Thursday, May 11, 2017

በአማራ 7ኛና 8ኛ ክፍል ትምህርቶችን ወደአማርኛ መመለስን ስለመቃወም

በአማራ 7ኛና 8ኛ ክፍል ትምህርቶችን ወደአማርኛ መመለስን ስለመቃወም
Young woman reading
በሚቀጥለው አመት በአማራ “ክልል” ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል የሳይንስ ትምህርቶች ወደአማርኛ ይቀየራሉ የተባለው ነገር በጣም ጎጅ ነው፡፡ ከወዲሁ ተወግዞ ሊቆም ይገባዋል፡፡ ለተማሪዎች ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍልን በእንግሊዝኛ መማር አስረኛ ክፍል እና ዘጠነኛ ክፍልን ቀላል ያደርግላቸዋል፡፡ ሲቀጥል የአስረኛ ክፍል ፈተና አገር አቀፍ ስለሆነ በእንግሊዝኛ እየተማሩ ከሚያድጉት ጋር በሚኖረው ውድድር የአማራ “ክልል” ተማሪዎች ተጎጅ ይሆናሉ፡፡ በራስ ቋንቋ መማር ጥሩ እንደሆነ ማንም አይክድም፡፡ ነገር ግን በራስ ቋንቋ መማር የሚጠቅመው ወይ ሁሉ የኢትዮጵያ ክፍሎች በአማርኛ ሲሰጥ ወይም የአማራ “ክልል” ተማሪዎች ከዘጠነኛ እስከ ዩኒቨርሲቲ መጨረሻ ድረስ ከራሳቸው “ክልል” ተማሪዎች ጋር ብቻ እየተወዳደሩ “በራሳቸው “ክልል” ብቻ የሚኖሩ ከሆነ ነው፡፡ ከዛ ውጭ ግን የአማራ “ክልል” ተማሪዎችን ወደሁዋላ ለመጎተት፣ ማለትም ሆነ ተብሎ ለመጉዳት እንደሚወጣ ፖሊሲ ይቆጠራል፡፡ ለምሳሌ እኔ ራሴ ሰባተኛና ስምንተኛን በአማርኛ ነበር የተማርኩት፡፡ በኋላ ዘጠነኛ ክፍል ስገባ ሁለት አመት ሙሉ የተማርኩትን እንደገና በእንግሊዝኛ ማጥናት ነበረብኝ፡፡ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ይህም ማለት አሁን የአማራ “ክልል” ተማሪዎች በአማርኛ የሚማሩ ከሆነ ዘጠነኛ ክፍል ሀሳቦችን እና ጽንሰ ሀሳቦችን መረዳታቸው ይቀርና ትግላቸው ቋንቋውን ለማጥናት ይሆናል፡፡ ስለዚህ የአማራዎቹ ገና ቋንቋውን ሲለማመዱ ሌሎቹ በእንግሊዝኛ የተማሩት ራሱን ትምህርቱን በተሻለ የሚረዱበት እና በውድድሩ መሪዎች የሚሆኑበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይሄን ድርጊት እንደሚጎዳን አውቀን እንቃወም፡፡ Read more here

No comments:

Post a Comment