Sunday, May 27, 2018

ዲ/ን ዳንኤል በጌጤ ዋሚ ላይ መምህር ግርማን ለመንቀፍ ባደረገው እይታ ላይ ትምህርት ይሆነው ዘንድ

ዲ/ን ዳንኤል በጌጤ ዋሚ ላይ መምህር ግርማን ለመንቀፍ ባደረገው እይታ ላይ ትምህርት ይሆነው ዘንድ
"1ኛ ቆሮ 10፥10 ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ።"
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- ሰው ተዋርዶ ሰይጣ ከብሮ
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- ለታይትልክ ማስተካከያ ብንጠቁምህ " የእግዚአብሔር ክብር ተገልጦ ሰይጣን ተዋርዶ ሰው ከበረ"
ከርእሱ እንጀምርና ሰይጣን ከብሮ ብለሀል። ብዙ ህዝብ የሚልህ የተለየ አይን አለህ እንዴ? እኛ ያየነው ያሰቃያት ሰይጣን ሲጮህ ሲያለቅስ ሲገሰፅ ነው :: መጨረሻ ድና እሷ ስትከብር ሰይጣኑ ተዋርዶ ሲባረር ነው። አንተ ከየት አመጣህው እይታህ ተጣሞል።
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- የቤተ ክርስቲያናችን የገድላትና የተአምራት መጻሕፍት ሲጻፉ፣ የሰዎቹን ክብር በሚጠብቅ መንገድ ካልሆነ በቀር ችግር ደርሶባቸው ተአምር የተደረገላቸውን ሰዎች የተጸውዖ ስም አይገለጡም፣ ወይም የክርስትና ስማቸው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሰዎቹን በስማቸው መጥራት ቢያስፈልግ እንኳን ለዝርዝር ማንነታቸው በማይመች ስም ይገለጣሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረግበት ዋናው ምክንያት የሰውን ልጅ ሰብአዊ ክብር(Human dignity) ለመጠበቅ ነው፡፡ እነርሱ ቢያልፉም እንኳን ልጅና ልጅ ልጅ ይኖራልና፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- እዚህ ጋር ሀሳብህ ከወንጌል ጋር የተቃረነ ነው።ወደ መንፈሳዊ ህይወት ከእግዚአብሔር ጋር የግልፅነት ህይወት የሚጀምሩ ሰዎች ።መንፈሳዊ ድህነት እፍረት የለውም። ለትውልድ እንካን ከልጅ ልጅ ቢተላለፍ መንፈሳዊ ኃይል እንጂ ውርደት አይደለም።ባይሆን ለመተተኞችና በጨለማ ለሚሰሩ ለሚመላለሱ ያስደነግጣቸዋል። እንዴት ተቃረንክ?
ክርስቶስ በህዝብ ፊት ያረገውን ሁሉ እኮ እንደዚሁ እየኮነንክ ነው :: የመቅደላዊት ማሪያም ይክርስቶስ ማዳን እኮ ለህዝብ ሁሉ የድህነት ትምህርት ነው። በአንተ አስተሳሰብ እኮ ውርደት ሊመስል ነው እኮ
"ሉቃስ 11፥39 ጌታም እንዲህ አለው። አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል እናንት ደንቆሮዎች፥ የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን? ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።"
