Thursday, July 19, 2018

መንግሥት በዶላር ጉዳይ መግለጫ ሰጠ


በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትእዛዝ መሰረት በርካቶች በእጃቸው ያለውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ወደ ባንክ እያስገቡ መሆኑን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የውጭ ምንዛሪ በእጃቸው የያዙ አካላት በፍጥነት ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ ባሳለፍነው ሰኞ ሐምሌ 9 2010 በሰጡት መግለጫ ማሳሰባቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በወቅቱም፥ የውጭ ምንዛሪውን ያከማቹ አካላት በእጃቸው ያለውን ገንዘብ በፍጥነት ወደ ንግድ ባንኮች ገቢ በማድረግ ከኪሳራ እንዲድኑም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውሰዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ
ተከትሎም በርካቶች በእጃቸው ያለውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ወደ ባንክ እያስገቡ ነው ብለዋል።
በዚህም በጥቁር የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሲዘዋወር የነበረው አብዛኛው ገንዘብ ወደ ተለያዩ የንግድ ባንኮች እየመጣ መሆኑን የገለጹት አቶ አህመድ፥ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ክምችትም እየጨመረ መጥቷል ነው ያሉት።
ህብረተሰቡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጥሪ በዚህ ፍጥነት ምላሽ በመስጠቱም የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ሀላፊ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አቶ አህመድ አክለውም፥ አሁንም የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘብን በተለያየ መልኩ ያከማቹ ሰዎች በአፋጣኝ ወደ ባንክ እንዲወስዱ 
አሳስበዋል። የውጭ ምንዛሬ የጥቁር ገበያን ለማዳከም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አቶ አህመድ ሽዴ በመግለጫቸው ተናግረዋል።
ከሚሰወዱት እርምጃዎች ጎን ለጎንም ከወዳጅ ሀገሮች እና ተቋማት በልማት ፋይናንስ መልክ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ የተሰራው ስራም ውጤታማ መሆኑን ገልፀዋል።
መንግስት ህብረተሰቡን ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ተጠቃሚ ለማድረግ አዳዲስ የፖሊሲ አቅጣጫዎች መያዛቸውንም አቶ አህመድ ሽዴ በመግለጫቸው አብራርተዋል።
በዚህም መሰረት በመንግስት የልማት ድርጅት ስር የሚገኙ አራት ድርጅቶችን አብዛኛውን ድርሻ መንግስት ይዞ ቀሪው ድርሻ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች እንዲተላለፉ መወሰኑን ገልፀዋል።
ሌሎች የመንግስት የልማት ድርጅቶችም ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል እንዲዘዋወሩ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አቶ አህመድ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
ይህ የሚሆንበት ዋናው ምክንያትን በሀገሪቱ እየተመዘገበ የመጣውን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል ነው ሲሉም አቶ አህመድ አብራርተዋል።
በተጨማሪም የግሉ ሴክተር በኢኮኖሚው ላይ ያለውን ሚና ለማሳደግ እና ዓለም አቀፍ እንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ ያለመ መሆኑንም ገልፀዋል።
ምንጭ መንግስት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time