Sunday, June 13, 2021

ወልቃይት የአማራ የግፍ ጥግ ማሳያ!

 ወልቃይት የአማራ የግፍ ጥግ ማሳያ!

በወልቃይት ዘመናቸውን ሙሉ በግፍ እና በጭቆና ጫንቃቸው የጎበጠ አይናቸው እያየ ልጆቻቸው የታረዱባቸው እናቶች የባሎቻቸውን የተቆራረጠ አካል የቀበሩ ሚስቶች የአባታቸው ሰውነት ሲበለት የተመለከቱ ህፃናትን መስማት እንዴት ያማል።
መስማት ብቻም ሳይሆን በአይን የሚታዩ የግፍ ቅሪቶችን መመልከት ከአእምሮ በላይ የሆነ ስብራት ነው። በአንድ ጉድጓድ ከ40-50 ንፁሐን በተቀበሩበት በማይካድራ የጅምላ መቃብር መቆም ዘመንን ሙሉ የማይረሳ ስቃይ ያሸክማል። ስለራሳቸው ልጆች ብቻ ሳይሆን ስለማያውቋቸው በግፍ ስለተገደሉ ቀን ሰራተኞች ጭምር በየቀኑ አመሻሽ ላይ በመቃብር ስፍራው እየተገኙ "እናቶቻችሁ ምን ይሉ ይሆን" እያሉ ስለሚያለቅሱ እናቶች መስማት ደግሞ ከአዕምሮ በላይ ነው።
በህመም ላይ ሳሉ አልጋቸው ላይ የታረዱ፣ ልጆቻቸው ፊት የተቆራረጡ፣ በህይወት እያሉ እሳት የተለቀቀባቸው፣ አጥንታቸው ተለቃቅሞ የተቀበሩባት ምድር ማይካድራን በሀዘን ተሰናበትናት።
ይህ ሁሉ ግፍ ከጥቂት ቀናት ፕሮፖጋንዳ ውጪ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ሚዲያዎች ሊናገሩት ያልደፈሩና ይልቁኑ ሆን ብለው የሸፈኑት እውነት መሆኑ ከልብ ያስቆጫል፤ያንገበግባል፤ያስተዛዝባልም፤ እሳትን በልብስ ውስጥ ሸሽጎ መኖር ይቻላል?

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time