አንተና ሌሎች ከውጪ ለሚመጣው የወሬ ተፅእኖ ላይ በጣም ደንግጠህና ተጨንቀህ ለማጥራት ትሞክራለህ። መምህር ግርማ ግን ውስጣ የጠፋበትን ቦታ በኢየሱስስ ክርስቶስ አጠሩላት ። አየህ የት ቦታ እንዳለህ ሰው ውስጡ ካልዳነ ለውጪው አይሆንም። የሰው ማንነቱ ከውስጥ ሲድን ነው መጀመሪያ ስለ ውስጥህ ድከም ከውጪው ከዚያ በሃላ የሚስተካከል ነው
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- እኅታችን ጌጤ ዋሚ ‹ሩጫን በሚከለክሉ በአጋንንት› ተያዘች ተብሎ የተለቀቀባትን ቪዲዮ ስመለከት
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- በኃላፊነት የለቀቀው አካል የቪዲዮ Title የሚለው ይህ ነው Memhir Girma VCD 53A &B አንተ ከየት አገኝህው ። እውነተኛ ምንጭ ማየት ይገባህ ነበር:: አየህ የአንተና እይታቸው የተበላሸባቸው ይህ ነው ችግራቹሁ ። እውነታውን ከትክክለኛ ምንጩ ቀጥታ ከማየትና በጥሞና ከመረዳት ይልቅ የራስ ትርጉማዊ የቃላት ጥበብ ስንጠቃ ውስጥ ገብተህ ልክ እንደ ፈሪሳዊና እንደ ፃሕፎች ለሚደረገው የተቸገሩትን በመንፈስ ቅዱስፀጋ የመጎብኝት ግልጋሎት ላይ ጠማማነትን ቶሎ በምስጊን ምእመን ልብ ውስጥ ትተክላለህ:: አንድ ምክር ላንተ ላቀብልህ እባክህን ትምህርታቸውን በንፁህ ልቦና ተከታተለው ። ይህን ስትገነዘብ ከዚያ የፈውሱ ነገር ትረዳዋለህ።ችግርህ ቀጥታ የፈውሱን ነገር ፈጥነህ የማየት ችግርም ይመስላል።
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- በእምነት ስም የሚነግዱ ሰዎች የደረሱበትን ሞራላዊ ኪሣራ አየሁት፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- ብዙ ጊዜ ከችግርህ አንዱ ይህ ነው።ብር እና፣ዝና ።መንፈሳዊነቱን ትተከዋል ፤ የሚሰበክ የቃል ታሪክ አርገከዋል። ጥያቄ ላንተ :: የቱ ጋር ነው እምነትን ወደ ንግድ ያደረጉት ? ነጋዴ ለትርፉ ይሮጣል፤ በመንፈስ የተጠቃ ህዝባችንን ይህን አይቶ ሌላውም የድህነት መነቃቃት ውስጥ እንዲመጣ ማድረግ ምኑ ላይ ነው ንግድ የሚያሰኘው ። ነው ወይስ ከህዝበ ክርስቲያን ተማሪዎች ጋር የበረከት ስራ መስራት ፤ ለድሃ ምግብ አልባሳት ብር መስጠት ንግድ ያሰኛልን ? እንደሚገባን የራስህን ገበና ወደ እሳቸው ማዛወር ይመስለናል። የአንተ እና የሌሎች ግልጋሎት ከመንፈሳዊነት ይልቅ ንግድ ይመስላል። እንዴት በለኝ ? በአመት ስንት ጊዜ ነው በአገልግሎት ስም የተለያዩ የአሜሪካና አውስትራሊያ አውሮፓ ቋሚ ምድብ ጥሪ ተይዞላቹ የአገልግሎትና ዳጎስ ያለ የብር ምንጭ ዋጋ የሚገኝበት የእራት ጥሪዎች ያላቹሁ:: እነዚህ የማይነቃነቁ ጥሪዎች እኮ ከእምነት ይልቅ ጥቅም ተኮር ድብቅ ኔትዎርክ አይደል እንዴ? እርስ በርስ ነባር ሰባኪዎች የምትጠቃቀሙበት ስልት ይህ ለነገሩ ከስቴት ወደ እስቴ እና ከአዲስ አበባ ወደ እስቴት ያለ ስልት አካሄዳቹህ ንግድ ነው ወይስ ግልጋሎት ? ሰባኪና አገልጋይ በየቤተክርስቲያን ጠፍቶ ነው እንዴ? ሌላ ከፍ ብሎ ካገለገለ የተለያየ ስምና ታፔላ የምታወጡለት። ትዝብት ነው!
