በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ በሚል ስም የጦርነት አዋጅ እያወጀ ያለው አካል ፣ እያደረገ ያለው ነገር እንዲያስብበት እና ወደትክክለኛው መንገድ እንዲመለስ ኦቦ ለማ መገርሳ አስጠነቀቁ። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦቦ ለማ መገርሳ የጦርነት አዋጅ ያወጀውን ቡድን ያስጠነቀቁት፣ ትናንት በኦሮሚያ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ነው። “ከዚህ በፊት ቀጥታ ሲዋጉን የነበሩ አካላት ዛሬ ስፓንሰር በመሆንና ገንዘባቸውን በመርጨት የክልሉት ፀጥታ ለማደፍረስ እንቅልፍ አጥተው እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት አቅቶ ለማ፣ ከስፓንሰሮቹ የሚለገሳቸውን ገንዘብ በመቀበል የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስፈፀም ዝግጁ የሆኑ በርካታ የእኛው ወንድሞችም በመከላችን ይገኛሉ” ብለዋል፡፡ “ለዚህ ህዝብ ሁላችንም እንሥራለት በሚል ውሳኔ ሁሉም ወደ ሀገር ተመልሶ በሀሳብ በመፋለም አንድ ላይ መስራት አለብን ብለን ጥሪ ከማድረግም በላይ ፣ ህዝባችንን አምነን ብዙዎቹን ከሰሩት ወንጀልም ነፃ እንዲሆኑ አደረግን “ ያሉት ር ዕሰ መስተዳድሩ፣ የፓለቲካ ታርጋ ተለጥፎባቸው በሰው ሀገር የተበተኑ ወገኖቻችን ተመልሰው ለሀገር እንዲሰሩ በራፉን በከፈትንበት ፣ ብዙዎች ጥሪዎን ተቀብለው እየገቡ ባለበት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን እየፈታን ባለንበት እና አጠቃላይ የፓለቲካ ምህዳሩ እየሰፋ ባለበት ጊዜ ፣”አይ! የኦሮሞ ነፃነትን ለማስከበር ትክክለኛ የጦርነት መክፈቻው ጊዜ አሁን ነው” ተብሎ በኦሮሞ ህዝብ ስም የሚደረግ እንቅስቃሴ ትርጉሙ ምን እንደሆነ በግሌ አልገባኝ”ብለዋል። አቶ ለማ አክለውም፦”ለኦሮሞ ነፃነት ለማስከበር የሚያስቡ ከሆነ ፣እስከዛሬ ይሄን ሁሉ ዘመን የት ነበሩ?…ሲሉ ጠይቀዋል። . “ እነዚህ ወገኖች ከልጅ ፊት አባት ገድለው ሬሳውን አቃጥለዋል።ሬሳ በማቃጠል የህዝብ ነፃነት እንዴት መከበር እንደሚችል አላውቅም። ኦሮሞ-ኦሮሞን ነው እየገደለው ያለው።…በምዕራብ ኦሮሚያ እየሆነ ያለው ነገር ይሄ ነው፡፡” ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አክለዋል። “ቄሮ ለዓመታት በመሪነት ባደረገው ትግልና በከፈለው መስዋዕትነት አሁን እያየነው ያለነው ለውጥ እንዲመጣ እና ዛሬ የመጣውን ውጤት እንድንጎናፀፍ አድርጎል.” ያሉት ኦቦ ለማ መገርሳ፣ “ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በቄሮ ስም ለመነገድ የሚሞክሩ ወጣቶች እዚህም እዛም የመዝረፍና አንዳንድ አካባቢዎችን የማወክ አዝማሚያ እያሳዩ እንደሆነ አልሸሸጉም። “ቄሮዎች ግን ይሄ በታሪክ ማህደር ላይ የተከተበ የጀግንነትና ለህዝብ መስዋዕትነት የከፈሉት ደማቸው ባክኖ እንዲቀርባቸው ስለማይፈልጉ፣ አሁንም እነዚህን ቅጥረኞች አደብ በማስገዛት እና ወደመስመር በማስገባት ረገድ ትልቅ ምሳሌ የሚሆን ስራ በመስራ ላይ ይገኛሉ”ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ “ህዝባችንም እንደዛው እያደረገ ነው፡ብለዋል። ይህ ሕግን የማስከበርና ሰላምና መረጋጋትን የማረጋገጥ ተግባር በሁሉም አካባቢ ተጠናክሮና ተስፋፍቶ መተግበር እንዳለበትም አቶ ለማ አሣስበዋል፡፡ “በአሁኑ ወቅት በክልላችን መዋቅር ውስጥ እንደ ኦሮሚያ ፖሊስ ለህዝቡ ዋልታና መከታ የሆነ አካል አኔ በግሌ አላውቅም” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በዛ በጭንቀትና በመከራ እና አይዟችሁ የሚለን ባጣንበት ጊዜ ከጎናችን ቆሞ ደሙን እያዛራ እና ህይወቱን እየሰጠ ለዚህ ለዛሬው ቀን እንደንደርስ የሚችለውን ሁሉ ያደረገ የህዝብ አካል ነው”ብለዋል። አቶ ለማ አክለውም፦”የኦሮሚያ ፓሊሶች ለሚከፈላቸው ደሞዝ አየይደለም ፋቲኩን የለበሱት፡፡ እኔ እንደ ኦሮሚየ ፓሊስ በቁርጠኝነት ለህዝብ የቆመ አላውቅም።ቁርስ በልቶ ምሳ ሳይደግም ፀሀይና ንፋስ እየተፈራረቀበት መካራውን በማየት ከገዛ ስንቁ ለህዝቡ እየቀነሰ ሲሰቃይ የነበረ የህዝብ ወገን ነው።ለህዝባቸው ሲሉ ቤተሰባቸውን በትነው በየቆላውና በየድንበሩ በርካቶቹ ህይወታቸውን አጥተዋል። …. ታዲያ እንዴት ዛሬ በኦሮሚያ ፓሊስ ላይ ልክ እንደህዝብ ጠላት ቦንብ ይጣልበታል…? ይህ ፖሊስ እንዴት ዛሬም ይገደላል……?ምን ተፈልጎ ነውአሁን አንዳችን በሌላችን ላይ ቂም እንድናወጣ ጥሪ እየተደረገ ያለው?”ሲሉ በአጽንዖት ጠይቀዋል። “ኦሮሚያ ውስጥ አናርኪ ለመፍጠር ገንዘብ በመርጨት የሚሰራ ስራ አለ ። እንስራለን ብለን ያቀድነውን ስራ ትተን ሌላውን ስራ እድንሰራ ነው እየተፈለገ ያለው” ያሉት አቶ ለማ፣ …ዛሬም ችግሮች ቢኖሩም ቄሮዋች ከጎናችን ሆነው እየታገሉ ናቸው “ብለዋል። አሁንም የኦሮሞ ነፃ አውጪ በሚል ስም የጦርነት አዋጅ እያወጀ ያለው አካል ድርጊቱን ቆም ብሎ እንዲያስቡበት እና ወደትክክለኛው መንገድ እንዲመለስ የመከሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ይሄን ያሉት ለመንግስት ችግሩን መቆጣጠር ከባድ ሆኖበት ሳይሆን ወዳልተፈለገ የኃይል እርምጃ ከመግባት ይልቅ ጉዳዩ በሰላም እልባት እንዲያገኝ ካላቸው ፍላጎት በመነሳት እንደሆነ አብራርተዋል።ኦቦ ለማ መገርሳ ንግግራቸውን ሲቋጩም፦”ጭቆና መሸከም አንችልም ብለን ታግለንና መስዋእትነት ከፍለን ወደ ነጻነት መንገድ መሸጋገር ጀምረናል..ዛሬስ ነፃነትንም መሸከም የማንችል ህዝቦች ነን እንዴ..?”ሲሉ ጠይቀዋል።
