ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶር መረራ ጉዲና መታሰራቸው “በመናገር ነጻነት ላይ የተወሰደ ቅጥ ያጣና አናዳጅ እርምጃ ነው” ብሎታል
ዋሽንግተን ዲሲ —
"የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲጎናፀፍ በሰላማዊ መንገድ ያላሰለሰ ትግል የሚያደርጉትን ዶ/ር መረራ ጉዲናን ማሰር የአምባገነንነት ማሳያ ነው" ሲሉ የቀድሞ የሕወሓት ታጋይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ሸንጎ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ተናገሩ።
ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶር መረራ ጉዲና መታሰራቸው “በመናገር ነጻነት ላይ የተወሰደ ቅጥ ያጣና አናዳጅ እርምጃ ነው” ብሎታል
የአምነስቲ የምስራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የታላላቅ ሃይቅ ሀገሮች ምክትል ስራአስኪያጅ ሚሸል ካጋሪ የዶር መረራ እስራት “ለወራት የዘለቁ የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋባቸውን ሰልፎች ከመቆስቆስ ባለፈ መፍትሄ አይሆንም” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቡን የሰብዓዊ መብት ሮሮዎችና የአስተዳድር መከፋቶችን ተጨማሪ የመብት ጥሰቶችና እስራትን በማከል መፍታት እንደማይችል አምነስቲ አሳስቧል።
ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት Read more here
No comments:
Post a Comment