Sunday, September 4, 2016

የእስረኛ ቤተሰቦች ፤ ዘመዶቻቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ገለፁ

ቂሊንጦ እስር ቤት በእሳት ሲቀጣጠል (ፎቶ፡ አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ)
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ስር በሚገኘው ቂልንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ በትክክል ማረጋገጥ አልተቻለም።
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ስር በሚገኘው ቂልንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ በትክክል ማረጋገጥ አልተቻለም።
ቂልንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ታሳሪ ቤተሰቦቻቸው የት እንደሚገኙ ማወቅ እንዳልቻሉ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።
የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ቃል አቀባይ በበኩላቸው በአጭር ጊዜ ምናልባትም ነገ የተሟላ መረጃ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲ፤ የእሳት አደጋ ማጥፊያ ሰራተኞች የአደጋ ጥሪ ደርሷቸው ቦታው ላይ ከደረሱ በኋላ ሰባት ሰዓት የፈጀ ጥረት አድርገው እሳቱን መቆጣጠራቸውን ገልጸዋል።
የእሳቱን መንሰኤ፣የጠፋውን ሕይወትና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ መስሪያ ቤታቸው ያጠናቀረው መረጃ እንደለሌ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል አደጋውን በተመለተ ሀገር ውስጥ የሚገኙ ብዙሃን መገናኛ ዌብሳይታቸው ላይ ዘግበውታል። ከእንዚህ ውስጥ በእንግሊዘኛ ጋዜጣ የሚታተመው ፎርቹን ጋዜጣ ምንጮቹን ጠቅሶ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉንና በ20 ሰው ላይ የተለያየ ጉዳት መድረሱን አስፍሯል።
ጽዮን ግርማ ሁሉንም ወገን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች። Read more here

No comments:

Post a Comment