Wednesday, March 26, 2025

በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተመረተ ነው!

 በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተመረተ ነው!

ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቀን ከ14 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት የሚገኝበት አቅም መፈጠሩን በግብርና ሚኒስቴር ዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ሃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ገለጹ።
ኢትዮጵያ እምቅ የዓሣ ሀብት ቢኖራትም በተለያዩ ተግዳሮቶች ምክንያት በዘርፉ ተጠቃሚ ሳትሆን መቆየቷን በግብርና ሚኒስቴር ዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ሃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ተናግረዋል።
በሀገር ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ የዓሣ ልማት ዘርፍ ማነቆ የሆኑ ተግዳሮቶችን በመፍታት ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።
በዚህም በዓሣ ምርታማነት ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አንስተው፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውስጥ የዓሣ ሀብት ልማት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን በአብነት ጠቅሰዋል።
በግድቡ በስፋት ተፈላጊ የሆኑ የዓሣ ዝርያዎች እየተመረቱ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህም በቀን ከ14ሺህ 500 ቶን በላይ የዓሣ ምርት የሚገኝበት አቅም መፈጠሩን አብራርተዋል።
በሕዳሴ ግድብ ውስጥ የተለያዩ የዓሣ ዝርያዎች መኖራቸውን የገለጹት ዶክተር ፋሲል የሚመረተው ዓሣ ተፈላጊነት ከፍተኛ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።
ዘርፉ ካላው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባለፈ ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ በቀጣይ የዓሣ ምርትን የበለጠ ለማሳደግ የዓሣ ጫጩቶችን ማሠራጨት እና ዓሣ በሌለባቸው የውሀ አካላት ላይ ዓሣ የሚመረትባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ የዓሳ ሀብት ባለሙያ አቶ ቡሸን ፉፋ በበኩላቸው፥ የሕዳሴ ግድቡ በክልሉ የዓሣ ምርት መመረቱ የክልሉን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንስተዋል።
በዘርፉ 64 ማኅበራት መደራጀታቸውንና ከእነዚህ ውስጥ 23 ማኅበራቶች የሥራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
በቀጣይም ወደ ሥራ ያልገቡ ማኅበራትን ወደ ሥራ ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
All reactions:
1.8K

Tuesday, March 18, 2025

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ደፋር ማሻሻያዎችን እና አፍሪካን የሚመሩ መፍትሄዎችን ከፒአርሲ ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ አሳሰቡ!

 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ደፋር ማሻሻያዎችን እና አፍሪካን የሚመሩ መፍትሄዎችን ከፒአርሲ ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ አሳሰቡ!


የመጀመርያው የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) እና አዲስ የተሾሙት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አመራር አባላት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂደዋል። ስብሰባውን በኤች.ኢ. ማህሙድ አሊ የሱፍ፣ የAUC ሊቀመንበር እና ኤች.ኢ. በአፍሪካ ህብረት የአንጎላ ሪፐብሊክ ቋሚ ተወካይ እና የፒአርሲ ሊቀመንበር አምባሳደር ፕሮፌሰር ሚጌል ሴሳር ዶሚኒጎስ ቤምቤ የአፍሪካ ህብረትን ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለማድረግ የስራ ዘዴዎችን በማሻሻል እና በPRC እና AUC መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርገዋል።


በመክፈቻ ንግግራቸው ኤች.ኢ. ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ህብረትን አላማዎች ወደ ተጨባጭ ውጤቶች መተርጎም አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል። "ህብረታችንን በአህጉራችን ወደ ውጤታማ የእድገት ሞተር ለመቀየር በተግባራዊነት እና በቁርጠኝነት መስራት አለብን" ሲል ተናግሯል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ቢሮክራሲውን ለመቀነስ እና የአሰራር ቅልጥፍናን ለማጎልበት የተጀመረውን ለውጥ ማጠናቀቅ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

ኤች.ኢ. ዩሱፍ የችሎታ ኦዲት እና የብቃት ምዘና (SACA) ፕሮግራምን አስፈላጊነት በማጉላት የAUCን ውጤታማነት እና ቅንጅት ለማሻሻል እንደ ቁልፍ ማንሻ ገልፀውታል። "የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ህዝቦቻችን የሚጠብቁትን ለማሟላት ምላሽ ሰጪ እና በተሻለ ሁኔታ የተቀናጀ መሆን አለበት" ሲሉም አክለዋል።

