Sunday, August 12, 2018

በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል


በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የሰዎች ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።
አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር ሞሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ለይ መሆኑን የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።
በአደጋውም የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱንም አቶ አዲሱ ገልፀዋል።
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ላለፈ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎችም የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።
ከአደጋው ጋር ተያይዞም አንድ የሻሸመኔ ከተማ የፀጥታና አስተዳደር በሮ ተሽከርካሪ በእሳት መጋየቱንም አቶ አዲሱ አስታውቀዋል።
ተሽከርካሪው ፀጥታ የማስከበበር ስራ ላይ በተሰማራበት ወቅት ቦምብ ጭኗል በሚል በተሳሳተ መረጃ በእሳት መጋየቱን አቶ አዲሱ ገልፀዋል።
ሆኖም ግን በተሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት ቦምብ እንዳልነበረ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ማረጋገጣቸውንም አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅትም አደጋው ጋር ተያይዞ ወጣቱን በመምሰል የህገ ወጥነት እንዲስፋፋ መንገድ የመዝጋት፣ የዝርፊያ እና በፍቅር አብሮ የኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች ላይ ጉዳት ለማድረስ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ምልክቶች መታየታቸውንም ገልፀዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች እና ወጣቶች ከዚህ ተግባር በመቆጠብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time