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- ከመጀመሪያው ሰይጣንን እየቀዱ ለገበያ ማዋል በየትኛውም የቅዱሳን ሕይወት ውስጥ የማናየው ነው፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- ይህውልህ ከዚህ በፊትም ነግረንክ ነበር አንተ ሰይጣን ሲያለቅስ ሰምተህ ውስጥህ ይረበሻል። ነገር ግን በሚልዩን የሚቆጠር ምእመን ደግሞ ይህን አይቶ ጠላትን ለይቶ በማወቅ ነብሱን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያረገ ብዙ ነው።አንተ እንዲህ የለም እያልክ እንደ ፈሪሳዊ መፅሐፍ ላይ ታሪክ ስታፈላልግ ።ብዙ ሺህ ምእመን ደግሞ ታሪኩን ወዶ አልፎክ መንፈሳዊ ጎዳናና በረክት ውስጥ ገብቷ ። አንተ ከምትለው በላይ ከመምህር ግርማ በጣም ብዙ ተምሮ በንቃት አልፎክ ሄዳል። አንተ ገና ፈሪሳዊያን የወደቁበት የነገር መቆፈር ላይ ወድቀሃል።የመምህር ነገር የልቡ አይን የተከፈተለት ብቻ ነው የሚያስተውለው ያለበለዚያ በአይኑ ላይ የተጋረጠው መንፈስ የተለያየ ስልታዊ ምክንያቶች እያሰባሰበ የሌሎችን ልብ መፈታተን ህይወቱ ይሆናል።
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- መቼም ሰይጣን እንደዚህ ዘመን በክብር መድረክ ያገኘበት ጊዜ የለም፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- የእይታ ችግር ላይ ነህ ። የ7 አመት ልጅ ይህን አይቶ ምን እንደሆን ሊያስረዳክ ይችላል።ሰይጣን ሲዋረድ አየን እንጂ ሲከብር አላየንም። አንተ ብትሆን ሰባኪያችን ምን ያህል ልባችንን ለጥላቻና ለክፋት እንደምትቀርፅብን እገነዘባለሁ። አንተ የምታስበው ላንተና እርስ በእርስ ለአገር ይህን ሁሉ አደረገ እየተባ እርስ በእርስ ለምትሸላለሙበትና ለምትሞካሹበት መድረክ እንዲሆን እንጂ ፤ የተጨነቀ ነፍስ ሰይጣን ተባሮለት ሲወጣ በጣም ይከነክንሃል። የተገላበጠና አቅጣጫውን የሳተ መካሪ ሆንክብን
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- ከዚህም አልፎ ልጅ፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ዓለም አቀፋዊ ተክለ ሰብእና ያላትን አትሌት በዚያ ዓይነት ክብርን በሚነካ ሁኔታ እያሰቃዩ በቪዲዮ ማሳየት ፈጽሞ የእግዚአብሔርን ክብር መግለጥ ሊሆን አይችልም፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- ይህ ያንተ እይታ ነው ብዙ ቤተሰብ በመድረኩ ላይም በውጭም የመዳኑን ደስታ እንጂ የሰይጣን ማልቀስ አይደለም የሚያስቡት ። በሰይጣን ሲሰራ የኖረ ሰው ህብረተሰብ አገልጋይ ድንጋጤ ውርደት ክፉኛ ታሪክ እንደሆነበት ሁሌ ይነዳል ይበሳጫል።
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- ሰውነትን ማዋረድ እግዚአብሔርን ማዋረድ ነውና፡፡ አስፈላጊ ነው ካለች እርሷ ራሷ ትንገረን እንጂ ይህንን የመሰለ ቪዲዮ እንኳን ሌላው እርሷም ልታሳየን የተገባ አይደለም፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- ሊዋጥልህ ያልቻለው በውስጥ ተደብቆ ደባ ያደረሰው ሰይጣን የሱ ተንኮል መነገሩ ለምን ያንገፈግፍሃል? የሰይጣን ተንኮልና በህዝብላይ የሚያደርሰው ደባ መታወቁ መሸነፉ ለምንስ ያበሳጫቹሃል
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- ሃይማኖት ታረደ ደሙን ውሻ ላሰው
ከንግዲህ ልብ ልብ አልተገናኘም ሰው