ሊቀመንበሩ ሰላምና ፀጥታን በማስመልከት ግጭቶችን ለመከላከል እና ለመፍታት በአፍሪካ መሪነት የመፍትሄ ሃሳቦችን በማጠናከር ጠንከር ያለ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል። እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን መፍታት እና በአህጉሪቱ መረጋጋትን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጿል።

ኤች.ኢ. በአፍሪካ ህብረት የአንጎላ ሪፐብሊክ ቋሚ ተወካይ እና የፒአርሲ ሊቀመንበር አምባሳደር ፕሮፌሰር ሚጌል ሴሳር ዶሚንጎስ ቤምቤ የሊቀመንበሩን ሀሳብ አስተጋብተዋል። በአፍሪካ ልማት ውስጥ የመሠረተ ልማት አውታሮች ወሳኝ ሚና እና ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካውያን መፍትሄዎች አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል. አምባሳደር ቤምቤ የአፍሪካ ህብረት ይበልጥ ቀልጣፋ እና ቢሮክራሲያዊ እንዲሆን የሪፎርም አስፈላጊነትን አሳስበዋል።

በስብሰባው ወቅት የPRC አባላት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የስራ ዘዴዎችን ገምግመዋል እና ግልፅነትን እና ተጠያቂነትን ለማሻሻል ሀሳብ አቅርበዋል ። ውይይቱን ለማጠናከር እና ትብብርን ለማጠናከር ከኮሚሽኑ ጋር የጋራ ማፈግፈግ ቀርቧል።

ኤች.ኢ. ማህሙድ አሊ የሱፍ በፒአርሲ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መካከል ስላለው ጠንካራ ትብብር አድናቆቱን በመግለጽ ኮሚሽኑ አህጉራዊ አጀንዳውን ለማራመድ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል። "የአፍሪካ ህብረትን ከአፍሪካ ህዝቦች ጋር እናቀርባለን" ሲሉ የኮሚሽኑ ፒአርሲ የአህጉሪቱን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመቅረጽ የማያቋርጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
https://au.int/en/pressreleases/20250317/auc-chairperson-urges-bold-reforms-and-african-led-solutions-inaugural

ፀሐይ ባለበት የቫይታሚን D እጥረት ለምን?

 ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆነው ቫይታሚን ዲ የሚገኘው በፀሐይ ጨረር አማካኝነት በተፈጥሮ ሂደት ነው። ኢትዮጵያ ዓመቱን ሙሉ የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት የምታገኝ ሀገር ብትሆንም በቅርቡ የወጣ መረጃ ብዙዎች የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዳለባቸው ያመለክታል። ለምን ይሆን?



ቫይታሚን ዲ

የቫይታሚን ዲ እጥረት በመላው ዓለም ሰዎች ላይ ስለሚታይ አሳሳቢ መሆኑ ይነገራል። በተለይ በዓመት ውስጥ የፀሐይ ብርሃንም ሆነ ሙቀቷን በውስን ወራት ብቻ በሚያገኙ የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ሃገራት ሰዎች በተለያየ መልኩ በሚዘጋጁ ተጨማሪ የመድኃኒት ምግቦች ካላካካሱት ዘርፈ ብዙ የጤና ችግር እንደሚያስከትል ሀኪሞች ይመክራሉ።

በአብዛኛው በእነዚህ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዳለባቸው በምርመራ እንደተደረሰበት ሲናገሩ ሲሰማ ያሉበት ሀገር የፀሐይ ብርሃን እንደልብ ስለማይገኝ ነው ሊባል ይችላል። ይኽ ችግር ግን ኢትዮጵያም ውስጥ እንዳለ መነገሩ ግን መንስኤው ምን ይሆን የሚል ጥያቄን ያስከትላል።

የውስጥ ደዌ ከፍተኛ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ንብረት ገዳሙ በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህርና በደብረ ታቦር ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ። ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ቫይታሚን ዲ 90 በመቶ የሚሆነው የሚመረተው ከፀሐይ በሚገኝ ጨረር በቆዳችን አማካኝነት በተፈጥሮ እንደሚገኝ ነው የሚያስረዱት።

«ቫይታሚን ዲ ምንድነው የሚለውን ስናይ ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ ከሆኑትና ብዙ የሰውነታችንን እንቅስቃሴ ከሚቆጣጠሩ ቫይታሚኖች አንዱ ነው፤ ቫይታሚን ዲ 90 በመቶ የሚሆነው ከቆዳ የሚመረት ሲሆን ከቆዳ ለመመረት ደግሞ አልትራቫዮሌት ቢ የተባለ የፀሐይ ጨረር ያስፈልገዋል።»

