Friday, May 2, 2014

እስከመቼ?


እስከመቼ በጉልበት መነጣጠቅ ሥልጣንን በትንቅንቅ? 
እስከመቼ በሽኩቻ ሀገርን ማድረግ ገወቻ? 
እስከመቼ መሆን ሙጫ ያለዲሞክራሲ ምርጫ? 
እስከመቼ ወንጃ ወንጃ መፍትሔ መሻት በጠበንጃ? 
እስከመቼ…? እስከመቼ…? እስከመቼ ወተምተም ወተምተም አረጋግዞ ጥላቻና ቂም? 
እስከመቼ እንጎድ እንጎድ በመብረቅ ድምፅ በነጎድጓድ?
 እስከመቼ ቃሰንተኛ የሙስና ሱሰኛ?
 እስከመቼ ማቶንቶን ያለነፃነት መታፈን?
 እስከመቼ መርገጥ ጭቅጫቅ ያለ ፍትህ መንቦራጨቅ? 
እስከመቼ…? እስከመቼ…? እስከመቼ መጠላለፍ እያመጹ ጥሎ ማለፍ? 
እስከመቼ ምቀኝነት በቀልና መጥፎ ቅናት?
 እስከመቼ አምባገነን እየሾሙ የራስ ወገን፣ እየሻሩ የራስ ሕግን? 
እስከመቼ ማሰብ ሴራ የማይጠቅም ክፉ ሥራ? 
እስከመቼ…? እስከመቼ…? እስከመቼ ጌታ፣ ሎሌ መፈናከት በብርሌ? 
እስከመቼ በቅራኔ መወናጀል በኩነኔ? 
እስከመቼ እሳት መጉረስ፣ እሳት መድፈን፣ እሳት መላስ? 
እስከመቼ ቀዳዳ ቤት በፉክክር የማይዘጉት?
 እስከመቼ “ነፃ አውጭ ግምባር” ነፃ የማያወጣ ግርግር? 
እስከመቼ አለመስማማት ለራስ ብቻ ወየው ማለት? 
እስከመቼ…? እስከመቼ…? ***

Souirce: Unknown 

No comments:

Post a Comment

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...

Recent Articles

Recent Video Uploads

Subscribe Ethiopia Today Videos and Watch on You Tube

Ethiopia Today

  • Active a minute ago with many
  •  
  •  videos
Ethiopia Today bringing you recent information about Ethiopia. It bring you, news, Amharic movies,  Musics and many clips. subscribe and get many Videos on time