Sunday, December 18, 2016

ዘ ዊክኤንድ - ለ ዊክኤንድ

ዘ ዊክኤንድ/አቤል ተስፋዬ/
የሃያ ስድስት ዓመቱ አቤል ተስፋዬ የዘንድሮውን የአውሮፓ 2016 የመጨረሻ ሩብ ዓመት “ምርጥ” የተባለለትን አልበም ለማውጣት ሲማስን ሰንብቷል፡፡
“ስታር ቦይ” የተወራለት አልበሙ ነው፡፡ ካናዳዊው አቤል ተስፋዬ የአደባባይ ስሙ ወይም እርሱ በዋለበት የኪነቱ ዓለም የሚጠራበት “ዘ ዊክ ኤንድ” ነው፡፡ ለምን? እርሱን ለሌላ ጊዜ እናቆየውና የዛሬ ጉዳያችንን
ሰሞኑን ባደረገው ቃለ - ምልልስ ላይ በአጭሩ እናተኩር፡፡
አቤል ዛሬ በዓለማችን ከሚጠሩ የመድረክ ከዋክብት አንዱ ነው፡፡
ጥያቄ፡- አንተ የተለያዩ አካባቢዎችን የምትወክል ሰው ነህ፤ ቶሮንቶ፣ ኢትዮጵያ … እንዴት ይሆን ይህንን የምትይዘው?
አቤል (ዘ ዊክኤንድ)፡- ኢትዮጵያዊ መሆኔን አሳውቄአለሁ፤ ተናግሬአለሁ፡፡ በሙዚቃዬ ውስጥ አሳይቻለሁ፡፡ የአዘፋፈኔ ስልት ኢትዮጵያዊነት አብዝቶ የተጠናወተው ነው፡፡ በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ጨርሶ አልነበርኩም፡፡ ሀገሬ ሄጄ ዘሮቼን (መሠረቴን) ማየት እፈልጋለሁ፡፡
ጥያቄ፡- አንድ አድናቂህ “ከኢትዮጵያ ዘፋኞች ማንን ልሰማ?” ቢልህ ምን ትመክረዋለህ?
ዘ ዊክኤንድ፡- አስቴር አወቀን፤ ያለጥርጥር! በአዲሱ አልበሜ ወስጥ አንዱ ዘፈን “ፎልስ አላርም” መጨረሻ ላይ የእርሷ ድምፅ ይሰማል፡፡ የእርሷ ድምፅ ‘ ኮ እስከዛሬ ከተዜመባቸው ድምፆች ሁሉ እጅግ የበለጠው፤ እጅግ የተዋበው፤ እጅግ የረቀቀው ድምፅ ነው፡፡
ሙላቱ አስታጥቄ
ሙላቱ አስታጥቄ
ሙላቱ አስታጥቄ የሚባል ታላቅ የሙዚቃ ፀሐፊ (ኮምፖዘር) አለ፡፡ እርሱ ምናልባት አሁን እጅግ የታወቀው ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ነው፡፡ ጂም ያርሙሽ የእርሱን ሙዚቃ ተጠቅሟል፡፡ በሆነ ጊዜ አግኝቼው አብሬው ብሠራ ደስ ይለኛል፡፡ ማህሙድ አህመድ ታላቅ ዘፋኝ ነው፤ ጥላሁን ገሠሠም እንዲሁ፡፡ ቴዲ አፍሮ ይበልጡን የፖፕ ዓይነት ዘፋኝ ነው፤ ድንቅ ድምፅ! እኔ ያደግሁት እነዚህን እየሰማሁ ነው፡፡ ጠዋት ሰነሳ እናቴ ቡና እያፈላች የምትሰማው እነዚህን ዘፈኖች ነው፡፡
ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶሮንቶ ውስጥ ከኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ጋር እራሱን የቻለ ትምህርት እንዲሰጥበት ለማስደረግ እየጠረ መሆኑን አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክኤንድ)ተናግሯል።
የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ፡፡ Read more here

No comments:

Post a Comment