሚሞቱም አሉ ሲሉ የእንቅስቃሴው አደራጆች ገልጸውልናል።
የፀገዴ ወረዳና የሽሬ ፖሊስ እንዲህ የሚባል እስረኛ “እኛ ጋር አልነበረም። የኛ እስር ቤቶች የእስረኛ ዴሞክራሲያዊ መብት የሚከበረባቸው ናቸው” ብለዋል። የእንዳ አባ ጉና ፖሊስ ሃላፊ በበኩላቸው በአካል ካልተገኘን ምንም መረጃ እንደማይሰቱን ገልፀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time