Sunday, October 9, 2016

የመንግስታቱ ድርጅት ለኢትዮጵያ መንግስት ማሳሰቢያ ሰጠ


በኢሬቻ በዓል ላይ የተፈጠረው ክስተት ነፃ ምርመራ እንዲካሔድበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ፡፡ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በታደሙበት በዚህ በዓል ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች አሁንም መረጋጋት እንደሌለ የገለጹት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ሩፔርት ኮርቬይ፣ ተቃውሞውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የስልክ አገልግሎቶችን ከማቋረጥ ይልቅ በሀገሪቱ ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ እንዲያመጣ አሳስበዋል፡፡ ቃል አቀባዩ አክለውም ተቃውሞን ማዳፈን ይበልጥ ውጥረትን እንደሚያበረታ ገልጸዋል፡፡

አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን የተመለከቱ በርካታ መረጃዎች ለተመድ እንደሚደርስ የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ በሁለቱ ክልሎችም ዜጎች እየታሰሩ እንደሚገኙ ለድርጅቱ ከሚላኩለት ጥሪዎች መረዳት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ለተ.መ.ድ እየቀረቡ ያሉት አቤቱታዎች እንደሚያሳስቧቸው የገለጹት ሩፔርት ኮርቬይ፣ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው ብቻ የታሰሩ ዜጎች እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የተፈጸሙትን የመብት ጥሰቶች፣ ገለልተኛ ታዛቢዎች እንዲያጣሩ ጥሪያቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት ያስተላለፉት የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቃል አቀባይ፣ ባለፈው ነሐሴ ወር የኢትዮጵያ መንግስት ገለልተኛ አካል ገብቶ ጉዳዩን እንዲያጣራ ተጠይቆ አሻፈረኝ ማለቱን አስታውሰዋል፡፡ አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት እየቀረበለት ያለውን ጥሪ እንዲቀበል አሳስበዋል፡፡
እሁድ ዕለት በነበረው የኢሬቻ በዓል ላይ የተከሰተውን እልቂት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስለጣናት ስለ ድርጊቱ የሚሰጧቸው አስተያየቶች ለተቃውያ መባባስ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የገመቱት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ፣ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡ በዕለቱ የነበረውን የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ ሽሽት ሲሮጡ በርካታ ሰዎች ወንዝ እና ገደል ውስጥ ገብተው መሞታቸውን የገለጹት ቃል አቀባይ ሩፔርት ኮርቪይ፣ የኢሬቻን በዓል ጨምሮ ከዚህ በፊት በተካሔዱ ተቃውሞች እና ተቃውሞውን ተከትሎ የተወሰዱ እርምጃዎች ለተጠያቂነት እንዲረዱ ማጣራት እንዲደረግባቸው ጠይቀዋል፡፡ Read more here

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time