Saturday, September 23, 2017

ወያኔ እና የኢትዮጵያ ህዝብ የድሮ አባት እና ልጅ ቅጣት - በሁለት እጆችህ አፍክን ያዝ 'ዋ' ትፍሽ እዳትል!

ወያኔ እና የኢትዮጵያ ህዝብ የድሮ አባት እና ልጅ ቅጣት - በሁለት እጆችህ አፍክን ያዝ 'ዋ' ትፍሽ እዳትል!
==================
ወያኔ ኢሕአዴግ በፈራ ቁጥር የኢትዮጵያን ህዝብ በውድም ሆነ በግዴታ እያሸማቀቁ እና ፍርሐት ውስጥ ለመክተት የሚደርጉትን የመብት አፈና ቢተው ይሻለዋል። ሰሞኑን በአንዳንድ የሃገራችን ክፍሎች በተነሣው የጎሳ ግጭት ተከትሎ በተለያዩ ሚዲያዎች የተለያዩ መረጃዎች መውጣትን ተክትሎ ፍራሀት የገባው የወያኔ ኢሕአዴግ መንግሥት የኢትዮጵያን ህዝብ አንዳችም ነገር ትፍሽ ትሉ እና ዋ ወዩላቹህ እያለ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ህዝብ መረጃ የማግኘት እና የመለዋወጥ በጅጉ የሚፃረር የምታወሩትን እና በእንተርኔት የምትለዋወጡትን መረጃ ቴሌ እኔ ልወቀው እያለ ነው። ለዚህም ያላቹህን ሞባይል ሁሉ አስመዝግቡ እያለ ነው። ተፈጥሮ ለሰው ልጅ የለገሰችውን የመሰለውን የመናገር እና መረጃን የማግኘት መብት ማፈን ዙሮ ዙሮ የሚጎዳው ሃገሪቱን እና እሷን አስተዳድራአለሁ የሚለውን አካል ነው። የታፈነ ነገር አንድ ቀን መፈንዳቱ እንደማይቀር ማወቅ አለባቸው። የፈነዳ ግዜ ደሞ ብዙ ነገር እደሚያበላሽ የታወቀ ነገር ነው።

በሌላ በኩል ደሞ ባሁኑ ስአት ለወያኔ ኢህአዴግ ትልቅ  ማይወጣው ፈተና እየሆነ የመጣው ባገር ውስጥ የሚደረገው ተቃውሞ ሳይሆን ሀገር ውጭ የሚደረግ ተቃውሞ እና እዛው ሚተላለፉ ሜዳዎች ናቸው። ባሁኑ ስአት ትላልቅ ታዋቂ ባለሥልጣን እንደፈለጉ ሀገር ውጭ የመናገር እና የመዝናናት መብቱ የተገፈፈ ይመስላል። ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አስቶ እስከ  ተለያዩ ምኒስትሮች እና የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት፣ በዶክተር ቴድሮስ የምርጫ ዘመቻም ላይ ሲካሄድ የነበረውን እጂግ ከመረን የወጣ ፓለቲካውን ብቻ ሳይሆን የግለሰብን ስብእና የሚነካ ተቃውሞ እያየን ነበር።

ከዚህ የባሰው እና ለወያኔ ኢህአዴግ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነበት ግን  በውጭ ሚዲያዎች የሚወጣው መረጃ ነው። ዛሬ ከማንም ኢትዮጵያዊ የበለጠ ኢሳትን እና OMN እንዲሁም ያማራን ድምፅ እና ታዋቂ የፌስቡክ አክቲቨስቶችን የሚከታተሉት ትላልቅ የመንግሥት ባለሥልጣናት ናቸው። ይህም በአትኩሮት ሚከታተሉት መረጃው ለኢትዮጵያ ህዝብ ደርሶ አመፅ ይቀሰቅሳል በሚል ፍራቻ እና ቶሎ እርምጃ ለመውሰድ እዲያመቻቸው ነው።

ግን እስከመቼ በዚህ ይቀጥላሉ?  የውጭ ተቃውሞ እና የተደበቀን መረጃ ፈልፍሎ ማውጣት በተለይ ደግሞ የመንግሥትን ደካማ ጎን በመጠቀም መላ ሕዝብን ወደ ዓመፅ መገፋፋት ከዚህ ጋር ተያይዞ በሶሻል ሚዲያዎች እለታዊ የሆኑ መረጃዎች በተሎ ለተጠቃሚው ማድረስ ከዕለት እለት እየጨመረ መምጣቱ እና ሰውም መረጃ የማግኘት ፍላጎቱ ማደጉ ማንም የሚያቀው ሐቅ ነው።

መንግሥት ታዲያ ያገር ውስጥ ተቃውሞን በፈረጠመ ወታደራዊ ሀይልም ሆነ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ወይም እንደሰሞኑ በቀጥታ መሀተም እና ፌሪማ ያለው ደብዳቤ በመፃፍ እና ህዝቡን በፍርሃት በማሸማቀቅ አልፎም ተርፎ ሰዎችን በማሰር እና በማገላታት ትንሽ ያረገበ ቢመስለውም ከላይ የተጠቀሰውን ችግር መቋቋም ግን የእግር እሳት እንደሆነበት እያየን ነው።  ታዲያ ምንድነው መፍትሔው? ከዚህ ጋር በተያያዘ የመፍተሄ ሐሳብ ያልኩትን በሰፊው ይዠ እደምመለስ ቃል እገባለሁ። እስከዛው ግን ቸር እንሰብት!

No comments:

Post a Comment