የዐማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ፡ለሁለት ቀናት በባሕር ዳር ከተማ በሙሉዓለም የባህል ማዕከል ሲካሄድ የነበረው የዐማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) መስራች ጉባኤ ተጠናቋል።
‹‹አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፤ ሁሉም ዐማራ ለአንድ ዐማራ›› የሚል መርህ ያለው ድርጅቱ በሁለት ቀን ቆይታው የድርጅቱን ሊቀመንበርና የውስጠ ድርጅት ተግባራትን ከአባላትና ደጋፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
ዐብን በመሥራች ጉባኤው ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን ሊቀመንበር ፣ አቶ በለጠ ሞላን ደግሞ ም/ሊቀመንበርና የድርጅቱ የምርጫ ጉዳይ ሃላፊ አድርጎ መርጧል፡፡ በተጨማሪም ንቅናቂው የስራ አስፈፃሚ አባላትና የምክር ቤት አባላትን ሰይሟል ።
በሁለተኛው ቀን ውሎ ከአባላት እና ደጋፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል ። በምስረታው የተገኙ አባላትም የአማራ ምሁራን በባለፉት ዓመታት በፍርሀት ሁነው የአማራውን መብትና ተጠቃሚነት እንዲከበር ባለመስራታችው ድርጅቱ በምሁራን እንዲዋቀር መነሻ ሆኗል ብለዋል ።
የአማራው እንደብሔር መደራጀት በአማራው ላይ በባለፉት ጊዚያት ሲፈጠሩ የነበሩ የፓለቲካና የዘር ጥቃቶችን ለስማቆም ከሌሎች ህዝቦች እና ድርጅቶች ጋር አብሮ ይሰራልም ተብሏል ።
የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በምስረታው እለት በሰጡት መግለጫ ከባለፉት 50 ዓመታት ወዲህ የአማራው ህዝብ ህልውና ወድቆ ነበር ። በ1960ዎቹ የተፈጠረው የተማሪዎች አብዮት አማራውን የበላይ አድርጎ ሌሎችን ተጨቋኝ አድርጎ አማራውን የማሳደድ እና በትጥቅ ትግሎች ጣት እንዲቀሰርበት ተደርጓል ። በዚህም አማራው ከፍተኛ መሰደድና ጭቆና እንዲሁም የፓለቲካ የበላይነት ተወስዶበታል ብለዋል።
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የዐማራ ብሔር ንቅናቄም ለዘብተኛ ሊብራሊዝምን በመጠቀም የዐማራን ህዝብ ታሪክ ባህልና ትውፊት ተከብሮ በምጣኔ ሃብት ደረጃ ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተጠቃሚ ማድረግ ነው ። በቀጣይ ፓርቲው ዲሞክራስያዊ በሆነ መንገድ ህገ መንግስታዊ ለውጦች እንዲኖሩ፤ የአማራ ህዝብ የጸረ ጭቆናና የልማት ተጠቃሚነቶች እንዲረጋገጡ በክልሉና በሃገራዊ መድረኮች ተሳታፊ ይሆናል ብለዋል ።
ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ
Sunday, June 10, 2018
የዐማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Recent Articles
Recent Video Uploads
Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube
Ethiopia Today
- Active a minute ago with many
- videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies, Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time
No comments:
Post a Comment