Tuesday, July 3, 2018

ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ለዶ/ር አብይ አህመድ - Daniel tomas ኢትዮጵያዊ

ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ለዶ/ር አብይ አህመድ!
እስከዛሬ ድረስ ባደረጉት ቀና ተግባርም ሆነ አስደናቂ ንግግር እንዲሁም ይቅርታ ብዙም አልተደነቅሁም ነበር።ባጭሩ እወድዎት አከብርዎት ነበር እንጅ ለአንዲትም ደቂቃ አምኘዎት አላውቅም ነበር።አይፍረዱብኝ በህወሃት የማስመሰል ፕሮፖጋንዳ ዘመን ያደግሁ ብላቴና ስለሆንኩ ነው።አሁን ግን እርስዎን ማመን እንዳለብኝ ይሰማኛል።ባሁኑ ሰዓት እርስዎን አለማመንና እርስዎን መተቸት ከማናቸውም አይነት ኢትዮጵያዊ ዜጋ አይጠበቅም።ስለዚህ በሰውኛ ሚዛን 99%አምኘዎታለሁ።99% ወድጀዎታለሁ።
ይህ ሙሉ እምነትና ሙሉ መውደድ አይደለምና እባክዎ100% እንድወድዎትና እንዳምንዎት አንዲት ጩኸት በመስማት ይርዱኝ!?አይዞዎት ከባድ የሆነ ጥያቄ አይደለም የምጠይቅዎ።
እርስዎ ኢትዮጵያን ልክ እንደ እኔ እስከመጨረሻው እንዲወዱና እንዳከበሩዋት እንዲያልፉ ነው የምፈልገው።
ሆኖም ስጋት አለኝ።ዘወትር የሚረብሸኝ አንድ ስጋት!ይህንን ስጋቴን ላካፍልዎ የደፈርኩትም፤"ብረት ግሪስ እንዲቀባ ከፈለገ መጮህ አለበት!ብረት ጩኸት ካላሰማ ግሪስ የሚቀባው የለም!ስለዚህ መንግስት መልእክታችሁን እንዲሰማችሁና ችግሩን እንዲቀርፍ ከፈለጋችሁ መጮህ አለባችሁ!ያልጮኸ ብረት ግሪስ አይቀባም!ስለዚህ ጩኹ"በማለት በአርቲስቶች ስልጠና ወቅት ሲናገሩ ስለማሁ ነው።ስለዚህ የብዙዎቻችን ምናልባትም የመላው ዜጋ ጩኸት ነውና ይስሙን!
በግልጽ እንደሚያውቁት በእርስዎ ስልጣን መያዝ ምእራባውያኑ ደስተኞች ናቸው።ምናልባትም ከኛ እኩል ደስተኞች ሳይሆኑ አይቀርም።
ህወሃቶች ኢትዮጵያን እድሜ ልካቸውን ብቻቸውን ለመዝረፍና አገሪቱን በዘላቂነት ሊያራቁቱ ተዘጋጅተው ስለነበር ምእራባውያኑ የዝርፊያው ተሳታፊና ተካፋይ እንዲሆኑ አልፈቀዱም ነበር።ጅብ ብቻውን መብላት ከመውደዱም በላይ ከራበው የራሱንም ወገን ይበላል።ጅብ ጅብን ስለሚበላው አይደል ከሌላው አውሬ በተለየ ሁኔታ ባለመተማመን ምክንያት ጎን ለጎን ተሰልፎ የሚሄደው?ስለዚህ ጅቦቹ ለአገራቸው አስበው ሳይሆን፤ወከልነው ለሚሉት ለትግራይ ህዝብ አስበው ሳይሆን፤
ብቻቸውን ኢትዮጵያን ለመብላት ሲሉ፤(መብላትስ በልተዋታል) የቀራትን አጥንት ብቻቸውን ለመጋጥ ሲሉ፤አንዱን ብሄር ከሌላው ብሄር በሃሰት ፕሮፖጋንዳቸው እያጋጩ ዝርፊያቸውን ቀጥለው ቆይተዋል።ሲቀጥሉም
በብዙ ነገር ለምእራባውያኑ መንገዱን ዘግተውባቸው ነበር።
