Friday, October 28, 2016

ኢህአዴግ "ሕጋዊና ፍትሃዊ" ያላቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚሠራ አስታወቀ

በኢትዮጵያ "የምርጫ ሥርዓት ማሻሻል ብቻውን የተሻለ የፓርቲዎች ውክልና ሊያመጣ አይችልም" ሲሉ የኢትዮጵያ ፓርላማ የቀድሞ አባልና የፓን-አፍሪካ ፓርላማ የክብር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ተናግረዋል።
የአራት ቀናት ስብሰባውን ትላንት ያጠናቀቀው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሕጋዊና ፍትሃዊ ያላቸውን ጥያቄዎች በአጥጋቢ ሁኔታ ለመመለስ እንደሚሠራ አስታውቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ዶክተር አሸብር ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ በሕግ ያልተፃፉ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ውሣኔዎች እንደ አማራጭ ሊወሰዱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
"መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከማስፈፀም ጎን ለጎን የሕዝብን ጥያቄዎች ለመመለስና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት መሥራት አለበት" ብለዋል።
ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

No comments:

Post a Comment