ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በታች ያላትና የበሬ ግንባር የምታክለው አገር ጅቡቲ የመላው ሃያላን አገራት የጦር ካምፕ መመስረቻ ሆናለች።ባለፉት ጊዜያቶች አሜሪካ በአካባቢው ሊሞንየር የተባለ የጦር ካምፕ ነበራት።
ፈረንሳይም እንደዚያው።
በቅርቡ ደግሞ ቻይና ከአሜሪካ ጎን አስደናቂ የተባለ የጦር ካምፑውማን መስርታለች።ጦሩዋንም አስፍራለች።
አሁን ደግሞ ፈረንሳይ ከቀድሞው በተሻለና በዘመነ መልኩ በአዲስ መልክ የተዋቀረ ጦር ሰፈር እየገነባች ሲሆን፤የቀድሞ ጦሩዋን በአዲስ መልክ ማዋቀርና የጦር ካምፑዋንም ተጨማሪ ቦታ በመውሰድ ለማስፋፋት ተፈራርማለች።
በዚህ በያዝነው ወር ደግሞ በማይታመን ሁኔታ ጀርመን፣ጃፓን፣ኢጣሊያ፣ሩሲያ፣ቱርክ እና ሌሎች የ G8 እና የG20 አገራት መንግስታት በከፍተኛ የገንዘብ በጀት ከጅቡቲ መንግስት ቦታ እየገዙና በኮንትራት እየተዋዋሉ ሁሉም ለማለት በሚቻልበት ሁኔታ የጦር ካምፖቻቸውን በረቀቀና ዘመናዊ መንገድ በመመስረት ላይ ይገኛሉ።
በዚህም ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የሰሞኑን የሃላን አገራት መንግስታት ፈጣን የጅቡቲ ርብርብ በማጤን ጅቡቲን "ሚሊቴሪ ሪል ስቴት"ብለው እየገለጹዋት ይገኛሉ።
የየአገራቱ መንግስታት የጦር ካምፖቻቸውን በጅቡቲ የመመስረት ምክንያቶች አሳማኝ ካለመሆናቸውም በላይ የሚያስገቡት የጦር ሰራዊት ብዛትና የሚያሰማሩዋቸው የጦር መርከቦች፣የጦር ጀቶች፣ዘመናዊ ሚሳኤሎች የዓለምን ህዝብ ትኩረት በእጅጉ ስቦዋል።ሀኔታው በማወዛገብ ላይም ይገኛል።
የጅቡቲ መንግስት ደግሞ ለሃያል አገራቱ የጦር ካምፕ መመስረቻ ቦታዎችን በመቸብቸብ ብቻ ከአገሪቱ አቅም በላይ የሆነ መጠኑ የበዛ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እያጋበሰ ይገኛል።ሃያል አገራቱ ይህን ያህል ገንዘብ የሚከፍሉት ለጦር ሰፈር ግንባታና ለዘመናዊ ሚሳየሎች ማጥመጃ፣ለባህር ሃይል ሰራዊቶቻቸውና ለጦር መርከቦቻቸው፣ለአየር ሃይል ሰራዊቶቻቸውና ለጦር ጀቶቻቸው ማስፈሪያ ነው።