Esat
በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተመረተ ነው!
26 Mar 2025 Ethiopia Todayየአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ደፋር ማሻሻያዎችን እና አፍሪካን የሚመሩ መፍትሄዎችን ከፒአርሲ ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ አሳሰቡ!
18 Mar 2025 Ethiopia Todayፀሐይ ባለበት የቫይታሚን D እጥረት ለምን?
18 Mar 2025 Ethiopia Today"እንደ አሮጌ ምንጣፍ የተጣለ" - የቻይና መንግሥት ጋዜጣ የቪኦኤ በጀት እንዲቋረጥ መወሰኑን አወደሰ!
18 Mar 2025 Ethiopia TodayKillings, abductions, funding shortfalls stifle WFP relief efforts across Ethiopia!
15 Sep 2024 Ethiopia TodayEthiopia : Dialogue Commission wants gov’t to create “enabling condition
30 Jun 2024 Ethiopia TodayStruggles of High-Rise Living
30 Jun 2024 Ethiopia TodayTPLF regains political legitimacy with Justice Ministry’s blessing
29 Jun 2024 Ethiopia TodayA father who lost 2 sons in a Boeing Max crash waits to hear if the US will prosecute the company
29 Jun 2024 Ethiopia TodayEthiopia’s dam fills threaten Egypt’s lifeline: Calls for international intervention
29 Jun 2024 Ethiopia TodayFashion event brings Kanu, others to Ethiopia
29 Jun 2024 Ethiopia TodayEconomic, conflict spurring human trafficking in Ethiopia: US State Department
29 Jun 2024 Ethiopia TodayEthiopian gov’t forces killed 27 civilians in the Amhara region
29 Jun 2024 Ethiopia Todayበአማራ ክልል በዚህ ሳምንት ከ27 በላይ የሚሆኑ ‘ሰላማዊ ሰዎች’ “በመንግሥት ኃይሎች” መገደላቸው ተነገረ
29 Jun 2024 Ethiopia TodayAMHARA MASSACRE: A GRIM REMINDER OF ETHIOPIA’S FRAGILE PEACE
23 Jun 2024 Ethiopia TodayMore details emerging about ethnic Amhara Generals led public meeting in Addis
23 Jun 2024 Ethiopia TodayDr. Fisseha Eshetu’s Claims Under Scrutiny: A Closer Look
23 Jun 2024 Ethiopia Todayበአማራ ክልል ሁለት የጎጃም ዞኖች በቀናት ልዩነት “በመንግሥት ኃይሎች” ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
18 Jun 2024 Ethiopia Todayጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ
18 Jun 2024 Ethiopia TodayJiga, Ethiopia : Government Forces Reportedly Execute 25 Civilians in Following Ambush Loss
18 Jun 2024 Ethiopia Today
Widget by Making Different
Wednesday, July 11, 2018
በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ በሚል ስም የጦርነት አዋጅ እያወጀ ያለው አካል ፣ እያደረገ ያለው ነገር እንዲያስብበት እና ወደትክክለኛው መንገድ እንዲመለስ ኦቦ ለማ መገርሳ አስጠነቀቁ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Recent Articles
Recent Video Uploads
Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube
Ethiopia Today
- Active a minute ago with many
- videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies, Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time
No comments:
Post a Comment