እርስዎ ደግሞ ዓላማዎ የተበታተነን አንድ ህዝብ መልሰው ማገናኘትና ማዋሃድ፣በግፍ የታሰሩትን መፍታትና ጸበኞችን ማስታረቅ፣ስትበዘበዝ የኖረችውን፣ በጅቦች የጋራ ጥርስ ውስጥ ገብታ 27 አመት ስትጋጥ የኖረችውን አገር፤ ጅቦችን አባርረው ከቁስሉዋ እንድታገግም ማድረግና ልጆቹዋን አስተባብረው እናታቸውን እንዲጠብቁና ከጥቃት እንዲከላከሉ ማድረግ፣ወደ ታላቅነቱዋ መመለስና ሰላም አስፍኖ በአንድነት መኖርን ነው።ለዚህም በማናቸውም አይነት መንገድ የምእራባውያን እገዛ ሊያስፈልግዎ ይችላልና እነሱን ወደጎን ማድረግ ለጊዜውም ቢሆን ላይችሉ ይችላሉ።እነሱም በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸው አይቀርም።ግድ የለም ይግቡ።ነገር ግን ክቡርነትዎ አንድ ነገር ማስታወስ ይጠበቅብዎታል!እነሱ ማለት በእርስዎ የስልጣን ዘመን የግብረሰዶማውያንን ባንዲራ በምድራችን በመዲናችን ያውለበለቡ ናቸው!በወቅቱ እርስዎ ውጥረት ላይ ነበሩና ልብ ላይሉት ይችላሉ።ሜይ 17 2018 በአዲስ አበባ የተፈጸመው ተግባር ለኛ ለኢትዮጵያውያን እጅግ የሚያሸማቅቅ የድፍረት ተግባር ነበር።
አባቶቻችን በነጭ አንገዛም ሲሉና መስዋእት ሆነው ይችን የተከበረች አገር ነጻ አድርገው ሲያስረክቡን፤የነጮችን ሴራና ዝርፊያ ጠልተው ብቻ አይደለም።በዋናነት ሐይማኖት እንዳይፈርስ፣ባህል እንዳይደፈርስ፣ወግ እንዳይገሰስ፣ማንነት እንዳይቆሽሽ፣ሉአላዊነት እንዳይሸጥና እንዳይለወጥ፣ዜጎች በገዛ አገራቸው ባእድ እንዳይሆኑና ያለፍላጎትና ያለእምነታቸው በባእዳን ትእዛዝና ፍላጎት እንዳይነዱ በሚል ነው!ስለዚህ አገራቸውን በፍቅር አንድ ሆነው ከጠላት ተከላክለው አቆይተው እርስዎን በወንበራቸው ላይ አስቀምጠዋል።
ይችን ቅድስትና ምስኪን አገር መምራት የሚችለውና መምራትም ያለበት ደግሞ እንደ እርስዎ አይነት አገሩንና ህዝቡን የሚወድ፣ጅቦችን ጅብ ጀግኖችን ጀግና የሚል፣በጀግኖች አባቶቹ የሚኮራ፣አባቶቹን እናቶቹን፣እህቶቹንና ወንድሞቹን ከእነ ጥፋታቸው ይቅር ብሎ፤ የራሱ ወገኖች፣ የራሱ አካሎች መሆናቸውን ቆጥሮ የሚያከብር፣ወንበራቸውን ቤተመንግስታቸውን የሚያከብር፣ከማጠልሸት ይልቅ የሚያድስ፣ከማፍርስ ይልቅ የሚገነባ፣ጥሩ ስብእናና ፍቅር ያለው ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው።ስለዚህ እርስዎ ወንበሩ ይገባዎታልና ይዘውታል።ሲይዙትም ኢትዮጵያን መያዝዎ ነው።ኢትዮጵያን ሲይዙም ህዝቡን መያዝዎ ነው።ህዝብ የሚባለው ደግሞ አምኖበትና ተስማምቶ ራሱ ባወጣው ህግ የሚመራ ማለት ነው።የሚወጣው ህግ ደግሞ የአገሪቱን ክብርና ህልውና የማያስደፍር ህግ ነው።የህዝቦችን ባህል፣ ልማድ፣ ወግና ሐይማኖት የማይዳፈር ነው።