ዶክተር ንብረት እንደገለጹት ቫይታሚን ዲ በዋናነት በሰውነታችን ውስጥ ካልሲየም የተባለውን ንጥረነገር እንቅስቃሴ ይወስናል። ካልሲየም ደግሞ በተለይ ለአጥንት ጥንካሬ ያለው ጠቀሜታ ወሳኝ ነው።

የውስጥ ደዌ ህክምና ባለሙያው እንደገለጹልን ቆዳችን ቫይታሚን ዲ እንዲያመርት የፀሐይ ጨረር ይፈልጋል። ይኽ በሌለበት እንዴት ነው በየቀኑ የሚያስፈልገንን ቫይታሚን ዲ ሰውነታችን የሚያገኘው የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። ዶክተር ንብረት፤ እንደሚሉት ከፀሐይ ጨረር በተጨማሪ ከተለያዩ የዓሣ ዓይነቶች እንዲሁም ከእንቁላል አስኳል ቫይታሚን Dን ማግኘት ይቻላል። በመድኃኒት መልክ የተዘጋጁ የቫይታሚን ዲ እንክብሎችን በተጨማሪ ምግብነት መውሰድም ሊረዳ እንደሚችል ጠቁመዋል። በዋናነት ግን እነዚህ በገንዘብ የሚገዙ እና እንደልብ የማይገኙ ምግቦች በሌሉበት ያለምንም ወጪ የፀሐይን ጨረር መጠቀሙ በተፈጥሮ ቫይታሚን ዲን ለማግኘት እንደሚረዳ ነው የህክምና ባለሙያው አጽንኦት የሰጡት።

የቫይታሚን ዲ እጥረት መረጃ

የኢትዮጵያ የ13 ወር ፀጋ የሚለው የቱሪዝም መሪ ቃል በዋነኝነት የፀሐይን ብርሃን እና ሙቀት መነሻ ያደረገ መሆኑ ነው የሚገለጸው። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ይፋ የወጣ መረጃ ዓመቱን ሙሉ ፀሐይ በምታገኘው ሀገር በርካቶች ለቫይታሚን ዲ እጥረት መጋለጣቸውን ያመለክታል። እንዴት ሊሆን ቻለ?

ዶክተር ንብረት ኢትዮጵያ ውስጥ ለጤና እጅግ አስፈላጊ የሆነው ቫይታሚን ዲ ለማግኘት በነጻ እና እንደልብ ተፈጥሮ ያቀረበችውን የፀሐይ ጨረር መጠቀም አማራጭ የለውም። ሆኖም ግን ዓመቱን ሙሉ ፀሐይ እንደልብ በምትገኝበት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎች ለቫይታሚን ዲ እጥረት መጋለጣቸውን የምርመራ ውጤት አሳይቷል። በጥናቱ መሠረትም ከገጠር ነዋሪዎች ይልቅ የከተማ ነዋሪዎች በይበልጥ ለቫይታሚን ዲ እጥረት የተጋለጡ ናቸው።

ኢትዮጵያውያን በአብዛኛው የቆዳ ቀለማችን ጥቁር እንደመሆኑ ረዘም ላለ ጊዜ ፀሐይ መሞቅ ሊኖርብን ነው። ግን በየትኛው ሰዓት ይሆን ለዚህ የሚትጠቅመንን ፀሐይ የምናገኘው? ዶክተር ንብረት እንደሚሉት በኢትዮጵያ አቆጣደር ከጠዋቱ አራት ሰዓት እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ከ20 ደቂቃ ጀምሮ ረዘም ላለ ጊዜ ሰውነታችን በቂ የፀሐይ ጨረር እንዲያገኝ ማድረግ ይኖርብናል። የፀሐይ ጨረር ማግኘት ያለበት ደግሞ በተለይ ፊታችን እና የእጃችን ክንድ መሆን እንዳለበትም ነው የመከሩት።

እርግጥ ነው በተጠቀሰው ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ጃንጥላ ይዞ መሄድ፤ አለያም ጥላ ባለበት አካባቢ መቀመጥን የመሳሰለ ልማድ አለ። ዶክተር ንብረትም በተለይ በከተማ አካባቢ ይህንኑ ታዝበዋል። በዚያ ላይ የኢትዮጵያን የቆዳ ቀለም ረዘም ላለ ጊዜ የፀሐይ ከሚያስፈልጋቸው ወገን ነው። ብዙውን ጊዜ ጃንጥላን ለፀሐይ መከላከያ መጠቀሙ ወገኖችም ሰውነታቸው የሚያስፈልገውን ቫይታሚን ዲ እንዳያገኝ እንቅፋት እየሆኑ መሆኑን አመልክተዋል። 

