ከተለያዩ የሕይወት መስኮች የተሰባሰቡ ከስድስት መቶ በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች በጆርጂያ ግዛት ዋና ከተማ አትላንታ ላይ ያደረጉት ጉባዔ ተጠናቅቆ የሥራ ሠነድ አውጥቷል፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
የጉባዔው ዓላማ የተለያዩ ሃሣቦችና አቋሞች ያሏቸው የኦሮሞ ድርጅቶች ኃላፊነት ባለው መንገድ እንዲንቀሣቀሱና በአንድ መድረክ እንዲታገሉ ለማስቻል፣ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የነቃና ሥፋት ያለው ውይይት ለማካሄድ መሆኑን ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሣ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
የሠብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት እንዲቋቋምም ሃሣብ ቀርቧል፡፡
“የኦሮሞ አብዮት” ሲል የጉባዔው መግለጫ በጠራው እንቅስቃሴ ውስጥ ከሌሎች ነፃነት አፍቃሪ ሕዝቦች ጋርም እጅ ለእጅ ለመያያዝ እንደሚሠሩ ተሣታፊዎቹ አመልክተዋል፡፡
ከፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሣ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ Read more here
No comments:
Post a Comment