Monday, May 30, 2016

ውድ ኢትዮጵያውያውያን አስተውሉ! አሜሪካውያን በቀጣዩ አመት ማይክሮ ቺፕ ሊገጠምላቸው ነው


ውድ ኢትዮጵያውያውያን አስተውሉ!.ከዚህ በፊት ስለ ማይክሮችፕ ሰፋ ባለ ሁኔታ ጽፌላችሁዋለሁ።አሁን ደግሞ ይህ ዜና ይፋ ሆኖዋል።
ይህ ዜና ይፋ የሆነው ከ2 ቀናት በፊት ነው።ዘገባው የ NBC ሲሆን፤NBCን ጠቅሶ የአገራችን ሚዲያ ፋና እንዲህ ዘግቦታል።
"አሜሪካውያን በቀጣዩ አመት ማይክሮ ቺፕ ሊገጠምላቸው ነው አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ ወይም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ) " አሜሪካ በቀጣዩ አመት ሁሉም ዜጎቿ እጅ ላይ ማይክሮ ችፕ ልትገጥም ነው። ይህ የሚሆነው የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥና እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነው እየተባለ ነው። የማይክሮ ችፕ ገጠማው በቀኝ እጅ ላይ የሚከናወን ሲሆን፥ ተጠቃሚው በመሳሪያው አማካኝነት መገበያየት፣ መግዛት፣ ገንዘብ መላክ እና ሌሎችን ነገሮች ማድረግ ይችላል ተብሏል። በአጋጣሚ መንገድ የወጣ ሰው ገንዘብ ባይኖረው እና ችግር ቢያጋጥመው እንኳን፥ መሳሪያው ስለተገጠመለት የተሰጠውን የአይ ፒ አድራሻ በማስመዝገብ የፈለገውን መግዛትና መገብየት ይችላል ነው የተባለው። ቀጠን ያለ የሩዝ ፍሬ የሚያክል መጠን ያለው መሳሪያ የተገጠመለት ሰው እያንዳንዱ እንቅስቃሴም በመንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚሆን ኤን ቢ ሲ ኒውስ የሰራው ዘገባ ያሳያል። በተለያዩ ግዛቶች ተዘዋውሮ በተሰራው በዚህ ዘገባ፥ መሳሪያው ከጨቅላ ህጻናት እስከ አዋቂዎች ከዚህ አልፎም በእንስሳት ላይ እንደሚገጠም ያሳያል። ይህም የዜጎችን እንቅስቃሴ መቆጣጠር እና ብሎም የሚጠፉ ህጻናትን ለመከታተል ያስችላል ብለዋል በኤን ቢ ሲ አስተያየታቸውን የሰጡ ባለሙያዎች እና የቴክኖሎጂው ተጠቃሚዎች። “ለስራ ከቤት ስወጣ አሳሳቢ የሚሆንብኝ የልጆቸ ጉዳይ በዚህ ቴክኖሎጅ ይቀረፋል” ብላለች የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ የሆነች እናት። እንደ እርሷ ገለጻ በልጆቿ ላይ የሚገጠመው
ቴክኖሎጅ የእነርሱን አጠቃላይ ውሎ መከታተል ስለሚያስችል ከክፉ ነገር የራቁ ናቸው፤ እናም ወድጀዋለሁ ብላለች። ከዚህ ባለፈም ህገ ወጥ እንቅስቃሴንና እንደ ሽብር ያሉ አለም አቀፍ ስጋቶችን ቀድሞ መለየት እና መከላከል የዚህ መሳሪያ አላማ መሆኑም ተገልጿል። ይህ ቴክኖሎጅ እንደ ችካጎ ባሉ ግዛቶች በርካታ ተጠቃሚዎች ሲኖሩት፥ በቨርጅኒያ ግን እንዳይተገበር ቅስቀሳ ተጀምሯል። ምክንያቱ ደግሞ “የምናደርገው እንቅስቃሴም ሆነ የዕለት ተዕለት ውሎ እና አለፍ ሲልም የጤናችን ሁኔታ በዚህ መሳሪያ ክትትል መደረጉ ምቾት አይሰጠንም” በማለት።