Source: https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%89%AB%E1%8B%AD%E1%89%B3%E1%88%9A%E1%8A%95-d-%E1%8A%A5%E1%8C%A5%E1%88%A8%E1%89%B5/a-71964087


"እንደ አሮጌ ምንጣፍ የተጣለ" - የቻይና መንግሥት ጋዜጣ የቪኦኤ በጀት እንዲቋረጥ መወሰኑን አወደሰ!

 የቻይና መንግሥት ጋዜጣ የአሜሪካው ፕሬዝንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) በጀት እንዲቋረጥ መወሰናቸውን አወደሰ።



የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) እና ራድዮ ፍሪ እስያ (አርኤፍኤ) በቻይና መንግሥት ዙሪያ ለዓመታት ሲዘግቡ የቆዩ ሲሆን ትራምፕ የጣቢያዎቹ በጀት እንዲቀነስ ወስነዋል።

ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው አርብ ነው። 1300 የቪኦኤ ሠራተኞች በግዴታ እረፍት እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።

ተቺዎች ውሳኔው ዲሞክራሲን ወደኋላ የሚጎትት ነው ቢሉም ግሎባል ታይምስ የተባለው የቻይና መንግሥት ጋዜጣ ቪኦኤ አሁን "እንደ አሮጌ ምንጣፍ ተጥሏል" ብሏል።

ዋይት ሐውስ የትራምፕን ውሳኔ በተለመከተ በሰጠው መግለጫ "ግብር ከፋዮች ከዚህ በኋላ ለፕሮፖጋንዳ ገንዘብ አይከፍሉም" የሚል አስተያየት።

ትራምፕ ያስተላለፉት ውሳኔ በኮንግረሱ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን ዩኤስ ኤጀንሲ ፎር ግሎባልድ ሚድያ የተባለውን ድርጅት ዒላማ ያደረገ ነው። ይህ ኤጀንሲ ቮኦኤ፣ ራድዮ ፍሪ እስያ እና ራድዮ ፍሪ አውሮፓ የተባሉትን ጣቢያዎች ያስተዳድራል።

እኒህ ጣቢያዎች የፕረስ ነፃነት የላቸውም በሚባሉ ሥፍራዎች በሚሠሯቸው ዘገባዎች ይታወቃሉ። ቻይና፣ ካምቦዲያ፣ ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ከእኒዚህ ሥፍራዎች መካከል ይመደባሉ።

ቪኦኤ ቻይና ውስጥ እንዳይሰራጭ ቢታገድም አድማጮች በአጭር ሞገድ ራድዮ አሊያም 'ቪፒኤን' ተጠቅመው ማግኘት ይችላሉ።

አርኤፍኤ በተለይ በካምቦዲያ ስላለው የመብት ጥሰት በመዘገብ የሚታወቅ ሲሆን የቀድመው የሀገሪቱ አምባገነን መሪ ሁን ሴን የትራምፕን ውሳኔ "ለሐሰተኛ ዜና ትልቅ አስተዋፅዖ የሚያበረክት" ሲሉ አሞግሰውታል።

በቻይና ዢንግጂያንግ ግዛት በሚገኙ ካምፖች የቻይና መንግሥት የኡጉር ሙስሊሞችን አፍኖ ማስቀመጡን ቀድመው ከዘገቡት መካከል አንዱ አርኤፍኤ ነበር።

ቤይጂንግ ይህን ወቀሳ የማትቀበለው ሲሆን ሙስሊሞች በፍላጎታቸው "ትምህርት ለመቅሰም" ነው የገቡት፤ የካምፖቹ ዓላማ ደግሞ "ሽብርተኝነት እና ኃይማኖታዊ ፅንፈኝነትን" መከላከል ነው ትላለች።

ቪኦኤ ከሰሜን ኮሪያ ጠፍተው ስለሚወጡ ዜጎች እንዲሁም የቻይናው ኮሚዩኒስት ፓርቲ በኮቪድ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎችን ለመደበቅ ስላደረገው ሙከራ በሠራው ዘገባ ሽልማት ተበርክቶለታል።

