1885 Gonder Gondar City |
ጎንደር ቀደም ሲል የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዛሬ የጎንደር ክፍለ ሐገር እና የጥንትዋ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበር። ጎንደር ክፍለህገር በሰባት አውራጅዎች ይከፈላል። እነዚህም አውራጃዎች ከነዋና ከተማቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ወገራ አውራጃ ዋና ከተማው ዳባት፣ ሰሜን አውራጃ ዋና ከተማው ደባርቅ፣ ደብረታቦር አውራጃ ዋና ከተማው ደብረታቦር፣ ሊቦ አውራጃ ዋና ከተማው አዲስ ዘመን፣ ጋይት አውራጃ ዋና ከተማው ንፋስ መውጫ፣ ጭልጋ አውራጃ ዋና ከተማው አይክል፣ ጎንደር ዙሪያ አውራጅ ዋና ከተማው ጎንደር ናቸው።ዛሬ በስሜን ጎንደር ዞን በአማራ ክልል ሲገኝ ከጣና ሃይቅ ሰሜን አንገረብ ወንዝ ላይ ከሰሜን ተራራ ወደ ደቡብ ምእራብ ሰፍሮ ይገኛል። በ12°36′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው። አጼ ፋሲለደስ ጎንደርን እንደ ዋና ከተማነት ለመጀመሪያ ጊዜ ይጠቀሙ እንጂ ከዚያ በፊት በአካባቢው ሰወች ይኖሩበት እንደነበር ታሪክ አለ። ሆኖም ግን ከተማው በታሪክ የገነነው አጼ ፋሲለደስ በአሁኑ ፋሲል ግቢ ወይም የነገሥታት ግቢ ውስጥ የፋሲል ግንብን በ1636 ሲያንጽ ነበር።
የማእከላዊ እስታቲስቲክ ባለስልጣን በ1998 ቁጥሩ ጎንደር 194,773 የህዝብ ብዛት ስትይዝ ከነሱም 97,625 ወንዶች ሲሆኑ 97,148 ሴቶች ናችው።
No comments:
Post a Comment