ዋሽንግተን ዲሲ —
መሠረት ንጉሤ መደበኛ ትምህርቷን ከ10ኛ ክፍል ብታቋርጥም በዳንግላ ከተማ ትሠራበት በነበረ ሆቴል ውስጥ ግን በርካታ ደምበኞችን ያፈራች የምግብ ዝግጅት ባለሙያ ነበረች።
ቤተሰቦቿን ትደጉምም ነበር። ሰሎሞን በላይ ከተባለ እኩያ ጓደኛዋ ጋር ሰላማዊ የፍቅር ግንኙነት ነበራት። ከሦስት ዓመት ጓደኝነት በኋላ ያለመግባባት በመካከላቸው በመከሰቱ የፍቅር ጓደኝነታቸው ተቋረጠ።
የመለያየትን ነገር ያልተቀበለው ጓደኛዋ ግን መውጫ መግቢያዋን ተከታትሎ ባላሰበችው ሰዓትና ቦታ ፊቷና ሰውነቷ ላይ በአሲድ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶባታል። የተበየነበት ወንጀለኛ ባደረሰው አደጋ የአስራስምንት ዓመት ፅኑ እሥራት ተፈርዶበታል።
ስለፍርዱ አሰጣጥና አሁን ስላለችበት የጤና ሁኔታ መሠረት ንጉሤ ትናገራለች።
በተጨማሪም ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ወ/ሮ ሳባ ገብረ-መድኅን የኢትዮጵያ የሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዋና ኃላፊ በአጠቃላይ በሴቶች ላይ ስለሚደርስ ጥቃትና ህግን በተመለከተ አጠር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል።
ለዝርዝሩ የመስታወት አራጋውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ Read more here
No comments:
Post a Comment