በዋነኛነት በራድዮ የሚተላለፈው የአሜሪካ ድምፅ በአማርኛ እና በማንድሪን እንዲሁም በበርካታ ቋንቋዎች በተለያዩ ሀገራት ይተላለፋል።

የቻይና መንግሥት ሚድያ የሆነው ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ የቪኦኤን መዘጋት አወድሶ ጣቢያው "የውሸት መፈብረኪያ ነው" ብሏል።

የቀድሞ የቢቢሲ ጋዜጠኛ የነበረችው እና በቪኦኤ መዘጋት ምክንያት ሥራዋን ያጣችው ቫልድያ ባራፑትሪ የቻይናው ጋዜጣ ያወጣው ዘገባ "የሚያስደንቅ አይደለም" ስትል ለቢቢሲ ትናገራለች።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ ፕሮፖጋንዳንድ ለመገዳደር የተቋቋመው ቪኦኤ በ50 ቋንቋዎች የሚተላለፍ እና ከ360 ሚሊዯን በላይ ሳምንታዊ አድማጮች ያሉት ጣቢያ ነው።

በቻይና፣ ሰሜን ኮሪያ፣ በኮሚዩኒስት ኩባ እና በቀድሞው ሶቪዬት ሕብረት ተላልፏል። በርካታ ቻይናዊያን እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲለምዱም አስተዋፅዖ አድርጓል።

የቪኦኤ ዳይሬክተር ማይክል አብራሞዊትዝ የትራምፕ ውሳኔ ቪኦኤን ነቅንቆታል ብለው "በተቃራኒው እንደ ኢራን፣ ቻይና እና ሩሲያ ያሉ ሀገራት ቢሊዮን ዶላሮች እያፈሰሱ የአሜሪካን ስም እያጠለሹ ነው" መሆኑን ተናግረዋል።

Source: https://www.bbc.com/amharic/articles/c93nx15wxl2o

Sunday, September 15, 2024

Killings, abductions, funding shortfalls stifle WFP relief efforts across Ethiopia!

 

Killings, abductions, funding shortfalls stifle WFP relief efforts across Ethiopia!

Eight personnel dead as org. takes USD 30mln loan to sustain operations


The World Food Program says security concerns are straining its ability to deliver crucial aid assistance in Ethiopia as no less than eight humanitarian workers lost their lives to violence over the past year, while a further 20 were the victims of abductions.


Zlatan Milišić, WFP country director in Ethiopia, told The Reporter that seeing through humanitarian assistance programs and deliveries has grown increasingly challenging for the United Nations agency.


“Security challenges are often linked to banditry or robbery on the road by unidentified armed groups. They pose risks, threats, and challenges for us,” he said.


The movements of the world’s largest humanitarian organization are being deeply affected by protracted conflicts and security threats in Oromia, Gambella, Somali, parts of Tigray, and Afar, as well as by the silent battles going on between armed groups and government forces in the Amhara region, according to the Director.

“It’s difficult logistically and it’s difficult security-wise,” he said. “There are issues particularly in the Amhara Regional State.”

During a sit down with The Reporter, Milišić praised his staff for prevailing against the life-threatening challenges while drawing attention to what he says is an increasingly difficult and worrisome work environment.

Ensuring the safety and security of the staff, partners, contractors and cargo have become the organization’s top priority as the WFP finds itself walking a tightrope in its attempt to deliver life-saving assistance to target populations while keeping its personnel out of harm’s way.

“If we send our convoy and one, two, or five of our trucks get offloaded by people with guns, that’s a problem,” said Milišić. “We can resolve it once, but if it happens again and again, you start questioning what assurances we have sending this. Our donors start asking why we are sending food to areas where we get robbed. But not sending food isn’t an option because people are going to be hungry.”

A chronic shortfall in support from traditional donors has forced the WFP wing operating in Ethiopia to take a loan of USD 30 million from its global umbrella contingencies fund.

“If we didn’t take that loan, we would have fully stopped some of our programs by September and we would have zero food by now,” said Milišić.

The Director noted concerns that WFP Ethiopia’s once stellar reputation for resilience, livelihoods, nutrition, and school feeding programs has dwindled over the past couple of years.

“If one wishes to do more of these works, which we are strong at and for which the potential exists, it can be done. But a lack of resources and some of the traditional donors focusing on humanitarian assistance is not allowing us to do more. We cut numbers there as well,” he said.

Despite the threats, abductions, and killings, WFP Ethiopia claims it has managed to meet 90 percent of its goal in reaching people in need.

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time