በመሆኑም ከጦር ሰፈር ግንባታው በሁዋላ የሚያሰፍሩዋቸው ሰራዊቶችና አሁንም እያሰፈሩዋቸው ያሉት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራዊቶች ናቸውና መኖሪያቸውን ጅቡቲ ስለሚያደርጉ አገሪቱ ለእነሱ የሚሆን ዘመናዊ አገር መሆን እንዳለባት ወስነው የማዘመን ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ። ሆቴሎች እና ምቹ ምቹ መዝናኛዎችን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች መሙዋላት እንዳለባቸው አምነውም ምእራባውያኑ በግንባታ ዘርፍ መሰማራት ጀምረዋል።በዚህም ጅቡቲ በቅርቡ በዓለማችን ካሉ ምቹና ዘመናዊ አገራት አንዱዋ ልትሆን ትችላለች ተብሎዋል።
ወደፊት ዘመናዊ ሆና የምትገነባው ጅበቲ የምትነጻጸረው ከዱባይ ወይም ከቱርክ ኢስታንቡል ጋር እንደሆነ ነው የሚዘገበው።
ጅቡቲን በሁሉም ዘርፍ ከዱባይ የምትበልጥ አገር አድርገው ለመገንባት ተዘጋጅተዋል፤ግንባታውም ተጀምሮዋል።
ይህ ፈጣን ርብርብ የዓለምን ህዝብ ትኩረት መሳቡ እንዳለ ሆኖ፤ በተለይ በያዝነው ወር የጃፓን ወደ አካባቢው መምጣት ግን ለምን?የሚለውን ጥያቄ የበለጠ አክርሮታል።
ለምን?የሚለው የሁሉም ጥያቄ ግን አጥጋቢ ምላሽ አላገኘም።
ይህ ሁሉ ሲሆንና የዓለም ህዝብ ትኩረት በጅቡቲና በጦር ሰፈር ግንባታዎች ላይ ሲሆን፤የኢትዮጵያ መንግስት ግን ምንም ያለው ነገር የለም።
ሚዲያዎቻችንም ለኢትዮጵያ ህዝብ የሰጡት መረጃ የለም።
ምናልባት ስለ ጅቡቲ አይመለከተንም፣ጉዳዩም አያገባንም ተብሎ ሊተው ይችል ይሆናል።
ሆኖም መንግስት እንደ መንግስት በጎረቤት አገር ይህን ያህል ሚሳየልና ሃያል አገር ከነሰራዊቱ ከእነ ሚሳየሉ ሲንጋጋ ስለጉዳዩ ማብራሪያ ጠይቆ ቢያንስ ምላሹን ለህዝብ መጠቆም ሲኖርበት ያን አላደረገም።
ምናልናትም ባለስልጣኖቻችን አልሰሙ ይሆናል።ሰምተውም ከሆነ የጅቡቲው ፕሬዘዳንት በሚሸጠው ቦታና በሚያገኘው ገንዘብ ምራቃቸውን እየዋጡ ስለ እድለኝነቱ እያነሱ በቅናት በመንገብገብ ላይ ናቸው ማለት ይሆናል።
የኛ መንግስት እንትን የተባለው ግዛት የእንትን ብሔር ቦታ ነው....።እያለ በውስጥ መሬት ጉዳይ ሲያወራና ሲያስወራ፤ኢትዮጵያ ደግሞ ከግዛቱዋ ወሰን ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብሎ በሃያል አገራት ሚሳኤል፣ በጦር ጀት፣ በጦር መርከብና በኮማንዶ ስምሪት ተከብባለች።
የሚገርመው ደግሞ ሁኔታው በጅቡቲ ብቻ ተወስኖ የቀረ አለመሆኑ ነው።
ባሁኑ ውቅት ከበባውም በሉት ስምሪቱ ከጅቡቲ አልፎ ወደ ኤርትራና ሱዳን ተገብቶዋል!