ከዚህ ባለፈ “ምናልባትም መንግስት ታዛዥ አይደሉም ብሎ ያሰባቸውን ሰዎች፥ በዚህ ቴክኖሎጅ አማካኝነት የመቅጣት አቅም አለው” ሲሉም ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። ያም ሆነ ይህ ግን እያንዳንዱ አሜሪካዊ ወደደም ጠላም ይህን መሳሪያ በቀጣዩ አመት ማስገጠምና፥ በልዩ ክትትል መኖር
ግዴታው ነው ተብሏል። ይህ ማይክሮ ችፕ በ10 አመታት ውስጥ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች እንደሚገጠምም ባለሙያዎች ተናግረዋል።
በኦባማ ኬር አማካኝነት የተዘጋጀው ማይክሮ ችፕ ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ ያለቀ ሲሆን፥ ከወራት በኋላ አሜሪካውያን እጃቸው ላይ ያስገጥሙታል።.... መረጃው የኤን ቢ ሲ ኒውስ ነው።"ይላል ዜናው።
ውድ ኢትዮጵያውያን እናስተውል!እናመዛዝን!ከላይ ያየነው ዜና ዘመኑን ጠብቆ እንደሚከሰት በመጽሐፍ ቅዱስ ቀድሞ ተነግሮናል። ያውም ግልጽ በሆነ ቁዋንቁዋ!ይህን ጉዳይ በሚመለከት የተወሰኑ ክፍሎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንይ። " በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።" (የዮሐንስ ራእይ 13:14)
" የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።"
(የዮሐንስ ራእይ 13:15)
" ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥"
(የዮሐንስ ራእይ 13:16)
" የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ።"
(የዮሐንስ ራእይ 13:17)
ውድ ኢትዮጵያውያን!ዛሬ አሜሪካ ነገ ኢትዮጵያ እንደሚሆን ግልጽ ነው።የዓለም መንግስታት ይህን ማይክሮችፕ መግጠም የፈለጉት እንደሚባለው ስልጡን አሰራር ለመጀመር ሳይሆን ህዝቡን ሁሉ ጠቅልለው ለአውሬው ለማስገዛት ነው።የመጥፊያው ዘመን መድረሱን ሲያውቅ ሰይጣን ያዘዛቸውን እየተገበሩ ነው።ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው።አማኝ ህዝብም ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ይፈተናል።ስለዚህ ምልክት የነገረን ፈጣሪም የምልክቱ ተቀባዮችና እራሱ አውሬው እንዴት እንደሚጠፉ አብሮ ነግሮናል።የምናምን የበለጠ ወደ አምላካችን የምንጠጋበት፤የማናምን እንደ አዲስ አማኝ መሆን የምንጀምርበት ጊዜ አሁን ነው።ምክንያቱም ታላላቅ የሚባሉ የዓለም መሪዎች በዓለም ህዝብ ላይ ማይክሮችፕ የመግጠም ሂደት መጀመራቸው ብቻውን የአምላክን ቃል ፍጹምነት አረጋጋጭ ነውና።ይህ ዘመን ብዙዎቻችን ተንተርሰነው የኖርነውን መጽሐፍ ቅዱስ የምንገልጥበት ዘመን መሆን ይኖርበታል።
