Saturday, November 19, 2016

ሲፒጄ በጥረቱ እንደሚገፋ አስታወቀ፤ መንግሥት ክሡን አጣጣለ

አንጄላ ኲንታል
የኢትዮጵያ መንግሥት ሃሣብን ለመግለፅ ነፃነት መድረኩን ክፍት እስኪያደርግና ያሠራቸውን ጋዜጠኞች እስኪፈታ መጎትጎትና ጫና እንዲደረግበት መግፋቱን እንደማያቆም ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅነንት ተሟጋች ቡድን - ሲፒጄ አስታውቋል፡፡
ሲፒጄ ትናንት ባወጣው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ባለፉ ቅርብ ሣምንታት ውስጥ ሁለት ጋዜጠኞችና ሁለት የኢንተርኔት ላይ አምደኞችን ማሠራቸውን አመልክቶ ነበር፡፡
በትናንቲ የሲፒጄ መግለጨ ላይ የተጠቀሱት ጋዜጠኞች ዛሬ የታሠሩትንና ቀደም ሲልም እሥር ለይ የቆዩትን የማይጨምር ሲሆን ሲፒጄ በስም የጠራቸው በፍቃድ ኃይሉ፣ ናትናዔል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላና አጥናፍ ብርሃኔ የሽብር ክሥ እንደተመሠረተባቸው ተሟጋቾች በማኅበራዊ ማድያ ላይ መፃፋቸውን አመልክቷል፡፡
የኦሮምያ ብሮድካስቲንግ አገልግሎቱ ጋዜጠኛ አብዱ ገዳ ያለበት እንደማይታወቅ ስፒጄ በትናንቱ መግለጫው ላይ ጠቅሶ የነበረ ቢሆንም በአንድ የአዳማ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተይዞ እንደሚገኝና ሄደውም ያዩት ሰዎች መኖራቸውን ምንጮች ለቪአኤ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች ዓለምአቀፉን የጋዜጠኞች ደኅንነት እንደሚያሳስበው የቡድኑ የአፍሪካ ጉዳዮች መርኃግብር ዳይሬክተር አንጄላ ኲንታል ለቪኦኤ ገልፃለች፡፡
የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ-ምልልስ የሲፒጄን ክሦች አጣጥለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ Read more here

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time