ኢትዮጵያ ደግሞ በሙስሊምም በክርስቲያንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሰችና የተከበረች፤ ስሙዋም በመልካም ተደጋግሞ የተነሳ ቅድስት አገር ናት።
በመሆኑም የምእራባውያን ፍላጎት ስለሆነ ብቻ፣እርዳታና ብድር ስለሚሰጡ ብቻ፣በተለያየ ዓለማዊ ህጋቸው፤ በየዘርፉ ከየአገራቱ ጋር ስለተሳሰሩ ብቻ፣ህጋቸውን ህጋችን አድርገው መቀበል እንደሌለብዎት ሳስጠነቅቅዎና ስጠቁምዎ፤ህጋቸውን እንደማይቀበሉት ከመገመት ጋር ነው።
ይህን የግብረሰዶማውያን ዓላማ በህጋችን ውስጥ እንዳያካትቱትና ብኩርናችንን በምስር ወጥ እንዳይሸጡብን እንደ አንድ ዜጋ በጽኑ ላሳስብዎትና ላስጠነቅቅዎት እፈልጋለሁ።
ጸሃፊው እንዳለው፤"ዓለማችን ብዙ የሚያስጨንቃት ነገር እያለ፤የዓለም ሃያላን አገራት መሪዎች ግን ብእርና ወረቀት ይዘው ከፍ ያለ በጀትም መድበው ስለዚህ አስጸያፊ ተግባር ሌት ተቀን የሚወያዩትና በየህጋቸው እያጸደቁ የሚገኙት፤ ፍላጎቱ የህዝብና የየአገራቱ ሆኖ ሳይሆን፤ የሌላ እርኩስ መንፈስ ኣላማ አስፈጻሚዎች ስለሆኑ ብቻ ነው"
ያ ባይሆን ኖሮ በሐይማኖትም፣በህገ ልቦናም፣የተከለከለውን፣በ
ፈጣሪ ዘንድ ያልተፈቀደውንና የተወገዘውን፣ሌላው ቀርቶ እንደ ሰው ማሰብ አይችሉም የምንላቸው እንስሳት እንኩዋን የማይፈጽሙትን፤ የተመሳሳይ ጾታ ወሲባዊ ግንኙነትን ባላቀነቀኑት ነበር።የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ባልደገፉት የህግ ከለላም ባልሰጡት ነበር!ሰዎችንም ወደዚህ መስመር እንዲቡ ባልገፋፉ ነበር።
እነሱ ግን አላረፉም።በዚህ ጉዳይ አምርረው የሚገኙ ሆነዋል!ዳቦ ያጣውን በዳቦ፣ስልጣኔ ያጠረውን በስልጣኔ፣ፍትህ ያጣውን በፍትህ እያሉ ሁሉም ህዝብና መንግስታት ላይ ጫና እያሳደሩ ነውና ወደኛም አገር ረጅም እጃቸውን ሰደው በዚህ ጉዳይ ላይ ጫና መፍጠራቸው አይቀርምና ከወዲሁ ይዘጋጁበት እላለሁ።
በዓመታዊ ክብረ በአላቸው ላይም በዘንድሮው ዓመት እንዳደረጉት፣ ባንዲራቸውን በዚች አገር እንዳውለበለቡት፣በዚያውም የማለማመድ ተግባራቸውን እንደጀመሩት፤በቀጣይ ተከታታይ ዓመታትም አጠናክረው መቀጠላቸው አይቀርምና ሙሉ እምነት የጣለብዎትን ህዝብዎን በዚህ በኩል እንዲታደጉትና ጠንካራ ተከላካዩ ሆነው እንዲገኙለት በኢትዮጵያ ስም እጮሃለሁ።
"ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ"የሚሉ መሪ ነዎትና፤ኢትዮጵያ በፈጣሪ ትባረክ ዘንድ ይህን የእርኩሰት ተግባር ከፊት ሆነው እንዲከላከሉ አደራ እልዎታለሁ።
መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎ።
በዚህ መልእክት የምትስማሙ ወገኖች ሼር በማድረግ ተባበሩ።
Daniel tomas ኢትዮጵያዊ

1 comment: