Tuesday, October 25, 2016

የአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ሕትመት አቆመ

አዲስ ስታንዳርድ ሎጎ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በጥቅል ያወጣቸው መመሪያዎች የማተሚያ ቤቶችም ስጋት ሆኗል
በኢትዮጵያ የሚታተመው አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ከያዝንው የጥቅምት ወር ጀምሮ የሕትመት ስርጭቱን እንዲያቆም መገደዱን አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የተላለፈው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማተሚያ ቤቶች ላይ የፈጠረው “ፍራቻና ስጋት” ለአሳታሚዎች እራስ ምታት እየሆነባቸው እንደሆነ የአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ፀዳለ ለማ ለቪኦኤ ገልጻለች።
በአዲስ አበባ የሚታተሙ የሀገሪቱ አቢይ ጋዜጦች ህትመታቸውን ቀጥለዋል። የአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጸዳለ ለማን ሔኖክ ሰማእግዜር አነጋግሯል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ Read more here

No comments:

Post a Comment