በፈጣሪ ለምናምን ሁሉ የህይወት ማንዋል ይሆነን ዘንድ ከአምላክ የተሰጠንን ቅዱስ መጽሐፍ የምንገልጥበት ዘመን ሊሆን ይገባል።ማይክሮ ችፕ ማለት የአውሬው ምልክት ሲሆን፤ያን የተቀበለ ሁሉ ከአሳቹ ሰይጣን የፍጻሜ ዘመን ጋር አብሮ ወደዘላለማዊው የእሳት ባህር ይጣላል!ማናችንም በፈጣሪ ህልውና የምናምን ሁሉ ነገሩ በግድ እንኩዋን ቢሆን መቀበል የለብንም።ምክንያቱም ስጋን ስለሚያጠፉ መንግስታትና አዛዣቸው የሆነውን ሳጥናኤልን ሳይሆን ነብስንም ስጋንም ስለሚያጠፋው ነው ቅዱስ አምላክ ነው ማሰብ ያለብን።በህያው ደም የተገዛን የአምላክ ገንዘቦች ነንና ለክፉው መንፈስ መገዛትም መስገድም የለብንም።ሰይጣን ተስፋ የለውም፤ነገር ግን ተስፋ አይቆርጥም ይባላል።እውነት ነው ።የመጥፊያው ዘመን እንደደረሰ ያውቃል። ስለዚህ በፈጣሪ አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች አጥፍቶ መጥፋት የመጨረሻ ግቡ ነው።ስለዚህ ልንስት አይገባም።መጽሐፍ ቅዱስ ሰማይና።ምድር ያልፋሉ፤-ቃሌ ግን አያልፍም ይላል።ይህን የፈተና ዘመን ጸንቶ ማለፍ መቻል የዘላለም ህይወትን መርጦ ፍጹም ከሆነው አምላክ ጋር መሆን ማለት ነው።በዚህ የሳተና ማይክሮችፕ የተቀበለ ግን እድል ፈንታው ከክፉው መንፈስ ጋር ይሆናል ማለት ነው።ምርጫው ደግሞ ለኛ የተተወ ነው።ማይክሮችን በሚመለከት ማንም ስለዘመናዊነቱና ስለ ምቾቱ ስለ ቀልጣፋ አሰራርና ስለ ስለ አስደናቂ የቴክኖሎጂ ውጤትነቱ ሊያብራራልን ይችላል።ነገር ግን እውነታው ባለሙያዎች የሚሉት ሳይሆን እግዚአብሔር ያለው ብቻ ነው!ይህን የተቀበለ ሙሉ ማንነቱን አስተሳሰቡን ጭምር ለክፉው መንፈስ አስረክቦ ህልውናውንም ህይወቱንም ሁሉንም ያጣ ሆነ ማለት ነው። ሌሎች የሚያዙበት እቃ ወይም በድን ሆነ ማለት ነው።ማይክሮ ችፕ የተገጠመበትን ሰው ልክ እንደ ኮምፒውተር ባለበት ሻት ዳውን ማድረግ/ማጥፋት/እጅግ ቀላል ስራ ይሆናል ።ነገር ግን ወደ ዋናው አሰራር እስኪገቡ ድረስ የተገጠመባቸው ሰዎች በህይወታቸው ላይ ቅንጣት አደጋ እንዳልደረሰባቸው ለማሳየት ሲባል ብዙ ዘዴዎችን ሊጠቀሙ ተዘጋጅተዋል።ምስክርነት የሚሰጡና ስለ ጥቅሙ የሚተነትኑ፣ከተገጠመላቸው በሁዋላ ህይወታቸው እንዳማረ ፣ነገሮች ቀላል እንደሆኑላቸው የሚመሰክሩ በርካታ ሰዎች ተዘጋጅተዋል።እኛ ግን መስማት ያለብን የአምላካችን ቃል ብቻ ነው።በየትኛውም ዘመን ወደ አገራችን አሰራሩ ይምጣ፤ለመሞት መዘጋጀት እንጂ መቀበል የለብንም።የምድር ህይወት ዘላለማዊ አይደለም።ዛሬ ታይቶ ነገ የሚጠፋ ባዶ ነገር ነው።ክፉው መንፈስም ቴክኖለጅውም የዓለም መሪዎችም እራሱ ሳጥናኤልና ተከታይ ጭፍሮቹ እንዲሁም የምድር መንግስታት ያልፋሉ።የፈጠረን አምላክ ግን አያልፍም።ስለዚህ እነሱ ስላመኑበትና መሆን አለበት ስላሉ ብቻ ልክ ናቸው ብለን አምነን ወይም ፈርተን ልንቀበል አይገባም።ማይክሮችፕን ከአውሬው ምልክት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብለው የሚያስተምሩንን የሐይማኖት መሪዎችም ልንሰማቸው አይገባም።
ሼር ይደረግ። Read more here

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time