Saturday, July 2, 2016

ስድስት ዩኒቨርስቲዎች 31 ሺህ 238 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቀዋል


ስድስት ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛ፣ በማታና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብሮች በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ዶክትሬት ዲግሪ ያሰለጠኑዋቸውን 31 ሺህ 238 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቀዋል። ተማሪዎቻቸውን ዛሬ ያስመረቁት የባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ፣ መቱና አምቦ ዩኒቨርስቲዎች ናቸው።
- የባህርዳር ዩኒቨርስቲ 8 ሺህ 321 ተማሪዎችን በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ዶክትሬት ዲግሪ ነው ያስመረቀው።
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲም 7 ሺህ 898 ተማሪዎችን በመሪጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ እንደሁም በዲኘሎማ አስመርቋል።
- የጐንደር ዩኒቨርስቲ ደግሞ በመደበኛ፣ በክረምትና በማታ የትምህርት መርሃ ግብር 6 ሺህ 344 ተማሪዎችን በዶክትሬት ፣ በሁለተኛና በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።
- የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲም 3 ሺህ 323 ተማሪዎችን በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።
- የመቱና አምቦ ዩኒቨርስቲዎችም 5 ሺህ 342 ተማሪዎችን አስመርቋል።Source Fana BC

No comments:

Post a Comment