Monday, October 17, 2016

"ብዙሃን መገናኛ በድረ-ገጽ አማካኝነት የተሰራጩ መረጃዎችን ማጣራት ኃላፊነት አለባቸው" አሜሪካዊት ባለሞያ - VOA

ኪቲ ከርት የሕዝብ ግንኙነትና የፖለቲካ ስልት ባለሞያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በሌላው የዓለም አካባቢ ትኩረት እንደሚስብ የተናገሩት፥ የህዝብ ግንኙነትና የፖለቲካ ስልት ባለሞያ፥ ተሞክሯቸውን ለኢትዮጵያውያን አካፍለዋል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን በምርጫው ሂደት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያስረዱት ኪቲ ከርት በፕሬዘዳንታዊ እጩዎቹ የሚወጡና የሚነገሩ መረጃዎችን የማጣራት ሥራ እንደሚሠሩም ገልጸዋል።
በዚህ የኢንተርኔትና የማህበራዊ ሚዲያ ዘመን፥ መረጃን ማጣራትና እንደወረደ አለመቀበል አስፈላጊ መሆኑንም አብራርተዋል። ኪቲ ከዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ያሉ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ልክ እንደ አሜሪካውያን ሁሉ የአሜሪካን ምርጫ እንደሚከታተሉ ከገለጹ በኋላ “በአሜሪካ የሚኖሩና በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ድምፅ መስጠት የሚችሉ በርካታ ሰዎች በቀረው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች የሚያውቁትን ያህል አለማዎቃቸው፤ የሚገዳቸውን ያህል ትኩረት አለመስጠታቸው ትንሽ የሚያሳዝን ነው፡፡” ብለዋል።
አክለውም “አንዱን ተወዳዳሪ ለይቶ ደጋፍ የሚገልፀው ርእስ አንቅፅ እንጂ ዜናው አይደልም፡፡ በመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ውስጥ በባለቤቶቹ ወይም በርእስ አንቀፁና በዜና ክፍል መካከል ትልቅ መስመር ወይንም የቻይና ግምብ ብለን የምንጠራው ወስን አለ፡፡ አንድ ጋዜጣ ለትራምፕ ወይንም ለሂላሪ ድጋፉን ቢግልፅ እንኳን የምርጫ ዝግጅቶችንና በምርጫው ሂደት እያሉ ነገሮችን እንደዘገብ ብታነቡ የሪፖርተሮቹ ዘገባ ጋዜጣው የሰጠው ድጋፍ አያንፀባርቅም፡፡ በዚህ ዓመቱ ለምሳሌ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ ሂላሪ ክሊንተንም ሆኑ ሪፓብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ በአንዳንድ የሚዲያ ዘገባዎች ደስተኛ እንዳልሆኑ የሚገልፁበት አጋጣሚ አለ፡፡” ብለዋል
የአሜሪካ ኤምባሲ - አዲስ አበባ
የአሜሪካ ኤምባሲ - አዲስ አበባ
ስለ ማኅበራዊ ሚዲያ ሲናገሩም “ኢንተርኔት እውነትን ማግኘት ቀላል የማድረጉን ያህል መገናኛ ብዙሃን ያ የተባለው ነገር እውነት መሆኑን የማረጋገጥ የቤት ስራቸውን መስራት አለባቸው፡፡አንድ ሰው ሰማዩ ጥርት ያለ ነው ደመና የለውም ብሎ ከፃፈ ወደ ውጭ ወጣ ብሎ እየዘነበ ነው ወይንስ እየዘነበ አይደለም ብሎ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ በአለንበት አለም በጣም አስቸጋሪ ስራ ነው፡፡ ምክንያቱም ማንኛውም ሰው ማንኛውንም ነገር በኢንተርኔት ሊጽፍ ይችላል፡፡አንዳንዴ እውነት ነው፤ አንዳንዴ እውነት አይደለም፡፡ ማንን እንደምታምን ማወቅ፤ ብዙ ቦታዎች ላይም ማጣራት፤ እውነታውን እያገኘህ ስለመሆኑም ማረጋገጥ ያስፈልጋል” በማለት ያብራራሉ።
አሜሪካዊቷ ባለሞያ ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ያደረጉትን ገለጻ የተከታተለው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ልኳል።
ዝርዝርሩን ከተያያይዘው ድምጽ ያድምጡ።

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time