እንደተባለው ሆኖብን ነው እንጂ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የቅድስና ሕይወትስ በሰውነት ክብር ላይ የሚቀልድ አልነበረም፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- አሁንም አንተ አጣመህ አልከው እንጂ ይህ የፈውስ ድህነት የቤተክርስቲያንና የአገራችን ክብርና መከታ የሚሆን እግዚአብሔር የሰጠን ነበር ግን በትልቅነት ላይ አንተና መሳሎች ስለሆናቹሁ ቀድማቹ ቁጭ ያላቹህበት ። "ሉቃ 11 ፥52 እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ። "ይህ ደግሞ እንድንታደል አላረግንም። በአንተና በመሳሎችህ ተንኮለኛ ሃሳብ እናዝናለን እናፍራለን ነገር ግን በመምህር ግርማ ግልጋሎት ግን ልኡል እግዚአብሔርን ሁሌ እናመሰግናለን። እግዚአብሔር ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- የአንድን ሰው ‹ፈዋሽነት› ለማሳየት የሌላን ሰው ዝና፣ ክብርና ሰብአዊ መብት መከስከስ በምንም መልኩ ጸጋ እግዚአብሔርን አያመለክትም፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- ተሳስተሃል የሰው ሳይሆን የሰይጣን እና የግብረ አበሮቹ ጉዳይ ነው የተዋረደው ። ጌጤ ግን በመጨረሻ ከበረች እንጂ።ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ በረከት ውስጥ የቆሙ ወይም አቅጣጫው የጠፋባቸው የጎደፈ እይታህን ነው ያስተዋልነው። እግዚአብሔር አገልግል ካለ የሚደበቅ ነገር የለም ቴክኖሎጂው ለእይታ አፋጠነው እንጂ ሌላ የሆነ ነገር የለም። ይህ ግልጋሎት እኮ የነበረ ነው:: አንተ በፅሁፍ አይተህ እንደሚመችህ ትሰብክበታለህ ለጥቅምክ እንጂ ፤ በቪዲዩ ቢሆን ኖሮ ግን አታምነውም ነበር::
=== መምህር ዲ/ን ዳንኤል ይህን ብለዋል :- ቅዱስ ሲኖዶስም የጳጳሳትን ዝውውር ከሚመለከት ይልቅ እንዲህ ያሉ ነገሮች ሕግና ሥርዓት እንዲኖራቸው ቢያደርግ መልካም ነበር፡፡ እና ሕግና ደንብ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡
*** አቶ ዘበነ ይህን ይላሉ :- "ማቲ 10፥17 ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤" ይህ እውነታ በአንተ እውን የሆነ ነው
ያላስተዋልከው ነገር አለ ከእግዚአብሔር ፀጋው ሲሰጥ የሰዎች የደከመ እይታ ጣልቃ አይገባበትም። ማስከልከል ከሆነ የኖርክበት ስልታዊ አኪያሄድ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የፀጋህን ቦታና የመምህር ግርማን ቦታ ለይተክ ያወቅ አልመሰለኝም። ፀጋህን በቦታክ ብታረጋት ተሰሚነትህ ይኖር ነበር ግን በሌለህበት ታላቅ ፀጋ ላይ ገብተህ የምትቃርመው ነገር መልሶ እንዳይጥልህ እባክህ አስተውል።
"1ኛ ቆሮ 10፥9 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን።" ከመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ጋር ከተቃረንክና እይታህን ካበላሸክ ቆይተካል። የአንድ የአንተ እይታ የህዝብ የሃይማኖት የመንግስት ሊሆን እንደማይችን ጠንቅቀህ መገንዘብ ይገባል።
አንድ ነገር ግን ልንገርህ ። አንተ የብዙ ሚሊዩን ህዝብን እይታ እየከለከልክ እኔ አውቅላቹሃለሁ እኛ በመረጥንላቹ ብቻ ነው መገልገል የምትለን ይመስለናል። የመምህር ግርማ ግልጋሎት ለህይወታችን የወንጌሉን ቃል ከተግባር ጋር ኖረውበት ለህዝብ እያፈሩበት መሆኑን ላስገነዝብህ እንወዳለን። አንተ ማሰብ ከምትችለው በላይ ብዙ መንፈሳዊ ሰዎች እየቀረፁበት ነው ።
የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ እንዲናገር መንፈስ ቅዱስ ቀሰቀሰውና ይህን አለ ። ይህ ላንተም ታላቅ ትምህርት ይሰጥሃልና ላሳስብህ
"ሐዋ 5፥38 አሁንም እላችኋለሁ። ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ። "
ይህ መንፈሳዊ ትምህርት ይሰጥሃል ብዩ አስባለሁ::አንተ ግን ተኝተሃል ንቃ!ንቃ!ንቃ! ለእይታህ የምንረዳህ ነገር ካለ እባክህን አሳውቀን እግዚአብሔር ይግለጥልህ ይርዳህ!
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን !
ከአቶ ዘበነ ማሞ
Read from the source here

No comments:

Post a Comment