ለምሳሌ ቻይና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አፍሪካ ውስጥ በልማት ወይም በልማት ሰበብ እንጂ በሌላ ፓለቲካዊ ጉዳይ ጣልቃ ስትገባ አይስተዋልም ነበር።ሆኖም ከዚህ ቀደም በስፋት እንዳስነበብኩዋችሁ ቻይና በጅቡቲ ከአሜሪካ የጦር ካምፕ አጠገብ የባህር ሃይልና የአየር ሃይል ጦሩዋን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቹዋን ከነ ተወንጫፊ ሚሳየሎቹዋ አስገብታ ካሰፈረች ረዘም ያሉ ወራቶች ቢቆጠሩም፤ አሁን ደግሞ የጅቡቲው እንዳለ ሆኖ፤ይህን ለየት ያለና ለመገመት አስቸጋሪ የሆነ እንግዳ ተግባሩዋን ቀጥላ በኤርትራ ቀይ ባህር የጦር ካምፕ ወደመመስረት አልፋለች።
ከቀናት በፊት ቻይና ኤርትራና ጅቡቲን ለመሸምገል በሚል በቀይ ባህር ጦሩዋን ማስፈር ጀምራለች።
ቻይና ወደ አወዛጋቢው የኤርትራና ጂቡቲ ድንበር የሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ለማስፈርና ሁለቱን ሀገራት ለመሸምገል ፈቃደኛ መሆንዋንዋን በአንባሳደርዋ በኩል ለአፍሪካ ህብረት ለይስሙላ ካስታወቀች በሁዋላ ነው ወደ ተግባር የገባችው።
በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደር የሆኑት ኩዋን ዊሊን መንግስታቸው ወደ አወዛጋቢው/አወዛጋቢ ጉዳይ ባይኖርም/ የኤርትራና ጂቡቲ ድንበር የሰላም አስከባሪ ጦር ለማስፈርና ሁለቱን ሀገራት ለመሸምገል ፈቃደኛ መሆኗን ለአፍሪካ ህብረት አሳውቃ ቦታዋን እየያዘች ነው።
ይህ ብቻ አይደለም፤የ G 20 እና የ G 8 አገራት በጅቡቲ በኩል ከተደላደሉ በሁዋላ በዚህ ሳምንት ፊታቸውን ወደ ኤርትራ አዙረው ተመሳሳይ ተግባራቸውን ቀጥለዋል።
ለምሳሌ በትናንትናው እለት የአሜሪካው ዶናልድ ያማማቶ ከሁዋይት ሃውስ ተልከው ወደ ኤርትራ ገብተው ነበር።ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ቀጥሎ ወደ ጅቡቲ ነው እቅዳቸው።
የኤርትራ ማዕቀብም ሙሉ በሙሉ እየተነሳ ነው።ይህ መልካም ዜና ቢሆንም፤ይህ ሁሉ ቅርርብና ያልተለመደ ልምምጥ ግን በኤርትራ የጦር ካምፕ ከመመስረት ጋር የተያያዘ መሆኑ ብዙዎቹን አወዛግቦዋል።
በዚህ ሳምንት ኤርትራ ሱዳን እና ጅቡቲ የ G 20 እና የG 8 አገራትን ባለስልጣናት እየተቀበሉ በማስተናገድ ስራ ተጠምደዋል።
ይህ ብቻ አይደለም፤ሩሲያም በሱዳን ተመሳሳይ የጦር ካምፕ ምስረታ የምታደርግበትን ስምምነት እየተፈራረመች ነው።
እነዚህ የ G 8 እና የ G 20 አገራት ባልጠፋ ቦታ ጅቡቲና ኤርትራን ከበው ይዘዋል።ከበው ሲይዙና ጦራቸውን ሲያሰፍሩም ብዙ ሚሊዮን ዶላር እየለፈሉ ነው
የሚሰጠው ሰበብም አንዳንዴ የጦር ልምምድ ለማድረግ፣አንዳንዴ የባህር ሃይል ልምምድ፣ ሌላ ጊዜ ቀጠናው ላይ ሰላም ለማስፈን፣እንደገና መርከብ ጠላፊዎችን ለመያዝ፣መልሰው በአፍሪካ ቀንድ ያሉ አሸባሪዎችን ለመከላከል እያሉ በማምታት ነው።ጃፓን ሳትቀር ይሄን ማለት ጀምራለች።
በእርግጥ ግን እንደዚያ ነው?ብሎ መጠየቅና መተንተን ማስተንተን ባይቻልም ቢያንስ ዜናው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚዲያ መገለጽ ነበረበት።በኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኩል ግን ይህ አልሆነም።በመሆኑም ባሁኑ ወቅት ከጅቡቲ መንግስት የበለጠ የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ሚዲያ ምንም አለማለቱ ነው የበለጠ ግራ አጋቢ ሆኖ የተገኘው።
ይህ ብቻ አይደለም በቅርቡ እነዚህ ሃያላን የተባሉ አገራት ኢትዮጵያ ውስጥ የኒውክሌር ግንባታ ለማካሄድ እየተፈራረሙ ነው።እንዴትና ለምን የሚለውን የምንመለስበት ይሁን!
Source: DanielTomas
No comments:
Post a Comment