የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የዩኒቨርስቲዎች አለመረጋጋት
በኢትዮጵያ መንግስት የታወጀዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ተፈጻሚ መሆን ከጀመረ በኋላ የመብት ጥሰቶች መባባሱን ስንዘግብ ቆይተናል።
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች፣ ማለትም በጅማ፣ በሃሮማያ፣ በወላጋና በአምቦ፣ አሁንም የተማሪዎች መታሰር፣ መባረር፣ ወደ የማይታወቁ ቦታዎች መወሰድና ሌሎች አለመረጋጋቶች መቀጠላቸዉን የሰባዊ መብት ተቆርቋርዎች ሲጽፉና ሲናገሩ ይታያል። ለምሳሌ በጅማ ዩንቨርስቲ ቴክኖ በሚባለዉ ካምፓስ ዉስጥ የተነሳዉን ተቃዉሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች ተማሪዎችን ሲደበደቡ እንደነበረ ተናግረዋል። በሃሮማያ ዩንቨርስቲም ተማሪዎች በጊቢ ዉስጥ በሚገኙት የኮማንድ ፖስቱ የደኅንነት ሃይል «እየተሸበሩ» መሆኑንና ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸዉ እየተባረሩ መሆኑን በጽሑፋቸዉ አመልክተዋል። ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች፣ ማለትም በጅማ፣ በሃሮማያ፣ በወላጋና በአምቦ፣ አሁንም የተማሪዎች መታሰር፣ መባረር፣ ወደ የማይታወቁ ቦታዎች መወሰድና ሌሎች አለመረጋጋቶች መቀጠላቸዉን የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች ሲጽፉና ሲናገሩ ይታያሉ። ለምሳሌ በጅማ ዩንቨርስቲ ቴክኖ በሚባለዉ ካምፓስ ዉስጥ የተነሳዉን ተቃዉሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች ተማሪዎችን ሲደበድቡ እንደነበር ተነግሮአል። በሃሮማያ ዩንቨርስቲም ተማሪዎች በጊቢ ዉስጥ በሚገኙት የኮማንድ ፖስቱ የደኅነት ሃይል «እየተሸበሩ» መሆኑንና ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸዉ እየተባረሩ መሆኑን በጽሑፋቸዉ አመልክተዋል።
መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ
No comments:
Post a Comment